May 23, 2020

የአዲስ አበባ አስተዳደር ከ1997 – 2007 ለነበረ ውዝፍ የግብር እዳ ምህረት ሰጠ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ በታክስ እዳ ማቅለያ እና ገቢ መሻሻያ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሣኔ አሥተላልፏል፡፡በዚሁ መሠረት:-

– ከ1997- 2007 ግብር ዘመን ውዝፍ እዳ ለነበረባቸው ግብር ከፋዮች እዳው በምህረት ቀሪ እንዲሆን፣

– ከ2008 – 2011 ግብር ዘመን እዳ ላለባቸው ግብር ከፋዮች ቅጣትና ወለድ ተነሥቶ ፍሬ ግብር በቻ እንዲከፍሉ ተወስኗል።

ካቢኔው በተጨማሪም ቤታቸው ለተቀመጡ ሠራተኞች ደሞዝ ለሚከፍሉ ድርጅቶችና ግለሠቦች እንዲሁም ለተከራዮቻቸው የኪራይ ቅናሽ ላደረጉ አከራዮች የታክስ ጫና ማቃለያ ውሣኔዎች አሥተላልፏል፡፡

በሌላ በኩል የከተማዋን ገቢ ለማሻሻል ሁሉም ሴክተር መስሪያ ቤቶች ያላቸውን አቅም በዝርዝር ፈትሸው ለከተማዋ ገቢ እድገት በቅንጅት መስራት በሚቻልበት ዙሪያና አፈፃፀሙንም የቅርብ ክትትል የሚደረግበት መንገድ ላይ ተወያይቷል።

የታክስ መሰረትን በማስፋትም በተለይም ማዘጋጃ ቤታዊ እና የከተማ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን አቅምና አስራር በተሻለ መልክ በማደራጀት የ2013 ዓም በጀት በመካከለኛ ገቢ ምጣኔ መሰረት ተዘጋጅቶ ለውይይት እንዲቀርብ መወሰኑን ከከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም

Leave a Reply

%d bloggers like this: