አጫጭር ወሬዎች

ዩናይትድ ኪንግደም 23 የሩሲያ ዲፕሎማቶችን አባረረች

ሩሲያ ውስጥ ተሰርቶ በሃገሯ ውስጥ በነበረ የቀድሞ ሰላይ ላይ ጥቃት ስለተፈፀመበት የነርቭ ጋዝ ሞስኮ ማብራሪያ አልሰጥም በማለቷ፤ ዩናይትድ ኪንግደም 23 የሩሲያ ዲፕሎማቶች ሃገሯን ለቀው እንዲወጡ ማዘዟን ጠቅላይ ሚኒስትሯ አሳወቁ። Advertisements

ሳዑዲ ከተመነተፈችው ውስጥ 107 ቢሊዮን ዶላር አስመለሰች፤

ሳዑዲ አረቢያ በሙስና ላይ በከፈተችው ከፍተኛ ዘመቻ እስካሁን 107 ቢሊዮን ዶላር ማስመለሷን የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለጹ፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ አብዛኞቹ ቢፈቱም ሃምሳ ስድስቱ ግን አሁንም በምርመራ ላይ እንዳሉም ተናግረዋል፡፡ የሳዑዲ አረቢያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሼህ ሳዑድ አል ሞጀብ ከፍተኛ ደረጃ ባላቸው… Read More ›

“እኔ ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ ከበላይ የተሰጠኝ ጥሪ በመከተል ኬንያ ሪፐብሊክን ፕሬዝዳትነት ተረክቤያለሁ”

የኬንያ የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ በመዲናይቱ ናይሮቢ በሺህዎች በሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ፊት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት መሆናቸውን አወጁ፡፡ ቃለ መሃላም ፈጽመዋል፡፡ ኦዲንጋ በእርሳቸው ቅሬታ ጭምር ባለፈው ጥቅምት በድጋሚ የተካሄደውን ውጤት ለመቀበል አሻፈረኝ ብለው ነው የራሳቸውን በዓለ ሲመት ያደረጉት፡፡

ጆርጅ ዊሃ ቃለ-መሃላ ፈፀመ፤ ” ሙስናን እዋጋለሁ”

የቀድሞው ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ተጫዋች ጆርጅ ዊሃ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ሆኖ ቃለ መሃላ ፈፀመ። ዊሃ ሞንሮቪያ ውስጥ ቃለ መሃላውን በፈፀመበት ሥነ-ሥርዓት ላይ ለተሰበሰበው ሕዝብ ባደረገው ንግግር ”ለበርካታ ጊዜያት ስታዲየም ውስጥ ተገኝቻለው፤ ዛሬው ግን ከሌሎቹ ጊዜያት እጅግ የተለየነው” ብሏል።

የሳምንቱ ወሬዎች

የአባዱላ አጣብቂኝ “የለውጥ አራማጆች” ተነስተዋል በሚባልበት እና የእርሱም የሥልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ከዚሁ የለውጥ ማዕበል ጋር የተያያዘ ነው በሚል ሲዘገብለት የነበረው “ጃርሳው” ከኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ በኋላ ጀርባውን ለኦህዴድ መስጠቱ ሁሉንም ነገር በዜሮ የሚባዛው ሆኗል። የገዱ አንዳርጋቸው ፈተና የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት… Read More ›

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አምስት ሀገራት ውስጥ ተመደበ – አጫጨር ዜናዎች

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አምስት ሀገራት ውስጥ ተመደበ (ኢሳት ዜና–ጥቅምት 15/2010)የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከአፍሪካ የመጨረሻዎቹ አምስት ውስጥ ሲመደብ ከአለም ደግሞ 185ኛ በመሆን ዝቅተኛ ደረጃ ላይ መገኘቱን ፓስፖርት ኢንዴክስ ይፋ ያደረገው አዲስ ሪፖርት አስታወቀ። የሀገራትን የጉዞ ሰነድ ወይንም ፓስፖርት ጥንካሬ የሚገመግመው ፓስፖርት… Read More ›

አጫጭር ወሬዎች

ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ አሳስቦናል አሉ (ኢሳት ዜና–ጥቅምት 10/2010) ሁለቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ ድባብ እንዳሳሰባቸውና አለመቻቻልና ከፋፋይ ፖለቲካ እየተባባሰ መምጣቱ ለሀገሪቱ አደጋ ነው አሉ። ባራክ ኦባማና ጆርጅ ቡሽ የወቅቱን ፕሬዝዳንት ስም ሳይጠቅሱ አሁን… Read More ›

መረን የወጣው የአፍሪካ አምባገነኖች – የጨለመ አመለካከታቸው

የአፍሪካ መሪዎች እንዴት ነው የሚያስቡት? በትክክል የሚያረካቸው ምንድን ነው? ዘመናቸውን ሁሉ በደም ተጨማልቀው መኖር እንዴት ያረካቸዋል? ለሌብነታቸውስ እንዴት ገደብ አይኖራቸውም? በእነሱ የስልጣን ጥማት ሳቢያ የሚፈሰው ደም መቼ ነው ጥማቸውን የሚቆርጠው? መቼ ነው ደም መጋት የሚበቃቸው? ለመሆኑ የመጨረሻ አላማቸው ምንድን ነው?… Read More ›

ናይሮቢ ፖሊስ ሰልፈኞችን በተነ

የኬንያ ፖሊስ ኬንያ ውስጥ ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ ሰልፈኞች መገደላቸዉን እና ሌሎች ሦስት ደግሞ መቁሰላቸዉን አስታወቀ። ሁለቱ ሰዎች ቦዶ በተባለችዉ ከተማ የሚገኝ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ሰብረው ለመግባት ሲሞክሩ ነው የተገደሉት ብሏል ፖሊስ። ከዚህም ሌላ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ ባገደባቸው ሦስት የኬንያ ከተሞችም… Read More ›

ዙማ ሊከሰሱ እንደሚችሉ ፍርድ ቤት ወሰነ

የደቡብ አፍሪቃ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጄኮብ ዙማ ሊከሰሱ ይችላሉ ሲል ዛሬ ውሳኔ አሳለፈ። በፍርድ ቤቱ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ውሳኔ መሠረት ዙማ በጎርጎሮሳዊው 1990 ከተፈፀሙ የጦር መሣሪያ ግዥ ውሎች ጋር በተያያዙ 800 በሚሆኑ የሙስና ክስ ጭቦች ሊከሰሱ ይችላሉ። በዙማ… Read More ›