May 23, 2020

የከፉው ጊዜ በደጅ – ! 61 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቁ መልካም ዜና – ” እንኳን ደስ አላቹህ” ይኸው ነው!

A gravedigger opens new graves with an excavator as the number of dead people rose after the coronavirus disease (COVID-19) outbreak, at Vila Formosa cemetery, Brazil's biggest cemetery, in Sao Paulo, Brazil, April 2, 2020. REUTERS/Amanda Perobelli

የህክምና ባለሙያዎች እጅ ሰጡ። ሁሉን አደረጉ ድል ግን የለም። ሽንፈትን አስተናግደው ቤታቸው መቅረትን መረጡ። የ52 ዓመቱ ሆዜ እህት እንባዋ እየተንቆረቆረ ጉሮሮዋን ሳግ እያነቃት ” እንዲህ ሆነ በቃ” አለች። መቃብር ቆፋሪው በዶዘር አፈር ይዝቃል። ” ዘወትር እየጸለይኩ ጉድጓድ እቆፍራለሁ፤ አማራጭ የለም ” ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ዓለም ወደ ጅምላ መቃብረነት እየገሰገሰች ነው። እኛም አገር ባለሟዎች የማይዝሉበት፣ የማይደክሙበት፣ የማይወድቁበት፣ ተአምር የለም። መሪዎችም በዚህ ወቅት ሌላ ተደራቢ ፈተና ሊያዝላቸው ይችላል። ቫይረሱን ብቻ ሳይሆን ሁሉንም ጉዳይ በጥበብ ማየት ግድ ነው። ዛሬ ላይ የፖለቲካም ሆነ የቅሸባ ንግድ አያምርም!!

ዛጎል ዜና – ሃዘን በላያችን ላይ አጥልቶ በስልጣን ግብግብ ሃብትና ጊዜ የምታባክን አገርና ያልታደለ ሕዝብ፣ ” ደሙን እኔ አወራርዳለሁ” በሚል የስልጣን ስካር አምራች ዜጎችን ወደ ሞት፣ ቤተሰቦችን ወደ ሃዘን የሚነዱ ሴረኞች የሚያነፍሯት ሀገር፣ በስማ በለው የሰሙትን ሁሉ የሚያግበሰብሱ ውርጋጮች የሚያናፉባት፣ አስተዋዮችና ምክንያታዊ ዜጎች የሚገፉባት፣ ባንዶችና ለከርሳቸው ቅድሚያ የሚሰጡ ጀግኖች የሚባሉባት፣ አራጆችና ነብሰበላዎች ” እኔም እገሌ ነኝ” በሚል የሚሞካሹባት ምድር ዛሬ የከፋው በደጇ ዜጎቿን ሊበላ በደጅ ደርሷል። ከበባውን አተናክሮ ወደ ጉድጓድ መማስ ሊያዛውረን ነው። ምን ቀረ? 

ልብ እንበል ኢትዮጵያ እስከ ዛሬዋ ቀን ድረስ ምርመራ ያካሄድችው ለ76962 ዜጎች ብቻ ነው። ከ120 ሚሊዮን ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር ምርመራ የተደረገላቸው ወገኖች በስንጥር እንኳን አይለኩም። እስከ 28 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በወረርሺኙ እንደሚጠቁ ግምት አለ። ይህንን ግምት ያኖሩ ባለሙያዎች ” ሟርተኞች፣ ለገዢው መንግስት ያጎበደዱ፣ አማራዎች፣ የቀድሞ ስርዓት ናፋቂዎች፣ አሃዳዊ መንግስት ለማስፈን የሚሰሩ …” እየተባሉ ይወገዛሉ። የተተፋውን ሁሉ የሚውጡ ክፍሎች ይህንኑ የስልጣንና የተቃውሞ አባዜ ያሰራጫሉ። ሰው ግራ ያጋባሉ። ያሳክራሉ። 

የህክምና ባለሙያዎች እጅ ሰጡ። ሁሉን አደረጉ ድል ግን የለም። ሽንፈትን አስተናግደው ቤታቸው መቅረትን መረጡ። የ52 ዓመቱ ሆዜ እህት እንባዋ እየተንቆረቆረ ጉሮሮዋን ሳግ እያነቃት ” እንዲህ ሆነ በቃ” አለች። መቃብር ቆፋሪው በዶዘር አፈር ይዝቃል። ” ዘወትር እየጸለይኩ ጉድጓድ እቆፍራለሁ፤ አማራጭ የለም ” ሲል ለቢቢሲ ይናገራል። ዓለም ወደ ጅምላ መቃብረነት እየገሰገሰች ነው። 

ለጤና ባለሙያዎች ተቆርቋሪ በመምሰል በጎሳና በክልል እንዲደራጁ በማድረግ ህዝብን የሚያዥጎረጉር መረጃ ያሰራጫሉ። እንደ ዶክተር ሊያ አይነት ጀዝመኛ ታታሪ ባለሙያዎችን በሾርኔ ይቀሽባሉ። እስኪ የዛሬውን ግርድፍ መረጃ እንመለከት። በ24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ የ3 ሺህ 757 የላብራቶሪ ምርመራ 61 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ይህንን የነገሩን ዶክተር ሊያ ናቸው። ትናንት 34 ነበር ዛሬ 61። ወደ ጣሊሊያን እንሂድ።

ጣሊያን ይህ እስከተጻፈበት ጊዜ ድረስ ከ61 ሚሊዮን ገደማ ህዝቧ ውስጥ 3 ሚሊዮን318 ሺህ 778 ዜጎቿን መርምራለች። አንድ ሁለት እያለ የጀመረው ወረሺኝ በዲሰምበር 23 ቀን 71ተጠቂዎች የተመዘገበበት ነበር። እስከዚህ ቀን ድረስ የሞተው አንድ ሰው ብቻ ሲሆን ከአንድ ወር በሁዋላ ማለትም ማርች 21 ቀን 6557 አዲስ ተጠቂዎች ተመዝግበዋል።  ይህ የቀኑ ተጠቂዎች ዳታ ብቻ ነው። 

ፌብሩዋሪ 23 ተመዝግቦ የነበረው የአንድ ሰው ሞት፣ በማርች 8 ወደ 133 ሄደ። በማርች 27 ደግሞ 919 ዜጎቿን ቀጠፈ። በዚህ ሁሉ ፈተና ውስጥ ጣሊያኖች ዓለም ያስተማሩት ግድየለሽነት ጉድ እንደሰራቸው ሲሆን፣ ከዚያ በላይ ግን የሙት ቡፌ መረጣ ውስጥ የመግባታቸው አስከፊ ዜና ነው። 

በጣልያን ጎረምሶች መስሚያቸው ተደፍኖ ቫይረሱን እያፈሱ ለእናቶቻቸው፣ አባቶቻቸውና አያቶቻቸው አራገፉ። በአዛውንቶች የህክምና ጣቢያ የሚሰሩ በተመሳሳይ ቫይረሱን ሰብስበው በማገገሚያና መቆያ ለሚኖሩት አቅመ ደካሞች አዳረሱ። በውጤቱ ለምቅበር እስኪያቅት ደረስ ጣሊያኖች ረገፉ። ሰው እንደ ቆሻሻ በጭነት መኪና እየተለቀመ በጅምላ መቃብር ተደፋ። ጣሊያን ሃዘን ገነደሳት። መንግስት፣ ባለሙያዎች፣ አዋቂዎች … ሁሉም ለሞት እጅ ሰጡ። ግልሙትና የነገሰባት አገር እጇን ወደ ፈጣሪ አነሳች። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ” አሁን ተሳፋው ከሰማይ ነው። አልቻልንም” ሲሉ በዓለም ፊት አነቡ። ዛሬ ተንፈስ ብለዋል።

ሌሎች አገሮችንም ማንሳት ይቻላል። እንግዲህ ይህ ወረርሺኝ ጣልያንን እንዲህ አስደግድጓል። አሜሪካን፣ ሩሲያና ብራዚል ከፊት መስመር ሆነው ገፈቱን እየተጎነጩት ነው። ይህ ሁሉ የሚሆነው ምድራችን ላይ፤ እያየን፣ እየሰማን፣ የሞት መርዶ ቢሆንም ደጋግመን እያጣጣምነው ነው። ከዚህ ሁሉ ጋር ተዳምሮ ዓለም ዓለም አቀፋዊነቷ ቀርቶ ከመንደር ወርዳ ሳሎንና ጓዳ ስትሆን የሚደርስባት ኪሳራና የኪሳራው ወላፈን እንዴት እንደሚያደርገን ከአንዱ በስተቀር የሚያውቅ የለም። እንደገናም መልሶ ወረርሽኙ ገጀራውን ላለማንሳቱ ማረጋገጫ የለም።

ይህ ልብን የሚያርድ፣ አናትን የሚያዞር፣ ህሊናን የሚያደማ ጉድ ውስጥ ሆነን ነው ፖለቲከኛ የሚባሉት ” ይህ ዓመት ካለፈ ክልል ይፈርሳል፣ ቀበሌ ይፈርሳል፣ መንግስት ይፈርሳል…” የሚሉን። እኛ ካልመራን በሚል የቱሃን ፖለቲካቸውን ሴራና ” ደሙን እኔ አወራርዳለሁ” በሚል የምስኪን ልጆችን ለመገበር የቋመጡ ተጋምደው ከየአቅጣጫው የትፉብናል። ጊዜው አሁን ነው በሚል ከጠላት ጋር አብረው እየተደጋገፉ ያስታውኩብናል። ጭፍሮቻቸው ያሰራጫሉ። የገባውም ያልገባውም ተቀብሎ ያከፋፍላል። ልክ እንደ ዛይረሱ!!

ዛሬ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 494 ደርሷል፡፡ አዲስ 61 ቫይረሱ የተገኘባቸው ከ15 እስከ 70 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። 48 ከአዲስ አበባ ፣ 3  ከአፋር ፣ 1 ከአማራ ክልል ፣ 7 ከሶማሌ፣ 2 ከኦሮሚያ ክልል ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 11 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ አላቸው ፣ 5 ሰዎች በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንኪኪ የነበራቸው ሲሆን 45 ሰዎች ግን ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን ዶክተር ሊያ አስታውቀዋል።
በተቃራኒው ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 23 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 151 ነው ተብሏል። ኢትዮጵያ እስከአሁን ድረስ 76 ሺህ 962 የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማከናወን እንደቻለች የሚኒስትሯ እለታዊ ሪፖርት ያስረዳል።
ይህ ምን ይነግረናል? የሰሞኑ የወረርሽኙ ዳታ መተኮስ ምን ያሳያል? በዚህ አካሄድ ከቀጠለ ምን ይደረጋል? ባለን የተንገዳገደ ኢኮኖሚ የከፋውን ጊዜ እንችለዋለን? ይህ ሁሉ እየሆነ ለስልጣን መባላቱ ይስኬዳል? ከመስከረም በሁዋላ አገር ይፈርሳል በሚል አገሪቱን ወድ ሽፍታ አስተዳደር ለማዛወር መጣደፍ ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አይታይም? የከፋ ጊዜ በደጅ እንዳለ አይሰማንም? ህዝብ ሆይ ለራስህ ስትል፣ ለናትህና አባትህ ብሎም ለአያቶችህ ስትል፣ ለልጆችህ ስትል ከዚህ ጉድ የሚአሻግረውን መንገድ ምረጥ!! ህዝብ እንጂ ተራራና ሜዳ ላይ መንገስ ስለማይቻል እናንት በስልጣን የሰከራቹህ ሃይሎች እባካችሁን አደብ ግዙ!! የሰማችሁትን ሁሉ እየዋጣቹህ በየሚዲያው አትትፉ!! በሁዋላ ለንስሃም አይመችም!!
 
Photo – A gravedigger opens new graves with an excavator as the number of dead people rose after the coronavirus disease (COVID-19) outbreak, at Vila Formosa cemetery, Brazil’s biggest cemetery, in Sao Paulo, Brazil, April 2, 2020. REUTERS/Amanda Perobelli

Leave a Reply

%d bloggers like this: