Advertisements

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት በቡራዩና አከባቢዋ በደረሰው የህይወትና ንብረት ውድመት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ገለጸ

 የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት በቡራዩና አካባቢዋ በተፈጠረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማው ተገለጸፀ።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በቡራዩና አከባቢዋ የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው ነው የተናገሩት።

ርዕሰ መስተዳድሩ ከተፈናቀሉት ውስጥ 300 አባወራዎች ወደ ቀያቸው መመለሳቸውን ጠቅሰው፥ ቀሪዎቹንም ወደ ቀያቸው ለመመለስና መልሶ ለመቋቋም የክልሉ መንግስት ሙሉ ኃላፊነት ወስዶ ይሰራልም ብለዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በግጭቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ከ200 በላይ ተጠርጣሪዎችና የተለያዩ የጦር መሳርያዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስታውቀዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ግጭቱን ወደተለያዩ አከባቢዎች ለማዛመት መሞከሩንም ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር ባደረገው ትብብር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አንስተዋል።

ይህንን ግጭት ሌላ መልክ በመስጠት ወደ አሰላ አከባቢ ለማስፋፈት መሞከሩንም ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡ በሰከነና ማስተዋል በታከለበት ሁኔታ ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም ተናግረዋል።

ከፌደራልና ከኦሮሚያ ፖሊስ የተውጣጣ ግብረ ኃይል ተዋቅሮ ያሉትን ሁኔታዎች ለማርገብና እንዲሁም ወደፊት ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎችና አክቲቪስቶች የሚያስተላልፉት መልዕክት ህዝቦችን የሚያቀራርብ ወደ አንድነት እንዲመጣ የሚያደረግ እንጂ የሚያለያይ ሊሆን እንደማይገባም አቶ ለማ አሳስበዋል።

መንግስት ነገሮችን በትዕግስት የሚያልፍበት ሁኔታ እንደማይኖርም ርዕሰ መስተዳድሩ አጽንዖት ሰጥተው ማንሳታቸውን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

(ኤፍ.ቢ.ሲ)

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: