ታዳሚን እንባ ያራጨው የችሎት ውሎ (በጌታቸው ሺፈራው)

የጓደኛዬ ማስታወሻ አገላበጥኩ። ዮናስ የተበደለው ማዕከላዊ ብቻ አይደለም። ከመታሰሩ በፊትም በቤተሰቡ ላይ በደል ደርሶበታል። ” ወንድሜን ሆን ብለው በኦራል(መኪና) ገጭተው ገደሉት፣ እናቴንም በተመሳሳይ መልኩ ገድለውብኛል። በማዕከላዊ አማራና ኦሮሞ ዘር እንዳይተካ ለምን ይደረጋል? የተማርነው ጥላቻ ነው። የእኛ ትውልድ ከእኛ ምን ይማራል? ሀይላንድ ተንጠልጥሎብኛል። በፒንሳ…… ሁላችንም ጉዳት ደርሶብናል”

Continue Reading

Advertisements

14 የፖለቲካ እስረኞች ተበየነባቸው

የአርበኞች ግንቦት 7 አላማን በመቀበል በቃፍታ ሁመራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ከሰኔ 25/2007 እስከ ሰኔ 28/2007 ዓም ከትግራይ ክልል ሚሊሻ፣ ከትግራይ ክልል ልዩ ኃይልና መከላከያ ጋር ውጊያ በማድረግ ከፍተኛ ጉዳይ አድርሰዋል የተባሉ 14 ግለሰቦች ከ 15 አመት እስከ ሞት በሚያስቃጣ ከባድ ድንጋጌ ስር እንዲከላከሉ ተበይኖባቸዋል።

Continue Reading

የሀሰት ክስ ሰለባዎች

 +ጌታቸው ሽፈራው
  • በቃጠሎው ወቅት አጠገባችን ሜዳ ላይ በጥይት የተገደሉ ወንድሞቻችን የጥይቱ ምልክት እንዳይታይ አሻራውን ለማጥፋት እና ከተጠያቂነት ለመዳን ሲሉ እየተቃጠለ በነበረ ቤት ውስጥ ከተው በእሳት አክስለዋቸዋል።
  • ሸዋሮቢት ተወስደን ኢሰብአዊ ድርጊት እንደተፈፀመብን፣ ጥፍራችን በፒንሳ እንደተነቀለ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ አይደገምም ተብሎ ሀውልት የተሰራለት የቶርች ገረፋ እንደተፈፀመብን፣ ውስጥ እግራችን እና ጀርባችንን በሚስማር እንደተበሳሳ… ተረጋግጧል።

ሚስባህ ከድር ዑመር (በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ 22ኛ ተከሳሽ

Continue Reading

ህገመንግስቱን በግልጽ የሚቃረን የፍርድ ቤት ትዕዛዝ!

የት እና ለማን አቤት ይባላል ?! አጠቃላይ የዳኝነት ሥርዓቱ የፖለቲካ ቅርቃር ውስጥ ገብቶ ፍትሕ’ን እንዴት ማግኘት ይቻላል ?! የጥያቄው መልስ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሱት የመንግስት ባለስልጣናት እንዳይመሰክሩ መደረጉ ህገመንግስቱን በግልጽ የሚቃረን ትዕዛዝ መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ እያለ፤ የተከሳሾት ሕጋዊ መብታቸው መነፈጋቸው አልበቃ ብሎ በተከሳሾች ላይ ፍርድ ቤቱ ተጨማሪ ቅጣት መጣሉ በይበልጥ የሚያሳዝን አሳፋሪ ድርጊት ነው።

Continue Reading

ዐቃቤ ሕግ ችሎት ላይ ሞባይሉን አውጥቶ ጌም ይጫወታል። እኔ ወደ እስር ቤት ተመልሼ የምጫወተው ከትኋን እና ከአይጥ ጋር ነው

“ማርም ሲበዛ ይመራል።……መረረኝ!….. በከፍተኛ ጥበቃ ሆኜ እንዳክም ጠይቄ ስላልተፈቀደልኝ የሞቱት ታካሚዎቼ ቁጥር 20 ደርሷል።” በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ ክስ መዝገብ 13ኛ ተከሳሽ ዶ/ር ፍቅሩ ማሩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ታህሳስ 30/2010 ዓም የተናገሩት ነው።

Continue Reading

በአማኙ የተረሱት መነኮሳት በደል በርትቶባቸዋል

በጌታቸው ሽፈራው —-

በእስር ላይ ከሚገኙት የዋልድባ መነኮሳት መካከል አባ ገ/ስላሴ ወ/ሀይማኖት ፀሎት ያደርጋሉ፣ ለእስረኞች ምግብ ያካፍላሉ፣ ፀበል ይሰጣሉ ተብለው ጨለማ ቤት ከገቡ ሰነባብተዋል። የምንኩስና ልብሳቸውን እንዲያወልቁ ሲጠየቁ አላወልቅም በማለታቸው ተደብድበዋል።

Continue Reading

በእነ ኦሊያድ በቀለ መዝገብ ተጨማሪ አራት የአቃቤ ህግ ምስክሮች ተሰሙ (ታህሳስ 18/2010)

★ ቀሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት ተለዋጭ ቀጠሮ ለሚያዚያ 24 እና ለሚያዚያ ተይዟል።

የእነ ኦሊያድ መዝገብ ለዛሬ ታህሳስ 18/2010 በአዳሪ ተቀጥሮ የነበረው ቀሪ የአቃቤ ህግ ምስክሮችን ለመስማት በሚል ነው። በአዳሪ ቀርበው እንደሚሰሙ የተነገራቸው ሶሰት ምስክሮች እና አንድ በዛሬው እለት የቀረበ ምስክር በአጠቃላይ አራት የአቃቤ ህግ ምስክሮች መቅረባቸው ተረጋግጧል። አቃቤህግም የቀረቡት አራቱም ምስክሮቹ በተለያየ ጭብጥ የሚመሰክሩ መሆናቸውን አሳውቆ፤ በመጀመሪያ የምስክርነት ቃሉን የሚሰጠው ዘነበ የተባለ ምስክር መሆኑን እና ከ1ኛ ተከሳሽ ኦሊያድ በቀለ እንዲሁም ከ4ኛ ተከሳሽ ኢፋ ገመቹ ኢሜል ውስጥ ( 358 ገፅ ከኦሊያድ እና 27 ገፅ ከኢፋ ) የተገኘ ማስረጃ ሲወጣ የታዘበውን የሚያስረዳ መሆኑን በጭብጥነት አስመዝግቧል።

Continue Reading

ፍ/ቤቱ በዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ አቃቤ ህግ ያቀረበውን ‹‹ገላጭ ማስረጃ›› ከመዝገቡ ጋር በማስረጃነት እንዲያዝ በመፍቀድ ብይን ሰጠ

የፌደራል ከፍተኛው ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ታህሳስ 20/2010 ዓ.ም በዋለው ችሎት ከሳሽ የፌደራል አቃቤ ህግ የኦፌኮ ፕሬዚዳንት በሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና ላይ ላቀረበው ክስ ተጨማሪ ገላጭ ማስረጃዎች አሉኝ በሚል ያቀረበውን 10 የድምጽና የምስል የሲዲ ማስረጃዎች ተቀብሏል፡፡

Continue Reading

ኦህዴድ እነ ለማ መገረሳ ለበቀለ ገርባ ምስክር እንደሚሆኑ አረጋገጠ፤ ተለዋጭ ቀጠሮ ተጠየቁ፤ “አንዷልም አራጌን አናቀርብም”

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ለምስክርነት ተጠርተው ሳየገኙ የቀሩት እነ አቶ ለማ መገርሳ ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጣቸው መጥየቃቸው ታወቀ። አዲስ ሃሳብ እናራምዳለን የሚሉት የኦህዴድ መሪዎች፣ “ወገኖቼ ላይ በሚደርሰው ጫና ሳቢያ ስራ በቃኝ” ያሉት አባዱላ ገመዳ ለምስክርነቱ ቅድሚያ አለመስጠታቸው ተቃውሞ አሰነዘረባቸው።

Continue Reading