Advertisements

ጥቁሩ ሰው አዲስ አበባ ገቡ – ለተጀመረው የእርቅ ጉዞ ትክክለኛው ድልድይ!!

“ትልቁ የአገራችን ችግር መተማመን መጥፋቱ ነው። መተማመን የሚፈጠረው በመነጋገር ነው። ካሁን በፊት ያጋጠመንን ችግር በመነጋገር ለማሰወገድ ስንሰራ ኖረናል። እርቅና ሰብአዊነት መመሪያችን ነው። ስንሰራ የኖርነው በመርህና በማስተዋል ነው። ዓላማችን ይህንኑ ላለፉት አስር ዓመታት ስንሰራ እንደነበረው ሁሉ አሁንም እንቀጥላለን” ሲሉ አቶ ኦባንግ ሜቶ ይናገራሉ።

አስራ ሁለት የሚሆኑ የልኡካን ቡድን በመያዘ ዛሬ አዲስ አበባ የገቡት አቶ ኦባንግ / ጥቁሩ ሰው/ ለዛጎል እንደተናገሩት ጉዟቸው ለመናገር ብቻ ሳይሆን በአብዛኛው ለመስማት ነው። መነጋገር ከተፈለገ አንድ ወገን ብቻ ሊያወራ ሰለማይገባ ማዳመጥ ለተናጋሪዎችና ለመነጋገር እድል ይሰጣል።

ምንም እንኳን ከአራት መቶ በላይ አኝዋኮች በአንድ ቀን ቢጨፈጨፉም፣ አቶ ኦባንግ በቀልን አለማሰባቸው በአብዛኞች ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ክብር ያሰጣቸው ጉዳይ ነው። እሳቸው እንደሚሉት ቂም በጎ ነገር አይደልም። ስሩም አይቆረጥም። ልክ እንደ ሃረግ ተያይዞ የሚሄድ በሽታ ነው። እናም ጭፍጨፋ በደረሰ ማግስት “ሁላችንም ነጻ ካልወታን ማናችንም ነጻ አንወጣም ” የሚለው ሃሳብ በልቦናቸው ውስጥ ተወለደ። ሃዘኑ የከፋ ቢሆንም ፍቅርን ከመስበክ ሌላ አማራጭ እንደሌለ አመኑ።

smne 1

የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና እምነት ከጎሳ በፊት ለሰብአዊነት ቅድሚያ እንስጥ፣ ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማናችንም ነጻ አንወጣም፣ ለመተማመን እንነጋገር፣ ስለሌሎች ከመናገር ስለ ራሳችን እንነጋገር የሚሉትን መሪ ሃሳቦች በማንገብ ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት ኦባንግ፣ ጉዟቸው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በያዙላቸው ሰሌዳ አማካይነት የተከናወነ ነው።

አራት ሴቶችን አካተው ወደ አዲስ አበባ ያቀኑት ኦባንግም ሆኑ አብረዋቸው የተጓዙት የልኡካን ቡድን አባላት የተለየ የአቀባበል ስነ ስርዓት እንዲዘጋጅ ፍላጎት እንደሌላቸው ለዛጎል ተናገረዋል። ያጋራ ንቅናቄው ባህልም ነገሮችን በርጋታና በመርህ መመራት በመሆኑ አዲስ የሚቀየር ነገር የለም።

በቆይታቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ጊዜ የሚኖራቸው ሲሆን፣ ከተለያዩ የፖለቲካ መሪዎችና አግባብ ካላቸው የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ምክክክር እንደሚያደርጉ ለማወቅ ተችሏል። በሁሉም መድረኮች በአገሪቱ እርቅና ሰላም እንዲወርድ፣ አዲሲቷ ኢትዮጵያ በፍቅርና በመግባባት እንዲሁም በመቻቻል እንድትገነባ የሚያስችል ስራ ላይ ብቻ ትኩረት ይደረጋል።

ተንኮል፣ ጥላቻ፣ ድንቁርና፣ ውሸትን አጥብቀው የሚጠሉት ኦባንግ ሜቶ ለኢትይጵያ በረከት ተደርገው የሚወሰዱ ሰው ናቸው። በአንድ ወቅት ከጎልጉል ጋር ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ

Image result for obang metho

የወገኖቼን ችግር ለመቅረፍ የማደርገው ጥረት ልዩ እርካታ ይሰጠኛል። ሰዎችን ለመርዳት ተንቀሳቅሼ ምላሹ መልካም ዜና ሲሆን ደስታዬ ልዩ ነው። የልፋቴን ዋጋ ስመለከት ቀኑን ሙሉ በደስታ እንዳለቅስ ያደርገኛል። እንዲህ ያለውን እርካታ በሌላ በምንም መንገድ ላገኘው አልችልም። እንዲህ ያለው ደስታ ቀኑ ሁሉ የተባረከ እንዲሆን ያደርግልኛል…”  ለሁሉም ጊዜ አለው። ፍትህ ለጠማቸው ወገኖች በሚቻለው ሁሉ መድረስ ግድ ነው። የሌሎችን ኑሮና ስቃይ መካፈል ሰው የመሆናችን አንዱ መግለጫ ነው።በእውነት፣ በቀጥተኛው መንገድ፣ የተከታዮችን ልብ ሳንሰብር ማገልገል ለማንም የሚተው ሥራ አይደለም፡፡ ሁላችንም ያገባናል። ባገራቸው ጉዳይ ከሚያገባቸው ዜጎች መካከል አንዱ ነኝ። ማለታቸው ይታወሳል። ዛሬ ያ ጊዜ ደርሶ ኦባንግና ድብቁ የአኢጋን ልኡክ አዲስ አበባ ግብቷል። 

 

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: