Advertisements

“አብዲ ኢሌ አስገድዶ ነው ብሩን የሠጠኝ እንጂ እኔ ፈልጌው አይደለም የወሰድኩት!” አቶ አህመድ ሺዴ

ይህንን አስቅኝና አሳዛኝ መልዕክት ያገኘነው ከራጆ ላይ ነው። ራጆ / Rajo በሶማሌ ክልል የጠራና ተአማኝ ሪፖርቶችን የሚያቀርብ መድረክ ነው። በርካታ ጉዳዮችን ሲዘግብ ያስተባበለው የለም። ይህንን አስገራሚ ታሪክ ከታች ባለው የቪዲዮ ማስረጃ ጋር አባሪ በማድረግ ሲያትም፣ አስቀድሞ ፍንጭ መስተቱንም አስታውቋል። ማጣራት የመንግስትና የክልሉ አዲስ ካቢኔ ጉዳይ ነው። ከራጆ የተወሰደው ጽሁፍ ሙሉ በሙሉ እንደዚህ ይነበባል።

“እኔ ብሩን አብዲ ኢሌ አስገድዶ ነው የሠጠኝ እንጂ እኔ ፈልጌው አይደለም የወሰድኩት!” አቶ አህመድ ሺዴ ከአብዲ ኢሌ ለምን ከግማሽ ቢልዮን ብር በላይ እንደወሰደ ሲጠየቅ የሰጠው አስቂኝ መልስ!

ከሁለት ቀን በፊት አቶ አህመድ ሺዴ ከግማሽ ቢልዮን (500 ሚልዮን) የሚደርስ ብር ከአብዲ ኢሌ መውሰዱን ገልፀን ነበር፡፡ ከብሩ መብዛት የተነሳ ይመስላል ብዙዎች የፃፍነው ለማመን ተቸግረዋል፡፡ ይህም የሚንረዳው ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን እኛ ከጠቀስነው ብር በላይ መውሰዱ እርግጥ መሆኑ ነው፡፡ ማረጋገጥ ይቻላል ወይ? አዎን በደንብ ይቻላል፡፡ በተለይ እነዝህን ሁለቱን፡፡ ምክንያቱም የአብዲ ኢሌ ርዥራዥ ባለስልጣናት በሚገመገሙበት ወቅት እሱም ከነርሱ ጋር በሙስና መዘፈቁን በሰነድ ማስረጃ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ አህመድም ገንዘቡን መውሰዱን እንድህ ብሎ አረጋግጧል፡-“እኔ ብሩን አብዲ ኢሌ አስገድዶ ነው የሠጠኝ እንጂ እኔ ፈልጌው አይደለም የወሰድኩት!”
1. 140 ሚልዮን የቀብርደሃር ቴክንክ ኮሌጅ ለማሰራት በእህቱ ቀድራ አማካኝነት ወስዷል፤
2. 350 ሚልዮን ከተፋሰሶች ቢሮ አሁንም በእህቱ አማካኝነት ተቀብሏል፡፡ መሬት ላይ የሠሩት ምንም ነገር የለም፡፡

የጠቀስነው 50 ሚልዮን አብዲ ኢሌን ከቲም አብይና ለማ ጋር ለማስማማት ብሎ የተቀበለው የሚለውን ማስረጃ ያገኘነው ከአብዲ ኢሌ ቅርብ ሰዎች ነው፡፡ እንደሚታወቀው አብዲ ኢሌ ከዶ/ር አብይና ለማ ጋር ለመስማማት ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡ ከጥረቶቹም የሚጠቀሰው በቲቪ ቀርቦ ወንጀል እንዲፈፅም ያስገደደኝ አቶ ጌታቸው አሰፋ ነው ማለቱን፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ለፕሬዝዴንት ኢሳያስ አፈወርቂ ግመል በስጦታ መልክ እንዲሰጠው ሀሳብ ያቀረበው አቶ አህመድ ሺዴ ናቸው፡፡ ከዝህ ሁሉ የሚከፋው ደግሞ አብዲ ኢሌ በሥልጣን እንዲቆይ አቶ አህመድ ሺዴ መተት በሚሰራው ዘመዱ አማካኝነት ለአብዲ ኢሌ መተት ማሰራቱን በወቅቱ ረጆ መዘገቧ ይታወሳል፡፡ ደግነቱ እውነት የመጣ ግዜ መተት ድራሹ ይጠፋል እናም መተቱ ሳይሰራ ቀርቷል፡፡ በዝህ ሳቢያ የ50 ሚልዮኑን ጉዳይ አቶ አህመድ ሺዴ መቀበላቸውን ሊናምን በቅተናል፡፡ እዝህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ሙስና ብዙ ግዜ ማስረጃ የለውም፡፡ መውሰዱን የሚናውቅ ቢሆንም እንኳ፡፡

አብዲ ኢሌ የሴይጣን ቁራጭ መሆኑን ማንም አይክደውም፡፡ ለምን አህመድ ሺዴን በተደጋጋሚ ለሚኒስቴርነትና ለምክትልነት አጨው ለምንስ ይህን ያህል ብር ሰጠው አብዲ ኢሌ ብር እንድሁ አይሰጥም ምክንያት ይኖረዋል የቬኒሱ ነጋዴ የተሰኘው የዊሊያም የሸስፒር ስራ ሻይሎክ የተሰኘው ጨካኝ አራጣ አበዳሪ አይሁድ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ለሰጠውም ገንዘብ በምላሹ ስጋን (ነፍስን) ቢሆን ይጠይቃል፡፡አቶ አህመድ ሺዴ ለተሰጠው ገንዘብና የፌዴራል ቦታውን አስጠብቆ እንዲቀጥል ለአብዲ ኢሌ ምን ሥራ ሠርቶለታል? ጥያቄው ይሄው ነው መልሱን ደግሞ ከታች ያገኙታል፡፡

1. አብዲ ኢሌ በሥልጣን እንዲቆይ አህመድ ሺዴ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ አብዲ ኢሌ ያን ሁሉ ጥፋት ሲያጠፋ እንዳላየ በመሆን የአብዲን ጥሩነት ሲያቀነቅን እንደነበር ከታች ያለውን ቪድዮ በማየት መመስከር ይቻላል፡፡ ሶማሊኛን መናገር ለማይችሉት ዋናው መልዕክቱ አብዲ የሚቃወሙት ሰዎች ክልሉን የደረሰበትን ዕድገትና ሰላም የሚቃወሙ ጠላቶች ናቸው ብሎ ነው የሚደሰኩረው፡፡
2. በፌዴራል የአብዲ ኢሌ ስም ገንኖ እንዲወጣና በክልሉ የተንሰራፋውን ሕግ-አልበኝነትንና ሙስና እንዳይነገር ማነቆ ሆኖ ቆይቷል፡፡
3. አብዲ ኢሌ ከመውረዱ በፊት እንኳ የመንግስት ሚድያዎች ስለ አብዲ ኢሌ ተቃዋሚዎች ምንም ነገር እንዳይነገር የበታቾቹን አስጠንቅቋል፡፡
4. የፌዴራል ባለስልጣናት ከክልሉ ገንዘብ ፈሰስ እንድደረግላቸው የደላላነት ሥራ ሰርቷል፡፡
ለአቶ አህመድ ፍትሃዊና ሚዛናዊ ሆነን ለመዘገብ ፈልገን አንድ እንኳ በጎ ነገር ለክልሉ ሰርቷል የሚለን ሰው ሊናገኝ አልቻልንም፡፡ እውነታው አቶ አህመድ ሺዴ ላለፉት 20 ዓመታት ክልሉን ሲመዘብር የኖረ ግለሰብ ነው፡፡ አሁን ደግሞ የወሰደውን ብር መመለስና ለፍርድ መቅረብ እያለበት የክልሉ ገዥ ፓርቲ ሊቀ-መንበር ሆኖ ተሰይሟል፡፡ የፌዴራልም ባለስልጣን ናቸው፡፡ የዶ/ር አብይ ሙስናን እዋጋለሁ የሚለውን አቋማቸው የሚረጋገጠው የያዙትን ሌባ ከሥራ ሲያሰናበቱ ነው፡፡ ቢልዮን የበላ ሌባ እያለ በሺዎች የበላን ሌባ ማሳደድ በራሱ ጡር አለው፡፡

ፍትህ ለሶማሊ ሕዝብ! ሌቦች ከስልጣናቸው ይነሱ!

Rajo

Advertisements

Zaggolenews. የዛጎል ዜና

Editor of zaggolenews.com contact editor - zaggolenews2016@gmail.com

You may also like...

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

%d bloggers like this: