Advertisements

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ነገ ማለዳ አዲስ አበባ ይገባል – አቀባበሉ የጋለ ነው

” ቅንጅት መንፈስ ነው ሲሉ የነብሩ አልተሳሳቱም ይላል” አያሌው ስሜነህ የሚባል የአዲስ አበባ ነዋሪ። መክንያቱን ሲገልጽ ብዙ ማብራሪያ የለውም። ግን ” በቃ ብርሃኑን አይቼ ልሙት” ነው የሚለው። እንደ እሱ ገለጻ የዶክተር ብርሃኑ እርምጃዎች ልክ የመንፈሳዊ ህይወት ያህል ይባርኩታል። ያረሰርሱታል። ለምን ሲባል አሁንም የሚለው ” የብሬን ፊት ማየት በቃኝ ” ሲል ነው የሚመለሰው። ያስዝነዋል።

የዶክተር ብርሃኑ እናት ” እንባ የሚባል ነገር ለአይኔ አላሳየውም” አሉ። ደስታ በሚፈስበት ፊታቸው ልጃቸውን ለማየት ቤታቸውን በድግስና በባህላዊ ጭፈራ አውዝተውታል። ትናንት ዛሬ አይደለምና ፋና ቴሊቪዥን ቤታቸው ግብቶ ጉራጊኛ እየጨፈረ ቤተሰብ የሚያደርገውን አቀባበል ዝግጅት አሳይቷል። በትልቁ ግቢ ውስጥ የአቶ አንዳርጋቸው ምስል ከልጃቸው ጋር በትልቁ ይታያል። የክትፎ  ጎመን ይከተፋል። ይጨፈራል። አዲሱ መሪ ለዚህ ቀን ምክንያት ሆነው ሲወደሱ ተሰምቷል።

አያሌው የዶከተር ብርሃኑ ፍቅር ቢንጠውም አርበኞች ግንቦት ፯ ለሱ ልክ ገኖ እንደከሰመው ቅንጅት ያህል ነው። ” በመጨረጫው የ፩፱፱፯ ማዕበል የድጋፍ ስልፍ የንብ ቆዳ ያለው እያልኩ እጮህ ነበር። ነገም ማልጄ አቀባበሉ ላይ እገኛለሁ። በህይወት ግባ በህይወት ግንቦት ሰባት እላለሁ” ሲል ነገን በጉጉት እንደሚጠብቅ ይናገራል።

የአቀባበሉንና የአገባቡን ሂደት አስመልክቶ ፋና እንዲህ ብሏል ። ነገ ማለዳ ወደ አዲስ አበባ ሲገባ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮችና አባላቶቹም ይኖራሉ ተብሏል፡፡ ነገ ማለዳ አርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ወደ አዲስ አበባ ሲገቡ የመዲናዋ ነዋሪ ደማቅ አቀባበል እንደሚያደርግም ይጠበቃል፡፡ አርበኞች ግንቦት 7 እስከአሁን ለውጡ የሄደበትን ርቀት በማጤን በሀገር ውስጥ ህጋዊና ሰላማዊ ትግል በማድረግ የተጀምረው የለውጥ ሂደት ወደ እውነተኛ ዘላቂ ለውጥ ለመሸጋገር የሚያስችል ሁኔታ አለ የሚል ድምዳሜ ላይ በመድረሱ ነው ወደ ሀገር ቤት የሚገባው፡፡

ነገ በሚደረገው የአቀባበል ስነስርዓትም ሀገራዊ አንድነትና መቀራረብ በሚያጎለብት መንገድ እንዲጠናቀቅ ጥረት ማድረግ እንደሚገባ የጠቀሱ ሲሆን ዕለቱ ፍቅር፣ መደጋገፍና መቻቻል የሚጎለብቱበት ጠላትነት፣ መራራቅንና መከፋፈል የሚሟሽሹበት ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ከዚህ ቀደም በኤርትራ ያለውን ወታደራዊ ካምፕ መዝጋቱ የሚታወስ ነው፡፡ መንግስት በውጭ ከሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ስምምነት ላይ መድረሱ ተከትሎ በውጭ ሀገራት የሚንቀሳቀሱ በርካታ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ መወሰናቸው ይታወሳል።

ከእነዚህ ውስጥ አርበኞች ግንቦት 7 ጨምሮ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)፣ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ)፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ተጠቃሽ ናቸው።

መንግስትም ነፍጥ አንግበው የነበሩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታጣቂዎች ትጥቅ የሚፈቱበትን፣ ከህረተሰቡ ጋር የሚቀላቀሉብትንና ዘላቂ ኑሮ እንዲመሩ ለማስቻልም በጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ውስጥ የመልሶ ማቋቋሚያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ተቋቁሟል።

Advertisements

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: