ኢትዮጵያ፤ ግጭት ምክንያቱ እና መፍትሔዉ

በየሥፍራዉ ደም ለሚያቃባዉ ግጭት ሐገሪቱ ከ1983 ጀምሮ የምትከተለዉ በብሔር፤ በጎሳ ወይም በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌደራዊ ሥርዓትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አሉ።ሌሎች ግን ይሕን አይቀበሉትም።በየስፍራዉ ለሚነሳዉ ግጭትም ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አልገዛም ማለቱን ዋና ምክንያት ያደርጉታል

ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሶማሌ እና በኦሮሚያ መስተዳድሮች መካከል በተነሳዉ ግጭት እስካሁን ቁጥሩ በዉል ያልታወቀ ሰዉ ሕይወት ጠፍቷል።ሐብት-ንብረት ወድሟል።ከሐምሳ-አምስት ሺሕ በላይ ሕዝብ ተፈናቅሏል።ሰዎችን በተለይም ኦሮሞዎችን ከየነበሩበት ሥፍራ ማባረሩ እንደቀጠለ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።

ብዙ ጥፋት በማድረሱ የምሥራቅ ኢትዮጵያዉ ግጭት ጎላ እንጂ ባሌ እና ቦረና ዉስጥም በኦሮሞና በሶማሌ፤ በጉጂ ኦሮሞና በጉርጂ መካከል፤ አማራ እና ቅማንት፤ አማራና አፋር በገጠሟቸዉ ግጭቶች የሰዉ ሕይወት መጥፋቱ እየተነገረ ነዉ።ኢትዮጵያ፤ ከዚሕ ቀደም ያልነዉን ለመድገም የመጤ ወይም  የሠፋሪዎች እና የነባሮች ግጭት፤ የአማራና የኦሮሞ ግጭት፤ የወልቃይት ጠገዴ ወይም ፀገዴ ግጭት፤የኮንሶ ግጭት፤የወላይታና የሲዳማ ዉዝግብ፤ የአፋርና የኢሳ (ሶማሌ) ግጭት፤ የሱማሌና የኦሮሞ ግጭት፤ የኑዌርና የአኝዋክ ግጭት፤ ወዘተ እያለች፤ በግጭት ማግሥት ግጭቶን እያስተናገደች ሃያ ስድት ዓመት አስቆጥራለች።

በየአካባቢዉ የሚያነሱ የአስተዳደር እና የማንነት ጥያቄምዎችም እስከ ዛሬ ድረስ እንደቀጠሉ ነዉ።

በየሥፍራዉ ደም ለሚያቃባዉ ግጭት ሐገሪቱ ከ1983 ጀምሮ የምትከተለዉ በብሔር፤ በጎሳ ወይም በቋንቋ ላይ የተመሠረተ ፌደራዊ ሥርዓትን ተጠያቂ የሚያደርጉ አሉ።ሌሎች ግን ይሕን አይቀበሉትም።በየስፍራዉ ለሚነሳዉ ግጭትም ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አልገዛም ማለቱን ዋና ምክንያት ያደርጉታል።በድንበር ግዛት ይገባኛል፤በሐብት ባለቤትነት፤ በአስተዳደር እና በማንነት ጥያቄ ሰበብ የሚጫሩትንም ግጭቶች ገዢዉን ፓርቲ ወይም ለፓርቲዉ ያደሩ ወገኖችን የሚወቅሱ አሉ።

የኢትዮጵያ መንግስት ግን ለሁሉም ዓይነት ግችቶች ፀረ፤ ሠላም፤ ፀረ ልማትና የዉጪ የሚላቸዉን ኃይላት ይወነጅላል።

ግጭት፤ ዉዝግብ፤ አለመግባባቶቹን ለማስወገድ የተለያዩ ወገኖች የሚሰጡት የመፍትሔ ሐሳብ ለየቅል ነዉ።የዛሬ ዉይይታችንም የግጭቱን ዋና ዋና መክንያቶች እና መፍትሔ የሚባሉ እርምጃዎችን ባጫጭሩ ለመቃኘት ያለመ ነዉ።

ነጋሽ መሐመድ , ልደት አበበ

Advertisements

“በቂሊንጦ ቃጠሎ ወቅት ጠባቂዎች ወደ እስረኞች ተኩሰዋል”

የማዕድን ቦታዎች ጉዳይ “የፍትሃዊነት፣ የእኩልነት፣ የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳይ ነው”

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ይበጃሉ ያላቸውን ተከታታይ እርምጃዎች እየወሰደ ነዉ፡፡ ከእነዚህ አንዱ በግል ባለሀብቶች ተይዘው የነበሩ የማዕድን ቦታዎችን ለስራ አጥ ወጣቶች እንዲሰጥ ማድረጉ ነው፡፡ በክልሉ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጥሬ ዕቃዎችን ከተደራጁ ወጣቶች እንዲገዙ የሚያስገድድ ውልም አስፈርሟቸዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ።03:46

የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ከተለመደው «ወጣ ያሉ» እና «ደፋር» አካሄዶች መምረጣቸው ያነጋግር ይዟል፡፡ እነዚህ አካሄዶች ትኩረት ያደረጉት ክልሉን ባለፈው ዓመት በናጠው ህዝባዊ አመጽ ዋና ተሳታፊዎች በነበሩ ወጣቶች ላይ ነው፡፡ ወጣቱ ከአካባቢው ሀብት ተጠቃሚ ካልሆነ ሊፈጠር የሚችለውን አደጋ በክልሉ ባሉ የግል ኢንቨስትመንቶች ላይ ከደረሱ ጥቃቶች ጋር በግልጽ ሲያይዙት ታይተዋል፡፡

በመፍትሄነት ከወሰዷቸው እርምጃዎች አንዱ “ምንም እሴት የማይጨመርባቸው” ያሏቸውን የማዕድን ማምረቻዎች ከግል ባለሀብቶች ወስዶ ለተደራጁ ወጣቶች ማስተላለፍ ነው፡፡ የሲሚንቶ ፋብሪካዎችም የምርት ግብዓቶችን ከወጣቶች እንዲገዙ ስምምነት አስፈርመዋቸዋል፡፡ ትናንት መጋቢት 13 መንግስታዊው ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ጋር አዲስ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እነዚህን እርምጃዎች የሚወስደዉ በዚህ ዓመት ብቻ በክልሉ ላሉ 1.2 ሚሊዮን ስራ አጥ ወጣቶች ስራ ለመፍጠር ከያዘው ዕቅድ ተነስቶ እንደሆነ የኦሮሚያ የስራ ዕድል ፈጠራና የከተሞች የምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ አወሉ አብዲ ይናገራሉ፡፡

“የስራ ዕድል ከሚፈጠርባቸው መስኮች አንዱ ማዕድን ነው፡፡ ማዕድን ምንድነው በመሰረቱ ተቆፍሮ [ከወጣ በኋላ] ፋብሪካ ውስጥ የሚገባ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ እሴት የሚጨመርበት አይደለም፡፡ ማዕድኑ ከምንጩ ላይ ባለው ብቻ ጥቃቅን እና አነስተኛ [ማህበራት] አደራጅተን አነርሱ የመነሻ ገንዘብ እያገኙ የራሳቸውን ቢዝነስ የሚፈጥሩበት ሁኔታ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ ጥቃቅኖች ጥሬ ዕቃ እንዲያቀርቡላቸው ከፋብሪካዎች ጋር ተሰማምተናል፡፡ ከሙገርም፣ ከደርባም፣ ከዳንጎቴም ሌሎች ክልሉ ውስጥም ካሉ 18 የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ለስራ ዕድል ፈጠራ ቁጭ ብለን ተስማምተናል፡፡ እነርሱም ‘ይህ ችግር ይመለከተናል፤ እኛም ችግሩን መካፈል አለብን’ ብለው ተሰማምተው በጋራ የተደረገ ነገር ነው” ይላሉ፡፡

Äthiopien Sabata Wirtschaft Arbeitsmarkt (DW/M. Y. Bula)

አቶ አወሉ ይህን ይበሉ እንጂ የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ ስምምነቱን እንዲፈጽሙ እንደተነገራቸውና ሁሉም የሆነው በአጭር ጊዜ ውስጥ ነው ሲሉ ቅሬታ ማቅረባቸው ተዘግቧል፡፡ የሲሚንቶ ግብዓቶች አቅርቦት ወደ ተደራጁ ወጣቶች መዞር በሲሚንቶ ምርት ላይ መስተጓጎል እንዳይፈጥርም አስግቷል፡፡ ከፋብሪካዎቹ ሌላ እንደ አሸዋ፣ ጠጠር እና ኖራ ያሉ ማዕድኖቹን ያመርቱ የነበሩ ባለሀብቶች “ማምረቻ ቦታዎቹን ልንነጠቅ ነው” የሚል አቤቱታ ማቅረባቸው ተገልጿል፡፡ “ሀብት የማፍራት ህገመንግስታዊ መብታችን ተጥሷል” ማለታቸውም ተሰምቷል፡፡

ቅሬታዎቹን ለአቶ አወሉ አንስተንላቸው ነበር፡፡ ከባለሀብቶች “የተነጠቀም ሆነ የሚነጠቅ ቦታ የለም” ሲሉ አስተባብለዋል፡፡

“አንደኛ ይሄ ማዕድን የሚባለው ነገር የጋራ ሀብት ነው፡፡ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚበለጽጉበት አይደለም፡፡ ለምሳሌ ምስራቅ ሸዋ አካበቢ ያለውን ማዕድን ሶስት፣ አራት ባለሀብቶች የሚባሉ ደላሎች ለብቻ ተቆጣጥረው እንደሚጠቀሙበት በጥናት ተረጋግጧል፡፡ ሁለተኛ ማሽን አልነካንም፡፡ ድንጋይ የሚፈጩ ማሽኖች አካባቢ ድንጋይ አሁንም እነርሱ ናቸው የሚፈጩት፡፡ ጥሬውን ድንጋይ ግን ልጆቹ አውጥተው ለእነርሱ ያቀርባሉ፡፡ እነርሱ ደግሞ ተቀብለው ይፈጫሉ፡፡ እሴት ጨምረው ይሸጣሉ፡፡ ስራ አጡ፣ ወጣቱ ይህን ነገር ሰብስቦ ቢሸጥ ምንድነው ወንጀሉ? ምንም ወንጀል የለውም፡፡ የፍትሃዊነት፣ የእኩልነት፣ የጋራ ተጠቃሚነት ጉዳይ ነው፡፡ ስለዚህ ይህንን ደግሞ በጋራ ተሰማምተን ከባለሀብቶቹ ጋርም ያለምንም ልዩነት ነው የተለያየነው፡፡ ስለዚህ ይህን በጎን የሚያቀርብ አካል ካለ በራሱ ችግር ያለበት አካል ስለሆነ ራሱን በዚያ መልኩ ቢያርም ጥሩ ነው” ሲሉ አቶ አወል ያስጠንቅቃሉ፡፡

ስለ ጉዳዩ በፌስ ቡክ ገጻችን እና በዋትስ አፕ አድራሻችን አስተያየታቸውን ያጋሩን  ተከታታዮቻችን ለክልሉ እርምጃ አዎንታዊ አመለካከት አላቸው፡፡ ተግባራዊነቱን የሚጠራጠሩ  እንዳሉ ሁሉ እርምጃዎቹን የተቹም በርካቶች ናቸው፡፡ ተስፋዬ ደሳለኝ የተባሉ ተከታታይ“ወጣቶች ከአካባቢያቸው ሐብት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገቢ ነው፡፡ ችግሩ የሚመስለኝ መጀመሪያውኑ ከማደራጀት ያገዳቸው ማን አለ የሚለው ይመስለኛል፡፡ የ25 ዓመት ጥፋትን በችኮላ ማስተካከል አይቻልም” ብለዋል፡፡ ጌች ድሪባ ለታ የተባሉ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው “ልማት አንዱን ሀብታም አንዱን ድሀ ማድረግ ነው ወይስ ሁሉንም የማከለ መሆን አለበት?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

ተስፋለም ወልደየስ    ነጋሽ መሐመድ

አዎንታዊ ምላሽ ካልተገኘ መድረክ ውይይቱን ሊያቋርጥ እንደሚችል አስታወቀ

22 ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ሸንጎ ላይ መደራደር እንደማይቻልና የመድረክ ፍላጎት ከገዢው ፓርቲ ኢሐዴግ እና ከመንግሥት ጋር ብቻውን መደራደር እንደሆነ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጼጥሮስ ተናግረዋል።

በድርድሩ አካሄድ ላይ ያቀረቧቸው ጥያቄዎች አዎንታዊ ምላሽ ካላገኘ ውይይቱን ሊያቋርጡ እንደሚችሉ የመድረክ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ተናገሩ። መድረክ መሪ ተዳዳሪ ሆኖ እንዲቀርብ አለበለዚያም ጎን ለጎንና ብቻውን ከገዢው ፓርቲ ጋር እንዲደራደር ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል።22 ፓርቲዎች በሚሳተፉበት ሸንጎ ላይ መደራደር አይቻልም ብለዋል ፕሮፌሰር በየነ።

ሕጻናት እንዳያዳምጡት የተባለው የአቶ ሃብታሙ አያሌው ምስክርነት፤ “ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም”

“አንድ እስረኛ ተመርምሮ ሲመለስ መጀመሪያ የሚቀርብለት ጥያቄ ‘ተሰቅለህ ነበር ወይም አልተሰቀልክም?’ የሚል ነው የሚሉት ከእስር የተለቀቁት አቶ ሐብታሙ አያሌው ለማመን የሚከብድ ከባድ መከራዎች በእስር ቤት ውስጥ እንደሚፈፀም ይናገራሉ። አቶ ሃብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት የወላጆችን ትብብር እንጠይቃለን። የቃለምልልሱ ሁለተኛ ክፍል ቅዳሜ ምሽት ይቀርባል።

 

የቀድሞው የተቃዋሚው አንድነት ፓርቲ ቃል አቀባይ በሽብር ወንጀል ተከሰው እሥር ቤት በቆዩባቸው ሁለት ዓመታት በምርመራ ሳቢያ ደረሰብኝ ያሉት ከባድ ስቃይ አሁን ለሚገኙበት የጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ይናገራሉ።

ወህኒ ቤቶች ውስጥ የሚፈጸሙ ጭካኔ የተሞላባቸው ልዩ ልዩ የምርመራ ዓይነቶች በአብዛኞቹ እሥረኞች ላይ ሕልፈትን ጨምሮ ለተመሳሳይ የጤና ችግሮች እንደሚዳርጉም አቶ ሃብታሙ ያስረዳሉ።

አቶ ሃብታሙ አያሌው በዚህ ፕሮግራም ላይ ስለ ምርመራ ዓይነቶች በዘረዘሩበት ወቅት የሰጡት ማብራሪያ እጅግ ዘግናኝ በመሆኑ ሕጻናት ልጆች እንዳያደምጡት የወላጆችን ትብብር እንጠይቃለን። አቶ ሃብታሙ አያሌውን ያነጋገራቸው የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ ሰሎሞን ክፍሌ ነው።

አቶ ሃብታሙ አያሌው በታሰሩበት ወቅት በመንግስት የቀረበባቸው ክስ“ሕጋዊውን የፖለቲካ ፓርቲ በሽፋንነት ተጠቅመው በአሸባሪነት ከተፈረጀው ግንቦት ሰባት ጋር በመገናኘት በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ተግባር ለመፈጸም አሲረዋል። ይህንንም ደርሰንበታል፤” ማለቱ አይዘነጋም።

የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን-ነክ ጉዳዮችና አዲሱ ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ተከታታይ ውይይት

“በተለያዩ ሁኔታ በፍርድ ቤት ሂደቶች አልፈው ጉዳያቸው ሳይሳካላቸው ቀርቶ ነገር ግን ወንጀል ስለሌላቸው ሊሆን ይችላል ከአገር ያልተባረሩ፤ በዓመት ወይ በስድስት ወር አንዴ ወደ ኢሚግራሽን መሥሪያ ቤት እየፈረሙ በሰላም የመሚኖሩ .. ለእነኚህና ለሌሎች አሁን አሳሳቢ ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።” የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር።

በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ በዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውንና ሌሎችን ያሳሰበ ርዕሰ ጉዳይ ነው። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጂያ ያወጡትን አዲሱን ፕሬዝዳንታዊ ማዘዣ ጨምሮ በዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን ፖሊሲ ዙሪያ እየመጡ ያሉና “ይመጡ ይሆናል” የተባሉ ለውጦችና አንድምታ በጥልቀትና በቅርበት ለማየት የሚጥር ከሕግ ባለሞያዎች ጋር የተካሄደ ውይይት ነው።

ተወያዮች:- የሚ ጌታቸው በካሊፎኒያ ክፍለ ግዛት በሳንሆዜ የአሜሪካ የሕግ-ጠበቆች ማኅበር የሳንታክላራ ቫሊ ሊቀመንበር ናቸው። በስደተኞች ጉዳይ ተሟጋችነትም ይታወቃሉ። አቶ ፍጹም አቻምየለህ በዋሽንግተን ዲሲና ቨርጂኒያ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩና በስደተኞች ሕግ ዙሪያ ለረዥም ጊዜ ያገለገሉ ናቸው። አቶ ተክለሚካኤል አበበ ደግሞ በካናዳ ቶሮንቶ በጥብቅና ሥራ የተሰማሩ ናቸው። የውይይቱን የመጀመሪያ ክፍል ከዚህ ያድምጡ።

Part 1 , 2 , 3

 

 

VOA Amharic

 

 

በጋምቤላ የታፈኑ ሕጻናት ጉዳይ የተዳፈነ ይመስላል፤ መንግስት “ግጭቱን ለማስወገድ ድልድይ እየሰራሁ ነው” አለ

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን በጎን እና በጆር ወረዳ በሚገኙ ቀበሌዎች ዉስጥ ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በጣሉት ጥቃት ከአስራ ስምንት ሰዎች በላይ መገደላቸዉንና ከ 22 በላይ ሕጻናት ታግተው መወሰዳቸውን ተቀማጭነቱን ለንደን ላይ ያደረገዉ «አኝዋ ሰርቫይቫል» የተሰኘዉ ድርጅት ገለፀ።

 አውዲዮውን ያዳምጡ።04:19

መንግሥት ርምጃ አልወሰደም

«አኝዋ ሰርቫይቫል» የተሰኘዉ የጋምቤላ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር መንግሥት ምንም አይነት ርምጃ አለመዉሰዱን ገልፀዋል። የአካባቢዉ ነዋሪዎች በበኩላቸዉ ታጣቂዎቹ በየጊዜዉ ጥቃት በመጣል ልጆቻችንን አፍነዉ ሲወስዱ መንግሥት ድርድር ይካሄድ ከማለት በስተቀር ርምጃ ለመዉሰድ እና አካባቢዉን ከጥቃት ለመከላከል ዝግጁ አይደለም ሲሉ ያማርራሉ። የጋምቤላ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ሕጻናቱን ለማግኘት ጥረት ላይ መሆኑን ተናግሯል።

«አኝዋ ሰርቫይቫል» የተባለዉ የጋምቤላ ሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅት ለዶቼቬለ በላከው መረጃ  መሰረት ከደቡብ ሱዳን የመጡ የሙርሊ ታጣቂዎች መጋቢት አንድ ምሽት ላይ በጋምቤላ ክልል አኝዋክ ዞን ጉድ ወረዳ ኦባዋ ቀበሌ ባደረሱት ጥቃት ነዋሪዎችን ገድለዋል ህጻናትንም አፍነው ወስደዋል ። መንግሥት ምንም አይነት ርምጃ ባለመውሰዱ ታጣቂዎቹ ከአንድ ቀን በኋላ የመንግሥት የጥበቃ ኃይላት ብዙም ሳይርቁ በሚገኙበት ጆር ወረዳ አንጌላ ቀበሌ በከባድ መሣሪያዎች ተጨማሪ ሰዎችን ገድለዋል ፣ሕጻናትም አፍነዉ ወስደዋል ንብረትም አውድመዋል ሲሉ የድርጅት ሃላፊ ኒኪያዉ ኦቻላ ገልፀዋል።

Äthiopien Pressebilder Anywaa Survival Organisation (Anywaa Survival Organisation/Nyikaw Ochalla )

«በመጀመርያ ደረጃ የካቲት ወር አካባቢ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የሙርሌ ታጣቂዎች ኦትዊልን በማጥቃት ስምንት ሰዎችን ገድለዋል። ከዝያ በኋላ 18 የሚሆኑ ሕጻናትን አፍነዉ ወስደዋል። ይሄ የመጀመርያ ጊዜ አid,ለም። ነገርግን በከፍ መልኩ ሁለትቀን ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ኣ,ንጌላና ኦባዋ በሚባል ተከታታይ ጥቃት ሰንዝረዋል። በዚህ ወቅት በአንጌላ ስድስት ሰዎች ሲሞቱ አራት ሕጻናት ታፍነዉ ተወስደዋል።  ኦባዋ ላይም በከፍ መልኩ ንብረቶች ወድመዋል፤ መንደር በአጠቃላይ ተቃጥሎአል፤ በዝያ ወቅe የሞቱት ሰዎች ከ 18 በላይ ይሆናሉ የሚል መረጃ ነዉ የደረሰን። 22 ሕጻናቶች ታፍነዉ ተወስደዋል፤ እስካሁን ግን የመንግሥት ምላሽ ይህ ነዉ ማለት አይቻልም። ዝምታዉ ለምን እንደሆነ የሚገርም ነገር ነዉ።»

በእሁድ እለቱ ጥቃት ከ 60 በላይ መኖርያ ቤቶች መቃጠላቸዉን በጋምቤላ አስተዳደር የዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ኃላፊ ፔተር ገብርኤል ገልፀዋል።

« በርግጥ እሁድ እለት ማታ ኦባዋ በሚባል ቀበሌ የሙርሊ ታጣቂዎች ወደ 13 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል ፤ 21 የሚሆኑ ሕጻናት ታፍነዉ በሞርሊ ተወስደዋል። 60 የሚሆኑ ቤቶች ተቃጥለዋል።  ነገሩ አሳዛን ነዉ።» ከደቡብ ሱዳን የሚመጡት የሙርሊ ታጣቂዎች ከዚህ ቀደም ያደረሱት ጥቃት ያስታወሱት የአኝዋ ሰርቫይቫል ድርጅት ሃላፊ ኒኪያዉ ኦቻላ መንግስት ስለ ባለፈዉ ሳምንቱ ጥቃትና ስለ ታፈኑት ሕጻናት ጉዳይ የገለፀዉ ነገር የለም ይላሉ ።

« በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን እስካሁን ስለ ጋምቤላ ስለአኝዋክ ብሔረሰብ የሞቱ ሰዎችና የታፈኑ ሕጻናቶች በምን አይነት መንገድ ወደ ቤተሰቦቻቸዉ እንደሚመለሱ መንግሥት ያወጣዉ መግለጫ የለም። እና ይህ ትንሽ ሃላፊነት የጎደለዉ አካሄድ ነዉ ብዬ ነዉ የማምነዉ።» ይህን ችግር በድርድር ከመፍታት ይልቅ መንግሥት ርምጃ ቢወስድ ታጣቂዎች ወደ ቦታዉ ዳግም ባልመጡ ነበር ያሉት፤ በጋምቤላ አስተዳደር የዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ኃላፊ ፒተር ገብርኤል ነዋሪዉ የመንግሥትን ምላሽ እየጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል።

« የሙርሊ ታጣቂ ሃይል ከደቡብ ሱዳን ነዉ የሚመጡት ፤ ለምን መንግሥት ዝም ይላል? ለምን ርምጃ አይወስድም? ተደራጅተዉና ድንበርን አቋርጠዉ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ሲገባ እርምጃ አለመዉሰዳቸዉ ነዉ። ሁልጊዜ የሚደረግላቸዉ ድርድር ነዉ፤ ስለዚህ በሙርሊ ላይ ርምጃ ካልተወሰደ ጥቃታቸዉን መቼም አይተዉም። ሕዝቡ አሁን ተሰዶ ሜዳ ላይ ነዉ ያለዉ ። ስለዚህ የመንግሥት ቁጥጥር ላልቶአል።

Äthiopien Pressebilder Anywaa Survival Organisation (Anywaa Survival Organisation/Nyikaw Ochalla )

 የድንበር አዋሳኝ በሆኑ የጋምቤላ አካባቢዎች የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት ከደቡብ ሱዳን መንግሥት ጋር እየሰራ መሆኑን የገለፁት በጋምቤላ መንግሥት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ ኦሞት ኦቶዎ በበኩላቸዉ ፤ ሁኔታዉ በመረጋጋት ላይ ነዉ፤ የመንግሥት ሰራዊት እየተከታተለ ነዉ። » ከሃያ በላይ ታፍነዉ የተወሰዱት ሕጻናትስ ጉዳይ እንዴት ነዉ? « ሕጻናቱ ያሉበት ቦታ አይታወቅም ገና አልተገኙም» ባለፈዉም ጊዜ ከ መቶ በላይ ሕጻናት ታፍነዉ ተወስደዉ ነበር 90 ሕጻናት ተመልሰዉ 40 ሕጻናት ቀርተዋል። አሁን ግን የታፈኑት ሕጻናት 22 ናቸዉ። አዲስ ነገር ካገኘን ይፋ እንናገራለን።»

መንደር ቀዉድመዉ ሕጻናትን እያፈኑ ወስደዉ የሚሸጡት የሞርሊ ታጣቂዎች ቀደም ባሉት ዓመታት የቀንድ ከብትን ለመዝረፍ ብቻ ነበር ሲሉ በጋምቤላ አስተዳደር የዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ኃላፊ ፒተር ገብርኤል ተናግረዋል።

ፋና ይህንን አስፍሯል

ከደቡብ ሱዳን የተነሱ የሙርሌ ጎሳ አባላት በጋምቤላ ክልል ያደረሱትን ጥቃት በተመለከተ የአስቿኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሴክሬተሪያትና የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ፥ የመከላከያ ሰራዊቱ በአካባቢው የሚስተዋሉ የጎሳ ግጭቶችን ለመቆጣጣር የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እየሰራ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ግጭቶችን ለመቆጣጣርና ቁጥጥሩን ለማጥበቅ የድልድይ ግንባታ እየተከናወነ መሆኑም ተናግረዋል።

ሰሞኑን በአካባቢው የተፈፀመውን ጥቃት ተከትሎም በጥቃቱ የታገቱ 30 ህጻናትን ለማስመለስ ከጋምቤላ ክልል ጋር በጥምረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሲራጅ አስታውቀዋል።