Advertisements

ስለ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟት ከስሜታዊነት ፀድተን ሚዛናዊ አስትያየት መስጠቱ ይበጃል

የኢንጂነር ስመኘውን አሟሟት ከተለያዩ ሚዲያዎች ከተከታተልኩ አና ከአሟሟታቸው ጋር በተያያዝ ያሉትን ዂነቶች በደንብ ካገናዘብኩ በኋላ ገና የፖሊስ ምርመራ ውጤት ይፋ ሳይሆን እራሳቸውን ስለማጥፋታችው ምንም ያህል ጥርጣሬ አልነበረኝም ፡፡ በጣም የሚገርመኝ የነበረው ኢንጂነሩ በሰው እጅ ነው የተገደሉት ቢባል ነበር ፡፡

አንድ ሰው ድምዳሜ ላይ መድረስ ያለበት ያሉትን ተጨባጭ ሁኔታዎች በሙሉ በሎጂክ በማገናዘብ ግራ ቀኙን ከወገናዊነት በፀዳ መልኩ ሚዛናዊ ሆኖ በመርመር መሆን አለበት እንጂ እንዲሆን የሚፈልግውን ውጤት ብቻ የሚጠብቅ ከሆነ እውነታውን ለመቀበል ያስቸግረዋል፡፡

እኔ ከላይ ወደጠቀስኩት ድምዳሜ ላይ የደረስኩበት ዋናው ምክንያቶች ፡

1፡ በሰው ነው የተገደለው ከተባለ ገዳዮቹ ፊልም እየሰሩ ሳይሆን ወንጀል እየሰሩ መሆኑን አንዘንጋ ፡፡ ስለዚህ ህዝብ በሚበዛበት አደባባይ ላይ ይህንን ካባድ ጥንቃቄ የሚፈልግ ወንጀል ለማድረግ ያሚያስቡበት ምክንያት ያለ አይመስለኝም፡2፡ አላማቸው መግደል እስከሆነ ድረስ ምንም ሪስክ በሌለበት እና በማይጋለጡበት ቦታ ላይ  ከፈለጉ እዛው የሚሰራበት ግድቡ አካባቢ ወይም ከአዲስ አበባ ወደ ግድቡ በሚወስደው መንገድ ላይ ጠብቀው በቀላሉ መግደል እየቻሉ ይህንን የተወሳሰብ ወንጀል ሰርቶ የማምለጥ ዕድሉ አጅግ በጣም ጠባብ የሆነውን ድርጊት ያውም ሰው በሚበዛበት ቦታ ላይ ያደርጋሉ ብሎ ማሰብ ከባድ ነው፡፡

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ክሪቲካሊ ነገሩን አናላይዝ ከማድረግ ይልቅ በደፈናው መጀመሪያ ሌላ ቦታ ገድለውት ከዛ መስቀል አደባባይ አምጥተውት ነው ይላሉ፡፤ በማውራት ደረጃ ቀላል ሊመስል ይችላል ግን በተግባር ይቻላል ወይ?

እስቲ የሚናፈሱትን መላምቶች እንመርምራቸው ፡

1፤ መኪና ውስጥ ገብተው አስገደደውት ወይም አታለውት መስቀል አደባባይ አምጥተውት መኪናውን ካስቆሙት በኋላ ሽጉጡን ቀምተውት በእራሱ ሽጉጥ ገድለውት ሸጉጡን አስይዘውት የመኪናውን በር  በሪሞት ቆልፈው ሄዱ ፡፡

2፡ ሌላ ቦታ ገደሉት ካልን አስከሬኑን ይዘው መጥትው መስቀል አደባባይ ሲደርሱ የሹፌሩ ቦታ ላይ አስቀምጠውት ሽጉጡን አስይዘውት የመኪናውን በር  በሪሞት ቆልፈው ሄዱ ፡፡

ይህንን በለሊት ቢያደርጉት እንኳን ሊመስል ይችላል ግን  በጠራራ ፀሀይ  ይሀን ሁሉ ሲያደርጉ እንቅስቃሴያቸውን በአካባቢው በነበሩት ሰዎች እንዴት አልታየም? በጊዜው በአካባቢው የነበሩ ለቪቮኤ የአማርኛው ፕሮግራም ምሰክርነት የሰጡ  ሰዎች መኪናው አካባቢ አንድ ህፃን ልጅ እና አንድ ሰው እዛ አካባቢ ሲያንዣበቡ እንደነበር ግን ማንም መኪናው ውስጥ ሲገባም ሆን ሲወጣ እንዳላዩ ብዙ ልጆች እዛ አካባቢ ኳስ ሲጫወቱ እንደነበር ገልፀዋል  (http://www.tobiatube247.com/eye-witnesses-speak-about-engineer-simegnew-bekele-voa-amharic_cd1c4da1d.html) ፡፡ አሁንም በድጋሚ እዚህ ጋ ማንሳት ያለብን ዋናው ቁም ነገር ለምን መስቀል አደባባይ መምጣት አስፈለጋቸው? ማንም በህይወቱ ቁማር መጫወት የሚፈልግ የለም፡አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች በጭፍን እንደሚሉት ገዳዮቹ የፈለጉተን በፈለጉበት ቦታ ማድረግ እንደሚችሉ ለማሳየት ነው ይላሉ ፡፡ ይህ አባባል ግን እንዲሁ ለማለት ብቻ የተባለ ካልሆነ በስተቀር ምንም ውህ አይቋጥርም ፡፡ ምክንያቱም እንደዛ የማድረግ አቅም ቢኖራቸው ኖሮ ምስኪኑ ኢንጂነር ስመኘውን ሳይሆን ሰንት ጥርስ የነከሱባቸው የለውጥ አራማጆች አሉ እነሱ ላይ እርምጃ በወሰዱ ነበር፡

ሌላው የመኪናው ሞተር ሳይጠፋ በሩን መክፈትም ሆነ መዝጋት የሚቻለው በሹፌሩ በኩል ያለውን አውቶማቲክ በተን ፕሬስ በማድረግ ብቻ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡

ሌላው የሚነሳው አሉባልታ ደግሞ የፖሊሶቹ ታማኝነት ላይ ጥያቄ በማንሳት ፖሊስ በሰጠው መግለጫ ላይ ጥርጣሬ ያነሳሉ

1ኛ፡ መኪናው ጠዋት ይመጣ ወይመ ለሊት እዛው ይደር

2ኛ፡ ሞተሩ መጥፋት አለመጥፋቱ

3ኛ፡ የመኪናው በር ዝግ እንደነበር እና ፖሊሶች ሰብረው እንደከፈቱት

4ኛ፡ ፖሊሶች በደረሱበት ሰዓት ህይወቱ ገና እንዳልወጣች

ነገር ግን ከላይ እንደተጠቀሰው ለቪኦኤ ኢንተርቪው የሰጡት ሰዎች የተመለከቱትን ማስረጃ በማካፈል አረጋገጠዋል፡፡

ያም ሆኖ እስቲ ፖሊስ ትክክለኛውን የምርመራ ውጤት ደብቆ የተሳሳተ ድምዳሜ ነው የሰጠው ከተባለ ምንድነው ከጀርባው ሊኖር የሚችለው ምክንያት? ገዳዮቹ ከታወቁ ሊመጣው የሚችለው አደጋን በመፍራት? ወይስ የለውጡ ተቀናቃኞች ቀዳዳውን በመጠቀም መንግስት እና ህዝብን ለማጋጨት እንደሚያናፍሱት ግድያው ላይ የመንግስት እጅ ስላለበት?

በመጀመርያ ፖሊስም ሆነ መንግስት ይህን ያህል ከወንጀልም የከፋ ወንጀል እንደውም ኢንጂነር ስመኘውን ከመግደልም በላይ የከፋ ድርጊት በመፈፀም ለሀገሩ ሲል የደከመውን እና ሀይወቱን የገበረውን ጀግና ስም በማጉደፍ ይሀንን መግለጫ ይሰጣል ብለን የምናስብ ከሆነ በጣም ተሳስተናል፡፡

ዶ/ር አቢይ እኮ ነው እየመራን ያለው እንኳን የኢንጂነር ስመኘውን ገዳይ ለመደበቅ ይቅር እና 27 አመታት ሙሉ መንግስት ሲፈፅም የነበረውን ግፍ እና በደል ምንም ሳይፈራ ነው ያዝረከረከው፡፡ ገዳዮቹ ምን እንዳያመጡ ነው? መንግስት በመጀመርያ ደረጃ ኢንጂነሩን የሚገልበት ምንም ምክንያት ሊኖር የሚችል አይመስለኝም ፡፤ እንደውም የኢንጂነሩ መሞት መንግስትን በብዙ መልኩ ይጎዳዋል፡፡  ለላው ቀርቶ የግድቡን ገንዘብ እንደልባቸው ሲመዘብሩ የነበሩት ግለሰቦችን ተጠያቂ ለማድረግ  በቂ መረጃ እንኳን እንዳይገኝ ነው የሚያደርገው፡፡ የመንግስት እጅ አለበት ቢባል እንኳን መንግስት ነጉሩን ይህን ያህል ማወሳሰብ ሳያስፈለገው በሰው እጅ ነው የተገደለው ገዳዩን ለመያዝ አስፈላጊው ሁሉ እየተደረገ ነው ይላል አለቀ ፡፡ በተጨማሪም መስቀል አደባባይም ያን ያህል ትርዒት ማሳየት አያስፈልገውም፡፡

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መረዳት እንደቻልኩት የህወሀት መንገስት ላለፉት 27 አምታት ሲያደርግ የቆየው ወንጀል እና የተቀነባበረ ድራማ በአመለካክታቸው ላይ ተፅዕኖ ሰላሳደረባቸው ሁሉንም ነገር በጥርጣሬ እንዲመለከቱት ተገደዋል፡፡ በጥርጣሬ መመልክቱ ባልከፋ ግን በማስተዋል እና ምክንያታዊ መከራከርያ በመስጠት ከስሜታዊነት ነፃ በመሆን ገንቢ አስተያየት በመስጠት ጊዜአችንን ብናጠፋ ይሻላል፡፡

ፅሁፌን ከማጠናቀቄ በፊት ግን ለሀበሻ ዜና አዘጋጆች ምንም እንኳን ለእናንተ አክብሮት ቢኖረኝም የፖሊስ የምርመራ ውጤት ከመውጣቱ በፊት ያሰራጫችሁት ዜና ሙያዊ ስነምግባር የጎደለው እና የራሳችሁን አስተሳሰብ ሌላው ላይ ለመጫን ያለምንም ተጨባጭ መረጃ ህዝቡን እንድምትውከሉ እራሳችሁን ቆጥራችሁ ፖሊስ ሰለ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟት የሚሰጠውን የምርመራ ውጤት አብዛኛውን ኢትዮጵያውያ ሊያሳምን  አይችልም ያላችሁት ከየትኛው ጥናታዊ መረጃ ተነስታችሁ ነው። ዘም ብሎ እኮ ከመሬት ተነስቶ ያለምንም መረጃ የተፈለገውን ዜና መዘገብ የሙያ ግድፈት ነው፡አላስፈላጊ አንባቢን ቢያዝድ ማድረግ ትክክል ስላልሆነ ክዚህ ድርጊት በመቆጠብ በሃላፊነት መዘገብ አለባችሁ፡፤ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሚመስላችሁን የራሳችሁን አስትያየት ከመስጠት ውጪ ሌላውን ወክላችሁ መናገር የምትችሉት ፕሮፊሽናል በሆነ መንገድ ጥናት አድርጋችሁ በስታቲስቲክ የተደገፈ መረጃ ማቅረብ ስትችሉ ብቻ ነው፡፡

እግዚአብሄር አምላክ የወንድማችንን ነፍስ በአብርሀም እና በይስሀቅ ጎን ያሳርፍ፡፡ አሜን !!

በደሉ ብዛብህ

If you want to share your comment directly, please use the below email address bezabihbedelu2018@gmail.com

Advertisements


Categories: opinion/ ምልከታ

Tags:

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: