ዳጋ እስጢፋኖስ – የመነነው ገዳም

ዳጋ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሦስት ነገር ይታወቃል፡፡ የመጀመሪያው ገዳማዊው ሕይወት ነው፡፡ ከዓለም የራቀ እውነተኛ ገዳም ነው፡፡ ዙሪያውን በባሕር የታጠረና ከአእዋፍ ድምጽና ከሐይቁ የማዕበል ድምጽ በቀር ምንም አይሰማበትም፡፡ ሥራ፣ ትምህርትና ጸሎት አንድ ሆነው የተገመዱበት ገዳም ነው ዳጋ –

ዳንኤል ክብረት

በ13ኛው መክዘ መግቢያ(እንደ ገዳሙ ታሪክ በ1268 ዓ.ም) የሐይቅ እስጢፋኖስ የአቡነ ኢየሱስ ሞአ ደቀ መዝሙርና የዐፄ ይኩኖ አምላክ(1263-1277 ዓ.ም.) ወንድም በነበሩት በአቡነ ኂሩተ አምላክ የተመሠረተው ዳጋ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም እስካሁን ድረስ በታሪክ ጥንታዊ፣ በእምነት ኦርቶዶክሳዊ፣ በአነዋወር ገዳማዊ፣ በሕይወት ተባሕቷዊ ሆኖ እንደቀጠለ ነው፡፡

አቡነ ኂሩተ አምላክ ገዳሙን በሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስም የቆረቆሩት የሐይቅ እስጢፋኖስን ለማሰብ ይመስላል፡፡ ጥንታውያን የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከሚታወቁበት መለያ አንዱ ብዙ ጊዜ የሚጠሩት በሰማዕታት (ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ ቅዱስ ቂርቆስ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ በአርባዕቱ እንስሳ፣ በቅዱስ ሚካኤልና በቅድስት ድንግል ማርያም ነው፡፡ አቡነ ኂሩተ አምላክ ወደ ዳጋ ሲመጡ በእመቤታችን ስም የተሠራች ቤተ ክርስቲያን ማግኘታቸውን የገዳሙ ታሪክ ይናገራል፡፡ አካባቢ ከአኩስም ዘመን ጀምሮ ክርስትና የተስፋፋበት በመሆኑ ይህ የሚደንቅ አይደለም፡፡ የእመቤታችንን ታቦት ወደ ደቅ ደሴት በመውሰድ የቅዱስ እስጢፋኖስ ታቦት የገባው በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን መሆኑ ይነገራል፡፡

ገዳሙ ከጣና ሐይቅ በስተ ምሥራቅ በጣና ማዕከላዊ ሥፍራ ላይ ከደቅ ደሴት አጠገብ ይገኛል፡፡ የደሴቱ ስፋት ሦስት ኪሎ ሜትር ያህላል፡፡ ቤተ ክርስቲያኑ ከተራራው ጫፍ ላይ ሲገኝ የመነኮሳቱ መኖሪያ በዙሪያው ከትሟል፡፡ የመናንያኑ ምግብ ›መኩሬታ› የሚባል ምግብ ሲሆን ከዳጉሳ እህል የሚዘጋጅ ዳቦ የመሰለ ምግብ ነው፡፡ ምግብ የሚበላው ውሎ ነው፡፡ ያውም ወደ ሁለት ሰዓት የሚፈጅ ጸሎት ከተደረገ በኋላ፡፡

ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ(1426-1660 ዓ.ም.)፣ ዐፄ ሱስንዮስ(1600-1625 ዓ.ም.)ና ዐፄ ፋሲለደስ(1625-1600 ዓ.ም.) ለገዳሙ ቤተ ክርስቲያን ሠርተዋል፡፡ የነበረውን ጠግነዋል፡፡ ዳጋ እስጢፋኖስ በጣና ውስጥ የመጀመሪያው ገዳም ነው፡፡ ዐፄ ይስሐቅ(1406-1421 ዓ.ም.) ለጎሜ እና ዘጎር የተባሉትን ርስቶች ለገዳሙ ሰጥተው ነበር፡፡ በዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዘመን የገዳሙ መምህር የነበሩት አቡነ ይስሐቅ አባ ፍሬ ጽዮን የተባሉትን ሰዓሊ በመንበር ላይ የሚቀመጥ ሥዕል እንዲስሉ አድርገዋቸው ነበር፡፡ በወቅቱም ብዙ የግድግዳ ሥዕሎች ተሥለው ነበር፡፡ በመካከለኛው ዘመን አጋማሽ ዳጋ እስጢፋኖስ የነገሥታቱ የመቀበሪያ ገዳም ሆኖ ነበር፡፡ የዐፄ ዳዊት(1374-1406 ዓ.ም.)፣ የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ፣ የዐፄ ፋሲል፣ የዐፄ ሱስንዮስ፣ ዐጽሞች ዛሬም በገዳሙ ይገኛሉ፡፡ ዐፄ ናዖድ(1488-1500 ዓ.ም.) የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ዐፅም ከደብረ ነጎድጓድ አውጥተው ነው ወደ ዳጋ የወሰዱት፡፡ በ16ኛው መክዘ ገዳሙ የነገሥታቱና የንጉሣውያን ቤተሰቦች መቃብር ነበር፡፡

በ1556 አና በ1567 ዓም መካከል ባለው ዘመን የገዳሙ አበ ምኔት አባ ገብረ ክርስቶስ ከከንቲባ ገብረ ሚካኤል ባገኙት ድጋፍ ገዳሙን አንደገና አሳንጸውት ነበር፡፡ በገዳሙ የሚገኙ ሁለት የካንቫስ ሥዕሎች በዚህ ዘመን የተጠገኑ ሳይሆን እንደማይቀሩ ይገመታል፡፡ ዐፄ ሰርጸ ድንግል(1555-1589 ዓ.ም.) ከአዳሎች ጋር ለነበረበት ጦርነት ገዳሙን በጸሎት እንዲረዱት ጠይቆ ነበር፡፡ ሲመለስም ለገዳሙ በደቅ ደሴት ጉልት ሰጥቷል፡፡ አያሌ የከበሩ ዕቃዎችንም አበርክቷል፡፡ ድል አድርጎ የማረካቸውም ዕቃዎች በገዳሙ አኑሯቸዋል፡፡ ዐፄ ዘድንግል(1596-1597 ዓ.ም.) ያደገው በኋላም የተቀበረው በዳጋ ደሴት ነው፡፡

ዐፄ ፋሲለደስ(1625-1660ዓ.ም.) ለዳጋና ለክብራን በ1659 ዓም አካባቢ ደርደራ የተባለውን ጉልት ሰጥቶ ነበር፡፡ ዐፄ ዮሐንስም(1660-1674 ዓ.ም.) ይህንን ጉልት በ1670 አካባቢ አጽንተውታል፡፡ ዐፄ ፋሲል ከዚህም በላይ ቤተ ክርስቲያኑን ከ1654-56 ዓም ባለው ዘመን እንደገና ሠርቶ አጠናቅቆት ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ቤተ ክርስቲያን በ1707 ዓ.ም ተቃጠለ፡፡ ንጉሡም ዘቢድ የተባለውን ጉልት ለካህናቱ ሰጠ፡፡ በዚህም የተነሣ መጀመሪያ በአዞዞ የተቀበረው ዐፄ ፋሲለደስ በኋላ ዐጽሙ ወደ ዳጋ ተዛውሯል፡፡

ዐፄ ኢያሱ አድያም ሰገድ(1674-1698 ዓ.ም) ከ1673 ዓም ጀምሮ ዳጋን በተደጋጋሚ ይጎበኝ ነበር፡፡ በ1676 ዓም. አባ አርኩን የተኩት አበምኔት መምህር አስካል ለንጉሡ በጣም ቅርብ ነበሩ፡፡ እቴጌ ብርሃን ሞገሳ ናርጋ ሥላሴን ባሠሩ ጊዜ የዳጋ እስጢፋኖስ የነበረውን ጉልት ለናርጋ በመስጠታቸው ችግር ተፈጥሮ ነበረ፡፡

ዐፄ ተክለ ጊዮርጊስ በሐምሌ በ1774 ዓም ዳጋ የመማጸኛ ቦታ እንዲሆን ዐውጀው ነበር፡፡

ዳጋ እስጢፋኖስ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በሦስት ነገር ይታወቃል፡፡ የመጀመሪያው ገዳማዊው ሕይወት ነው፡፡ ከዓለም የራቀ እውነተኛ ገዳም ነው፡፡ ዙሪያውን በባሕር የታጠረና ከአእዋፍ ድምጽና ከሐይቁ የማዕበል ድምጽ በቀር ምንም አይሰማበትም፡፡ ሥራ፣ ትምህርትና ጸሎት አንድ ሆነው የተገመዱበት ገዳም ነው ዳጋ፤ በገዳሙ ከሚገኙት በላይ በአውሮፓ አብያተ መጻሕፍት ተበትነው የሚገኙት መጻሕፍቱ የገዳማውያኑን ዕውቀትና ትጋት ይመሰክራሉ፡፡ ገዳማውያኑ ከጠዋትና ከማታው ጸሎት በሚተርፈው ጊዜ አትክልት ይተክላሉ፣ ፍራፍሬ ያመርታሉ፤ ከዚያም አልፈው ዳጋን የተሳለመ ቱሪስት ሳይገዛው የማይወጣውን ቢለብሱት የሚሞቅ፣ ቢያለብሱት የሚያስመርቅ ጋቢ ይሠራሉ፡፡ ያ ጋቢ በጸሎትና በተባረኩ እጆች የሚሠራ ነውና በረከቱም የማይጠገብ ነው፡፡

ዳጋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ከግራኝና ከደርቡሽ ተርፎ ከተቀመጠባቸው ገዳማት አንዱ ነው፡፡ በዐፄ ሱስንዮስ ዘመን(1600-1625 ዓ.ም.) በገዳሙ የድጓ መጽሐፍ ላይ የተጻፈው የመጽሐፍ ዝርዝር የዳጋን የዕውቀት ማዕከልነት ያመለክታል፡፡

ኆልቈ መጻሕፍት ዘዳጋ

 1. ኦሪት -1
 2. ግብረ ሕማማት -1
 3. ዕዝራ -2
 4. ኢሳይያስ – 2 ዳንኤል – 2
 5. ነገሥት – 1
 6. መቃብያን – 1
 7. ምሳሌያተ ሰሎሞን – 1
 8. ሄኖክ – 1
 9. ሲራክ – 1
 10. ሕዝቅኤል – 1
 11. ጦቢት – 1
 12. ኤርምያስ – 1
 13. ደቂቀ ነቢያት – 1
 14. መልከ ጼዴቅ – 1
 15. ኢዮብ – 1

16.ኩፋሌ – 1

 1. ዳዊት – 2
 2. ሳቤላ – 1

19.ወንጌል -3

20.ጳውሎስ ዘምስለ ትርጓሜ -1

 1. ግብረ ሐዋርያ – 1

22.ግጻዌ – 2

23.ጸሎተ ቁርባን – 1

24.ሲኖዶስ -3

25.ቀሌምንጦ – 1

26.ዲድስቅልያ – 1

27.ኪዳን – 3

28.ፍካሬ ኢየሱስ – 1

29.ምእዳን – 1

30.ተአምር – 2

 1. ስንክሳር – 2

32.ገድለ ሰማዕታት – 3

33.መጽሐፈ ዶርሆ – 1

34.መጽሐፈ ልደቱ – 1

35.መጽሐፈ በአታ ወቁስቋም – 2

36.መጽሐፈ ፍልሰታ – 2

37.አርአያ ማርያም – 1

38.ላሐ ማርያም – 1

39.ድርሳነ ሚካኤል – 1

40.ድርሳነ ገብርኤል – 1

 1. ድርሳነ አርባዕቱ እንስሳ ወካህናተ ሰማይ – 1

42.ድርሳነ ሩፋኤል ወአፍኒን – 1

43.መዝሙር – 3

44.ዝማሬ… ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – 1

45.ገድለ ሐዋርያት – 2

46.ምዕላድ (መጽሐፈ) – 1

47.ርቱዓነ ሃይማኖት – 1

48.መጽሐፈ ምስጢር – 1

49.መቃቢስ – 1

50.አፈወርቅ – 1

 1. መጽሐፈ ዜና አበው – 2

52.ሥርዓተ ምንኩስና – 1

53.እንጦንዮስ – 1

54.ኪሮስ – 1

55.ገብረ ክርስቶስ (ገድለ) – 1

56.ገድለ አቢብ – 1

57.ገድለ … – 1

58.ዜና እስጢፋኖስ – 1

59.ገድለ እስጢፋኖስ – 1

60.(ገድለ) ጊዮርጊስ – 1

61.ገድለ ፋሲለደስ -1

62.ገድለ አበ ከረዙን – 1

63.ገድለ አባ ኖብ – 1

64.ገድለ ዮስጦስ – 1

65.ገድለ ቴዎድሮስ – 1

 1. ገድለ አባ በኪሞስ – 1

67.ገድለ አባ ነብዩድ – 1

68.ማርቆስ ዘቶርመቅ – 1

 1. ገድለ አባ ብሶይ

70.ገድለ ሄሮዳ – 1

 1. ሳቤላ – 1

72.ዮሐንስ መጥምቅ – 1

73.ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ – 1

74.ስሞኒ ወአሮን – 1

75.ገድለ አባ ገሪማ – 1

76.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን – 1

77.ገድለ…. -1

78.ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት – 1

79.ገድለ አባ ተክለ ሐዋርያት – 1

80.ገድለ አባ በጸሎተ ሚካኤል – 1

 1. ድርሳነ ሰንበት – 1

82.እግዚአብሔር ነግሠ – 1

፻(ወ)፳ወ፯ ዝየ ኆልቈሙ ቦ እለ ባሕቲቶሙ ወቦ እለ በአኅብሮ ዘተጽሕፉ  መጻሕፍት ዘደብረ ዳጋ

(ከዚህ በኋላ እነዚህን ይጨምራል)

83.ጉባኤ ነቢያት -1

 1. ረድእ ወመምህር – 1

85.መጽሐፈ ኅዳር – 1

86.ማር ይስሐቅ – 1

87.መጽሐፈ ብርሃን – 1

88.ዮሐንስ ከማ – 1

89.መጽሐፈ ጥምቀት – 1

90.ገድለ ኢየሱስ ሞአ – 1

91.ቅዳሴ – 1

92.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን

በአድያም ሰገድ ኢያሱ ዘመን በዳጋው ወንጌል ላይ በተመዘገበ ሌላ የቆጠራ ዝርዝር ደግሞ ቀጥለው ያሉት ተዘርዝረዋል፡፡

 1. ገድለ አባ ኢየሱስ ሞአ -1
 2. ተአምረ ቅዱስ ጊዮርጊስ – 1
 3. ገድለ ቅዱስ ቴዎድሮስ – 1
 4. ገድለ ማር ዮሐንስ -1
 5. ገድለ አባ ኖብ ወአርከሌዲስ- 1
 6. መጽሐፈ ዶርሆ – 1
 7. መጽሐፈ ቄድር – 1
 8. ፍካሬ ኢየሱስ – 1
 9. ድርሳነ ሚካኤልና ገብርኤል – 1
 10. መጽሐፈ ጥምቀት – 1
 11. ግጻዌ – 1
 12. መጽሐፈ ፍትሐት – 1
 13. ድጓ -2
 14. ዝማሬ -2
 15. የያሬድ እግዚአብሔር ነግሠ -1

16.መጽሐፈ ሰንበት – 1

 1. ቅዳሴ -3
 2. ታሪክ -1

19.መጽሐፈ ምግባር -1

20.መጽሐፈ ሐዊ- 1

 1. ርቱዓ ሃይማኖት -1

22.ክብረ ነገሥት – 1

23.ጊዮርጊስ ወልደ አሚድ -1

24.መጽሐፈ በርለዓም -1

25.አርባዕቱ ወንጌል 4

26.ጳውሎስ – 2

27.ግብረ ሐዋርያት – 1

28.ቀለምሲስ – 1

29.ሐዋርያ -1

30.ሲኖዶስ – 2

 1. ዲድስቅልያ -1

32.ቀሌምንጦስ -1

33.ፈውስ መንፈሳዊ፣ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን – 1

34.ሃይማኖተ አበው -2

35.ድርሳነ ቄርሎስ -1

36.አፈወርቅ -1

37.ረድአ እንጦንስ -1

38.ማር ይስሐቅ – 1

39.አረጋዊ መንፈሳዊ -1

40.አረጋዊ ዜና አበው – 1

 1. ፊልክስዩስ -1

42.ፍትሐ ነገሥት -2

43.ስንክሳር -2

44.ተአምረ እግዝእትነ ማርያም -2

45.ተአምረ ኢየሱስ -1

46.ትርጓሜ ጳውሎስ -1

47.ገድለ ሐዋርያት -3

48.ገድለ ጴጥሮስ ወጳውሎስ -1

49.ገድለ ሰማዕታት -2

50.መጽሐፈ ኅዳር -1

 1. መጽሐፈ ኪዳንና ሰርጊስ -1

52.መቃቢስ – 1

53.ፈረጅ -2

54.ዜና አይሁድ – 1

55.ግብረ ሕማማት – 1

56.መጽሐፈ ነቢዩድ – 1

57.ዜና አበው – 2

58.ረድእ ወመምህር – 1

59.አክሲማሮስ – 2

60.ድርሳነ ሩፋኤል -1

61.ጉባኤ መልክእ – 1

62.ገድለ ጻድቃን – 1

63.ገድለ ወለቱ – 1

64.ሰንጠረዥ – 1

65.ላሐ ማርያም – 1

 1. መጽሐፈ ምንኩስና – 1

67.ገድለ ቂርቆስ – 1

68.ገድለ ያሳይ – 1

 1. ድርሳነ ኢየሱስ – 1

ወኩሎሙ ድሙር ኆልቆ መጻሕፍት ፻ወ፴

ኆቆ መጻሕፍት

70.ኦሪት – 2

 1. ዕዝራ፣ ኢዮብ – 1

72.ጉባኤ ነቢያት – 1

73.ኢሳይያስ -1

74.ዳንኤል – 1

75.ኤርምያስ፣ ዳንኤል – 1

76.ነገሥት -1

77.ጦቢትና መጽሐፈ ኪዳን – 1

78.ሲራክ – 1

79.ኩፋሌ -1

80.ደቂቀ ነቢያትና ሰሎሞን -1

 1. ሕዝቅኤልና ዕዝራ – 1

82.መቃብያን – 1

83.ዳዊት -1

84.ሄኖክና ድርሳነ ገብርኤል -1

85.ገድለ ገብረ መንፈስ ቅዱስና ገድለ አፍቅረነ እግዚእ -1

86.ገድለ ተክለ ሃይማኖትና ገደለ ተክለ ሐዋርያት -1

87.ገድለ አባ ሳሙኤል -1

88.ገድለ አባ ከረዙንና አባ ጌርዳ

89.ገድለ አብርሃም

90.ገድለ አባ ገሪማና ገድለ እስጢፋኖስ -1

91.ድርሳነ ማርያም -1

92.ገድለ አቡናፍርና መልከ ጼዴቅ – 1

93.መጽሐፈ ፍልሰታ – 1

94.ገድለ ቴዎድሮስ ገድለ ኪሮስ -1

95.ገድለ አባ በግዑ ገድለ መብዐ ጽዮን – 1

 1. ገድለ አርሲማ ገድለ በርበራ – 1

97.ገድለ አባ ጰንጠሌዎን – 1

98.መጽሐፈ ምስጢር- 1

 1. ገድለ አባ በጸሎተ ሚካኤል -1
 2. ገድለ ላሊበላ – 1

101.መጽሐፈ ምዕላድ – 1

 1. መጽሐፈ ብርሃን -1
 2. ገድለ ጳውሊና መጽሐፈ እንጦንስ -1
 3. ገድለ ኪሮስ – 1
 4. ገድለ ፋሲለደስ – 1
 5. ድርሳነ ማርያምና በኪሞስ – 1
 6. ርቱዓ ሃይማኖት – 1
 7. የሐፄ እግዚአብሔር ነግሠ ከነ ተአምሩ – 1
 8. እግዚአብሔር ነግሠ የአርኬ – 1

110.ገድለ ገብረ ክርስቶስና ገድለ አቢብ – 1

111.ገድለ እስጢፋኖስና ገድለ ገላውዴዎስ – 1

ይቀጥላል፡፡

Advertisements

“የሰይጣኑ መንገድ” የኢትዮጵያው ታላቁ ግንብ?

ቦታው ሰሜን ጎንደር በለሳ ወረዳ ነው። ከአፄ ሲስኒዮስ ቤተመንግስት ባሻገር ይገኛል። በልጅነታችን ከምንፈራው ቦታ መካከል አንዱ ነው። ባለቤትነቱን ማን ለሰይጣን እንደሰጠው ግልፅ አይደለም። የጠየኳቸው ሰዎች ሁሉ ሊያስረዱኝ አልቻሉም። ምንጩን ስለማያውቁት ይመስላል፣ የሰይጣን መንገድ ብለውታል። ተፈጥሮው ትንግርት ሆኖባቸው ይመስለኛል።

Continue Reading

ግልጽ ደብዳቤ ለሐይማኖት አባቶች

 አያሌው አስረስ (መምህርና ጋዜጠኛ፤ የቅንጅት የቀድሞ የአዲስ አበባ ተመራጭ) Addisabmass – በአለፉት 45 ቀናት ውስጥ ሁለት ጊዜ ያህል በቴሌቭዥን መስኮት ቀርባችሁ ስለ ሰላም አስፈላጊነትና ጠቃሚነት ምክር ሰጥታችኋል፡፡ ያንን ምክር ከተከታተሉት ሰዎች አንዱ እኔ ብሆንም ድፍረት ባይሆንብኝ፣ ነገሩ ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ ሆኖ ታይቶኛል፡፡ ስለ ሰላም እያስተማራችሁ ያላችሁት፣ የሰላምን ዋጋን የሚያውቀውን፣ የሚፈልገውን፣ ሰላም በሚፈልገው መንገድ ማግኘት አልሆንለት ብሎ የሚይዘው የሚጨብጠው ያጣውን፣ ቁጣውን በልዩ ልዩ መንገድ እየገለጠ ያለውን ሕዝብ ነው፡፡

Continue Reading

የባላምባራስ ሻህእርገጥ ስለአድዋ ጦርነት የዓይን ምስክርነት

(አቅራቢ፥ ጌታቸው ኃይሌ)

ባ፲፰፻፸፱ ዓ ም ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ጃንሆይ አጼ ምኒልክ ሐረር ጨለንቆ አሚር አብዱላሂን ድል አድርገው ወዲያው ባላምባራስ መኰንን ነበሩና ደጃዝማች ብለው ሐረርን ሾሟቸው።

Continue Reading

እየተዘነጋ ያለው የተዋሕዶ አባቶች ሚና በዐድዋ ዘመቻ — ሐራ ዘተዋሕዶ

“ውጊያው የተጀመረው በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ቃል ነው፤“ “ጦርነቱን ድል ያደረግነው በካህናት አባቶቻችንም አስተዋፅኦ ነው፤“ “ወደ ሮም ከሔዱት ዲፕሎማቶች ቄስ ወ/ሚካኤል አንዱ ናቸው፤“ ††† (ዘ አዲስ/Ze Addis) የዐድዋን ጦርነት ዘመቻ ከመሠረቱ እስከ መደምደሚያው ድረስ ለድል ካበቁት ኢትዮጵያውያን ወገኖች መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ:: የዐድዋ ዘመቻ ከመታወጁ በፊት ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ […]

via እየተዘነጋ ያለው የተዋሕዶ አባቶች ሚና በዐድዋ ዘመቻ — ሐራ ዘተዋሕዶ

እየተዘነጋ ያለው የተዋሕዶ አባቶች ሚና በዐድዋ ዘመቻ

 • ውጊያው የተጀመረው በሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ቃል ነው፤
 • “ጦርነቱን ድል ያደረግነው በካህናት አባቶቻችንም አስተዋፅኦ ነው፤
 • ወደ ሮምሔዱት ዲፕሎማቶች ቄስ ወ/ሚካኤል አንዱ ናቸው፤

†††

(ዘ አዲስ/Ze Addis)

የዐድዋን ጦርነት ዘመቻ ከመሠረቱ እስከ መደምደሚያው ድረስ ለድል ካበቁት ኢትዮጵያውያን ወገኖች መካከል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች በዋናነት ይጠቀሳሉ::

የዐድዋ ዘመቻ ከመታወጁ በፊት ጉዳዩ በሰላም እንዲያልቅ ካህናት አባቶች በዲፕሎማሲው ተመድበው ሮም ድረስ ተጉዘዋል:: ጦርነቱም ከመጀመሩ በፊት ምሕላ አስይዘው ሕዝቡን ለውጊያ ሲያዘጋጁ ነበር:: ጦርነቱ ሲታወጅም የወቅቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣ ዕጨጌው፣ እጅግ በርካታ ካህናት እና መነኰሳት ታቦታትን ይዘው ዘምተዋል:: በዝርዝር እንመልከተው፡፡

**********

ቅድመ ውጊያ

የዐድዋ ዘመቻ ከመታወጁና ጉዳዩ ወደ ጦርነት ከማምራቱ በፊት በሰላም ለመጨረስ ኢትዮጵያ ብዙ ርቀት ሔዳለች:: ተወካዮቿን ሮም – ጣልያን ድረስ በመላክ ኹኔታውን በሰላም ለመጨረስ ሰፊና ብልሃት የተሞላበት የዲፕሎማሲ ጥረት አድርጋ ነበር:: ይኸው በራስ መኰንን የተመራው የዲፕሎማቶች ቡድን ወደ ጣልያን በማምራት ከጣልያኑ ንጉሥ ኡምቤርቶ እና ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ክሪስፒ ጋራ ዝርዝር ውይይት አድርጓል::

28058963_2033852436892830_838589383464906887_n

የዲፕሎማት ቡድኑ አባልና ዋና ሰው ከነበሩት መካከል፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ካህን፣ ቄስ ወልደ ሚካኤል አንዱ ናቸው:: ካህኑ፣ ከራስ መኰንን ቀጥለው የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ቡድን ኹለተኛው ሰው ነበሩ:: በሐርቫርድ ዩንቨርስቲ የታተመው የፕሮፌሰር ሬይመንድ ጆናስ “Battle of Adwa : African Victory in the Age of Empire” የተባለው መጽሐፍ ገጽ 82 ላይ እንዲህ ይላል፡-

“Ras Mekonnen delegation included translator Joseph Niguse, Orthodox priest WoldeMichael, and five other high ranking figures. They were supported by thirteen bodyguards and twenty one persola aides.”

**********

የዐድዋ ዘመቻ እና አበው ካህናት፤

የጣልያን ጉዳይ በዲፕሎማሲ እንደማያዋጣና መፍትሔውም ራስን የመከላከል ፍልሚያ መኾኑን በተደጋጋሚ ያስታወቀችው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ናት:: የወቅቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ማቴዎስ ጉዳዩን ጠንክረው የገፉበት ሲኾን፣ በቤተ መንግሥቱም ግፊት አድርገዋል:: ለጦርነቱ ክተት ሲታወጅም የቤተ ክህነቱ ዋና ዋና ሰዎች፣ እጅግ በርካታ ካህናትና መነኰሳት ወደ ዘመቻ ተመዋል:: ከታቦታቸው ጋራ ሦስት ወራት የፈጀ መንገድ ተጉዘዋል:: በየመንገዱ ከመገዘት ጀምሮ እስከ መጨረሻው የውጊያ ግንባር ድረስ በአካል ተሰልፈው ተዋጊዎችን በማበረታታት፣ የደከሙትን በማጽናት፣ የተሠዉትን በመፍታት( ጸሎተ ፍትሐት) በአካል መሣርያ ይዘው በመዋጋትም ትልቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል::

ይህን እውነት በወቅቱ የነበረ ካፒቴን ሞልቴዶ የተባለ የኢጣልያ ጋዜጠኛ እንዲህ ሲል ጽፎታል (Moltedo , G L assedio Di Maccale)፤

“የሐበሾች ጦር .. ከሁሉም ብሔረሰብ ተውጣጥቶ ቀርቧል:: ..ጦርነቱንም ከወታደሮች ጋር ብቻ አልገጠምንም:: ..ቄሶች ሳይቀሩ ወጉን፤” በማለት ውጊያ ላይ የተሳተፉት ካህናትም ጭምር እንደነበሩ ይነግረናል:: (ጳውሎስ ኞኞም፣ “ዐጤ ምኒሊክ” በሚለው መጽሐፉ ገጽ 162 ጠቅሶታል)

28279049_564349027263327_1473745430431071812_n

በተለይ ከዘማቹ ቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ጋራ ተያይዞ ገና ከመነሻው ብዙ ተኣምራት ይታዩ ነበር:: በዘመቻው ወቅት ታሪክ ጸሓፊ የነበሩት- ጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ፣ በወቅቱ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጽላት ጋራ የነበረውን ተአምራት- “ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒልክ” በሚለው መጽሐፋቸው ገጽ 230 እንዲህ ሲሉ ዘግበውታል፡-

“በዚህም ዘመን በጥቅምት ሁለት ቀን ካዲስ አበባ ከተማ ተነሥተው ወደ ትግሬ ዘመቻ ተጓዙ::.. በዚያም ቀን እንደ ቀስተ ደመና ያለ እሳት የሚመስል ከሰማይ ላይ በምዕራብ በኩል ሲሔድ በአራት ሰዓት ታየ:: ጢሱም ሳይጠፋ ብዙ ቆየ፤ የጢሱም መልክ አረንጓዴ ይመስል ነበር፤ ድምፁም እንደ መድፍ ተኩስ ኾኖ ተሰማ::”

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መነኰሳት፣ በገዳማችን ወይ በደብራችን ቁጭ ብለን ስለ ዘመቻው እንጸልያለን፤” አይደለም ያሉት:: ከዘማቹ ጋራ አብረው ታቦታቸውን ይዘው ዘመቱ:: ታቦቱን ተሸክመው ሦስት ወር ሙሉ ተጓዙ::

**********

“ሒዱና ተዋጉ” ብለው ባርከው ያሰናበቱት ሊቀ ጳጳሱ ነበሩ፤

Abune Mathewos

አንቶኒ ሞክለር ስለ ዐድዋ ጦርነት የመጨረሻ ምዕራፍ ሲጽፍ እንዲህ ይላል፤

“ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ቅዳሴውን በሚመሩበት ግዜ ኹለት ጥይት ከውጭ ተተኮሰ:: .. ራስ መኰንንም የኢጣልያኖችን መምጣት ተናገሩ:: .. አቡኑም መስቀላቸውን በቀኝ እጃቸው ይዘው፣ልጆቼ ዛሬ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚገለጽበት ቀን ነው:: ሒዱ:: ለሃይማኖታችሁና ለንጉሣችሁ ተከላከሉ:: ኹላችሁንም ከኃጢአት እግዚአብሔር ይፍታችሁ፤ አሉ:: መኳንንቱም መስቀል ተሳልሞ ወደ ውጊያ ገባ ይላል፤ ጳውሎስ ኞኞ፡፡ (ዐጤ ምኒልክ፣ ገጽ 203)

የኢትዮጵያ ዋና ዋና የጦር መሪዎች ቅዳሴ ላይ ነበሩ:: ጣልያን የመጀመርያውን ጥይት እንደተኮሰ -ቅዳሴውን አጠናቀው የጦር መሪዎቹን ባርከው “ሒዱና ተዋጉ” ብለው መንፈሳዊ ቡራኬና የማበረታቻ ቃል ሰጥተው ኢትዮጵያውያንን ያሰናበቱት ጦርነቱን ያስጀመሩት – እዚያው በቦታው የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ናቸው::

የጦር አዝማቾቹ ወደ ውጊያ ሲገቡም ሊቀ ጳጳሱና ሌሎቹ ካህናት እጃቸውን ዘርግተው ይጸልዩ ነበር:: ይህን ጉዳይ ጸሓፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ፣ በ“ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ዐጤ ምኒሊክ” ገጽ 268 እንዲህ አስፍረውታል፡-

አቡነ ማቴዎስም ታቦተ ማርያምን ይዘው ካህናቱም መነኮሳቱም ኾነው ምሕላ ይዘው የጊዮርጊስን ስብሐተ ፍቁር ሳይጨርሱ ድል ለኢትዮጵያ ኾነ:: እኛም ለጊዜው የፊተኛ ሰልፍ ድል ቢሆን የተኩሱ መጨረሻ መስሎን ደስ አለን፡፡

የዐድዋ ጦርነት ላይ በአካል ተገኝተው ታሪክ ሲዘግቡ የዋሉት ጸሓፌ ትእዛዝ፣ በዚሁ ዘገባቸው ገጽ 264 ላይ እንዲህ ሲሉ ይቀጥላሉ፤

“የዘመቱትም የኢትዮጵያ መነኰሳት እጅግ ብዙ ነበሩ:: ወይባ፣ ኣጥፍ፣ የዳባ ቀሚስ የለበሱ፣ የሰሌን ቆብ ያደረጉ ብዙ ነበሩ:: የጦርነቱም ለት እኩሉ ከንጉሠ ነገሥቱ ጋር፣ እኩሉ ደግሞ ከንግሥቲቱ ከእቴጌ ጣይቱ ጋር፣ እኩሉ ደግሞ ከሰልፈኛው ጋር ኾነው ወደ ጦሩ የሚሔደውን እየናዘዙ፣ የደከመውን እያወገዙ ሲያዋጉ ዋሉ::”

በዐድዋ ዘመቻ ድል አድርገው ነጻነታችንን የሰጡን አርበኞች አባቶቻችንና እናቶቻችን ብቻ አይደሉም:: ሰማዕት ኾነው ነጻነታችንን የሰጡን፣ አበው ካህናት እና መነኰሳት አባቶቻችንም ጭምር ናቸው:: ለሀገራችን ነጻነት ካህናትና መነኰሳት ከወታደሩ እኩል እንደ ወታደር ተጉዘዋል:: እንደ ጦረኛ ተዋግተዋል:: አዋግተዋል:: ካህናቱ ብቻ ሳይኾኑ ታቦታቱም ዘምተዋል::

battle-of-adwa-1896

ድሮ የዐድዋ በዓል ሲዘከር፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት በምልዓት ይነገር እንደነበር ድርሳናት ይገልጻሉ:: በዐድዋ ክብረ በዓል የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕልም ይታተም ነበር:: ይህ ሥርዓት ከቀድሞው መንግሥት የኮሚኒዝም አስተሳሰብ ወደ ሥልጣን መምጣት ጋራ ተያይዞ እንደቀረ ከዚያም በኋላ እስከ አኹን የቤተ ክርስቲያኗ ድርሻ እንዲወሳ አይፈለግም::

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የዐድዋ ድል ዋነኛ ባለውለታ ናት:: ዐድዋ ሲወሳ የቤተ ክርስቲያኗ አስተዋፅኦ ይነሣ! ሌላው ባያደርገው ለእኛ ለኦርቶክሳውያን ግን ታሪካችን ነው:: በዓሉ በሚከበርበት ጊዜ ኹሉ የቤተ ክርስትያንዋ አስተዋፅኦ ይወሳ፤ ይነሳ::

**********

የኢትዮጵያ ጦር የተዋጋው ሑዳዴን እየጾመ ነውታቦተ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ጦር መሀል ነበረ

 • “የኢትዮጵያ ጦር አሰፋፈሩ የቤተ ክርስቲያንን ፕላን የተከተለ ነበር፤
 • ጦርነቱ የተደረገው በሑዳዴ ጾም ውስጥ ነው:: ጾም እንዳይሻር ጳጳሱ ገዘቱ፤
 • አቡነ ማቴዎስ ከዋናዎቹ የጦር አማካሪዎች አንዱ ነበሩ፤

†††

እየጾመ የተዋጋው የኢትዮጵያ ጦር፤

የዐድዋ ጦርነት የተካሔደው በገና እና በሑዳዴ አጽዋማት ወቅት ነው:: የዓምባላጌ እና የመቐሌው ውጊያዎች የተካሔደው በገና ጾም ሲኾን ዐድዋ ላይ በአሻሾ፣ ራዕዮ እና ሰማያታ ተራራ እና ሜዳ ላይ የካቲት 23 ቀን የተደረገው ዋናው የዐድዋ ውጊያ ደግሞ የተደረገው በሑዳዴ ጾም ነው:: የያኔው ጾም ደግሞ እንዳሁኑ አልነበረም:: ምእመኑ ቀኑን ጾሞ ምሽት ላይ ነበር የሚመገበው::

በዚህ ምክንያት “ሠራዊቱ እንዳይደክምብኝ በማለት ንገሠ ነገሥቱ ዐፄ ምኒልክ፣ ለጦርነቱ ሲባል የዘንድሮውን ጾም እንዳይጾም ዘማቹን ወታደር ይፍቱልኝ:: ጾሙ ለወታደሮቼ ይሻርልኝ፤” ብለው አቡኑን ጠይቀው ነበር:: አቡነ ማቴዎስ ግን እምቢኝ አሉ:: “ወታደርም ቢኾንዘመቻም ቢኾን ጾምን ሻሩ አልልም፤” ብለው እምቢ አሉ::

ጳውሎስ ኞኞ፣ “ዐጤ ምኒልክ” በሚለው መጽሓፉ ላይ ይህን አስገራሚ ታሪክ እንዲህ አስፍሮታል፡-

የዐድዋ ጦርነት የተካሔደው በገና እና በሑዳዴ ጾም ነው:: ክርስቲያኑ ዘማች በዚያን ግዜ እንደነበረው አጿጿሙ ራቱን በልቶ እስከሚቀጥለው ጀምበር መጥለቅ ምንም አይቀምስም:: ውኃ እንኳን አይጠጣም ነበር:: ይህን የተገነዘቡት ዐጤኒልክ ጳጳሱን አቡነ ማቴዎስንጦርነት ላይ መኾናችንን ያውቃሉ:: ሠራዊቱ በጦርነቱም በጦሙም ተደራራቢ ጉዳት እንዳይደርስበት ያገኘውን እየበላ እንዲዋጋ ይፍቱት:: ቢያስፈልግ ከጦርነት መልስ ይጾማልቢሏቸው አቡኑአልፈታምብለው እምቢ አሉ:: ምኒልክም በዚህ አዝነውእግዚአብሔር የየዋህ አምላክ ይርዳው፤ አሉ::” ይላል::(ገጽ 172)

ሌላኛው ደራሲ ደግሞ፣ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ዐፄ ምኒልክን፣ ስለ ኢትዮጵያ የሚዋጋው እግዚአብሔር ነው:: ሰልፉ የሰው ሳይኾን የእግዚአብሔር ነው:: ድሉም የኢትዮጵያ ይኾናል፤ ብለው መናገራቸውን ዘግቧል:: አቡኑ ተሳስተው ይኾን? ያነ የኾነውን እስኪ እንመልከት?

የካቲት 22 ቀን ሌሊት የጣልያን ጦር ለውጊያ ከመነሣቱ በፊት ከባድ ድግስ ተዘጋጅቶለት በፌስታ ነበር:: የጣልያን ወታደሮችም የኢትዮጵያን ሠራዊት ለመውጋት ከሳውራ ተነሥተው ገንዳብታ ሲደርሱ ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት ነበር:: ውጊያ ከመግባታቸው በፊት ዕረፍት እንዲያደርጉና በሚገባ እንዲመገቡ ታዘዙ:: በቆርቆሮ የታሸጉ ምግቦችን በልተው የሚበቃቸውን ያህል ውኃ ጠጥተው ዝግጅታቸውን አጠናቀው የኢትዮጵያ ሠራዊት ወዳለበት መሥመር በደፈጣ መግባት ጀመሩ::

የኢትዮጵያ ጦር መኰንኖች ደግሞ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት ላይ ነበሩ:: የጣልያኖች የተኩስ ድምፅም እንደተሰማ ኢትዮጵያውያኑ የጳጳሱ አቡነ ማቴዎስን መስቀል እየተሳለሙ ወደ ውጊያ ገቡ:: እህል አልቀመሱም:: ውኃም አልጠጡም:: በጥድፊያ ወደ ሰልፋቸው አመሩ:: ውጊያው ተጀመረ:: የጣልያን ጦር በሦስት አቅጣጫ ተለጥጦ በመምጣቱ ጦርነቱ ከጠዋቱ ዐሥራ ኹለት ሰዓት ጀምሮ ቀኑን ዋለ::

የኢትዮጵያ ጦር ቀኑን የተዋጋው እህል ውኃ ሳይቀምስ ነበር:: ጦርነትን ምክንያት አድርጎ የገናን ጾም ሳይሽር፣ አሁንም ውጊያውን ምክንያት አድርጎ ሁዳዴን ጾም ሳይሽር እየጾመ ተዋግቶ የኢትዮጵያ ሠራዊት ደል አደረገ:: አቡነ ማቴዎስ አልተሳሳቱም ነበር:: ጳጳስ ይሉሃል እንዲህ ነው:: ሐሞተ ኮስታራ:: የእምነት ሰው::

**********

አቡነ ማቴዎስ የዐድዋን ጦርነት ከሚመሩት ሰዎች አንዱ ነበሩ፤

28378136_2034495193495221_6061582747875982063_n

አቡነ ማቴዎስ በመንፈሳዊው ጉዳይ ብቻ ሳይኾን የኢትዮጵያን ጦር የበላይ ኾነው ከሚመሩትና ከሚያስተባብሩት አዝማች መሪዎች ውስጥ አንዱ ነበሩ:: የጦር ዕቅዱ ላይ ከጦር መሪዎቹ ጋራ አብረው ይመክራሉ:: የጦር ውሎ ግምግማ ላይም ተሳታፊና ዋነኛ ተዋናይና ገምጋሚም ነበሩ:: ለምሳሌ፣ የዓምባላጌን የጣልያን ምሽግ የሰበሩትና ድል ያደረጉት ጀግናው ራስ መኰንን መቐሌ ላይ ያን መድገም ባለመቻላቸው ራስ መኰንን ላይ የሰላ ትችትና ወቀሳ ካቀረቡት መሀል አንዱ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ::

“The Battle of Adwa” የሚለውን ግሩም መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር ሬይመንድ ጆናስ፣ አቡነ ማቴዎስ ከኢትዮጵያ ጦር ዋና መሪዎች አንዱ እንደነበሩና በእያንዳንዱ የውጊያ ውሎ ግምገማ ላይ እንደሚሳተፉ እንዲህ ሲሉ ይጠቅሱታል/Jonas, Raymond; Jonas, Raymond Anthony. Battle of Adwa : African Victory in the Age of Empire, p.139/

“On the ninth, Ras Meconen forces launched a major assault on the fort (Mekeles fort), taking heavy casualities. The loss of life pained Ras Meconnen, but the reaction from Ethiopian leadership was pitliess. Taitu, Menelik, Tekle Haymanot and Abune Matewos turned on Meconnen and accused Ras Meconeen.”

ከዚህ መረዳት የምንችለው “Ethiopian leadership” ብሎ በአራተኛነት ያስቀመጣቸው አቡነ ማቴዎስን ነው:: አቡኑ ከሠራዊቱ ጋራ ኾነው የሚያጽናኑ ብቻ አልነበሩም::የኢትዮጵያ ጦር አመራር አካል ውስጥ አንዱ ነበሩ:: ውጊያ ሲበላሽ ይገሥጹ ነበር:: ራስ መኰንን ከፍተኛ ባለሥልጣን ቢኾኑም አቡኑ ሥልጣናቸውን ፈርተው ዝም አላሉም:: በውጊያ ውሎ ግምገማ(post combat evaluation) ላይ ተገኝተው ወቅሰዋቸዋል::

**********

ዐፄ ምኒልክከባድ ውሳኔ ሲያጸኑ አቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር፤

ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ኢጣልያን ድል ካደረጉ በኋላ ምርኮኞችን በተመለከተ በኢትዮጵያ አመራሮች መካከል ከፍተኛ ክርክር ተደርጎ ነበር:: የመጨረሻውን ውሳኔ ንጉሡ የወሰዱት አቡነ ማቴዎስን አማክረው ነበር:: አሁንም ዝነኛው ፕሮፌሰር ሬይመንድ ጆናስ በዚያው መጽሐፋቸው ገጽ 234 ላይ እንዲህ ይላሉ፡-

“By all accounts, Menelik represented the voice of moderation. As Paul Lairbar put it, ” his natural goodness inclined him toward forgiveness. In the end Menelik took counsel of ABUNE MATEWOS, who sides with Taitu, Alula, Mengesha and the others.”

በጦርነቱ ወቅት በተከናወኑ ሌሎችም በርካታ ውሳኔዎች አቡነ ማቴዎስ ኹነኛ ተሳትፎ ነበራቸው፡፡

እና ምን ለማለት ነው? በቅድመ ጦርነት ዲፕሎማሲያዊ ዘመቻ፣ አንዷ ዲፕሎማት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ዲፕሎማሲው ፈርሶ ጦርነት ሲታወጅ አንዷ ዘማች የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ነበረች:: የቀረ የለም:: ጽላቱ፣ ካህኑ፣ መነኩሴው፣ ጳጳሱ ዘምቷል፡፡ ጦርነቱን በበላይነት ሲመሩ፣ የውጊያ ውሎውን ሲገመግሙና በከፍተኛ ውሳኔዎችም ጠቅላይ አዛዡን ሲያማክሩ ከነበሩ አካላት አንዱ ጳጳሱ አቡነ ማቴዎስ ነበሩ፡፡

**********

ዘማች ሠራዊቱን ያሰፍሩና ቦታ ያስይዙ ከነበሩት ካህናትም ነበሩ፤

የዐድዋ ዘማች ሠራዊት አሰፋፈር ዕቅዱ የወጣውም የተካሔደውም በቤተ ክህነቱ ፕላን ነበር፡፡ ከሰባ ሺሕ በላይ የነበረውን የዐድዋን ጦረኛ ያሰፍሩና ቦታ ያስይዙ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መነኰሳት ነበሩ፤ ይሉናል- በቦታው ተገኝተው የነበሩት የታሪክ ጸሐፍት – ሐበሻውም ፈረንጁም::

በጦርነቱ በቦታው ተገኝተው ያዩትን የጻፉት ጸሐፌ ትእዛዝ ገብረ ሥላሴ – ታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ምኒሊክ” በሚለው መጽሐፋቸው (ገጽ 225) – የጦሩን አሰፋፈር በካርታ ሥለውታል:: እዚህ ላይ የለጠፍኩትም እርሱን ነው:: አረንጓዴ ቀስቶቹንና ቀዩን ክበብ የጨመርኩበት እኔ ነኝ:: ቀይዋን ክበብ ውስጧን በደምብ ይመልከቱት – ታቦት ይላል:: ታቦቱ የሰፈረው ቦታ ላይ ነበር:: በደንብ እንዲታይ ብዬ ነው በቀይ የከበብኩት::

ጸሓፌ ትእዛዝ ያስቀመጡት ካርታ ብዙ ይናገራል:: መጀመርያ ይህ አሰፋፈር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክብ የቤተ ክርስትያን ሥሪት(ዲዛየን) ነው:: ዲዛየኑ ወይም ፕላኑ ሙሉ ለሙሉ ይመሳሰላል:: ቤተ ንጉሥ በመባል የሚታወቀው ክቡ የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አሠራር ነው:: መቅደስ፣ ቅድስት እና ቅኔ ማሕሌት:: በስተምሥራቅ በኩል ታቦት ይቀመጣል:: ቤተ መቅደሱ መሀል ላይ መቅደሱ አለ:: መቅደስ ውስጥ የሚገቡት ሥልጣነ ክህነት ያላቸው አገልጋዮች ብቻ ናቸው:: ኹለተኛው ዙር ቅድስት ላይ ደግሞ ሥጋ ወደሙን ለመቀበል የወሰኑና ወደ እግዚአብሔር የቀረቡ ወገኖች ቦታ ነው:: ቅኔ ማሕሌት የመዘምራን ሊቃውንቱ ቦታ ነው:: ከዐድዋ ዘማች አሰፋፈር አንጻር ካርታውን በጥሞና ይመልከቱት::

28377520_2034958610115546_4157590406379621223_n

የመጀመርያው መሀል ላይ ያለው ክበብ – የንጉሠ ነገሥቱ፣ የንግሥቲቱና የሚራዷቸው የአገልጋዮቻቸውና የጠባቂዎቻቸው ቦታ ነው:: ኹለተኛው ክበብ ደግሞ፣ ዋና ዋና የጦር አበጋዞች ሙሉ ክብ ሠርተው ሰፍረውበታል:: እነዚህ ለንጉሠ ነገሥቱ በጣም የቀረቡ አዋጊ መኰንኖችና ጭፍሮቻቸው ናቸው:: ሦስተኛውና የመጨረሻው ዙር ክበብ ደግሞ የተለያዩ ራሶችን ይዟል:: እዚህ ዙር ላይ ያለው ጦር እጅግ ብዙ ነበር፡፡ ምናልባትም የዘማቹ 60 በመቶ እዚህ ዙር ላይ እንደነበረ ተጽፏል:: የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ደግሞ ጊዜያዊ ማደርያ ድንኳን ተሠርቶለት በስተምሥራቅ በኩል ተተክሏል::

ይህን በሚመለከት ያገር ውስጥ ታሪክ ጸሓፊዎችና እነበርክሌይን የመሰሉ የውጭ የታሪክ ጸሓፍትም ተባብረው የመሰከሩት ነገር ደግሞ እንዲህ ይላል፡-

የዐድዋን ዘማች የአሰፋፈር ንድፍ አውጥተው ወታደሩን ቦታ ሲያሲዙ የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መነኰሳትና ካህናት ነበሩ፤” ይሉናል:: ዲዛየኑ ከነአሰፋፈሩ ራሱ እኮ ይናገራል:: መቅደስ፣ ቅድስት፣ ቅኔ ማሕሌት – ቤተ ንጉሥ ዲዛየን እንደኾነ::

የኢትዮጵያ ሠራዊትም ሲዋጋ የነበረው በዚህ አሰላለፍ ነበር:: ሦስተኛው ዙር ላይ ያለው የራሶች ዙር የመጀመርያውን ጥይት ይተኩሳል ወይም የመጀመርያውን ማጥቃት ያከናውናል:: ይህ ዙር ሲሳሳ ቀጣዩ ዙር ወደ ውጊያው ይገባል:: ከዚያ ደግሞ በወቅቱ የተሻለ ትጥቅና ልምድ የነበረው የንጉሠ ነገሥቱ እና የንግሥቲቱ ጦር እና ፈረሰኞች ይከተላሉ:: የኢትዮጵያ ጦር ብዛት ቢኖረውም በመልክ በመልኩና የተቀመጠውም በዙር ስለነበር ንጉሠ ነገሥቱ ለማዘዝ አላስቸገራቸውም:: ጣልያንም ይሄን ሦስት ዙር ሰብሮ መግባት አልቻለም::

ለጥቁር ሕዝብና በቅኝ አገዛዝ ሥር ለነበሩ ወገኖች ኹሉ የተስፋ ብርሃን የኾነው የዐድዋ ጦርነትና ድል አንዷና በዘመኑ ቋንቋ ወሳኟ መሐንዲስ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን! የነጻነታችን እናት! የኢትዮጵያ ባለውለታ! ተገቢው ክብር ይሰጣት:: ውለታዋ አይዘንጋ! ዕዳ አለብን ጎበዝ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የማን ናት?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከአምስቱ ጥንታዊ የኦርየንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክሪስቲያናት ማለትም ከኮፕት (ግብጽ)፣ ህንድ፣ ሶርያና አርመን ቤተ ክርስቲያናት መካከል አንዷ ናት። ኢትዮጵያ በመጽሐፍ ቅዱስ ከ፵ ጊዜ በላይ የተነሳች ሲሆን ከክርስትና በፊት የብሉይ ኪዳንን እምነትና ባህል ተቀብላ እግዚአብሔርን ታመልክ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል……

Continue Reading

” ወዮልህ ቴዲ አፍሮ፣ ወዮልህ ሃይሌ፣ ወዮልሽ ኤልሳ ቆሎ ” ትንቢተ እህተ ማርያም

ዛሬ ቢጫ ለብሳ ” ትንቢት” ያሰራጨች አንዲት ሴት የቲዎድሮስ ካሳሁንን፣ የሃይሌ ገብረስላሴን፣ የኤልሳ ቆሎን በመጥራት ” ወዮላችሁ ” ስትል ማስጠንቀቋ እያነጋገረ ነው። መልዕከቱን በቪዲዮ የሰራጨው አዲስ ነገር በሚል የዩቲዩብ ሊንክ ሲሆን በበጎና በትችት ሰፊ አስተያተም ተሰንዝሮበታል።

Continue Reading

በወልዲያ የተፈጸመውን ጭፍጨፋ የሃይማኖት አባቶች አወገዙት

በውጭ የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገር ቤት የሚገኘው ቤተክህነት በጉዳዩ ላይ ዝምታን መመረጡ እጅግ እንዳሳዘናት በመግለጽ መግለጫ አውጥታለች።

Continue Reading

የቅዱስ ጳውሎስ የእግር ብረት! (ሊነበብ የሚገባው)

የእሥር ቤቱ ጠባቂ ከእንቅልፉ ሲነቃ በሮቹ ሁሉ ተከፍተው አየ፥እስረኞቹ ያመለጡ ስለመሰለውም ራሱን ለማጥፋት ሰይፉን መዘዘ።በዚህን ጊዜ ቅዱስ ጳው ሎስ ድምፁን ከፍ አድርጐ “በሰውነትህ ልዩ ክፉ አትሥራ፥በገዛ እጅህ ታርደህ አትሙት፥ማንም ያመለጠ እስረኛ የለም፥ሁላችንም ከዚህ ነን፤”አለው።የገረፈውን ያሰቃየውን እና ያሠረውን ወታደር ከሞት አዳነው።“ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉ አትመልሱ፥በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ፤”ብሎ በቃል ያስተማ ረውን በተግባር አሳየ

Continue Reading

Photos: The architectural mastery of Ethiopia’s ancient churches

Ethiopia is legendary for its medieval, rock-hewn churches, the cruciform and colorful frescoes of which have attracted tourists from across the world. The ancient kingdom of Abyssinia, which we now know as modern-day Ethiopia and Eritrea, was probably the site of the first Christian nation, and the churches still serve as religious sanctuaries and draw pilgrims celebrating the Ethiopian Christian calendar.

Continue Reading

ወንጌላዊው ‘መምህር’ ግርማን “ይዋጣልን” ሲል ጋበዛ

“ሃዋሪያ” ሃብታሙ፣ ይዲዲያ “መምህር” ግርማ ወንድሙን በአካል ተገናኝተው እንዲጸልዩ፣ አስፈልጊም ከሆነ እሳቸውን መሰል በሙሉ ተሰባስበው እሱ ብቻውን መጥቶ ትክክለኛው መንፈስ እንዲገለጥና ትውልድ እንዲድን ጥያቄ አቀረበ። ብዙም ጭፈራና ዝላይ የማይወዱ አገልጋይ ከሆኑት መካከል አንዱ ” ጉዳዩ የመንፈስ ጉዳይ ነው፤ በጸሎት ማሸነፍ እንጂ የአደባባይ ፉከራ ዋጋ የለውም፤ መንፈስ የሚሸነፈው በመንፈሳዊ ጦርነት እኒ በአደባባይ ግብግብና በቲፎዞ ፊት በሚደረገ ግጥሚያ አይደልም” ብለዋል።

Continue Reading

የሮማው ጳጳስ፤ አባታችን ሆይ ፀሎት ማሻሻያ ያስፈልገዋል አሉ

ፓትርያርኩ አባ ፍራንሲስ፣ እነዚህ አባባሎች፣ በተሳሳተ አተረጓጎም ሳቢያ የተዛባ መልዕክት ያዘሉ ናቸው ብለዋል። ፈጣሪ ለፈተና ይዳርገናል የሚል የተዛባ መልዕክት የያዙ የተሳሳቱ አተረጓጎሞች እንዲስተካከሉ እፈልጋለሁ ሲሉም ተናግረዋል – ጳጳሱ። “…let us not into temptation” በሚል አባባል መስተካከል እንዳለባቸውም ጳጳሱ ገልፀዋል።

Continue Reading

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ መሠረት ሶስት ካህናት ላይ እገዳ ጣለባቸው

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኑን ሕግና ቀኖና ለማሰከበር ባለበት ኃላፊነት በተለይም የምእመናን መለያየት ክፉኛ ስላሳስበው የወሰደው መንፈሳዊ እርምጃ መሆኑ ታውቆ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ፣ ቄስ አብርሃም ቦጋለ እና ቁስ አለምእሸት አብርሃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አገልግሎታቸው እውቅና የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው ምዕመናን ይህንኑ በመረዳት ማንኛውንም ክህነታዊ አገልግሎት ከነዚህ ግለሰቦች ባለመቀበል ለቀኖና ቤተክርስቲያን ዘብ እንዲቆም ቤተክርስቲያን ጥሪዋን እንደምታቀርብ ውሳኔው ዘግቧል።

Continue Reading

“ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም።” (ቅዱስ ሲኖዶስ)

ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክስ ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
አባ ጴጥሮስ፣ የአውስትራልያ ሀገረ ስብከት ጳጳስና፣ የሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ

“ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም ።” መዝ 33 ፥ 16 ።

በዓለም ላይ ሰዎች የራሳቸውን ሥልጣን ለማስጠበቅና ዘላለማዊ ለማድረግ ብዙ እንደ ጣሩ ከታሪክ እንረዳለን ። እንደነዚህ ያሉ መሪዎች ሥልጣናቸውን ለማቆየት እጅግ የበዛ ግፍ በሕዝባቸው ላይ ይፈጽማሉ ። ይህን ግፋቸውን የሚፈጽምላቸው የታጠቀ ሠራዊት ያዘጋጃሉ ። ሠራዊቱም ተቀጣሪ ስለሚሆን ያገኘውን ይገድላል ፥ ያሰቃያል ፥ ያስራል ፥ ያሳድዳል ። ግፈኞች ይህን ድርጊታቸውን “ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት ነው” በማለት የመልካም መንግሥት ስም ይቀቡታል ።

ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም press releas

Continue Reading

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ሁለት ወገኖችን የማቀራረብ ጥረት

በሃገር ውስጥና በውጭ ያሉትን ሁለቱን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስትያን ሲኖዶሶች ወደ አንድ ለማምጣት አዲስ ጥረት ተጀምሮ እየተካሄደ ነው። በሁለቱም ጎራ ያሉ አባቶችን ለማቀራረብና ወደ አንድነት ለመመለስ የተለያዩ ጥረቶች በተለያዩ ጊዜዎች ተደርገዋል።

የሰላምና የአንድነት ጉባዔ ሁለተኛ ዙር የሚባል የሁለቱም ወገኖች ተጠሪዎች ያሉበት ቡድን እነሆ አሁንም በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ከመላው ዓለም የተጠራሩ የቤተክርስትያኒቱ አባቶች የተካተቱበት ሃያ አራት አባላትና አሥራ ሁለት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ያሉት እንደሆነ መሪዎቹ ተናግረዋል። አበረታች ምላሾችን ከሁለቱም አቅጣጫ እያገኘን ነው ይላሉ በጥረቱ ውስጥ ያሉ አሸማጋዮች

የቡድኑ ሰብሳቢ መላከ-ሕይወት ሃረገወይን ብርሃኑ የኢትዮጵያው ቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑ ቶሮንቶ ካናዳ የሚገኘው የደብረ-ገነት ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስትያን አገልጋይና በውጭው ቅዱስ ሲኖዶስ ሥር ያሉት የዋሺንግተን ዲሲው ደብረ-ኃይል ቅዱስ ገብርዔል ቤተክርስትያን አገልጋይ መምህር ፍሬሰው ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ውይይት ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የቅ/ሲኖዶስ ከጥቅምት 27 ቀን ጀምሮ የኹለት ሱባዔ ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፤ ባለ17 ነጥቦች መግለጫ አወጣ

 

ስለ ወቅታዊ የሀገራችን ኹኔታና ሰላም፡- በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት፣ ከጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ፣ ለኹለት ሱባዔ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግ ተወስኗል፤ ሰሞኑን በተለያየ ምክንያት በወገኖቻችን መካከል የተከሠተው ግጭት ተወግዶ ሙሉ ሰላምን የማስፈኑ ሥርዓት ተፋጥኖ እንዲረጋገጥ ጠይቋል፤ በግጭቶቹ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን፣ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አህጉረ ስብከት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባለው መዋቅር የብር 6 ሚሊዮን ድጋፍ […]

via የቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቀቀ፤ ከጥቅምት 27 ቀን ጀምሮ የኹለት ሱባዔ ጸሎተ ምሕላ ዐወጀ፤ ባለ17 ነጥቦች መግለጫ አወጣ — ሐራ ዘተዋሕዶ

ስለ ወቅታዊ የሀገራችን ኹኔታና ሰላም፡-
 • በመላ ሀገሪቱ ባሉት ገዳማትና አድባራት፣ ከጥቅምት 27 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ፣ ለኹለት ሱባዔ ጸሎተ ምሕላ እንዲደረግተወስኗል፤
 • ሰሞኑን በተለያየ ምክንያት በወገኖቻችን መካከል የተከሠተው ግጭት ተወግዶ ሙሉ ሰላምን የማስፈኑ ሥርዓት ተፋጥኖ እንዲረጋገጥ ጠይቋል፤
 • በግጭቶቹ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖቻችን፣ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አህጉረ ስብከት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ባለው መዋቅር የብር 6 ሚሊዮን ድጋፍ እንዲደረግ ተስማምቷል፤
 • ኅብረተሰቡ፥ በትዕግሥትና በመቻቻል፣ በመከባበርና በመናበብ፣ በመደማመጥና በመግባባት መንፈስ በአንድነት ተባብሮ እንዲሠራ ጥሪውን አስተላልፏል፤
 • ሀገራችን ኢትዮጵያ ለአፍሪቃ አህጉር የነጻነት ምልክት እንደኾነች ኹሉ የሰላምና የጸጥታም ምልክት መኾን አለባት፤
 • በውጭ ሀገር ከሚኖሩ አባቶች ጋር ቀደም ሲል ተጀምሮ የነበረው ዕርቀ ሰላም አኹንም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ውሳኔ አሳልፏል፤

የውግዘት እና እግድ ውሳኔዎች፡-
 • በጋሻው ደሳለኝ የተባለ ግለሰብ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ለበርካታ ዓመታት ለምእመናን ሲያስተላልፍ የነበረው የክሕደት ትምህርት በመረጃ ተሰብስቦ ችግሩ ለቅዱስ ሲኖዶስ ከቀረበ በኋላ፣ ከ15/02/2010 ዓ.ም. ጀምሮ የክሕደት ትምህርቱን በማውገዝ ከቤተ ክርስቲያናችን እንዲለይ ተደርጓል፤ በቤተ ክርስቲያናችንም ስም እንዳያስተምር ተወግዟል፡፡
 • በተመሳሳይ መልኩም፣ በአሜሪካን ሀገር በዋሽንግተን ዲሲ የሚያገለግሉት አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ፣ እያስተማሩት ያለው የክሕደት ትምህርት ለቅዱስ ሲኖዶስ በመረጃ ቀርቦ የተረጋገጠባቸው ስለኾነ፣ ሥልጣነ ክህነታቸው ተይዟል፤ ያሉበትን ቤተ ክርስቲያን ጨምሮ በማናቸውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዳይሰጡ ታግደዋል
 • “ወልደ አብ” በሚል ርእስ፣ ገብረ መድኅን በተባለ ግለሰብ የተጻፈው የክሕደትና የኑፋቄ ትምህርት፣ የቅብዓትንና የጸጋን የክሕደት ትምህርት የሚያስፋፋ በመኾኑ፣ ካህናትን ከካህናት፣ ምእመናንን ከምእመናን የሚያጋጭ ከመኾኑ ጋር፣ ከቤተ ክርስቲያንም አልፎ በሀገራችን ሁከት ለማስነሣት ታስቦ የተዘጋጀ ኾኖ ስለተገኘ፣ መጽሐፉ ከማናቸውም አገልግሎት እንዲለይ ተወግዟል
 • “ተሐድሶ” እየተባለ የሚጠራው የኑፋቄ እምነት ማኅበር፣ ራሱን ኦርቶዶክሳዊ በማስመሰል፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ህልውና እየተፈታተነ ከማስቸገሩ የተነሣ ቅዱስ ሲኖዶስ ቀደም ሲል የፀረ ተሐድሶ ኮሚቴ በየአህጉረ ስብከቱ ተቋቁሞ የመከላከልና ቤተ ክርስቲያኒቱን የመጠበቅ ሥራ እንዲያከናውን ውሳኔ መስጠቱ የሚታወስ ነው፡፡ አኹንም ከማእከላዊ አስተዳደር እስከ አህጉረ ስብከት ባለው መዋቅር የተቋቋመው የፀረ ተሐድሶ ኮሚቴ ተጠናክሮ የመከላከሉን ሥራ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ አመራር ሰጥቷል፡፡
 • የቤተ ክርስቲያናችን እምነትና ሥርዓተ አምልኮ እስከ አኹን ድረስ ተከብሮና ተጠብቆ እንደኖረ ኹሉ አሁንም፣ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አህጉረ ስብከት የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ያለው የመንፈሳዊና የማኅበራዊ አገልግሎት መዋቅር በበለጠ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ መመሪያ ሰጥቷል፡፡
 • የ36ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የጋራ መግለጫ፣ አንዳንድ ማሻሻያ በማድረግ፣ የጋራ መግለጫው፣ የ2010 ዓ.ም. በጀት ዓመት ተግባር ኾኖ ያገለግል ዘንድ ምልአተ ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
 • በቃለ ዐዋዲው የቤተ ክርስቲያናችን መተዳደርያ ደንብ መሠረት፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች የኾኑት ወጣቶች፣ በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው በሰንበት ት/ቤት ተደራጅተው በየሰበካ ጉባኤው አመራር ሰጭነት እንዲማሩምልአተ ጉባኤው አመራርን ሰጥቷል፡፡
 • በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት የሚገኘው የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የካህናት ማሠልጠኛ ተቋም ወደ ኮሌጅ ደረጃ ማደግ ያስችለው ዘንድ ከክፍሉ ሊቀ ጳጳስ የቀረበውን ፕሮፖዛል ጉባኤው ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡
 • በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ማሠልጠኛ አቋቁመው ለሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ማኅበራት የሚያገለግል እስከ አኹን ድረስ የተዘጋጀ የማኅበራት ማደራጃ ደንብ የሌለ በመኾኑ፣ ለወደፊቱ ሕገ ቤተ ክርስቲያኑንና ቃለ ዐዋዲውን መሠረት ያደረገ የማኅበራት ማደራጃ ደንብ በሕግ ባለሞያዎች እንዲዘጋጅ ጉባኤው ተስማምቶ ወስኗል፡፡
 • ለገዳማት መተዳደርያ እንዲኾን የተዘጋጀው ደንብ፣ ረቂቁ ተስተካክሎ የቀረበ በመኾኑ በሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
 • በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ሒሳብና በጀት መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው፣ የ2010 ዓ.ም. በጀት የክፍያው ጣሪያ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ምልአተ ጉባኤው ተስማምቷል፡፡
 • የነገድ፣ የሃይማኖትና የጾታ ልዩነት ሳይኖር፣ ለጋራ ህልውና፣ ለጋራ ዕድገትና ለጋራ ብልጽግና ለሀገራችን ኢትዮጵያ ለጎረቤት አህጉር ብሩህ ተስፋ ሰንቆ እንደሚመጣ የተነገረለት የዓባይ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ኢትዮጵያዊነቱን እያስመሰከረ ስለመጣ አሁንም የፕሮጀክቱ ሥራ ተጠናክሮ ለውጤት እስከሚበቃ ድረስ ኹሎችም ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ድጋፍ በመለገስ እንዲተባበሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡
 • ምልአተ ጉባኤው፣ እስከ ግንቦት ርክበ ካህናት ድረስ ባሉት ቀጣዮቹ 6 ወራት፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ጋራ በመኾን የውሳኔዎቹን አፈጻጸም የሚከታተሉ የሦስት፣ የሦስት ወራት የቋሚ ሲኖዶስ ተለዋጭ አባላትን ሠይሟል፡፡ በዚህም መሠረት፡– ከኅዳር እስከ ጥር፡- ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ ብፁዕ አቡነ ሰላማ፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ እና ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ናቸው፡፡ ከየካቲት እስከ ግንቦት፡- ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እና ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ናቸው፡፡

ዳያስፖራና “Halloween”

(መክብብ ማሞ)

አገራችንን ለቅቀን ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ በባዕድ አገር በርካታ የምንማራቸው፤ የምንለምዳቸው ባህሎች አሉ፡፡ የዚያኑ ያህል መማር የሌለብን ወይም እንዳልተማርን መሆን ያለብንም አሉ፡፡ በተለይ በአሜሪካ ከበርካታዎቹ ሸግዬ ባህሎች መካከል የምስጋና ቀን “Thanksgiving Day” የሚጠቀስ ነው – ወደ ታሪኩና ዝርዝሩ ሳልገባ እንደው በደፈናው ማመስገን መልካም ነው፤ ለዚያም ቢያንስ በዓመት አንዴ ቀን መመደብ ተገቢ ነው በሚለው እሳቤ ብቻ፡፡ ከማማረርና ማጉረምረም አንዳንዴም ባርኮትን ቆጥሮ (ጥቂትም ቢሆን) ማመስገን ሸጋ ነው – ምስጋናው ደግሞ ለፈጣሪ ብቻ ሳይሆን፤ ለወላጅ፣ ለቤተሰብ፣ ለፍቅረኛ፣ ለትዳር ጓደኛ፣ ለልጆች፣ ለወገን፣ ላገር ልጅ፣ … ማብቂያ የለውም፡፡ ታዲያ “ሃሎዊንስ”? የመሰልጠናችን፣ የፈረንጁን ባሕል የመልመዳችን፣ ከኋላ ቀርነት የመላቀቃችን፣ … ምልክት ስለሆነ ይሆን የምናከብረው? እየፈራን ስለምናስፈራ፤ እያስፈራራን ስለምንፈራ …?

ከላይ እንዳልኩት በዚህ የውጪ አገር ብዙ ነገሮችን ከመማራችን የተነሳ ምርቱን ከግርዱ መለየት ያቃተን ይመስላል፡፡ አገር ቤት ሳለን ፈጽሞ የማንነካውን የአሳማ ሥጋ እዚህ መጥተን ከነቆዳው እናስነካዋለን፡፡ እኛ እንኳን ባናደርገውም ልጆቻችን ከአሳማ ሥጋ እስከ አምባዛ፣ ሽሪምፕ፣ … ባገኙት ቦታ – ትምህርት ቤት፣ ምግብቤት፣ … እንዲመገቡ ከመፍቀድ አልፈን ሃይማኖታችን እና የምናነበው መጽሐፍ (በእስልምናም ሆነ በክርስትና) እንደማይፈቅድ እያወቅን “እነርሱ እዚህ ስለተወለዱ ነው፤ ባሕላቸው ነው፤ … ” የሚሉ ሰንካላ ምክንያቶች እየሰጠን ይህ ሥልጣኔ መስሎን የተሸወድን ጥቂቶች አይደለንም፡፡ ሌላው የተሸወድንበት ደግሞ ይኸው ከጥቂት ቀናት በኋላ የኦክቶበር ወር ሲያልቅ የሚከበረው “ሃሎዊን” የተባለውን በዓል በማክበር ነው፡፡ ለመሆኑ ሃሎዊን ምንድነው? እንዴት ተጀመረ? ታሪካዊ አመጣጡስ ምን ይመስላል? ከተለያየ ቦታ የቃረምኩትን ባጭሩ እንዲህ ላቅርበው፡፡ በነገራችን ላይ የሃሎዊን ትክክለኛ አመጣጥና አከባበር ዝርዝር በምሁራን ዘንድ እስካሁን ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት አጨቃጫቂ ጉዳይ መሆኑን ሳልጠቁም አላልፍም፤ አጠቃላይ ስምምነት የተወሰደበት ታሪክ ግን ይህንን ይመስላል፡፡

አሁን አየርላንድን፣ እንግሊዝን እና ሰሜን ፈረንሳይን በሚያካልለው ስፍራ ከመካከለኛው ዘመን በፊት ይኖር የነበረ “ሴልቲክ” የሚባል ህዝብ ነበር፡፡ ሴልቲኮች ወቅቶቻቸውን አሁን እንዳለው ሳይሆን በሁለት ነበር የተከፈሉት – በጋውን “ግማሽ ብርሃን” ክረምቱ ደግሞ “ግማሽ ጨለማ” በማለት፡፡ እነዚህ ሁለቱ ወቅቶች የሚቀያየሩት ደግሞ ኦክቶበር 31 ነበር – በጋው የሚያበቃበትና የቀኑ ብርሃን አጭር በሆነውና በሞት በሚመሰለው የክረምት ወራት የሚተካበት፡፡ በሴልቲኮች እምነት ወራቶቹ ሲቀያየሩና ብርሃን በጨለማ ሲተካ ኦክቶበር 31ቀን የሕያዋን ምድርም ሆነ የሙታን ምድር በብዥታ የተሞላ ይሆናል፤ ሙታንም ነፍሳትን ለመጎብኘት ወደዚህ የህያዋን ምድር ይፈልሳሉ፡፡ እነዚህ የሙት መናፍስት ጉብኝታቸውን ሲያደርጉ ለመደበቅና ላለመታወቅ የሚፈልጉት ሴልቲኮች ጭምብል (ማስክ) በማድረግና ራሳቸውን በመቀየር ለማምለጥ ሙከራ ያደርጋሉ – (trick the ghosts)፡፡ እንዲያውም የሴልቲክ ካህናት ለሕዝቡ የሚሰጡት ምክር ነበር – ነዋሪው ሁሉ በየቤቱ እየሄደ ከሰዉ ሁሉ ጣፋጭ ምግቦችን እንዲሰበስብና ጭራቅ፣ አጋንንት፣ መናፍስት፣ ወዘተ በመምሰል ሊጎዷቸው ለሚመጡት የሙታን መናፍስት ጣፋጩን በመስጠት እንዲያባብሏቸው፡፡ አለበለዚያ መናፍስቱ በሚገባው ካልተስተናገዱ በሰዉ ላይ የማታለል ተግባር (trick) እንደሚፈጽሙ … ምን ያስታውሳችኋል? ባሁኑ ጊዜ ሃሎዊን ሲከበር ለልጆች ከረሜላ ሲሰጥ ምንድነው የሚባለው – (trick or treat) – ነገሮች ከምንም አይጀመሩም፡፡

ሌላው በዚህ የወቅት መለወጫ ጊዜ “የብርሃን ዘመን” መጠናቀቁን ለማወጅና መናፍስቱ ከመጪው የክረምት ወራት ሕዝቡን እንዲታደጉ የችቦ ደመራ ይበራል – ጭለማው የክረምት ጊዜያት የበራ እንዲሆን በመመኘት፡፡ በዚህ ምሽት በርካታ ጥንቆላ፣ ከአጋንንት የመነጋገር ተግባራትም ይፈጸማሉ፡፡ ሰዎች የሞቱባቸውን ዘመዶቻቸውን በመናፍስቱ አማካኝነት ይጠራሉ፤ መጪው የሰብል ዘመን ምን እንደሚሆን ይጠይቃሉ/ያስጠነቁላሉ፤ መስተፋቅር ይጠየቃል፤ ሴቶች መስታወት ፊት ሻማ ይዘው በመቆም የወደፊት የትዳር ጓደኛቸውን በመስታወቱ ውስጥ ብቅ ሲል ለማየት ጭለማ ውስጥ ያፈጥጣሉ፡፡ ሌሎችም እጅግ በርካታ መናፍስትን የመጥራትና ከአጋንንት ጋር የመገናኘት ተግባራት ይከናወናሉ፡፡

“የሰይጣን ዱባ”

በሃሎዊን ጊዜ በዋናነት ጥቅም ላይ የሚውለው ዱባ (እኔ ለዚህ ጽሑፍ ስል “የሰይጣን ዱባ” ያልኩት) ነው፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ሴልቲኮች የሙት መናፍስት እንዳይጎዷቸው ከእነርሱ ለማራቅ ከሚጠቀሙት ብልሃቶች መካከል አንዱ ይህ ነበር፡፡ ዱባውን በቅርጽ በማውጣት ውስጡን በሻማ በማብራት መናፍስቱን ለማስፈራራት ይጠቀሙበታል፡፡ ሌሎች ደግሞ “የኩራዙ ጃክ” (“Jack of the Lantern”) በሚባለው አፈታሪክ መሠረት አንድ ጃክ የተባለ ግለሰብ ለዲያቢሎስ አንዳንድ ቀልዶች በመንገር ሰይጣንን በልጦ ለመገኘት ባደረገው ሙከራ ዲያቢሎስ በመናደዱ ጃክ ዕድሜውን በሙሉ የበራ ኩራዝ ይዞ እንዲዞር በማድረግ ሰዎች ዲያቢሎስን እንዳያታልሉ የማስጠንቀቂያ መማሪያ እንዲሆን ብሎ ያደረገው ነው ይላሉ፡፡

ሃሎዊን ክርስትና ውስጥ እንዴት ሰርጎ ገባ?

በቀደምት ክርስቲያኖች ዘንድ “የሁሉም ቅዱሳን ቀን” ተብሎ በዘመናት ሰማዕት የሆኑ የሚዘከሩበት (ሰማዕታቱ “ዘክሩን” ብለው ባይጠይቁም) ቀን ነበር – የሚከበረው ኖቬምበር 1ቀን ነው፡፡ ከዚህ ቀን በፊት ያለው የዋዜማ ቀን “የቅዱሳን ዋዜማ ቀን” ወይም በእንግሊዝኛው “All Hallows Eve” እየተባለ መጠራት ሲጀምር አንዱ አላስፈላጊ በዓል ሌላ በጣም አላስፈላጊ የሆነ በዓልን እየፈጠረ መጣ፡፡ ይኸው “All Hallows Eve” የተባለው በዓል ስሙ ሰብሰብ፣ አጠር ተደረገና “Hallow-e’en,” ሲባል ቆይቶ በመጨረሻ “Halloween” እነሆኝ አለ!

ክርስትና ወደ ምዕራብ አውሮጳ ግስጋሴ ሲያደርግ በርካታ የአረማውያንን ሃይማኖቶች በመንገዱ ሲጋፈጥ ቆይቷል፡፡ ያገኛቸውንም “እነዚህን የጣዖት አምልኮዎችን አስወግዱ” በማለት ሕዝቡን ወደ አዲስ እምነት ከማምጣት ይልቅ “እናንተንም ሆነ ባዕድ አምልኳችሁንም እናጠምቃለን (ክርስትና እናነሳለን)” በማለት ጣዖት አምልኮ ወደ ቤ/ክ ሰተት ብሎ እንዲገባ በር ተከፈተ፡፡ የሳምንቱ ቀናት ተቀየሩ፣ ሥፍር ቁጥር የሌላቸው የባዕድ አምልኮዎች የክርስትና ስም እየተሰጣቸው ወደቤ/ክ ገቡ፡፡ ገና፣ ፋሲካ፣ … በዚሁ መልክ ነው ወደ ቤ/ክ ሰጥመው በመቅረት ክርስቲያናዊ በዓላት ሆነው የቀሩት፡፡

ከላይ የተጠቀሱት ሴልቲኮች ጣዖት አምላኪ አረማውያን ስለነበሩ የመኸር ወራት ተጠናቅቆ የክረምቱን ወራት ከመጀመራቸው በፊት ዝግጅት ያደርጋሉ፡፡ ሰብላቸውን ይሰበስባሉ፣ ክረምቱን ለማለፍ የሚያቅታቸውን እንስሳት ያርዳሉ፣ … ህይወት ዝግ እያለ ይመጣል፤ ቀኑ ያጥራል፤ ሌሊቱ ይረዝማል፤ የእርሻው መሬት እዳሪ ይሆናል፤ … ይህ ሁሉ በሞት፣ በአፅም፣ በራስ ቅል አፅም፣ በጥቁር ቀለም፣ … እየተመሰለ ከመሄድ አልፎ የዘመኑ ሃሎዊን ሲከበር ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ሆነ፡፡ ከዚሁ በዓል ጋር ተያይዞ የሚደረጉትን ሌሎች አጋንንት የመጎተት፣ መናፍስትን የመጥራት፣ ጥንቆላ፣ ወዘተ ተግባራት በመዘርዘር አላፈላጊ ወደሆነ አጀንዳ ውስጥ ለመግባት አልፈልግም እንጂ ይህንን መሰል እጅግ በርካታ ተግባራት ይፈጸሙ ነበር፡፡

የበዓሉ አመጣጥና ትርጉም ይህ ሆኖ ሳለ እኛ ኢትዮጵያውያን ለመሆኑ ከየትኛው አስተሳሰባችን፣ ባህላችን፣ አኗኗራችን ጋር ተዛምዶ ነው ለዚህ በዓል ይህንን ያህል ክብር በመስጠት የምናከብረው? ወይስ ሥልጣኔ ነው? ምዕራባዊነት? ፈረንጅ ካደረገው ትክክል መሆን አለበት-ነት? በነገራችን ላይ የሰሜን አሜሪካው ገበያ ከዚሁ በዓል 3.3 ቢሊዮን ዶላር ይሰበስባል ተብሎ ይጠበቃል – እኛም ተሳታፊ ነን፡፡

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም “ሥልጣን፤ ባህልና አገዛዝ፤ ፖለቲካና ምርጫ” በሚለው መጽሐፋቸው በርካታ አጥፊ ባህሎች እንዳሉን ይጠቅሳሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በየቦታው በሥልጣን ላይ የሚገኙ ሰዎች (በመንፈሣዊውም ሆነ በፖለቲካው) የሚሠሩትን ጥፋትና በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል እያነሳን እንደምንነጋገርባቸውና እንደምንነቅፍ ይጠቅሳሉ፡፡ በአንጻሩ ግን የራሳችን ጥፋትና በደል እንደማይታየን በዚሁ መጽሐፋቸው ላይ ይናገራሉ፡፡ “በየቤቱ በሚስቶችና ልጆች ላይ የሚደርሰው ጭቆናና ግፍ፤ በየቤቱ ሠራተኞች ያላቸው ሰዎች በሠራተኞቻቸው ላይ የሚፈጽሙት ጭቆናና ግፍ በጥሞና ካየነው ባለሥልጣኖቻችን ከሚያደርሱብን ግፍና ጭቆና ጋር የባህርይ ልዩነት የለውም” ይላሉ፡፡ ይህንን የመሳሰሉ አጥፊ ባህሎች ከእኛ መወገድ እንዳለባቸው በመምከር “በዘመናት ፋይዳቸው የማይለወጥ ለጨዋነትና ለመተማመን መሠረት የሚሆኑትን” ባህሎቻችንን እንድናዳብር ያሳስቡናል፡፡ ለኢትዮጵያውያን “የባህል ምሶሶ” ናቸው የሚሏቸውን አራቱን፡- ክብርና ኩራት፤ ቆራጥነትና ጀግንነት፤ መተዛዘንና መረዳዳት፤ ጨዋነት፣ አደራ አክባሪነትና ሃይማኖተኛነት፤ በመጥቀስ ጠለቅ ያለ ማብራሪያ ይሰጣሉ፡፡ ልናነበው፣ ልንለማመደው፣ ለልጆቻችን ልናወርሰው የሚገባ ምክር ነው፡፡

ስለሆነም መማር ያለብንና የሌለብንን እንወቅ፤ እንደ መልካም ባህል የሙጥኝ ያልናቸውን – ሰው ምን ይለኛል፣ ይሉኝታ፣ አድመኝነትን፣ ዘረኝነትን፣ ጠባብ ወገንተኝነትን፣ … አጉል ባህሎች አውልቀን በመጣል ግልጽነትን፣ የሌላውን መብት (ከማሰብ ጀምሮ እስከ መናገር) ማክበርን፣ ትህትናን፣ ቅንነትን፣ … በየዕለቱ ህይወታችን፣ በንግግራችን፣ በፓልቶክ ውይይታችን፣ በስብሰባችን፣ በቴሌኮንፍራንሶች፣ ወዘተ እንለማመድ፡፡ ሥልጣን ላይ ባሉት የሰላ ሒስ ስንሰነዝር እኛም በሌሎች ላይ ሥልጣናችንን እንዴት እንደምንለማመድ እንጠይቅ፡፡ ዕብጠትን፣ ከኔ በላይ ላሳር-ነትን እናስወግድ – የባህል ለውጥ እናካሂድ፡፡ ጥራዝ ነጠቅ አንሁን፡፡ ከምዕራቡ ዓለም ብዙ የምንማረው ባህል አለ፡፡ ሃሎዊንና የመሳሰሉት ግን ቢቀሩብን የሚቀርብን ምንም ነገር የለም፡፡

mekbma@yahoo.com

ለጽሁፌ ጥንቅር በዋቢነት የሚከተሉትን ድረገጾች ተጠቅሜያለሁ፡-
http://www.gty.org/Resources/Articles/1126
http://amazingdiscoveries.org/the-origins-of-halloween

ለአማርኛ ቋንቋ ተቆርቋሪዋ ኒዤሪያዊት የፊልም ባለሞያ

ፊልሟ ውስጥ አማርኛ ጽሑፍ በማስገባት ለአማርኛ ቋንቋ መቆርቋሯን አሳይታለች ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ፤ አማርኛ የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴን አላቋርጥም ትላለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች።

አውዲዮውን ያዳምጡ  «የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴ አይቋረጥም»

«የአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ ቋንቋ እስኪሆን ጥረቴ አይቋረጥም»

የምዕራብ አፍሪቃዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪየታ አማርኛ ቋንቋ ከአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ የሥራ ቋንቋዎች መካከል አንዱ እንዲሆን ጥረት ማድረግ ከጀመረች ሰነባብታለች። ጥረቷን ለማሳካትም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር መለስ ዜናዊን ጨምሮ በአፍሪቃ ኅብረት የተለያዩ ባለሥልጣናትን አነጋግራለች። አሁን ደግሞ  «የጋብቻ ቀለበቱ» የተሰኘው ረዥም የፍቅር ፊልሟን ርእስ እና የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝር ከፊልሟ መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ በአማርኛ ቋንቋ እንዲጻፍ አድርጋለች። «ይህ ጅማሮ ለጥረቴ መሳካት በግል የማደርገው አንዱ አካል ነው» ያለችው ኒዤሪያዊቷ የፊልም ዳይሬክተር በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ በመሳተፍ ለአማርኛ ቋንቋ መሟገቷን ቀጥላለች።

ምዕራብ አፍሪቃዊቷ ራማቱ ኪየታ የኒዤር ተወላጅ ጸሐፊና የፊልም ዳይሬክተር ናት።  በእንግሊዝኛ „The wedding ring“  የሚል ስያሜ የሰጠችው ፊልሟን በምዕራብ አፍሪቃ ሃገራት በሚነገረው የሐውሳ ቋንቋ «ዝናሪያ» ብላዋለች። ይህን ፊልም ታዲያ ራማቱ ሲኒማ ቤቶች ውስጥ ስታሳይ ርእሱን ወደ አማርኛ «የጋብቻ ቀለበቱ» በሚል ቀይራዋለች።

በፍቅር ታሪክ ላይ ያጠነጠነው የራማቱ ፊልም አንዲት አውሮጳ ውስጥ ዲግሪዋን ያገኘች የፉላኒ ወጣት አፍሪቃ ውስጥ በሳህል የገዢ መደብ ሥር ወደሚገኘው የዚንደር ሱልጣን ትመለሳለች። እዚያም በባሕላዊ መንገድ ለባል ልትሰጥ ስትል በሚኖረው ውጣ ውረድ ላይ ይሽከረከራል ፊልሙ።  በዋናነት ግን መሽኮርመም የዳሰሰው ፍቅር በአፍሪቃ ምን እንደሚመስል ለማሳየት ጥረት ያደርጋል።

ይህ የራማቱ ኪዬታ ፊልም አምስተርዳም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል (World Cinema Amsterdam) ላይ አምስተርዳም ከተማ ውስጥ ከመታየቱ በፊት እዛው ሆላንድ ሮተርዳም የተሰኘው ሌላ ከተማ ውስጥም ለእይታ በቅቶ ነበር።

ፊልምሽን እዚህ ሆላንድ ከተማ ሪያልቶ ሲኒማ ቤት ውስጥ ለእይታ ከቀረቡ ሌሎች ፊልሞች ለየት የሚያደርገው አንድ ነገር ተመልክቻለሁ፤ ያ ምን እንደሆነ ለአድማጮቻችን ብትገልጪላቸው ስል ጠየቅኳት ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያን።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )

ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ በስተቀኝ በኩል ሻሽ ያሰረችው

«ፊልሙ የፍቅር ታሪክ ነው። ምናልባት አንተ ኢትዮጵያዊ ስለሆንክ የምታወራው የፊልሙ ባለሞያዎች ዝርዝር በአማርኛ መጻፉን ነው። ፊልሙ ሲጀምር እና ሲጠናቀቅ የፊልም ባለሞያዎቹ ዝርዝር ሙሉ ለሙሉ በአማርኛ ቀርቧል።»

የራማቱ የፍቅር ፊልም ከመጀመሩ በፊት ለፊልሙ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማት ዝርዝር በአማርኛ እና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ተተርጉሞ ቀርቧል። ራማቱ የአማርኛ ጽሑፉን በደማቅ ብርቱኳንማ ቀለም ጽፋ ከፈረንሳዪኛው በላይ ነው ያሰፈረችው።

ለፊልሙ ድጋፍ ካደረጉ ተቋማትና ሃገራት መካከልም በቅድሚያ «የኒጀር ሪፐብሊክ» የሚለው ከመሀከል ብቅ ይላል። ከዚያም በተከታታይ «የኮንጎ ብራዛቪል ሪፐብሊክ»፤ «የአልጀሪያ ሕዝባዊ  ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ»፤  «የሩዋንዳ ሪፐብሊክ»፤ «የዩጋንዳ ሪፐብሊክ»፤ «የሞሮኮ ንጉሣዊ መንግሥት» እንዲሁም «የፓን አፍሪቃ ባህል ፌስቲቫል አልጀርስ -2009» የሚሉ ጽሑፎች በአማርኛ ይነበባሉ።

«መታሰቢያነቱ ሞያውን ለአወረሰኝ ለእናቴ ወንድም አጎቴ ሳማሪ ኤል-ሀዲ ሐሪንታ ጂቤ ዲያሎ (=1934 -2015)» የሚል የአማርኛ ጽሑፍ ከተነበበ በኋላ ደግሞ ጥንታዊ ህንጻ ውስጥ የተሰባሰቡ ወንዶች ይታያሉ።

ሙዚቃ እና የአካባቢው ድባባዊ ድምጽ ይሰማል። ግቢ ውስጥ መሬት ላይ ተቀምጠው በአንድ ትሪ ላይ በጋራ የሚመገቡ ሴቶች ይታያሉ። ግንባሯ ላይ የተነቀሰችው ቆንጅዬዋ የፊልሙ ዋና ገጸ ባሕሪ ቲያ ግን ተክዛ አቀርቅራለች።

ቲያ በሚቀጥለው ትእይንት ጓደኛዋ ጠጠር ቆጣሪ ዘንድ ይዛት ስትሄድ እሷ እውጭ አቧራማ ሜዳው ላይ ተቀምጠው ገበጣ የሚጫወቱት ልጆች ጋር ታመራለች። ጠጠር ቆጣሪው ጋር የገባችው ጓደኛዋ ተመልሳ በመውጣት ቲያ አብራት እንድትገባ ትጠይቃለች። ቲያ ግን «የእሱ ርዳታ የሚያሻው ለአንቺ እንጂ ለእኔ አይደለም። ደሞ አንቺን እንጂ እኔን ሊረዳ አይችልም» ትላታለች።

ጓደኛዋ በሩን በኃይል ዘግታ ወደ ውስጥ ስትመለስ «የጋብቻ ቀለበቱ» የሚለው የፊልሙ ርእስ በአማርኛ ይነበባል። ከዚያም ዝናሪያ የሚለው የሐውሳ ርእስ እና የእንግሊዝኛው„The wedding ring“  ይከተለዋል።  አሁንም በደማቅ ቡኒ ቀለም የተጻፈው የአማርኛ ጽሑፍ ነው ቀድሞ የሚነበበው።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )

ራማቱ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች ፊልሙ ውስጥ ጎልተው እንዲወጡ ለማድረግ ሞክራለች። ቲያ የምትለብሰው በእደ ጥበብ ባለሞያ በእጅ ስፌት የተሠራው ባህላዊ የሙሽራ ቀሚስን ለማጠናቀቅ ብቻ አንድ ዓመት ያህል ጊዜ መውሰዱንም ገልጣለች።  ከባህላዊ አልባሳቱና ቁሳቁሱ በተጨማሪ ራማቱ ፊልሟ ውስጥ የተለያዩ የአፍሪቃ ቋንቋዎችንም አካታለች።
በአፍሪቃ በእርግጥም «እጅግ በርካታ ቋንቋዎች አሉ» የምትለው ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ በሐውሳ ቋንቋ «ዝናሪያ» የሚል ርእስ የሰጠችው ፊልሟ ሦስት የአፍሪቃ ቋንቋዎች ይነገሩበታል፤ ሐውሳ፣ ሶንጎይ እንዲሁም ፉላኒ። ራማቱ የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝርን በአማርኛ መጻፉን የመረጠችው አማርኛ ቋንቋ በአፍሪቃ«ልዩ ስለሆነ እና እንክብካቤ ስለሚያስፈልገው ነው» ትላለች።

«የፊልም ባለሞያዎች ዝርዝርን በአማርኛ ለመጻፍ የመረጥኩበት ምክንያት፤ አማርኛ እጅግ ጥንታዊ ከሆኑ የዓለማችን የጽሑፍ ቋንቋዎች አንዱ በመሆኑ ነው። በዓለም እንዲህ አይነት ቋንቋዎች ጥቂት ናቸው። ይህ ውብ ፊደላት ያሉት ቋንቋ በኢትዮጵያ እና በጥቂት ሰዎች በኤርትራ ይነገራል። ከመቶ ሚሊዮን አይበልጥም ተናጋሪው፤ ያ ምንም ማለት ነው። ወደ ዐሥር ቢሊዮን እየተጓዘ በሚገኘው የዓለም ቋንቋ ያን ማድረግ እጅግ በጣም ወሳኝ ነው።»

በዓለም ዙሪያ የሚነገሩ እና በመጥፋት ላይ ያሉ ቋንቋዎች መረጃን ያሰባሰበው «ስነ-ሰብ የዓለም ቋንቋዎች» (Ethnologue: Languages of the World) የተሰኘው ድረ-ገጽ ሰባት ሺህ ግድም ቋንቋዎች በዓለማችን እንደሚገኙ ይጠቅሳል።
7.6 ቢሊዮን ግድም ነዋሪዎች ባሏት ዓለማችን የቻይና ማንዳሪን ቋንቋ በ898 ሚሊዮን ተናጋሪዎች በቀዳሚነት ይገኛል። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ ራማቱ ኪዬታ 1.2 ቢሊዮን ተናጋሪዎች ባሏት አፍሪቃ አማርኛ ቋንቋ ተገቢውን ሥፍራ አላገኘም ባይ ናት።

«ትግሌ ውብ ባሕላችን ተጠብቆ ለትውልድ እንዲሸጋገር ማድረግ ነው፤ ባሕላችንን ካልተንከባከብን እየደበዘዘ ለመክሰም ጊዜ አይፈጅበትም» ያለችው ራማቱ፦ በተጓዘችበት ሥፍራ ሁሉ አማርኛ ከአፍሪቃ ኅብረት ይፋዊ መግባቢያዎች አንዱ እንዲሆን መወትወቷን አታቋርጥም።

«አፍሪቃ ውስጥ በኛ በፓን አፍሪቃ ፊልም ሠሪዎች ፌዴሬሽን አባልትም ኾነ በአፍሪቃ ኅብረት መካከል ስብሰባ በሚኖርበት እና ጉዞ በማደርግበት ጊዜ አማርኛን ይፋዊ የመግባቢያ ቋንቋቸው አድርገው እንዲጨምሩ እንደወተወትኩ ነው። ብዙውን ጊዜ ታዲያ ይስቁብኛል።»

ራማቱ ሰዎች ሳቁብኝ ብላ ግን ጥረቷን በእንጭጩ አልቀጨችም። ከታዋቂ ሰዎች እስከ ሀገር መሪዎች ድረስ ባገኘችው አጋጣሚ ውትወታዋን አልተወችም። በአንድ አጋጣሚ እንደውም የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንሥትር መለስ ዜናዊን አዲስ አበባ ውስጥ በዚሁ ጉዳይ አነጋግራ እንደነበር ገልጣለች።

«ራህማቱ ሙሉ በሙሉ ትክክል ነሽ አሉኝ። ግን ሠነዱ  ጽሑፍ ውስጥ የለም አሉኝ።  እናም እኔ ክቡር ጠቅላይ ሚንሥትር ፅሑፉን እኛ ነን የምናበጀው አልኳቸው።»

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )
የፊልም አፍቃሪዋ ፊዮና ፎሪክ በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል

ራህማቱ የጀመረችውን ጥረት ከዳሩ ለማድረስ «ቋልፉ በእጃችን ነው» ትላለች። እናም «እኛው ጀምረን ካላሳየን ሌላው ሊከተለን አይችልም» በማለት እንደ ፕሮፌሰር ኃይሌ ገሪማ እና አቶ ሰለሞን በቀለ ከመሳሰሉ አንጋፋ እና ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የፊልም ሠሪዎች ጋር በመነጋገር ፊልሟ ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን ለመንደርደሪያ ያህል በጽሑፍ አስገብታለች። ወደፊት ተባባሪ ካገኘች ሙሉ ፊልሟን በአማርኛ ቋንቋ አስተርጉማ ኢትዮጵያ ውስጥም የማሳየት ዕቅድ ነድፋለች።
«ይህን ፊልም ሙሉ በሙሉ በአማርኛ አስተርጉሜ ኢትዮጵያ ውስጥ ማሳየት እፈልጋለሁ።» ያን ለማድረግም በኢትዮጵያ የባህል ሚንሥትርን ማነጋገር እፈልጋለሁ ብላለች። ራማቱ ከአማርኛ ቋንቋ ባሻገር ፊልሟን በዓረቢኛ እና ኪስዋሒሊ ቋንቋዎችም ማስተርጎም ትፈልጋለች። ኒዤሪያዊቷ የፊልም ባለሞያ አፍሪቃውያን ቋንቋ እና ባህላቸውን እርስ በእርስ መተዋወቅ እና መለዋወጥ ያስፈልጋቸዋል ስትልም አስረግጣ ትናገራለች።

«አፍሪቃ በጣም ውብ ናት።  እናም ያን ውበቷን ማሳየት አለብን።  ያን እኛ ካላደረግን ማንም አያደርም። ባህላችንን እንዴት እርስ በእርስ ማስተዋወቅ እንዳለብንም ማጤን ያሻል። እኔ ወደ ኢትዮጵያ ስሄድ ሁሉም በአማርኛ ነው የሚያናግሩኝ። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ አይደለሁም። አንዳንድ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የጸጉር አሠራሩ ራሱ ከሀገሬ ጋር ተመሳሳይ ነው።» 

«የጋብቻ ቀለበቱ» በተሰኘው ፊልም ውስጥ ዋናውን ገጸ ባሕሪ የምትጫወተው ተዋናዪት የአዘጋጅዋ ልጅ ናት። የፉላኒ ቋንቋውን ከፊልም ዳይሬክተር እናቷ ነው የተማረችው። ግንባሯ ላይ የተነቀሰችው ምስል እና መልኳን ላየ ኢትዮጵያዊት ናት ብሎ ሊሳሳት ይችላል። ተወልዳ ያደገችው ግን ፈረንሳይ ውስጥ ነው።

«እኛ በምዕራብ አፍሪቃ የምንገኝ ሰዎች እናንተ ስለእኛ ከምታውቁት በተሻለ ስለእናንተ እናውቃለን። ያ ለምን እንደሆነ እንጃ። ግን እኛ ስለእናንተ ታሪክ፤ ለነፃነት ስላደረጋችሁት ተጋድሎ፤ ስለ ንጉሦቻችሁ እና ታሪካችሁ በአጠቃላይ እናውቃለን። እናንተ ግን ስለ እኛ አታውቁም። ለአብነት ያህል ትልልቅ ጥንታዊ ከተሞች እንዳሉን፤ በፊልሜ ውስጥ እንዳየኸው አይነት ቤተ-መንግሥቶች እንዳሉን፤ ስለ ውብ ሥነ-ሕንጻዎቻችንም አታውቁም። ስለዚህ ያን ማሳየት አለብን። ማንነታችንንም ለእራሳችን እና ለዓለም ማሳየት አለብን። ሌላው ዓለም ስለ አንተ እንዲያሳይ አትጠብቅ።  እነሱ ብዙውን ጊዜ እኛን የሚወዱ አይደሉም። አንተ ማን እንደሆንክ እነሱ ብቻ እንዲነግሩህ አታድርግ።»

ሆላንድ ውስጥ በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ ያገኘኋቸው የሲኒማ አፍቃሪዋ ፊዮና ፎሪንክ ላለፉት አምስት ዓመታት በፌስቲቫሉ የቀረቡ ፊልሞች አምልጧቸው አያውቅም። መሰል የፊልም ፌስቲቫሎች ስለ አፍሪቃ እና የአኅጉሪቱ ነዋሪዎች የበለጠ ለማወቅ ይረዳል ይላሉ።

Niederlande Amsterdam - Rahmatou Keita The wedding Ring in World Cinema Amsterdam 2017 (DW/M. Sileshi )
የፊልም አፍቃሪው ኡቱንግ ቡተር በአምስተርዳም ዓለም አቀፍ ፊልም ፌስቲቫል

«አፍሪቃን እንደ አንድ ሀገር መመልከቱ አስቂኝ ነው። አፍሪቃ የ,ራሳቸው ባህልና ማንነት ያላቸው በርካታ ሃገራት የሚገኙባት ግዙፍ አኅጉር ናት። በአንዳንድ ሃገራት እንደውም በርካታ ጎሳዎች ይገኛሉ። አፍሪቃ በርካታ ባህል ቢኖራትም እኛ የምናየው ድህነት እና ረሐብ ብቻ ነው። የምናየው ያን ነው እንጂ በዚህ ፌስቲቫል እንደቀረበው አይነት የበለጸገ ባህሏን አናይም። ስለዚህ ፌስቲባሉ የእያታ አድማሴን አስፍቶታል።»

በአምስተርዳም ከተማ ነዋሪ የሆኑት ኡንቱንግ ቡተር የራማቱ ኪየታን «የጋብቻ ቀለበቱ» ፊልም መመልከታቸው ስለ አፍሪቃ ባህል የበለጠ እንዲያውቁ አድርጓቸዋል።
«የትም ሳትጓዝ የተጓዝክ ያህል ዕድል ይሰጥሃል። የዘንድሮው ፌስቲቫል በተለይ የሌላኛው ዓለም ክፍል ምን እንደሚመስል በበርካታ ሃገራት ውክልና አሳይቷል። ለምሳሌ ትናንት አንድ የኒዠር ፊልም ተመልክቻለሁ። ቀደም ሲል ስለ ሀገሪቱ ምንም የማውቀው ነገር አልነበረም። ንጉሣዊ ሥርዓት እንደነበራቸውም አላውቅም ነበር።  ስለዚህ ፌስቲቫሉ ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ምን እንደሚሠሩ የማወቅ ዕድሉን ይሰጥሀል። የሌላ ሀገር ባህልን ከማስተዋወቅም ባሻገር ይበልጥ ቀርበህ እንድትመለከተው ያደርግሀል። ያ የፊልም ውበት ነው።»

«የጋብቻ ቀለበቱ» የተሰኘው የራህማቱ ኪየታ ሁለተኛ ረዥም ፊልም እንደ ቶሮንቶ ባሉ ተለቅ ያሉ ፌስቲቫሎች ላይም ለእይታ ቀርቧል። ራህማቱ «የጋብቻ ቀለበቱ»ን ከመሥራቷ በፊት ቀደም ሲል አሊሲ የተሰኘ በካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለእይታ የበቃ ዘጋቢ ፊልም ሠርታለች። ራህማቱ በሁለተኛ ፊልሟ ወደ ፊቸር ፊልም ብትዞርም ፊልሙ በአብዛኛው የዘጋቢ ፊልም ላይ በጉልህ የሚስተዋለው እውነታን እንዳለ የማቅረብ ስልት ጠንከር ብሎ ይታይበታል። ኒዠር፤ ቡርኪናፋሶ እና ፈረንሳይ ውስጥ የተሠራው የራህማቱ ፊልም ጀርመን ውስጥ በኮሎኝ እና በሐምቡርግ ከተሞች የታየ ሲሆን በተለያዩ የፊልም ፌስቲቫሎች ለእይታ ይበቃል። እንደ አማርኛ ቋንቋ አምባሳደር በየሀገሩ የምትዘዋወረው ራህማቱም ለአማርኛ ቋንቋ እድገት የጀመረችውን ጥረት መቀጠሏን አታቋርጥም።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አርያም ተክሌ

ቅ/ሲኖዶስ በአንድነት በመሥራት ለምእመናን አቤቱታ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ

“የተሐድሶ ኑፋቄ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ሊመክት ይገባል፤” ብፁዕ አቡነ እንጦንስ

 • የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ጸሎት ተካሔደ፤
 • የተሐድሶ ኑፋቄ፣ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ካልተመከተ፤ ከዮዲት ጉዲት ጥፋትና ከግራኝ ወረራ ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና እንደሚያናጋ ብፁዕነታቸው አሳሰቡ፤
 • የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን፣ በሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደሎች ያስቸገሩት ብፁዕ አባ ማርቆስ እንዲነሡ፥ ግፉዓን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ጠየቁ፤
 • ችግሮቹ መፍትሔ ሳይበጅላቸው ከቀጠሉ፣ ለሀገረ ስብከቱና ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች እንደሚያስከትሉ አሳስበዋል፤
 • “ምክር ዝክር የሌላቸው ግራ አጋቢ” ያሏቸውን ብፁዕ አባ ቶማስን አስጠነቀቁ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስን እየደገፉ በሚከተሉት፣ ወጣቱን ትውልድ ከቤተ ክርስቲያን የሚያርቅ አካሔዳቸው ወቀሷቸው፤
 • ከደብረ ማርቆስ፣ ብቸና እና ደጀን የተውጣጡትና በ7 አውቶቡሶች ተጓጉዘው የደረሱት ከ500 በላይ ካህናትና ምእመናን፣ የአቤቱታ ድምፃቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰምተዋል፤
 • የምልአተ ጉባኤው መክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በተደረገበት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ አቤቱታቸውን ያሰሙ በርካታ ምእመናን፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እና ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መከበር ጥብዓት ላሳዩት፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል፤

†††

 • በማዕከል የተቋቋመው፣ የፀረ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ጉባኤ፣ በአግባቡ ባለመሥራቱ ዳግም እንዲቋቋም፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ጠየቁ፤
 • የማኅበራት ኅብረቱ፣ ለምልአተ ጉባኤው ባቀረበው ባለ13 ነጥቦች አቤቱታ፤ በመዋቅር የተሰገሰጉ የኑፋቄው ቅጥረኞች ታግደው እንዲመረመሩ፤ ተወግዘው የተለዩት ለሕዝቡ በይፋ እንዲታወቁና ለኑፋቄያቸውም በሊቃውንት ጉባኤው ምላሽ እንዲሰጥ፤
 • ውጉዛኑ፥ በቤተ ክርስቲያን አስማተ ማዕርጋት፣ አልባሳት፣ ንዋያተ ቅድሳትና የትምህርት ማስረጃዎች እንዳይጠቀሙ በሕግ እንዲከለከሉ፤ ባለቤትነትና ባለመብትነት የሕግ ጥበቃ እንዲያገኝ፤
 • ታግደውና ተሰናብተው ጉዳያቸው በተያዘው ውሳኔ እንዲሰጥ፤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመምህራን ላይ የተደረገው“ጅምላ እግድ”እንዲስተካከል፤
 • በኑፋቄ ለተደናገሩ ምእመናን፣ በቤተ ክርስቲያናችን የብዙኃን መገናኛዎች ምላሽ እንዲሰጥና የዐውደ ምሕረት ጉባኤያትም እንዲዘጋጁ፤
 • በተለያዩ ቦታዎች፥ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን በማፍረስ፣ ታቦታትንና ንዋያተ ቅድሳትን በየቦታው በመጣል የሚፈጸመው ድፍረት እንዲቆም፤
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚደረጉ ጫናዎች ተወግደው፣ በቤተ ክህነቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ የአየር ሰዓት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፤

“ሕጋዊው” የኢት/ኦ/ቅ/ሲ/ – “ሕዝባችን አሁን ያለበት ሁኔታ በየትኛውም አቅጣጫ ተስፋ ያለው ሁኖ አይታይም”

ከሕጋዊው ኢት/ኦርቶዶስክስ ቅዱስ ሲኖዶስ  የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

«ለሀገርና ለከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።» ኤር 29፡7

ነቢዩ በስደት አገር ለሚኖሩት ስደተኞች እሥራኤላውያን ለሀገር ሰላም ፈልጉ የሀገር ሰላም የሕዝብ ሰላም ነውና ይላል ዛሬም ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ለሕዝባችን ለሀገር ሰላም ጸልዩ የሚል መልእክት ያስተላልፋል

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን! በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ምን እየተከናወነ እንደሆነ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል ሁሉ ይረዳዋል ብለን እናምናለን  አሁን አገዛዙ አቅም አጥቶ ነግሮች ሁሉ እየተበላሹ ናቸው የዚህ ወጤት ደግሞ ህዝባችን ወዴት ሊወሰደው እንደሚችል ከወዲሁ እየታየ ነው   ባለፉት ሳምንታት «በተባብሩ ጉባኤ» ላይ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረብው ሐሳብ የዚህን ስጋት ነበር

እንደ ወቅቱ ሁኔታ አገሪቷ ያልፈረሰቸው ሕዝባችን ፈረሃ እግዚአብሔር ያደረበትና  ጨዋ ሕዝብ ስለሆነ እንጅ መንግስት እንደ መንግሥት  ስለሚያሰተዳድር አይደለም ፤ እርሱ ከቀረ አመታት ተቆጥረዋል።  በዚህ አጋጣሚ ሕዝባቸን በማሳየት ላይ ያለው  ኢትዮጵያዊ  ጨዋነት በቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ ስም  ሳናመሰግን እናልፍም።  መንግሥት ተብየው  እንደሚሰራው ተንኮል ቤሆን ኑሮ  ኢትዮጵያ ሞቃድሾን በሆነች ነበር።  ከጥቂት የፖለቲከኞችን በተለይም የገዢውን ፓርቲ ተንኮል በሚያራምዱ ግለሰቦች አማካይነት  የሚያመጡት መፈናቀል ከልሆነ በቀር  በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ የተለየየ ቋንቋ  የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ፤ ሕዝብ እንደ ሕዝብ አንዱ በአንዱ ላይ ይህን አላደረግም እናም ሕዝባችን ምስጋና ይገባዋል። አንዱ በሌላው ላይ  ሳይነሳ እሰከ አሁን መንግሥት ያሰበው ሳይሳካ ሕዝብ  በሚያደርገው የአስተውሎት ሒደት  አገር እንደ አገር  አለች  ወደፊትም  በጣም አጭር አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች  አይኖሩም  አገርና ሕዝብ ግን ይኖራል።  ውድ ኢትዮጵያውያን! እስከ አሁን የተከተላችሁትን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይዛችሁ በመቻቻል ይህን የመከራ ቀን  እንድታሳልፉት ከአክብሮት ጋር  ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል።

የሚከተለው ጥሪ ለአማራጭ ኃይሎች ይሆናል፦ ውድ ወግኖቻችን! የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካና የታሪክ ምሁራን አገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አጣብቂኝና ሕዝባችን ላይ እያንዣባበ ያለውን አደጋ  ዛሬ አንድ ሆናችሁ  ለሕዝባችሁና ለአገራችሁ ካልሠራችሁ ነገ የዘገየ እርምጃ ነው ፤ ምን አልባትም እድልም ላይኖር ይችላል።  ዛሬ ግን  እግዚአብሔር እድልን ሰጥቷል  ስለሆነም ልዩነታችሁን ወደ ጎን ትታቸሁ አገር በማዳኑ  በወቅቱ ሁኔታ ላይ ትሰለፉ ዘንድ፤እየተራበ በሚገደለው፣ በታሠረው፣ በሚሰደደውና በሚሰቃየው ሕዝባችን ሰም  ጥሪ እንቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ Nov 1st ጀምሮ በኦሃዮ ኮሎምበስ በደብረ መድሐኒት መድኃኔ ዐለም ቤ/ክ በሚካሄደው  የሕጋዊ  ይቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ላይ መንፈሳዊና አገራዊ አጀንዳዎች መካከል በዋነኛነት የሜቀርበው አጀንዳ የሀገራችን የእርቅና የሰላም ጉዳይ ነው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት  መምሪያ

አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ዛሬም እንደ ትናንትናው ታሪካዊ ድርሻዋን ለመወጣት ዝግጁ ናት !

ከሁሉ አስቀድመን ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለመወያየት ይህንን ዝግጅት ያደራጁትንና ቤተ ክርስቲያንን በቅዱስ ሲኖዶስበኩል የጋበዙትን ሰዎች ልናመሰግን እንወድዳለን ። በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለን ስንገኝ

አንደኛ ቤተ ክርስቲያናችን ከእግዚአብሔር የተሰጣትን ሰማያዊ አደራና ሐዋርያዊ ተልእኮ መሠረት በማድረግ ፣

ሁለተኛ ኢትዮጵያ ሀገራችንና በታሪኳ የገጠሟትን ተመሳሳይ ሀገራዊ ፈተናዎችን እንዴት እንዳለፈችና ፣ እንዴትስ እኛ ትውልድ ዘንድ በክብር እንደደረሰች የሚያሳየውን አኩሪና መሳጭ ታሪካዊ የተጋድሎ ጉዞ በመመርመርና በዚያም ውስጥ የነበረውን የቤተ ክርስቲያናችንን ታላቅ አስተዋጽኦ መነሻ በማድረግ ፣

ሦስተኛ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ ሀገሮችና ሕዝቦች ከገጠማቸው ተመሳሳይ ችግሮች እንዴት በድል አድራጊነት እንደ ወጡና ህልውናቸውን አስቀጥለው የተጓዙበትን ልምድ ግብዓት በማድረግ ሲሆን ፣ ዛሬ ሕዝባችን ከደረሰበት ታሪካዊ ውርደትና ፈተና ፣ ሀገራችንን ካንዣበበባት የመተራመስና  የመፍረስ አደጋ ለመታደግ ይረዳ ዘንድ ፥ ከእናንተ ከልጆቿና ከወዳጆቿ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልታበረክት የምትችለውን አስተዋጽኦና የተጋድሎ ድርሻ በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያምንበትን የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ ነው ።

ክፍል አንድ

የት ነን ?

«እግዚአብሔር እንዲህ ይላል  የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ  ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች  የሉምና ስለልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች» (ኤር 31 ፥ 15)

የማኅበረሰብ መሪዎች ራሳቸውን የክፉና የደግ መለኪያ ቱንቢ አድርገው “ስገዱልን!” ሲሉ ፣ ጎልማሶች ራስ ወዳድነትን ሙጥኝ ብለው የእርስ በርስ መበላላት መኖርና ሥቃይ አንድ ሲያደርጋቸው ፣ ወጣቶች በመንፈስ ልዕልና ከመኖር ይልቅ በድንገት የሚገነፍሉ  የንዴት ስሜቶቻቸውን እየተከተሉ መልሕቅ እንደሌለው መርከብ በትርጉም አልባነት ማዕበል ሲንገላቱ ፣ በእግዚአብሔር ሕይወት ለዘለዓለም እንዲያብቡ የተፈጠሩት የሰው ልጆች የተፈጠሩበትን ክብር ዘንግተው ለመሞት ተራ የሚጠብቁ እንስሳት ሁነው መመልከት ሕሊናን ያቆስላል ።

ማኅበረሰብ ሲፈርስ ፣ የሰው ልጅ ክብሩ ሲጣል ፣ እረኞች በጎቹን እየቀለጣጠሙ ያለርኅራኄ ሲበሏቸው ማየት ሕሊናን ይጠዘጥዛል ። አልቃሻው ነቢይ ኤርምያስ ቁስሉ ቢያመው ሞት ልጆቿን እንደ ነጠቃት ራሔል ጉንጮቹ የእንባ መፍሰሻ ቦዮች ሆኑ ። መዝሙሩ ልቅሶ ፣ ጸሎቱም እዬዬ ሆነ ። የእስራኤል ስደተኞችም በመዝሙር መጽሐፋቸው ይህንኑ የእንባ መዝሙር በመዘመር ከኤርምያስ ጋር ተባበሩ ፣ እንዲህ ሲሉ

«በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን  ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን  በአኻያ ዛፎቿ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን  የወሰዱንም ፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን  የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድርእንዴት እንዘምራለን ? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ  ባላስብሽ  ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ  ከደስታዬ ሁሉ በላይኢየሩሳሌምን ባልወድድ» ። መዝ 136 ፥ 5 ።

እግዚአብሔር የሌለበት ዓለም ቢሆን ኑሮ የራሔል እንባ ፈስሶ በቀረ ፣ የመከረኞቹም ሥቃይ ትርጉም ባጣ ነበር ። ነገር ግን ፣ የድኻ አደግ አባት ፣ የተሰበሩት ምርኩዝ ፣ የተሰደዱት መጠለያ ወደብ ፣ የሕይወት ደራሲዋ የሆነው እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ አለ ። ስላለም የራሔል እንባ ፈስሶ አልቀረም ። የኤርምያስ ጉንጮች በሰቀቀን እንባ ተሸርሽረው አልቀሩም ። ምድር ላይ ጠብ ያለው የራሔል እንባ ምድሩን ብቻ አጨቅይቶ አልቀረም ፣ ሰማያትንም አረስርሷል ፤ ከዘለዓለም የታወጀው የእግዚአብሔር ምሕረት ደምቆ ታውጆበታል ።

ፖለቲካዊ ፈቃድ የተሰጣቸው ሌቦች ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ሥርዓተ አምልኮውን ተውኔት ባደረጉበት ፤ የእምነቱን አቡጊዳ የማያውቁ ሥራ አጦች የመምህራንን ካባ አጥልቀው ፣ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ቃል ከመምራት ይልቅ ፥ ኪሳቸውን ለመሙላት ሲሉ ከንቱነትን እየነገሩ ሰዉን የአእምሮ ድኻ በሚያደርጉበት ማኅበረሰብ ውስጥ ሥነ ምግባር ብርቅ ቢሆን ምን ይገርማል?

እነሆ ! ሁሉም በየፊናው የበላይ ለመሆን ይሮጣል ። በዙሪያው ያሉት ሁሉ በእርሱ ዙሪያ ተሰብስበው እስኪሰግዱለት ድረስ ይቸኩላል ። ራሱን የሁሉ ነገር ማዕከል (አምላክ) አድርጎ ለመገኘት የማይቧጥጠው ገደል ፣ የማይፈነቅለው ደንጊያ ፣ የማይቆርጠው ዛፍ የለም ። እየሆነ ያለው ይህ ነው ። እንደ ኤርምያስ ለሰው ልጆች ክብር ፣ ለወገኖቹ ርኅራኄ የተመላ ልብ ያለው ቅን ካለ ፣ ምንም እንኳ አስተሳሰቡ እንደ ዕብድ ቢያስቆጥረውም ያለቅሳል ። ስለ ወገኖቹ ስሕተትና ዕብደታቸው ስለ ወለደው ሥቃይ ያለቅሳል ። የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ፍቅር የልቡን በር ካልከፈተና ወንድሙን እንደ ራሱ ሊራራለት ካልቻለ ፣ የወንድሙን ሥቃይ የራሱ ሥቃይ አድርጎ ማሰብ ካልቻለ ፥ የትኛውም ፖለቲካዊ ዲስኩርና አደረጃጀት ከመበላላት አያድንም ።

አንድ የ20ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓዊ ፈላስፋ ማኅበረሰብንና የሥልጣን ጥምን በተነተነበት ድርሳኑ እንዲህ ይላል፡- “Every man would like to be God, if it were possible. Some few find it difficult to admit the impossibility. These are the men framed after Milton’s Satan, combining like him nobility with impiety.” [1]

ፈላስፋው እንዲህ ዓይነት ሰዎች ክቡርነትን ከክፉነት ጋር ቀላቅለዋልና ሰይጣንን ይመስላሉ ይላል ። ሰይጣንን በሚመስል ኑሮ እየኖርን የእግዚአብሔርን ዕረፍት ከወዴት ልናገኝ እንችላለን ?

ሕዝባችን አሁን ያለበት ሁኔታ በየትኛውም አቅጣጫ ተስፋ ያለው ሁኖ አይታይም ። በሀገሪቱ ያሉ ዐበይት ቤተ እምነቶች በየክፍላቸው አንዳቸውም የተስማሙ አይደሉም ። አንድ ቤተ እምነት ነው ተብሎ የሚጠራ ቡድን አምስት ስድስት ዓይነት ዶክትሪን ያስተምራል ። የእርሱን ዶክትሪናዊ ትንተና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ እርሱን የማይቀበሉትን ለማስጠላት በፍቅር ፈንታ ጥላቻን ይሰብካል ። ይህ ደግሞ ተከታዮቹን በጥላቻ ይመርዛቸዋል ። ከጥላቻ የተረፉትንም ተስፋ መቁረጥ ይጫናቸዋል ። በሥልጣን ላይ ያለው ሴኪዩላሪስት ቡድን እንዲህ ባለው ሃይማኖታዊ ውዥንብር ተጠቃሚ ነው ። የሃይማኖት ተቋማት የተጠናከረ ተቋማዊ አደረጃጀት እንዳይኖራቸው አበክሮ ይሠራል ። መንግሥቱ የቆመው ማኅበረሰቡን ከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲፈራራ በማድረግ ስለ ሆነ ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የአብሮነትና የደኅንነት ስሜት (sense of security) እንዲኖረው የሚያስችል ፣ እርሱ የማይቆጣጠረው ምንም ዓይነት ተቋም እንዲኖር አይፈቅድም ። ቡድኑ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ ነጻነት ማሳጣት የመጀመሪያ ሥራው ያደረገበት ምክንያትም ማኅበረሰቡን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ነበር ።

የሀገራችን ሕዝብ ንቅሐተ ሕሊና በተረዳው መጠን እግዚአብሔርን በመፍራት ላይ የተመሠረተ ስለ ነበር አኗኗሩ ሰብአዊ ርኅራኄ የተመላበት ነበር ። ማኅበረ ሰባዊ ልዩነቶች ተቻችለው የኖሩት ፣ ጎሣዎች ሲፋቀሩ ተጋርተው ፣ ሲጣሉ ዕርቅ አውርደው የኖሩበት ምክንያት ሕይወትን የሰው ልጆችን ሁሉ እኩል አድርጎ ከፈጠረው ከእግዚአብሔር አኳያ የመመልከቻ ነጥብ ስለ ነበራቸው ነው ። የሀገር ሽማግሌዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ ታላቅ ስፍራ ይዘው የኖሩበት ምክንያት በሰከነ መንፈስ ያንን ነጥብ ጠብቀው ጊዜያዊ ስሜቶችንና ግጭቶችን ማርገብ ይችሉ ስለ ነበር ነው ። ዛሬ ያ ሁሉ አለ ለማለት ያስቸግራል ።

ማኅበረሰቡ አሉኝ የሚላቸውን ማኅበረሰባዊ ተቋማቱንና ተቋማቱ ተገንብተውባቸው የነበሩበትን ማኅበረሰባዊ ዕሤቶች (social values) ሙሉ በሙሉ ማለት እንኳ ባንችል በአብዛኛው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ፈርሰዋል ። ዕድርና ዕቁብ ሳይቀሩ በካድሬዎች እይታ ሥር ናቸው ። “Big Brother is watching you!” እንዲሉ ። [2] የኢትዮጵያውያን መከራ ዛሬም አላቆመም ። የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ቡድን በሀገሪቱ ውስጥ ላለው ወጣት ትውልድ ሥራ መፍጠር አቅቶታል ። የወጣቶች ተስፋ ማጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር እንጀራ ፍለጋ በሊብያና በግብፅ በረሀዎች ሞትን እየተጋፈጠ ነው ። ጎሣዊ ቁርሾዎች የሚያስታግሣቸውና የሚያስታርቃቸው ማኅበረሰባዊ ሥርዓት አጥተዋል ። ትናንት በሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓቶች ይፈቱ የነበሩ ግጭቶች ዛሬ የአንድ አካባቢ ሕዝብ ከኖረበት ቀዬ እንዲፈናቀል እስከማድረግ እየደረሱ ነው ። የጎሣ ግጭቶች አሁን ፍጹም መንግሥታዊ መልክ ይዘዋል ። እንደ ድሮው በምሥራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ ያሉ ሱማሌዎችና ኦሮሞዎች ሲጋጩ ግጭቱ በሽማግሌዎች የሚፈታ የጥቂት ወጣቶች ጠብ ሳይኾን የጎሣ ክልሎቹ መንግሥታት የድንበር ግጭት ይሆናል ። በቅርብ ጊዜ የተፈጠረው ከምሥራቅ ኢትዮጵያ የተሰማው ክፉ ዜና በዚህ ዓይነት ሀገሪቱ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር መቀጠሏን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ።

ፖለቲካዊ ሥርዓቱ ወደ ዘመነ መሳፍንት እየተመለሰ ይመስላል ። ልዩነቱ ምናልባት የአሁኑ ዘመን መሳፍንት የታጠቁት መሣሪያ የመግደል ፍጥነቱ በጣም የተሻሻለ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን አይቀርም ። የምድሪቱ ድኾች አሁንም ይራባሉ ፣ አሁንም ይሰደዳሉ ፣ አሁንም በግፍ ይታሠራሉ ፣ አሁንም ይገደላሉ ። የተረፉትም በፍርሃትና በጭንቀት ተወጥረው ይኖራሉ ። ውኃ ፥ መብራት ፥ የመኖሪያ ቤት ፥ የተመጣጠነ ምግብ ለኢትዮጵያውያን ዛሬም ብርቅ ናቸው ። በዜና ማሠራጫዎች ዜና የሚሆነው ኢትዮጵያውያን ውኃ የማጣታቸው ሳይሆን የእንትን ቀበሌ ነዋሪዎች “ንጹሕ የመጠጥ ውኃ” ማግኘታቸው ነው ። ይዘረጋሉ የሚባሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ፥ ዐዋጅ ከተነገረላቸው ከዓመታት በኋላ እንኳ የት እንደደረሱ መጠየቅ አይቻልም ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በሥልጣን ላይ ያለው ሴኪዩላሪስት ቡድን ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን መከራ እየተመለከት ሲያዝን ፣ ግፉ እንዲያቆምም ሲያሳስብ ቆይቷል ። እኛ በስደት የምንገኝ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በምንሰበሰብበት ጊዜ ሁሉ ስለ ወገናችን ያልጸለይንበት ጊዜ የለም ። የኤርምያስ እንባ ዛሬም ይፈስሳል ። ቅዱስነታቸው ከሰው መወያየቱን ትተው በዝምታና በእንባ ከእግዚአብሔር ጋር መወያየቱን መርጠዋል ።

ባለፉት ከሃያ በላይ ለሚቆጠሩ ዓመታት ቅዱስ ሲኖዶስ ከአርባ በላይ የሰላምና የአንድነት ጥሪዎችን አድርጓል ። ጥሪዎቹ በአብዛኛው በመንግሥት ስም ለተቀመጠው ቡድን ብቻ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንቆረቆራለን ለሚሉ ፖለቲካዊ ቡድኖችም ነበር ። እንደ አለመታደል ሁኖ ለዚህ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በጎ አጸፋ የሰጠ ተቋምም ሆነ ግለ ሰብ ታይቶ አይታወቅም ። ይህ ከምን መጣ ? የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ነጻነት ለሀገሪቱ ነጻነትና ማኅበረሰባዊ ዕድገት ያለውን ትእምርታዊና ተግባራዊ (symbolic and practical) አስፈላጊነት ካለመገንዘብ ? ወይስ የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ ታሪክም ሆነ የአስተሳሰብ ሥሪት ለመረዳት የቤተ ክርስቲያን ሚና ምን ያህል ጕልሕ እንደ ሆነ ካለማስተዋል ? በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ግን አሁንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ጥሪውን አያቆምም ።

ብዙ ሰዎች “ይህ ፖለቲካ ነው ። ቤተ ክርስቲያን እዚህ ውስጥ ምን አገባት?” ይላሉ ። እርግጥ ነው ቤተ ክርስቲያን የእኔ የምትለው የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን ሊኖራት አይችልም ። ነገር ግን የትኛውም የፖለቲካ ቡድን የሰው ልጆችን ክብር ሲደፈጥጥ ስታይ ፥ “ስለ ምን ታሳድደኛለህ!” የሚለውን የሰው ልጆችን ስቃይ የራሱ ያደረገውን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን የምታመልክ ቤተ ክርስቲያን ግፍና በደልን እያየች ዝም ልትል አትችልም ። ዝም ካለችማ የተጠራችበትን ለሚገፉት ጠበቃ የመሆን ዓላማዋን አሽቀንጥራ ጥላዋለች ማለት ነው ።

ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነቷን ከኢትዮጵያውያን ነጻነት ለይታ አታየውም ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት የማያከብር ማናቸውም ፖለቲካዊ ሥርዓት ፥ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነቷን ሊያከብርላት አይችልም ።

ክፍል ሁለት

የታሪክ ምስክርነት

የዚህ ጉባኤ አዘጋጆችና ታዳሚዎች ወገኖቻችን !! የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ሀገራዊ ታሪክ ውስጥ በመውደቁም በመነሣቱም ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበረች ። እንዲሁ አሁንም ከፊት መሥመር ላይ ትገኛለች ።

ኢትዮጵያን በመገንባት ፣ በማሳደግ ፣ ድንበሯን በማስከበርና አንድነቷን በማጽናት ወዛቸውን ከደማቸው በመቀላቀል ደማቅ ታሪክ ፣ አኩሪ ሀገርና ፣ ኩሩ ሕዝብ ትተውልን ያለፉ ቀደምቶቻችን በጉዟቸው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና ታቦታቱን ከፊት በማስቀደም እንደ ነበር ታሪክ ያዘክረዋል ። የሀገራችን ታሪክ ሲጠና ከፊት ለፊት የሚታይ የሚጨበጥ የሚዳሰሰ ታሪክ ያለው ወይ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ፤ አልያም በቤተ ክርስቲያን የተሠራ ሁኖ ይገኛል ። ይህ ሊያስተባብሉት የሚችሉት ነገር አይደለም ። የኢትዮጵያን ማንነት ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት መሞከር የአውሮፓን ሥልጣኔ ከአውሮፓ ቤተ ክርስቲያን ወይም የመካከለኛው ምሥራቅን ባህል ከእስልምና ውጪ ለማቅረብ የመሞከር ዓይነት ከንቱ ልፋት ነው ። ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ሕዝብ ማንነት ከተሸመነባቸው ዋና ድሮችና ማጎች አንዷና ዋነኛዋ ናት ። ይህ በጎው ነው ።

በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ብሎም ለማፍረስ ፣ ሉዓላዊነቷን በመድፈር ፣ ሕዝቧን በማሰቃየትና በመግደል ፣ ታሪኳንና ባህሏን በማጥፋት ፣ በአጠቃላይ ሀገራዊ ህልውናዋንና የሕዝቧን አንድነት ፣ ሰላምና ነጻነት አደጋ ላይ የጣሉ ኃይሎች በሙሉ ማለት ይቻላል ተቀዳሚ የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት ይህቺኑ ቤተ ክርስቲያን ነው ።

ይህን ለመረዳት ብዙ የምርምር ሥራ መሥራት አስፈላጊያችን አይደለም ። ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ጥብቅ ውሕደት መቀበል የማይፈልጉ ወገኖች በምርምርና በእኵልነት ስም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያ የሚል ስም እንኳ ሳይቀር ለእነርሱ አጀንዳ እንዲመቻቸው ቀይረው አንዴ ሱዳን ሌላ ጊዜ ኩሽ ሲሉ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ታዝበናል ።

ይህ ሥራ ሲካሄድ በኢትዮጵያ ያለው በመንግሥት የተወከለው አካል አንድም ቃል ሲተነፍስ አልታየም ። በዚያ ፈንታ ሕጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያጥላላ ፥ ስም ሲስጥ ፣ በስደት ያለውን ማኅበረ ሰብ እንኳ እንዳያገለግልና የእነርሱን ጥፋት እንዳያጋልጥ ዘመቻ ሲያቀናብር ሃያ አራት ሰዓት ዕረፍት የለውም ። ሕዝቡም ጠላት የሰጠውን ስድብና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቀብሎ የገዛ ቤተ ክርስቲያኑን የሚያገለግሉትን አባቶቹን እየሰደበ ፣ ማኅበረሰባዊ ራስን የማጥፋት ትንቅንቅ ላይ ይገኛል ።

ቆም ብሎ ማስተዋል ይገባል ! ዐውደ ምሕረት ላይ ሰው በሽጉጥ የተገደለው በማን የፕትርክና ዘመን ነበር ? 1993 ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ተማሪዎችን አሳልፎ እንደ እባብ ለቀጠቀጣቸው የመንግሥት ኃይል የሰጠው ማን ነበር ? 1997 ያ ሁሉ ደም ሲፈስስ ሕዝቡን ጥፋተኛ አድርጎ ወንጅሎ መግለጫ ያወጣው ማን ነበር ? ከዚያም በኋላ በተደጋጋሚ ሕዝብና መንግሥት ሲጋጩ በቤተ ክርስቲያን ስም ሕዝቡን ጥፋተኛ እያደረገ በአደባባይ የወነጀለ ማን ነበር ? እልፍ አእላፍ በግፍ ሲታሠሩና ሲገደሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በቤተ ክርስቲያን ስም ስለ ልማትና ዕድገት የደሰኮረልን ማን ነበር ? ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ !

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎችን ምንነት ስለ መለየት ባስተማረበት ክፍል “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” እንዳለው ሁሉ የማንኛውም ግለ ሰብ ሆነ ስብስብ መታወቂያው ዕለት በዕለት የሚሠራው ሥራ ነው ። የቋንቋ ልዩነትን መሠረት ያደረገው በአንድ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሰለጠነው መንግሥት እንደ ቀደሙት ፀረ-ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰሜኑን የሀገራችን ክፍለ ሀገር ኤርትራን አስገንጥዬ ፣ ትግራይን እገነጥላለሁ ብሎ ሲነሣ ቀጥተኛ ትርጉሙ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ማለት ነው ።

አላማዬን ለማሳካት እንቅፋት ይሆናሉ በሚል በቅድሚያ እንዲጠፉ ከተፈረደባቸውና በግንባር ቀደምትነት የጥቃት ኢላማ ከተደረጉት ሁለት ዋነኛ አካላት መካከል ይህቺው ቤተ ክርስቲያናችን አንዷ ናት። የዚህ ማሳያ ሁኖ የሚቀርበው ለራሱ ሥራ አስፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የመደባቸው ሟቹ አባ ጳውሎስ የሥራ ቀናቸውን የጀመሩት የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ቅርጽ ይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓርማ በመቀየር ነው ።

ይሁን እንጂ ፣ ኢትዮጵያ በቀላሉ የምትፈራርስ ሁና አትታይም ! የሕዝቧን አንድነት ፣ ሰላምና ነጻነት እናስከብራለን ብላችሁ የምትደክሙ ወገኖቻችን ! እንደ ቀደሙት የሀገራችንና የሕዝባችን ባለውለታ አባቶቻችን በመንገዳችሁ ያስቀደማችሁት ፣ በጉባኤዎቻችሁ የምትጋብዙትና ፣ የትግላችሁ አጋር ያደረጋችሁት ይህቺኑ ቤተ ክርስቲያን ነው ። በዚህም ቅዱስ ሲኖዶሱ እጅግ በጣም ደስተኛ ነው ።

ውድ ወገኖቻችን !! ዛሬ በዚህ ቦታ ከእናንተ ጋር በዚህ ጉባኤ በመገኘት ስለምንወዳት ሀገራችንና ስለምንሳሳለት ሕዝባችን አንድነት ፣ ሰላምና ህልውና ስንመክር በቀደሙት ደጋግና እውነተኛ አባቶቻችን እግር ሥር ስለ መተካታችንና የነሱንም ፈለግ ተከትለን እየተጓዝን ስለ መሆናችን ማረጋገጫ ይሰጠናል ። በዚህም አባቶቻችን የሰጡንን የነጻነት ዓርማ ይዘን አሁን ያለብንን ብዙ ዓይነት ችግር በድል እንደምንወጣው ተስፋችን ብሩህ ፥ እምነታችንም ጽኑ ነው ። ይኽ ችግራችን እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ከአለው መለኮታዊ አላማና ከእኛ እነድነት በላይ አይደለም

በአንጻሩ ደግሞ ከእናንተ ጋር በመሆናችን የተደሰትነውን ያህል በዘር ላይ ብቻ ተመሥርቶ በመንግሥት ስም የተቀመጠው  በመንግሥት ስም በተቀመጠውና በግብረ አበሮቹ በመገፋታችንና በመሳደዳችን እንዲሁ እጅግ ደስተኞች ነን ። ምክንያቱም የእኛ ስደት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፍረስ አቅደውና አልመው በተነሡ ፣ የሕዝብን ሰላምና ነጻነት በጠመንጃ ኃይል በቀሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች አሳዳጅነት በመሆኑ ነው ። በዚህም የእውነተኞቹ አባቶቻችን የእነ አቡነ ጴጥሮስና የእነ አቡነ ሚካኤል ልጆች የመሆን ዕድልን አግኝተናል ። በአንጻሩም አሳዳጆቻችን በምግባራቸው የእነማን ልጆች ስለመሆናቸው ነጋሪ አያሻውም ። ለዚህም ታሪክ ሕያው ምስክር ነው ።

ክፍል 3

የቤተክርስቲያን የመፍትሔ ሐሳብ

ይቅርታና ዕርቅ

አማኙ ማኅበረሰብና ሌላውም ዜጋ በጠቅላላው ምን ቢያደርግ አሁን ካለንበት አጣብቂኝ ውስጥ መውጣት ይችላል ? ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቀድሞ መጠየቅ ግድ ነው ።

ሀ/ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ዛሬ ከምትገኝበት ችግር ላይ እንዳትደርስ መደረግ የነበረበት ፣ ነገር ግን ሳይደረግ የቀረ ያልተሞከረ መፍትሔ ምንድን ነው ?

ለ/ የተሞከረውና ያልተሳካውስ ምንድን ነው ?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ከተቻለ ችግሩን ለመፍታት የምንሄድበትን አቅጣጫ በግልጽ እናየዋለን ። ከዚህ በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማቋቋምና ያሉትንም ለማስተባበር ተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገዋል ። በኢትዮጵያ ከመቶ በላይ ፓርቲዎች ተቋቁመው እንደ ነበር መረጃዎች ያሳያሉ ። አሁንም እንኳ የተለየያዩ በቋንቋና በዘር የተቋቋሙ ፓርቲዎች አንድ ልንሆን ነው እያሉ በየጊዜው መግለጫ ይሰጣሉ ። ለየብቻ ያሉትንና በውል የታወቁትን ከቆጠርን ከሃምሳ በላይ ፓርቲዎች አሉ ። ነገር ግን እነዚህ ፓርቲዎች በልዩ ልዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተነሣ ለሕዝቡ ማበርከት የሚገባቸውን አገልግሎት መስጠት ተስኗቸው እዚህ ደርሰናል ። ስለዚህ ዛሬ አዲስ ፓርቲ መመሥረት ለችግራችን መፍትሔ ሊሆን አይችልም ።

ፓርቲዎችን የሚያስተባብር ኮሚቴ ለማቋቋም መሞከርም ከዚህ ቀደም ከታየው ተሞክሮ በመነሣት ዛሬ ላለው ችግር መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም ። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ፓርቲዎችን ለማስተባበር ተሞክሯል ። ሙከራዎቹ ሁሉ ግን ከማስተባበር ይልቅ በማለያየት ፣ ከማቀራረብ ይልቅ በማራራቅ ሲጠናቀቁ ተመልክተናል ። አንዳንድ የአስተባባሪ ኮሚቴዎችም ፓርቲዎችን ይበልጥ ከማራራቅም አልፈው የራሳቸውን ፓርቲ ወደ ማቋቋም ደርሰዋል ።

የፓርቲዎች ውሕደትስ ? በዚህ ውጥረት በተሞላ ጊዜ ውስጥ ለማካኼድ መሞከር በራሱ ችግር ፈጣሪ ሊሆን ይችላል ። ከዚህ በፊት ፓርቲዎች ተባበሩ ተብሎ የተመሠረቱት እንደ ኢድሀቅ ቅንጅት ፥ ኅብረት ፥ መድረክ ፥ ኢሕአዴግ ፥ ወዘተ ችግር ፈቺ ከመሆን ይልቅ የሀገሪቱ ችግር አካል ሁነው ታይተዋል። በመሆኑም ፣ ዛሬ የፓርቲዎች ኅብረት ወይም ውሕደት ለመመሥረት መሞከሩ ለኢትዮጵያ ችግር አፋጣኝ መፍትሔ የማምጣት ዐቅሙ ሚዛን የሚደፋ አይደለም ።

*ፖለቲከኞችን አስተባብሮ አሁን ያለውን ሥርዓት ለውጦ የሽግግር መንግሥት ቢቋቋምስ ? ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪኳ ሦስት የሽግግር መንግሥታትን አይታለች-

= የልዑል አልጋ ወራሽ የሽግግር መንግሥት ፣

= የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥት ፣

= የኢሕአዴግ የሽግግር መንግሥት” ።

እነዚህ ሦስቱም የሽግግር መንግሥት እየተባሉ ቢቋቋሙም ሀገሪቱን ከጭንቅ ወደ እፎይታ ፣ ከጭቆና አገዛዝ ወደ ሕዝባዊ መንግሥት የወሰዱ አልነበሩም ። ይልቁንም ሁሉም የአገዛዝን ቀንበር በሕዝቡ ጫንቃ ላይ በመጫን ዛሬ ካለንበት የጥፋት አፋፍ አድርሰውናል ።

ታዲያ ምን ይሻላል ? ቤተ ክርስቲያን ምን ብታደርግ ከዚህ ሀገራዊ አጣብቂኝ መውጣት እንችላለን ? ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት መንግሥት አፍርሶ መንግሥት በመተካት የመገዳደልና የበቀል መንፈስ ተጠምደን እዚህ ግባ የሚባል የሕዝቡን ሕይወት የሚለውጥ የልማት ሥራ ሳንሠራ ይኸውና አራት ትውልድ አለፈ ። እነሆ አሁን የህልውናችን ጉዳይም ጥያቄ ውስጥ ከገባበት ዘመን ላይ ደረስን ።

በግፍ የሚፈስ የንጹሐን ደም መዘዙ ብዙ እንደ ሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስም ከታሪክም እንማራለን ። ትናንት በግፍ የፈሰሰ ደም ለዛሬ መከራ ከዳረገን ፣ ዛሬ የሚፈስሰው ደም ምን እንደሚያመጣ ለምን ማስተዋል ተሳነን ? የትናንት ፖለቲከኞች እርስ በርስ መበላላት ለዛሬው መከራ ዳርጎናል ። ዛሬ ካለፈው ተምረን እርስ በርሳቸው የማይበላሉ ፖለቲከኞች ማየት ያልቻልነው ለምንድነው ? አንድን ስሕተት ደግመን ደጋግመን እየሠራን ከቅድሙ መጥፎ ውጤት የተለየ ውጤት የምንጠብቀውስ ስለ ምን ይሆን? አልበርት አንስታይን“Insanity is doing something over and over again and expecting something different.” ይላል ።

ክፉውን ያርቅልንና ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሕዝብ ዕልቂት በሦስት መንገዶች ሊፈጠር ይችላል ።

ሀ/ በገዢው አካል በሚቀነባበር ሤራ ምክንያት ።

ገዢው አካል አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ እንደምናስተውለው ሁለት አማራጮች ብቻ ያሉት ይመስላል ።

አንደኛው ሀገር ማስተዳደር እንደ ተሳነው በማመን ለራሱ የመውጫ መንገድ አበጅቶ የአደራ መንግሥት በመመሥረት ገለል ማለት ነው ።

ሁለተኛው ደግሞ ፣ አሁን እየሆነ እንዳለው በአምባ ገነንነቱ ቀጥሎበት የቻለውን ያህል ሕዝቡን ፈጅቶና አፋጅቶ በመጨረሻ ራሱ መጥፋት ነው ። ዛሬ አገዛዙ የያዘው መንገድ በዚህኛው ትልም ላይ ያለ ስለ ሆነ ከዚህ የጥፋት መንገድ ለማምለጥ የሚደረገው ጥረት በይደር የሚተው አይደለም ።

ለ/ ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ባሏቸው የፖለቲካ ቡድኖች ምክንያት ።

በሀገሪቱ ያለው ማዕከላዊ አስተዳደር መዳከም በልዩ ልዩ ቦታ የሚገኙ ቡድኖች ኃይል እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል ። የእነዚህ ቡድኖች መጎልበት በራሱ መጥፎ ባይሆንም ቡድኖቹ ከሀገራዊ ራእይ ይልቅ ጥቃቅን አካባቢያዊ ጥቅሞች ላይ ብቻ በማተኮር ጠላቶቻችን ያሏቸውን ወደ መፍጀት ሊያመሩ ይችላሉ ። ይህ አሁን በዓይናችን የምናየው የሶማሌና የኦሮሞ ግጭት ፣ አንዱን አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ “ሁለት ነህ ! የአንተ ስም ቅማንት ነው !” “የአንተ ደግሞ አማራ ነው !” “አንተ በእርሱ ስትጨቆን ኑረሃል ፤ ለዚህ ጭቆና እኔ መፍትሔ ይዣለሁ ። የያዝኩት መፍትሔ እርስ በርስህ ስትጋደል ብቻ ነው” በማለት መሣሪያ ወድሮ ሳንጃ መዞ ለማጋደል የተጠነሰሰው የጥፋት መጠጥ ውሱን ጥቅመኞች ለመጠጣት ተዘጋጅተዋል ። ይህ ለእነርሱ የሚጠቅም ይምሰላቸው እንጂ መጨረሻው መላው ምሥራቅ አፍሪካን ለውድመትና ለቀውስ ሊዳርግ የሚችል አደጋ ነው ። በሦስተኛው ዓለም ውስጥ ያለች የ100 ሚሊየን ሕዝብ ሀገር ስትፈራርስ የአካባቢው ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ ሕይወት በነበረበት ይቀጥላል ብሎ ማሰብ ትልቅ ጭፍንነት ነው ።

በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፖለቲካ አቀንቃኞች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጥበብና በሀገራዊ ተስፋ ላይ መመሥረት እንዳለበት አበክሮ ማሳሰብ ያስፈልጋል ። ሀገራዊ ተስፋን ችላ በማለት ጊዜያዊ ቀበሌያዊ ሥልጣንና የቢሆን ዓለም ምኞታቸውን (utopia) ብቻ እንከተላለን ቢሉ የሚሠሩት ስሕተት የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ በጣም ከባድ የደም ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል መገንዘብ አለባቸው ። ሕዝቡ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ በመሆን በጎሪጥ እንዳይተያይ ሀገራዊ ተስፋ ላይ የተመሠረተ ከፍተኛ ሕዝብን የማንቃትና ተስፋን የማስጨበጥ ሥራ የመሥራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል ። በዚህ ረገድ እነርሱ ላይ ከፍ ያለና የማያቋርጥ የውትውታና የማሳሰብ ሥራ መሠራት አለበት ።

ሐ/ የተበዳይነት ስሜት ባዘሉ ሰዎች ቂም ምክንያት ።

ሌላው አስፈሪውና የእልቂት ደመና ያንዣበበው በሀገሪቱ ውስጥ ላለፉት 26 ዓመታት በኢሕአዴግ ጎሠኛና ጨቋኝ አገዛዝ የተፈጸመው ተቆጥሮ የማያልቅ ግፍ በብዙ ሰዎች ላይ ያልሻረ ቁስልና የግንባር ጠባሳ ማሳረፉ ነው ። የአገዛዙ ዐቅም ማጣት እነዚህ ግለሰቦች አጠቁን በሚሏቸው ሰዎች ላይ ቂማቸውን የሚወጡበት አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላል ። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ ደግሰውልን የነበረውን የሩዋንዳ እልቂት በሰው አእምሮ አስቀምጠው አልፈዋል ። ዛሬም ቢሆን አሉ ከሚባሉ የመለስ ራእዮች አንዱ ይህ መሆኑን አሁን በዓየናችን እያየነው ነው ። ይህ ግን ማኅበረሰቡን ወደማያልቅ የመገዳደል አዙሪት ከመድፈቅ ውጪ የሚፈውሰው አንድም ማኅበረሰባዊም ሆነ ግለሰባዊ ነቀርሳ እንደሌለ የማሳመን ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅብናል ። በተለይ የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጽኑዕ ታምናለች ።

ሕዝብን ከእልቂት ለማዳን የሚያስፈልጉ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች

ለእንዲህ ያለ ድርጅት የሃይማኖት ተቋማት ትልቅ ተሳታፊ መሆን አለባቸው ። ከዚህም ጋር ፓርቲዎች ሕዝብን በሚያደራጁበት ወቅት ሀገራዊ ተስፋን እንጂ ማኅበረሰባዊ ቂምና ጠባሳ ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የሚያቅብ የሥነ ምግባር ሕግ ማውጣት ፣ የምክርና የማስተባበር ሥራ መሥራት ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የሚቀጥሉት ሥራዎች ደግሞ የሚከተሉት ሲሆኑ መተግበር ያለባቸውም በፖለቲከኞች ፥ በሀገር ሽማግሌዎችና በምሁራን ይሆናል ።

1/ ጊዜያዊ የአደራ መንግሥት ማቋቋም 

2/ ሕገ መንግሥት ማርቀቅ ።

3/ የይቅርታ የእርቅ  ኮሚሽን ማቋቋም

ቤተ ክርስቲያን እነዚህን  መፍትሔዎች መጠቆም እንጂ  እነዚህን ሁሉንም ራሷ   በኃላፊነት ተረክባ መሥራት አትችልም ። የይቅርታና የእርቁን ጉዳይ ግን ፥ ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎችንም ሰላም ወዳድ ወገኖችን ይዛ መሥራት እንዳለባት ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል ።

የሚያፍለጉንና የምናደርጋቸው ጉዳዮ

1/ እውነተኝነትና ግልጽነት፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እውነትም አርነት ያወጣችኋል» ብሏል ። በኅብረተሰባችን ዘንድ አሁን የጠፋው መተማመን የሚለው ቃል ነው ። ቀድሞ ሲባል የምንሰማው “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” ነበር ። አሁን ግን የችግራችን ምንጭ የሆነው ድብቅ አጀንዳ የሚባለው ነገር ነው ። በአንድ ወቅት አንድ ስለ እውነት ፍልስፍና ያጠና ወንድም ስለ ኢትዮጵያውያን አብሮ የመሥራት ጅግር ሲናገር “ለእውነት ቦታ ያለ መስጠት ጅግር ነው” ይል ነበር ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ በዚህ በእጅጉ ተጎድቷል ። አንዱ የፖለቲካ ድርጅት ሌላውን ማመን አይችልም ። በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እንኳ ካለው አለመተማመን የተነሣ ብዙው ነገር ለገዛ አባላት ሳይቀር ምሥጢር ነው ።

አንድ ምሥጢር ያልሆነ ነገር አለ- እርሱም የኢትዮጵያውያን ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ነው ። ይህ ፈላስፋ ይህንኑ ጉዳይ ሲያብራራው ለእውነት ቦታ ስለማንሰጥ በቦታው እውነት ያልሆነ ነገር ይተካበታል ። ያ በእውነት ቦታ የተተካ እውነት ያልሆነ ነገር በግልጽ ሲቀመጥ ውሸት ይሆናል ። እያንዳንዱ ሰው ከዚህ እውነት ካልሆነ ነገር ላይ ልቡን ካሳረፈ በውሸት ላይ ቁሟል ማለት ነው ። ይህ ሰው ራሱ እውነት ስለሌለው ሌሎችን እያምንም ማለት ነው ። እርሱንም ሌሎች ሰዎች ባያምኑት አይደንቀውም ምክንያቱም እርሱም ያው ስለ ሆነ ።

ብዙዎች እንደሚያስቡት ሐሳብ የማመንጨትና መርሐ ግብር የመንደፍ ችግር የለም ። ችግሩ ያለው ሐሳብና ራእይን በአንድ ላይ አድርጎ መሄድ ላይ ነው ። ከዚህ የተሰበሰብን ሁላችን ለሕዝብ ዕድገት ለሀገር ብልጽግና እውነተኛ ግንዛቤ እንዲኖረን ያስፈልጋል ። መቼም ራስን ከማቃጠል የበለጠ ሌላ ሊታይ የሚችል የችግር መግለጫ ቋንቋ የለም ። ለሕዝብ ፍትሕ ቁሙ ። ደግሞም አጽናኑ ። እውነተኛ ሁኑ ። በአመክንዮ ላይ የተመሠረተ ውይይት ተወያዩ ። አንዱ ሲሠራ ሌላው አይቀልድ ። አንዱ ሲሞት ሌላው አይሳቅ ። ግትር አቋም በፖለቲካ የሚሠራ አይደለም ። ባለፉት አርባ ዓመታት ይደረግ የነበረ የሽኩቻና ያለመተማመን ፖለቲካ አካሄድ እስካሁን ድረስ ለፖለቲከኞቹ አልበጀም ። ለሕዝቡም መከራን እንጂ በረከትን አልሰፈረለትም ። ታዲያ ይህ ገና በውጥኑ የከሸፈ አካሄድ ስለ ምን በመተማመን ፣ በመደማመጥ መንገድ አይቀየርም ? የየትኛውም የሠለጠነ ሀገር ፖለቲካ በግትርነት ሲራመድ ታይቷልን ? መደማመጥን ፥ መቻቻልን ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ ወንድሜ ከእኔ ይሻላል እርሱን ማድመጥ ይገባኛል ብሎ ማሰብን እንደ እሾህ የሚፈራ ትውልድ ቢሆንም መነገር ግን አለበት ። በአንድ ጉዳይ ላይ ልዩ ልዩ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሲነሡ አንጃ ተብለው ድምጥማጣቸው ይጠፋል ። ትግሉ  ሥልጣን መያዝን ሳይሆን ሀገራዊ ተስፋን ማዕከል ባደረገ መልኩ የጋራ ወደ ሆነ አስማሚ ነጥብ መጓዝ ግድ ይላል ። ለዚህ ደግሞ የሚጀመረው ከይቅርታና ከእርቅ ላይ ነው ።

2/ የይቅርታና የሰላም ሂደት ማካሄድ

የደቡብ አፍሪካው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱም የማኅበረሰባዊ ይቅርታን አስፈላጊነት ሲያሳስቡ “ያለ ይቅርታ የወደ ፊት መልካም ዕድል የሚባል ነገር የለም” ብለዋል ። “There is no future without forgiveness”

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዚህም ረገድ እንደሌላው ሁሉ እንዋሻለን ። እኔ ከማንም ጋር አልተጣላሁም እንላለን ። ግን ሁላችንም በበቀል መንፈስ የሰጠመ ልብ እንደያዝን አጋጣሚዎች ሁሉ ይመሰክሩብናል ። ለዚህም ዋነኛው ማሳያ ለበጎ ነገር አብረን መሥራት አለመቻላችን ነው ። ብዙዎቻችን ሳናውቀው በልባችን ያጠራቀምነው ቀን ጠብቆ የሚፈነዳ የቂም መግል በቀል አለብን ። ይህ መርዝ በይቅርታ ፈርጦ ካልተፈወሰ ቀን የሚጠብቅ ፈንጂ ነው ። ስለዚህም ይህን ማኅበራዊ ነቀርሳ መንግሎ ለማውጣት ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰባዊ ይቅርታን በኃላፊነት መምራት ይገባታል ብሎ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል ።

ፖለቲከኞች ኅብረት የሚሉት የፖለቲካ ስምምነት ብቻውን ፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም አይሰጥም ። ይህ ዓይነት ስምምነት ፣ ከአሁን ቀደም ተሞክሮ ያልተሳካ ውጤት አምጥቶ ዛሬ ለሚዘንብብን የመከራ ዶፍ ዳርጎናል ።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ፣ ከስደት ተመልሶ ሕጋዊ መስተዳድር ሲያቋቁም ፣ ሦስቱን ቡድን አቀራርቦ በይቅርታና በዕርቅ ፣ ችግሩን በማቃለል ፈንታ በዐዋጅ አንድ ሁኑ በሚል ማስተዋል የጎደለው መንግሥታዊ ትእዛዝ ደም የተቃቡ ዐርበኛና ባንዳን ፣ በጎሪጥ የሚተያዩ ዐርበኛና ስደተኛን ፣ የሚጠላሉ ባንዳንና ስደተኛን በጉልበት አንድ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ።

ይህ ውሳኔ የንጉሡን ሥልጣን ለማቆየት ቢጠቅምም ማኅበረሰቡን ግን አንድ ከማድረግ ይልቅ በቂምና በጥላቻ ልቡ እየሻከረ እንዲሄድ አድርጎታል ። የደም አብዮት ወልዶ ፣ የደም ጦርነት አሳድጎ ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት አናግቶ ፣ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ንዶ ፣ እጅግ ክፉ የአገዛዝ ቀንበሮችን በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ተክሎ ኼደ ። አሁንም መንፈሳዊ የይቅርታና የዕርቅ ሂደት ካልተከናወነና የማኅበረሰቡ መንፈስ በይቅርታ ካልታደሰ ፣ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ብቻውን ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሀገሪቱን ወደሚፈለገው የሰላምና የአንድነት ጉዞ ማድረስ አይችልም ።

በአሁኑ ጊዜ የሚጻፉ መጻሕፍት ፣ የሚያሳዩት ይህን ያለ ይቅርታና ዕርቅ የተደረገ በሰው ልጅነት መተዛዘንንና መደጋገፍን ሳይሆን እከክልኝ ልከክልህ የሚል ጊዜያዊ መጠቃቀምን ብቻ መሠረት ያደረጉ ስምምነቶችን ውጤቶች ነው ። ቀደም ሲል የተቋቋሙትን ኢድሀቅ ከተባለው የፖለቲካ አንድነት አንሥቶ አሁን አገራዊ ንቅናቄ እስከ ተባለው ድረስ ያሉትን ስምምነቶችና እነርሱንም ተንተረስው የሚጻፉትን ከ“ያ ትውልድ እስክ ባለቤት አልባ ከተማ” ድረስ ስንመለከት ፣ ውስጣዊ በቀልና ፉክክር የተሞሉ ናቸው ። በኅብረተ ሰባችን ያለውን የበቀል ጥርቅም በሚያሳዝን ሁኔታ ያስነብቡናል ። ለምሳሌ ያህል እነዚህን፣ ጥቂቶቹን ገለጽን እንጂ ፣ በየትኛውም በማኅበረ ሰባችን ውስጥ በየአቅጣጫው ያለው የበቀል ጥርቅም እንዲህ በቀላሉ ተገልጦ የሚያልቅ አይደለም ፤ ባጤኑት ቁጥር ልብ የሚያስበርግግ ይዘት አለው ።

በዚህ በቀል ውስጥ እንዳሉ ፣ አንድነት መመሥረት ማለት ፈንጅ በተጠመደበት ድልድይ ላይ እያወቀ መኪና እየነዳ በመሄድ ሞትን የመረጠ ሰው መሆን ነው ። ለዚህ መድኃኒቱ ዕርቅ ነው ። ቤተ ክርስቲያን ይህን ዕድል ተጠቅማ በአማራጭ ኃይሎች ወገን በኩል የሚከናወን የዕርቅና የሰላም ሂደት ማድረግ ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን ። ምክንያቱም የቅዱስ ሲኖዶስ የስደቱ መነሻ በሀገሪቱ  የፖለቲካ ነጻነት አለመኖር  የሃይማኖት ነጻነትም እንዳይኖር ስለ አደረገው ነው ። በሌላ አባባል ቤተ ክርስቲያንም የዚሁ የመንግሥት ፖለቲካ ተጠቂ ስለ ሆነች ይመለከታታል ማለት ነው ።

በወያኔ ዘመነ መንግሥት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ይካሄድ የነበረውና አሁንም እየተካሄደ ያለውን የሃይማኖት ተጽዕኖ ስንመለከት ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ግን ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ የሃይማኖት ተጽዕኖ በመካሄድ ላይ ነው ። በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደት ፣ እንደ ግለሰቦች ጉዳይ ተደርጎ ነበር የተወሰደው ። ግን አሁንም የገዳማት መደፈር ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል ፣ እንደ ቀጠለ ነው ። አሁን እኛ ክዚህ እየተወያየን የኢየሩሳሌሙ ገዳማችን  በመፍረስ ላይ ነው አሁን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን የሚክል አካል ስለሌለ ምንም ነገ እንዳልተፈተረ ዝም ብለዋል ምንስ ሊሉ ይችላሉ የሚፈልጉት ከተሳካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን  መዳከም በዚህ ምክንያት ፣ በኢትዮጵያ የሕዝብንና የሃይማኖትን ነጻነት የሚያከብር መንግሥት እስኪቋቋም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ጥረቷን ትቀጥላለች ። ከሥራዋም አንዱ ፣ ይህንን የሰላምና የዕርቅ ጉዞ በመሪነት ማከናወን ነው ።

ዛሬ በራሳችን ላይ ውሳኔ መወሰን ይኖርብናል ። አሁን ከስምምነት ያለፈ አንድነት ያስፈልጋል ። ከመቀናጀት ያለፈ አንድነት ያስፈልጋል ። አሁን ይቅርታን ለሀገራችንና ለሕዝባችን እንደ ሰጠነው ስጦታ አድርገን ልባችንን መክፈት ያስፈልጋል ። አሁን መጀመሪያ ራሳችን ከአምላካችን ይቅርታ መጠየቅና የተዘረጋችውን የይቅርታ እጁን በፍቅር መቀበል ያስፈልጋል ። ያን ባደረግን ጊዜ እኛ የይቅርታ ሰዎች እንሆናለን ። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንብቤ ሐሳቤን ልደምድም

«ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና  እርሱም  ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው  ነገር ግን እርስ በርሳችሁብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ» ። ገላ 5 ፥ 14-15 ።

እርስ በርስ ከመበላላት እርስ በራሳችን እንከባበር ፤ እንነጋገር ፥ ከሽፍታ ትክክለኛ ፍትሕ አንጠብቅም ። እኛ የፍትሕ ሰዎች ብንሆን ግን ፍትሕ ራሱ ከመካከላችን ይገኛል ። ከፍትሕም ሰላም ይመነጫል ። የሮም ሊቀ ጳጳሳት የነበሩት ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ እንዳሉት “ያለ ፍትሕ ሰላም ፣ ያለ ይቅርታ ደግሞ ፍትሕ የለም (There is no peace without justice and there is no justice without forgiveness) 

[1] Russel, Bertrand. 1948. Power: A New Social Analysis.

[2] George Orwell. 1949. 1984.