Advertisements

About

ዛጎል ዜና –
የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ዜናዎች፣ መጣጥፎች እንዲሁም የግል አስተያየቶች የሚሰራጩበት ሚዲያ ነው።
በዛጎል የተለየ እምነትና የፖለቲካ ዝንባሌ የለም። ቢቻል መረጃዎችን ለማጣጣም እንሞክራለን።
የዛጎል አዘጋጅ ሃላፊነት ውስዶ በራሱ እምነት የሚያትመው ርዕሰአንቀጽ ብቻ ነው። ዛጎል የተለያዩ አገራት የሚኖሩ አማካሪዎችና ረዳቶች አሉት። ሁሉም በበጎ ፈቃደኛነት በትርፍ ጊዜ የሚሰሩና መረጃን የማሰራጨት እምነት ያላቸው ናቸው።
ዛጎል ቢቻል እርቅን፣ መግባባትን፣ መቻቻልን፣ ለዩነትን በሰለጠነ መንገድ ለማራመደ ለሚተጉ ቅድሚያ አላት። ክብርም ትሰጣቸዋለች።
ለዛጎል ማንኛውንም መረጃ ለመስጠትም ሆነ አስተያየት ለመቀበል ገድብ ስለሌለ በኢሜል አድራሻችን zaggolenews2016@gmail.com ብትልኩልን ደስታችን ከፍ ያለ ነው።
ዛጎል ለተመጣጠነ መረጃ!!
ዓላማ

ዛጎል ዋና ዓላማዋ በተቻለ መጠን ሁሉ መረጃን ማራባትና ማዳረስ ሲሆን፣ የተለያዩ ሃሳቦችን ያለ ስጋት በማተም አንባቢያን የራሳቸውን ግምት እንዲወስዱ ማስቻል ነው
ከዚህም በተጨማሪ መረጃዎችን በማደራጀት የምርመራ ስራዎችን በተቆለፈ ገጽ ማቅረብ ነው
ራዕይ

ዛጎል ቀዳሚ ራዕይዋ ሬዲዮ መክፈት ሲሆን ለዚህም የረዳ ዘንድ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ላይ ነች። የሬድዮ ዝግጅታችን በውጪ አገር ያሉ ወገኖች ላይ ያለውን የብቸኛነት፣ የግናዛቤና፣ የስነ ለቦና መወዛገብ ለመቅረፍ በሚያስችል ሁኔታ ባለሟይዎች የሚሳተፉበት የሚሆን በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጠዋል
ዛጎል ሾው

የዛጎል ሾው ቲቪ ትልቁ ራዕያችን ነው። ከሬዲዮ ምስረታው ጋር ጎን ለጎን የሚካሄድ፣ ባለሙያዎችን ያካተተ ትልቅ ቲም የሚኖሩት ይሆናል። በዛጎል ሾው ” ኢትዮጵያዊቷ ኦጵራ” ተተዋወቃለች።

Advertisements