May 23, 2020

አና- ሮማኒያዊቷ የውሲብ ገበያተኛና ጄነራሉ በዲሲ ሳክስ ላውንጅ

በወቅቱ የትዕይንቱ ማብቂያ ግድም ላይ እንዳየሁዋት ጸጉሯ የልጥልጥ ነጭ ፈረስ ጋማ ይመስላል። ሰውነቷ ሙሉ ነው። እንደ ሰጋር በቅሎ የምትሰግር ምርጥ ሞያተኛ ለመሆኗ ጥር ጥር የለውም። ካልደከመው እሱ ካልተሸነፈ በስተቀር የተፈለገው ዓይነት ዙር ቢከር የምትረታ አትመስልም። ቅርጿ ያስመረቅናል። በደፈናው ትርፍ የሰውነት ክፍል የማይታይባት የውሲብ ጡብ ትመስላለች። በዚህ ላይ ዓይነ እርግቧ ተውቦ፣ ፊቷ ተኮስምኖ፣ ውድ አረቄ ተጎንጭታ ሳቅ ሳቅ እያላት ስላየሁዋት ያለማጋነን ቀንቼ ነበር።

የውሲብ ንግድ ደላሎች እዛም እዚህም አሉ። አዲስ አበባ ቦሌ የተሞላቀቀ ኑሮ የሚኖሩ የወሲብ አስጋላቢዎች መኖራቸውን ከጋላቢው አንዱ በሆነው ህንጻ ውስጥ ሳቅ እየኮመኮምኩ ሰምቻለሁ። ዱባይ ደርሶ መልስ እየቆረጡ ወሲብ የሚፈጽሙ ሹመኞችና ቅምጥ ልማታዊ ባለሃብቶችን ከነ ስማቸው ሲዛበቱባቸውና ስንት እንዳስከፈሉዋቸው ሲናዘዙ በደንብ ሰምቻለሁ። ስራዬ የማይታወቅ ዳያስፖራ በመሆኔ ታሪኩ ሁሉ እኔን ከማዝናናት አንጻር ድብቅ የለውምና በቂ መረጃ ለማግኘት እድል ሰጥቶኝ ነበር።

ከሁሉም በላይ የሚገርምና በሳቅ የሚያፈርስ የስልክ ወሲብ በጆሮዬ ስምቻለሁ። ስም መጥቀሱ አግባብ ባይሆንም በስልክ ሲወስብ የሚያሰማው ድምጽ፣ የሰውየው ማንነትና እድሜው፣ እንዲሁም ያለው ክብር ሲታሰብ ” ወይ መአልቲ” ያሰኛል። ደውሎ ሲያሞካሻት፣ ሲጀነጅናት፣ ቃል ሲገባላት፣ ” ይህን አድርጊ” እያለ ሲያዛት ማዳመጥ ቀደም ብዬ እንዳልኩት ከሰውየው አጠቃላይ ስዕል ጋር ሲመዛዘን የልቡና መመሣቀል ይፈጥራል።

የወሲብ ደላሎቹ ቅምጥል፣ የሚያሽከረክሩት መኪና፣ የሚኖሩበት ቤት፣ ከታላላቆቹ ጋር ያላቸው ግንኙነት ” ወይ አገሬ ” ያሰኛል። ልክ እዚህ እንዳለው ሁሉ በምኖርበት ዋሽንግቶን ዲሲ ተመሳሳይ የወሲብ ደላሎች አሉ። እንተዋወቃለን። ደላሎቹን ብቻ ሳይሆን የሚደለልባቸውን የራሽያና የሮማኒያ … በዘርፉ የተሰማሩትን የስራዬ ባህሪ እንዳውቃቸው አድርጎኛል።

ጥያቄ – ወደ ሪዝ ካርተን ሆቴል ምራን፤

እኔ – ቅርብ እኮ ነው፤ እዚህች አጠገባችን፤

ጥያቄ – ሳቁ በጣም ሳቁ

እኔ – ምን ያስቃልችኋል ? ተናደኩ 

ጥያቄ – እኛ የመጣነው ከኒውዮርክ ነው የምናውቀው ነገር የለም። ምራን፤

እኔ – እሺ ተከተሉኝ

ደረስን አንዱ ወደ አጠገቤ መጣና ኪሱ ገባ። አራት መቶ ዶላር ሰጠኝና ” ያንሳል” ሲል አሁንም እየሳቀ ጠየቀኝ

በልቤ ዶላርን እንደ ብር የሚመነዝሩ የደሃ ለማኝ አገር መንዛሪዎች ብዬ አመስግኜ ተሸበለልኩ። ስራውን ያገናኘኝ የታክሲ አሽከርካሪ ባልደረባዬ ጋር ወዲያው ደወልኩ። አገኘሁት። ለስምንት ዶላር መንገድ 400 መቀበሌን ስነግረው ” እነሱ እኮ ዶላር እንደ ብር ነው የሚጠቀሙት፤ ያንሳል ብትለው ይጨምርልህ ነበር” አለና የሆነ ስድብ ተሳድቦ ” አይ ጊዜ ሰገጤዎች ” አለና ፈገገ። አንድ መቶ ሰጠሁትና የለሊት ስራዬን ትቼ ወደ ቤት ሄድኩ። ተኛሁ። ግን ዛሬም ድረስ አስባቸዋለሁ። ዶላሩን ከየት ያመጡታል? አሜሪካን በደንብ የማያውቁ የሰርግ ማግስት እንግዶች / ሰርገኛውን ስሙን አልጠራም/ ዶላር ከየት ዝቀው ነው እንዲህ የሚበትኑት? እንቆቅልሽ!! ግን ወርቅ የሌለው የሚታወቅ እንቆቅልሽ። 

ወደ ዋናው ጉዳዬ ልግባ። ሰርገኛው ከሰርጉ ሳምንት በፊት ጀምሮ መጠጥ ቤት እያዘጋ ይጋብዝ ነበር። በቃ ዶላር ይሸለቀቃል። “አጅሬ” በፌስታል ሰጥቶ በፌስታል ይሰበስባል። ላውንደሪ ያደርጋል። ዛሬም ባለጊዜ ስለሆነ ስሙ ይለፈኝ። ግን መንግስት ባይፈርድበት የፈጣሪ ፍርድ ከደጁ እንደሆነ ሁሌም አምናለሁ። ሰርገኛው መሬት የሚዘራው ዶላር ከዚህ ጋን የተቀዳ ነው። ሰገጤዎቹ ደግሞ የራሳቸው መንገድ አላቸው። በጥቅሉ በሁሉም አቅጣጫ መታለባችን ፍንትው ብሎ ይታያል። 

ዋናው ጉዳይ

saxwdc Instagram posts (photos and videos) - Picuki.comለፍዳዳ ነገር ነው። ቅንጦት አያምርበትም ወይም ቅንጦትን አይችልበትም። ወይም መቀናጣትና መዝናናትን አልተረዳም። አለያም ” ሰዎች ሲዝናኑ ክብራቸውን ይጣላሉ፤ አደባባይ ይንደባለላሉ፤ ይረክሳሉ” የሚል መርህ የተጋተ ይመስላል። ከመመሪያው በተጨማሪ  በዶላር እየሸመተ የተጋተው ውድ አልኮል ከልክ አልፎ ነብሱን ሰልቦታል። ድርጊቱን ላጤነው የመከላከያ የበላይ ከፍተኛ ኦፊሰር መሆኑን ለማመን ይቸገራል። የአገር አደራ እንዲሸከም መደረጉ ያሳፍራል። የግል አተያየቴ ነው። በውቅቱ ሳይሆን ዛሬም ሳስበው እደነግጣለሁ። እሸማቀቃለሁ። እንዲህ ያሉ ባለአደራዎች ለመደለል የተመቻቹ ስለሆነ አገራችንን እንዲሁም ትውላዳችንን ቢሸጡስ እላለሁ።

አስራ አንደኛው ጎዳና ኖርዝ ዌስት ዋሺንግተን ዲሲ፣ በ2012  በዓይኔ ያየሁት ትንግርት። ስራዬ አገልግሎት መስጠት በመሆኑ ታክሲ ስነዳ ብዙ ነገሮች አይቻለሁ። በርካታ የአገሪቱ የፊት ሰዎችና ” ልማታዊ” የሚባሉት ” ሃብታሞች” ሩሲያ ሰራሽ የኦንላይን ገበያተኞች ጋር ሲዳሩ፣ ሰክረው ሲያሽካኩ፣ አንደበታቸው እየተኮላተፈ ለውሲብ ፍልሚያ ወደ ተከራዩት ውድ ጊዚያዊ በረት አድርሻቸዋለሁ። ሲያደርሷቸውም አይቻለሁ። ያመለጠኝንም ሰማቻለሁ። በዚህ ሁሉ ውስጥ የታዘብኩት ብዙ ነው። ጉርሻ መቀበሌንም አልክድም። ሲያጎርሱኝ ፈገግ የምልላቸው ግን በደስታ አልነበረም። ከቀናኝ የኒውዮርኩን ገጠመኝ አስከትላለሁ። ለጊዜው ዲሲ እንቆይ፤

SAX Restaurant & Lounge - Klub nate dhe kërcimi - "Washington ...ከላይ በጠቀስኩት አድራሻ sax lounge ሳክስ ላውንጅ ሲጠጣ ያመሸው አጭር፣ ቦርጭ የጀማመረው ያገሬ ሰው ትልቅ የጦር መኮንን ነው። ትልቅ ስል በሹመቱ ስም እንደሆነ ይታወቅልኝ። በመዝናኛ ላውንጁ የመዝናናት እድል ባያጋጥመኝም በቂ መረጃ አለኝ። ዋጋውና አገልግሎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ዝም ተብሎ ዘው የሚባልበት ቤት አይደለም። ስትጎለጉሉት ቤቱ ውስጥ እነማን ሊገቡ እንደሚችሉ ቁልጭ ብሎ ይታያችኋል። ደግሞም ስለ አስራ አንደኛው ጎዳና ሲገባቹህ ይበልጥ የቤቱ ክብደት ፍንትው ይልላችኋል። 

ይህ ወንድሜ ከበረሃው ጊዜ ስቃይ ጋር ተዳምሮ ያለበትን ድብርት ወይም ስትረስ ለማራገፍ መዝናናቱን አልነቅፍም። ይህንን ስል ግን ለአንድ ጠርጴዛ የሚከፈለውን ከስር ከምስል ጋር የተደገፈውን የገንዘብ መጠን ለያውም በዶላር ሳስበው ” ከየት አመጣው” የሚለውን የዜግነት ጥያቄ በመቆርቆር ስሜት መጠየቄ እንዳለ ሆኖ ነው።

ይህ የአገር ዘብ ጀነራል የፈረንሳይ ፒኪኒ ተለብሶ ጨረር የሆነ ብርሃን እንደ አረር እየወረደ በሉርስ ሾው በሚታይበት የተንቆተቆጠ የዳንስ ሰገነት ውስጥ የተሰየመው በገበያ ከቀረበለት ከአንዲት ሮማኒያዊት  ሴትጋር ነበር። የዲሲ ወሲብ አቅራቢዎች ” ሃኒ ሃኒ” የምትለውን ሮማኒያዊት በምን ያህል ተደራድረው እንዳቀረቡለት መረጃ ባይኖረኝም ቀስ ብዬ እንዳጣራሁት ጉብሊቷ የኦንላይን ገበያተኛ ናት። አና ትባላለች!! ከዛ በሁዋላ በተደጋጋሚ አይቻታለሁ። ሰላምታም ተለዋውጠናል።

በወቅቱ የትዕይንቱ ማብቂያ ግድም ላይ እንዳየሁዋት ጸጉሯ የልጥልጥ ነጭ ፈረስ ጋማ ይመስላል። ሰውነቷ ሙሉ ነው። እንደ ሰጋር በቅሎ የምትሰግር ምርጥ ሞያተኛ ለመሆኗ ጥር ጥር የለውም። ካልደከመው እሱ ካልተሸነፈ በስተቀር የተፈለገው ዓይነት ዙር ቢከር የምትረታ አትመስልም። ቅርጿ ያስመረቅናል። በደፈናው ትርፍ የሰውነት ክፍል የማይታይባት የውሲብ ጡብ ትመስላለች። በዚህ ላይ ዓይነ እርግቧ ተውቦ፣ ፊቷ ተኮስምኖ፣ ውድ አረቄ ተጎንጭታ ሳቅ ሳቅ እያላት ስላየሁዋት ያለማጋነን ቀንቼ ነበር።

VIP Bottle Service Washington DC

The following Bottle Service packages are offered:– $500 excluding tax and gratuity for groups of 6-10 on the main floor  – $750 excluding tax and gratuity for groups of 6-10 on the balcony level – Only bottles of alcohol may be ordered at bottle service tables.  Each table area is allowed a maximum of 10 guests. 

ላውንጁ የኩታራ መተራቀሚያ ባለመሆኑ መስከር አይቻልም። ሞቅታ ደግ ቢሆንም በሞቅታ እላፊ መሄድ ክልክል ብመሆኑ ጋርዶቹ ያገሬን ጉድ በቋንቋችን አናገሬ እንዳስወጣው ነገሩኝ። መስከሩን ነገሩኝ። አሁን ባለበት ደረጃ ካልወጣ ጎትተው ወደ ውጭ እንደሚያወጡት ገለጹልኝ። ያከበሩት አና ” ጀነራል ነው” ስላለቻቸው እንደሆነም አስረዱኝ። ከዛም ገባሁና ሰላምታ ሳልሰጥ ” ጀነራል” አልኩት። ምላሱ መንቀሳቀስ አይችልም። መናገር ቸግሮታል። እግሩን እንደ ድልብ መሲና ጊደረ ከፍቶታል። እናም ከአና ጋር በምልክት ተጋባባንና የጋርዶቹን ድጋፍ ጠይቀን ተሸክመን አወጣነው።

ወደ ደጅ ከወጣ በሁዋላ ለመቆምና ራሱን ችሎ ለመቆም ተውተረተረ። አና ላይ ተሰጣባት። እኔም ተጨማሪ ድጋፍ ሆንኩ። ሁለት እጆቹን ዘርግቶ ማንን እንደሚያድን ባላውቅም እንደ ጌታችን ተሰቀለ። ታግለን ታክሲ ውስጥ አስገባነው። ወደ ዊልርድ ሆቴል ነዳሁ። የስካር እንግሊዝኛው ያዝናናል። አና ” ሃኒ፣ ሃኒ ” ትለዋለች። 

እንደ ሰንጋ እየነዳን ወደ መውደቂያው በረት አስጠጋሁት። አና ደገፍ አድርጋው የአገልግሎቴን አሰጥችኝ። ጀነራልን ቻው አልኩት። አናና እሱ በራቸውን ዘጉ። እንቅልፍ ይጣለው አናን ይጋልብ እንጃ፤ አና ግን የሞተም ከጎኗ ከተኛ ታስነሳለች። ወሲብ ናት ከሮማኒያ!! አንድ ቀን እንዴት ነበር ስላት “ጋለብኩት” አለችኝና ሳቀች። ነገሩ ተጨማሪ ይጠይቁ መሆኑ ነው። ዛሬ 2020 ነው። ስምንት ዓመት ወደሁዋላ። ጀነራል ኳራንቲ ይሁኑ ጡረታ ወይም ብልጽግና መረጃ የለኝም፡፤ ግን መግለጫ ሲሰጡ አይታዩም። ሰርገኛውም አስተካክሎ ከተኮሰ የስምንት ዓመት ልጅ አለው ማለት ነው። እናት አለም ጠኑ!! ዶላር እንደቅጠል በኒውዮርክ ይከተላል።

የካቤ ሲሳይ 

Leave a Reply

%d bloggers like this: