የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አዳዲስ የካቢኔ ሹመት አፀደቀ- ወይዘሮ አበበች ነጋሽን አፈ ጉባዔ አደርጎ ሾመ

የአዲስ አበባ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ወይዘሮ አበበች ነጋሽን የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አደርጎ ሾመ።

ምክር ቤቱ ላለፉት ዓመታት በአፈ ጉባዔነት ሲያገለግሉ የቆዩት ዶክተር ታቦር ገ/መድህን የትምህርት ቢሮ ሃለፊ ሆነው በመሾማቸው ወይዘሮ አበበችን አፈ ጉባዔ በማድረግ ሹሟል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት ዛሬ በካሄደው አስቸኳይ ጉባዔ ከተማን የተለያዩ ቢሮዎች ሊመሩ የሚችሉ ሀላፊዎችን በምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ አቅራቢነት አፅድቋል።

 

 

በዚህም መሰረት

1. ወ/ሮ አልማዝ አብርሃ የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሃላፊ

2. ወ/ሮ ፍሬህይወት ተፈራ የፍትህ ቢሮ ሃላፊ

3. አቶ ጀማሉ ጀምበር የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሃላፊ

4. አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የገቢዎች ቢሮ ሃላፊ

5. ዶ/ር ፍሬህይወት ገብረህይወት የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ

6. አቶ አሰፋ ዮሃንስ የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ

7. ኢንጂነር ኤርምያስ የኢንደስትሪ ቢሮ ሃላፊ

8. አቶ አብዱልፈታ የሱፍ የንግድ ቢሮ ሃላፊ

9. አቶ ፎኢኖ ፎላ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ

10. ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የኮንስትራክሽን ቢሮ ሃላፊ

11. ኢንጂነር ሽመልስ እሸቱ የመሬት ማኔጅመንት ቢሮ ሃላፊ

12. አቶ ደረጄ ፈቃዱ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር

13. አቶ ዘውዱ ቀፀላ የሰራተኛና ማህበራዊ ቢሮ ሃላፊ

14. ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ የጤና ቢሮ ሃላፊ

15. ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው የቤቶች አስተዳደር ሃላፊ

16. አቶ ነብዩ ባየ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ

17. ዶክተር ታቦር ገብረመድህን የትምህርት ቢሮ ሃላፊ

18. አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የጥቃቅን እና አነስተኛ ቢሮ ሃላፊ በመሆን ተሾመዋል።

FBC news

Advertisements

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s