የከንቲባው ነገር – የመሳይ መኮነን ኑዛዜ


የዛሬ ሁለት ወር አከባቢ አዲስ አበባ አዲስ ከንቲባ አግኝታ ነበር። በወቅቱ ህግ ተዛንፎ፡ የአሰተዳደሩ ምክር ቤት አባል ያልሆነ ሰው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አዲስ አበባን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲሾሙ ተቃውሞዎች ተነስተው ነበር። በሁኔታው ቅሬታን ካሰሙት ሰዎች አንዱ እኔ እንደነበርኩ አስታውሳለሁ። የቲም ለማ አባል የሆኑት ኢንጀነር ታከለ ኡማ የኋላ ታሪካቸውን በማንሳትና በአንድ ወቅት የተናገሩትን በመጥቀስ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት እንዴት ሊመጥኑ ይችላሉ የሚለው ደርዝና ነጥብ ያለው ሙግት ያን ሰሞን አየሩን ተቆጣጥሮት ሰንብቶ ነበር።


የከንቲባው ነገርየዛሬ ሁለት ወር አከባቢ አዲስ አበባ አዲስ ከንቲባ አግኝታ ነበር። በወቅቱ ህግ ተዛንፎ፡ የአሰተዳደሩ ምክር ቤት አባል ያልሆነ ሰው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ አዲስ አበባን እንዲመሩ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ሲሾሙ ተቃውሞዎች ተነስተው ነበር። በሁኔታው ቅሬታን ካሰሙት ሰዎች አንዱ እኔ እንደነበርኩ አስታውሳለሁ። የቲም ለማ አባል የሆኑት ኢንጀነር ታከለ ኡማ የኋላ ታሪካቸውን በማንሳትና በአንድ ወቅት የተናገሩትን በመጥቀስ ለአዲስ አበባ ከንቲባነት እንዴት ሊመጥኑ ይችላሉ የሚለው ደርዝና ነጥብ ያለው ሙግት ያን ሰሞን አየሩን ተቆጣጥሮት ሰንብቶ ነበር። ባለፉት ሁለት ወራት ኢንጅነር ታከለ ያሳዩት የስራ ትጋትና ኢትዮጵያዊ መልዕክቶች ስለአዲሱ ከንቲባ ዳግም እንድናነሳ አስገድዶናል። ምንም እንኳን ለውዳሴና ሙገሳም ሆነ ለወቀሳና ትችት ጊዜውና ሁኔታዎች የፈጠኑ ቢሆንም የከንቲባው የሁለት ወራት አፈጻጸም በተለይም ባገኙት መድረክ የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች የመሪነት ብቃታቸውን የሚያሳዩ፡ በብዙዎች ልብ ውስጥ የተቀመጠውን ስጋት የሚገፉ፡ እውነትም ቲም ለማ ከክልል የተሻገረ ሀገራዊ ራዕይ አንግቦ ለመነሳቱ ማስረጃ የሚሆኑ ናቸው። ቲም ለማ ስራውን እየሰራ ነው።ኢንጅነር ታከለ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጥርጣሬን በሚያስወግዱ እንቅስቃሴዎች ተጠምደው እያየናቸው ነው። ቢሮ ተቀምጠው ከመስራት ይልቅ ጉራንጉሩን እየዞሩ፡ መንደር ሰፈሩን እየጎበኙ፡ ከደሀ ቤት እየታደሙ፡ ከተቸገሩት ጓዳ ድረስ እየዘለቁ መፍትሄ ለማፈላለግ ሲባትሉ ነው የምናውቃቸው። ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ችግር ስር የሰደደ መዋቅራዊ ከመሆኑ አንጻር ግዙፍ ስራዎች ከፊት የተደቀኑ ቢሆንም በኢንጅነር ታከለ እየተከናወኑ ያሉት እንቅስቃሴዎች ለነገው ትልቅ ተግባር መንገድ የሚጠርጉ፡ መተማመንን የሚፈጥሩ ናቸው ማለት ይቻላል። ለችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁስቁሶችን በማበርከት፡ መኖሪያ ቤት ላጡ የአዲስ አበባ ደሀ ቤተሰቦች ቁልፍ እየነጠቁ ባለቤት በማድረግ፡ አስተዳደራቸው ለበጎ ፍቃድ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጠው በሚያደርጉ የተለያዩ ስራዎች በመጠመድ፡ ከቀደምቶቹ ከንቲባዎች በተለየ ህዝብ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ለመሆናቸው በየዕለቱ ከዜና ማዕድ ከማይጠፋው ስማቸው መረዳት ይቻላል። ድንገት የከተማ አውቶብስና ባቡር ውስጥ ገብተው በአጋጣሚ ለሚያገኟቸው ተሳፋሪዎች የአውዳመት ስጦታ ሲያበረክቱ እንደነበረ ከሰሞኑ ሰምተናል። ኢንጅነር ታከለ በየመድረኩ የሚያስተላፏቸው መልዕክቶች ድንቅ ናቸው። ለታማኝ በየነ አቀባበል በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተናገሩት አዲስ አበባን በሰፊው የሚመለከቱ ከንቲባ መሆናቸውን አሳይተውበታል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችን በተቀበሉ ጊዜም ፕ/ር ብርሃኑን የገለጹበት መንገድ ከንቲባው ውለታ የማይረሱ፡ ታላላቆቻቸውን አክባሪ በመሆን በአርዓያነት የሚጠቀሱ፡ በብሄር ፖለቲካ የተወጠረውን አየር ማርገብ የመቻል አቅም እንዳላቸው ያሳዩ ሰው ናቸው። ”መምህሬና፡ የዕውቀት አባቴ” ብለው ለፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሰጡት የአክብሮት አገላለጽ ለከንቲባው ያለኝን አድናቆት የጨመረው ሆኗል። ከአፋቸው ተደጋግማ የማትጠፋው ኢትዮጵያም የከንቲባውን ሀገራዊ ስሜት አጉልቶታል ማለት የሚያስችል ነው። ከታች በሚታየውና ለአዲስ አመት በተዘጋጀው የእንኳን አደረሳችሁ አጭር የቪዲዮ መልዕክት ላይ ከንቲባ ታከለ ኡማ ስለአዲስ አበባ ያላቸውን ራዕይ እንድንረዳው አድርገዋል። አዲስ አበባን የሁሉም ፡ ሁለም የአዲስ አበባ ነው የሚለውን ወሳኝ መልዕክት ከከንቲባው አግኝቼአለሁ። አዲስ አበባን በሰፊው የተመለከቱበት፡ ባለቤትነቷም የተወሰነ የህበረተሰብ ክፍል ሳይሆን የሁለም ለመሆኗ በሚያምሩና ጠንከር ባሉ አገላለጾች ያንጸባረቁበት አጭር ቪዲዮ ትኩረቴን ስቦታል። ‘አዲስ አበቤነት አስተሳሰብ ነው’ የሚለው አቋማቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተነሳ ያለውን አቧራ የሚያሰክን ነው የሚል እምነት አለኝ። ከንቲባ ታከለ ኡማ እንኳን አደረስዎ! አዲስ አበባ የእኔም ናት። ከንቲባዋ እኔም ነኝ! ገለቶማ! መልካም አዲስ ዓመት!!!!!Posted by Mesay Mekonnen on Sunday, September 9, 2018

ባለፉት ሁለት ወራት ኢንጅነር ታከለ ያሳዩት የስራ ትጋትና ኢትዮጵያዊ መልዕክቶች ስለአዲሱ ከንቲባ ዳግም እንድናነሳ አስገድዶናል። ምንም እንኳን ለውዳሴና ሙገሳም ሆነ ለወቀሳና ትችት ጊዜውና ሁኔታዎች የፈጠኑ ቢሆንም የከንቲባው የሁለት ወራት አፈጻጸም በተለይም ባገኙት መድረክ የሚያስተላልፏቸው መልዕክቶች የመሪነት ብቃታቸውን የሚያሳዩ፡ በብዙዎች ልብ ውስጥ የተቀመጠውን ስጋት የሚገፉ፡ እውነትም ቲም ለማ ከክልል የተሻገረ ሀገራዊ ራዕይ አንግቦ ለመነሳቱ ማስረጃ የሚሆኑ ናቸው። ቲም ለማ ስራውን እየሰራ ነው።

ኢንጅነር ታከለ ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጥርጣሬን በሚያስወግዱ እንቅስቃሴዎች ተጠምደው እያየናቸው ነው። ቢሮ ተቀምጠው ከመስራት ይልቅ ጉራንጉሩን እየዞሩ፡ መንደር ሰፈሩን እየጎበኙ፡ ከደሀ ቤት እየታደሙ፡ ከተቸገሩት ጓዳ ድረስ እየዘለቁ መፍትሄ ለማፈላለግ ሲባትሉ ነው የምናውቃቸው። ምንም እንኳን የአዲስ አበባ ችግር ስር የሰደደ መዋቅራዊ ከመሆኑ አንጻር ግዙፍ ስራዎች ከፊት የተደቀኑ ቢሆንም በኢንጅነር ታከለ እየተከናወኑ ያሉት እንቅስቃሴዎች ለነገው ትልቅ ተግባር መንገድ የሚጠርጉ፡ መተማመንን የሚፈጥሩ ናቸው ማለት ይቻላል።

ለችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁስቁሶችን በማበርከት፡ መኖሪያ ቤት ላጡ የአዲስ አበባ ደሀ ቤተሰቦች ቁልፍ እየነጠቁ ባለቤት በማድረግ፡ አስተዳደራቸው ለበጎ ፍቃድ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጠው በሚያደርጉ የተለያዩ ስራዎች በመጠመድ፡ ከቀደምቶቹ ከንቲባዎች በተለየ ህዝብ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ለመሆናቸው በየዕለቱ ከዜና ማዕድ ከማይጠፋው ስማቸው መረዳት ይቻላል። ድንገት የከተማ አውቶብስና ባቡር ውስጥ ገብተው በአጋጣሚ ለሚያገኟቸው ተሳፋሪዎች የአውዳመት ስጦታ ሲያበረክቱ እንደነበረ ከሰሞኑ ሰምተናል።

ኢንጅነር ታከለ በየመድረኩ የሚያስተላፏቸው መልዕክቶች ድንቅ ናቸው። ለታማኝ በየነ አቀባበል በተዘጋጀው መድረክ ላይ የተናገሩት አዲስ አበባን በሰፊው የሚመለከቱ ከንቲባ መሆናቸውን አሳይተውበታል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችን በተቀበሉ ጊዜም ፕ/ር ብርሃኑን የገለጹበት መንገድ ከንቲባው ውለታ የማይረሱ፡ ታላላቆቻቸውን አክባሪ በመሆን በአርዓያነት የሚጠቀሱ፡ በብሄር ፖለቲካ የተወጠረውን አየር ማርገብ የመቻል አቅም እንዳላቸው ያሳዩ ሰው ናቸው። ”መምህሬና፡ የዕውቀት አባቴ” ብለው ለፕ/ር ብርሃኑ ነጋ የሰጡት የአክብሮት አገላለጽ ለከንቲባው ያለኝን አድናቆት የጨመረው ሆኗል። ከአፋቸው ተደጋግማ የማትጠፋው ኢትዮጵያም የከንቲባውን ሀገራዊ ስሜት አጉልቶታል ማለት የሚያስችል ነው።

ከታች በሚታየውና ለአዲስ አመት በተዘጋጀው የእንኳን አደረሳችሁ አጭር የቪዲዮ መልዕክት ላይ ከንቲባ ታከለ ኡማ ስለአዲስ አበባ ያላቸውን ራዕይ እንድንረዳው አድርገዋል። አዲስ አበባን የሁሉም ፡ ሁለም የአዲስ አበባ ነው የሚለውን ወሳኝ መልዕክት ከከንቲባው አግኝቼአለሁ። አዲስ አበባን በሰፊው የተመለከቱበት፡ ባለቤትነቷም የተወሰነ የህበረተሰብ ክፍል ሳይሆን የሁለም ለመሆኗ በሚያምሩና ጠንከር ባሉ አገላለጾች ያንጸባረቁበት አጭር ቪዲዮ ትኩረቴን ስቦታል። ‘አዲስ አበቤነት አስተሳሰብ ነው’ የሚለው አቋማቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ዙሪያ እየተነሳ ያለውን አቧራ የሚያሰክን ነው የሚል እምነት አለኝ።

ከንቲባ ታከለ ኡማ እንኳን አደረስዎ! አዲስ አበባ የእኔም ናት። ከንቲባዋ እኔም ነኝ! ገለቶማ! መልካም አዲስ ዓመት!!!!!

Advertisements

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.