Advertisements

ከፍተኛ ጎርፍ በአሜሪካ የባህር ዳርቻ ከተማ የሆነቸውን ዊልምግተን ከተማን ከሌሎች ግዛቶች ለያት

ከፍተኛ ጎርፍ በአሜሪካ የባህር ዳር ከተማ የሆነቸውን ዊልምግተን ከተማን ከሌሎች ግዛቶች እንዳትገናኝ ማድረጉ ተገልጿል።

በሰሜን ካሮሊኒያ ባህር ዳርቻ ላይ የምተገኘው ዊልምግተን ከተማን ጎርፍ ከሌሎች የአሜሪካ ግዛቶች እንዳትገናኝ እንደደረጋት የተገለጸ ሲሆን፥ ከከተማዋ ለመውጣትና ወደ ከተማዋ ለማግባት የሚያስችሉ መንገዶድ በሙሉ በጎርፍ መያዛቸው ተገልጿል።

በዚህም ከከተማዋ ለተለያዩ ጉዳዮች የወጡና በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች በያሉበት እንዲቆዩ ጥሪ መተላለፉ ነው የተገለጸው።

የ120 ሺህ ያህል ዜጎች መኖሪያ የሆነችው የዊልምንግተን ከተማ አሁን ላይ እንደ ደሴት ከሌሎች ግዛቶች ተነጥላ እንደምትገኝ ታውቋል።

በጎርፍ አደጋው በአብዛኛው የከተመዋ አካባቢዎች ሃይል የተቋረጠ ሲሆን፥ 400 ያህል ዜጎች የጎርፍ አደጋ ስጋት ላይ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

የጎርፍ አደጋ ስጋቱ ለሚቀጥሉት 2 ቀናት ቀጣይነት እንደሚኖረውም የሀገሪቱ ብሄራዊ የሚትሮሎጂ ትንባያ ማመላከቱም ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ bbc (ኤፍ.ቢ.ሲ)

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: