May 20, 2020

ኮቪድ 19 ማረሚያ ቤቶች አልደረሰም፤ 24 አዲስ ተጠቂዎች ተገኙ!!

 የኮሮናቫይረስ በአንድም የሀገሪቱ ማረሚያ ቤት በሚገኝ ታራሚ ላይ አለመገኘቱን የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ለፋና እንዳረጋገጠው፥ ኮቪድ-19 በልደታ ክፍለ ከተማ በሚገኝ በአንድ በፖሊስ ጣቢያ በእስረኞች እና ጉዳያቸውን በሚያስፈፅሙ ሰዎች መካከል በተፈጠረ ንኪኪ በአንድ የቫይረሱ ታማሚ ምክንያት 66 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብሏል። ከዚህ ውጭ “በማረሚያ ቤት በሚገኙ የህግ ታራሚዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል” በሚል የተናሰፈው ምረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

በሌላ ዜና በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ3 ሺህ 460 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ የተኘባቸው ሲሆን፥ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ቫይረሱ ባለፉት 24 ሰዓታት ለ3 ሺህ 460 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 24 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ። ከዚህ ውስጥ 18 ወንድ ስድስቱ ደግሞ ሴት ሲሆኑ፥ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው ተብሏል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች እድሜያቸው ከ4 እስከ 58 አመት የሚገኙ መሆናቸውንም ሚኒስተሯ አስታውቀዋል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 9 ከአዲስ አበባ፣ 7 ከትግራይ ክልል እንዲሁም 8 ሰዎች በአማራ ክልል መተማ ለይቶ ማቆያ ያሉ ናቸው።

ከእነዚህ ውስጥ 12ቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ፥ ስምንቱ ደግሞ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት የነበራቸው ናቸው። እንዲሁም አራት ሰዎች ደግሞ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክም ሆነ ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ተገልጿል። ሚኒስትሯ አዲስ ያገገሙ 2 ሰዎች መኖራቸውን ጠቅሰው፥ ይህም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥርን 122 እንዳደረሰው ገልጸዋል።

#FBC

Leave a Reply

%d bloggers like this: