Category: ባህልና እምነት

ሰበር ዜና – በጋሻው ደሳለኝ: በሐዋሳ ሀ/ስብከት አድባራትና ገዳማት በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳያስተምር ሊቀ ጳጳሱ አገዱ!

በሐዋሳ፣ በዲላና በይርጋለም ከተሞች ምእመናንን በመከፋፈል የዓላማው መጠቀሚያ አድርጓል፤ በአማሮ ደብረ ብርሃን ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የቤተ ክርስቲያንን ክብር እና ልዕልና ተዳፍሮ ተናግሯል ምንም ዓይነት የጉባኤ ፈቃድከሀ/ስብከቱ ሳይሰጠው፣ በሐዋሳ ከተማ አዳራሽ ኑፋቄ አስተምሯል የቤተ ክርስቲያንን ክብር የሚነኩ የስድብ ቃላትን በመጠቀም፣ ምእመናንን ለቁጣ አነሳሥቷል የክሕደት ትምህርቱ በማስረጃ ተደግፎ፣ ለቅ/ሲኖዶስ እንደሚቀርብና እንደሚወገዝም ተጠቁሟል […]

” እኔ ጵጵስና የተሾምኩበትን ቀን የማስታውሰው በኀዘንና በልቅሶ ነው “

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ወደ ጵጵስናው የመጡት ብዙ ጫና ተደርጎባቸው ነበር፡፡ ከጵጵስናው ይልቅ በሶርያውያን ገዳም መኖርን ይመርጡ ነበር፡፡ ሺኖዳ የኮሌጅ ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ምኞታቸው እንደ አባ ገብረ ክርስቶስ በበረሓ መኖር ነበር፡፡ የወቅቱ ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስ ግን ገዳሙን እንዲረዱ ወደ ሶርያውያን ገዳም ላኳቸው፡፡ በወቅቱ የነበሩት የገዳሙ አበው ሺኖዳ ለገዳሙ መሻሻል […]

ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ- ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲቃወሙ ቀሰቀሱበት፤ አባ ተ/ሃይማኖት “ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን” ሲሉ ወተወቱ

“ማኅበሩ፣ ሕዝቡን ከፍሎ ይዞብናል” ያሉት ፓትርያርኩ፣ “አቋማችሁን ከእኛ ጋራ አንድ ማድረግ አለባችሁ፤” በማለት እንዲቃወሙት ቅስቀሳ አካሔዱበት፤ ማኅበሩ፥ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ መርሐ ግብሩ ብቻ፣ በየዓመቱ እልፍ ሐዲሳን ጥሙቃንን እያስመዘግበ ቢኾንም፣ ለምእመኑ ቁጥር መቀነስም ተጠያቂ አደረጉት፤ መለካዊነት የተጠናወታቸው ተሿሚው አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፥ “አቶ ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን፤” እያሉ የቅዱስ […]

የተቀደሰው የገነት ምንጭ ውኃ – ግዮን

Written by ታደለ ገድሌ ጸጋየ (ዶ/ር) መጽሐፈ ብሉይ እንደሚነግረን፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ሁልጊዜ በውኃ ላይ ነው፡፡ ውኃን በአንድ ስፍራ ተሰብስቦ ሲያዩት ጉልበት፤ ግርማ ሞገስና ውበት አለው፡፡ ውኃ ለሥነ ፍጥረት ሁሉ መሠረት መሆኑም እሙን ነው፡፡ እናም ከሰው የተባረከና የተቀደሰ የመኖሩን ያህል ከውኃም የተባረከና የተቀደሰ አለ፡፡ እግዚአብሔር  በዘፍጥረቱ ገነትንና በገነት ውስጥ […]

‹እኛና መንፈስ ቅዱስ› ማለት ሊቀር ነውን ?

(ዲ/ን ዳንኤል ክብረት) … ቅዱስ ሲኖዶስ የፓትርያርኩን እንደራሴ ሹመት በተመለከተ ለመወያት የያዘው አጀንዳ የመንግሥት ተወካይ ባለበት እንዲታይ መወሰኑን ዛሬ ጠዋት ሰማን፡፡ ከብጹዐን ጳጳሳት በቀር ካህናትና ቆሞሳት እንኳን የማይገቡበት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አማኝ ይሁን ኢአማኒ፣ ሙስሊም ይሁን ክርስቲያን የማይታወቅ የመንግሥት ተወካይ እንዲገኝበት መጋበዙ የደረስንበትን የውርደት ደረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ በአንድ […]

ዋልድባ፤ እመ ግሑሣን ወግሑሣት፤ እንዴት ከርመሽ ይሆን?

(ከትዝታዬ) – ጌታቸው ኃይሌ-profesor የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በረጅም ታሪኳ የጥቃት ነፋሳት ሲነፍሱባት፥ የአፍራሽ ዝናማት ሲዘንሙባት፥ ምንም ነገር እንዳልደረሰባት ሆና እኛ ዘመን የደረሰችው፥ መሠረቷ በዐለት የሚመሰሉ ጠንካራ ቅዱሳን ገዳማት ስለሆኑ ነው። ከዋናዎቹ ገዳማት አንዷ የግሑሣንና የግሑሣት እናት ቅድስት ዋልድባ ናት። መሥራቿ ኮከበ ገዳም ከተባሉት ሰባት ሳሙኤሎች አንዱ […]

እኔ የምለው ሤራ፣ ተንኮል፣ ስለላ፣ ማጭበርበር እና እምነት ምን አገናኛቸው?

(ዲያቆን ዳንኤል ከብረት) በዚህች ቤተ ክርስቲያን ላይ በተንኮል እና በሤራ የሚደረግ ወንጀል ሁሉ በሦስት ነገሮች ላይ የሚሠራ ወንጀል ነው፡፡ በክርስትና ላይ፣ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ እና በሀገር ላይ፡፡ በአንዳንድ የአውሮፓ ሀገሮች ተጀምሮ ምዕራቡን ዓለም መንፈሳዊነት ወደ ተለየው ክርስትና የከተተው የተሐድሶ ነፋስ በክርስትና እና በክርስቲያናዊ ሀብቶች ላይ የማይተካ ጥፋት አድርሷል፡፡ […]

የባህል አብዮት በኢትዮጲያ

ሃይማኖትና ፍልስፍና በነፃነት የመስራትና ንብረት የማፍራት መብት፣ በምዕራብ አውሮፓ ሆነ በሌሎች ዴሞክራሲያዊ ስረዓት ባላቸው ሀገራት በሕገ-መንግስት የተደነገገና የሕግ ጥበቃ የሚደረግለት መብት ነው። ለምሳሌ፣ በምዕራብ አውሮፓ በህዳሴው ዘመን ጀምሮ በተዘረጋው ፖለቲካዊ አስተዳደር ስረዓት ውስጥ የግለሰብ ኢኮኖሚያዊ መብቶች፣ በተለይ በነፃነት የመስራት፣ ንብረት የማፍራት እና ንብረቱን በፍላጎቱና ምርጫው የመጠቀም፣ በዚህም የተሻለ […]

ኤጲስ ቆጶስነት የተመረጡት አባት፣ “ሓላፊነት ለመጨመር አልበቃኹም” በሚል ዕጩነቱን ሳይቀበሉ ቀሩ፤

(አዲስ አድማስ፤ ቅዳሜ፣ ሰኔ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም.) ሐራ ዘተዋሕዶ ቅዱስ ሲኖዶሱ ለአዊ ዞን ሀገረ ስብከት በከፍተኛ ድጋፍ መርጧቸው ነበር 27 ዓመታት ባስቆጠሩበት የኢየሩሳሌም ገዳማት፣ በማገልገል ላይ ይገኛሉ “የአበውን አሠረ ፍኖት የተከለተ አቋምና ምላሽ ነው”/አስተያየት ሰጭዎች/ የሐምሌ ተሿሚዎችን ቁጥር በአንድ ይቀንሰዋል፤ በጥቅምቱ ጉባኤ ይታያል ቋሚ ሲኖዶስ፣ የዶ/ር አባ ኃይለ […]