የማለዳ ወግ…ሳውዲው ቢሊዮኔር ልኡል ወሊድ ዝምታቸውን ሰበሩ ..

* ”ከታሰሩት ውስጥ የመንግስትና የህዝብ ገንዘብ ያባከኑ አሉበት “ * “ይቅርታ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሆነው ረስቸዋለሁ ”

ልኡል ወሊድ ቢን ታላል ይባላሉ ። ሰማቸው ከሃብታቸው ጋር ከሳውዲ አልፎ በመላው አለም የተናኘ የሳውዲ ንጉሳን ቤተሰቦች አባል ናቸው። ባለሃብቱ ልኡል ወሊድ ቢን ታላል የሳውዲ መንግስት አስተዳደር እንደማንኛውም የሃገሪቱ ዜጋ ባለሃብት ከመሳተፍ ውጭ በየትኛውም የመንግስት ኃላፊነት ላይ የሉበትም ።

Continue Reading

Advertisements

ዲና ሙፍቲ – የሞያሌ ተፈናቃዮች ቁጥር ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ጥቅም ሲባል ተጋኗል ይላሉ፤ ከ600 ነብሰ ጡሮች 26 ወልደዋል፤ የስደተኞች ጉዳይ ለቀጠናው ችግር ሆኗል!

በኬንያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዲና ሙፍቲ የሞያሌ ስደተኞች ቁጥር የተጋነነ እና ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ትርፍ እየዋለ ነው ሲል ለፋና ተናገሩ። አምባሳደሩ በስፍራው አልተገኙም፤ ቁጥሩ የተጋነነ ስለመሆኑ መከራከሪያ ዳታና መረጃ አላቀረቡም። አቶ ዲና የዓለም ሚዲያዎችን፣ የኬንያን መንግስት፣ የኬንያን የሰባዊ ድጋፍ ሰጢዎች፣ ቀይ መስቀልና ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸውን በሙሉ ነው ያወገዙት።

Continue Reading

” የሚደበድቡኝ ሰክረው ነበር፤ … ሰውነቴ መግሎ ሕክምና አላገኘሁም ነበር ” የፍርድ ቤት ውሎ

“ከሚደበድቡኝ ሰዎች መሀከል የአሁኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለሰ አለም አንዱ ነበር። በማዕከላዊ ጥቃት ይደርስብኝ የነበረው በብሄሬ ነው፤ ‘ ጉራጌ ሌብነት እንጂ ፖለቲካን የት ያውቃል?’ እየተባልኩ ምራቅ እየተተፋብኝ ነበር ስደበደብ የነበረው።
“ከዚህ በፊትም ማዕከላዊ ተይዘው የገቡ ብዙ ጉራጌዎች ተደብድበዎል፤ ተኮላሽተዎል፤ በዚህ ቤሄር ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት ሊቆም ይገባል። ሰውነቴ ላይ የምታዩት እነዚህ ጠባሳዎች ከእናቴ ማህፀን ስወለድ ያገኘሆቸው ሳይሆኑ፣ በማዕከላዊ በደረሰብኝ ድብደባ ምክንያት ሰውነቴ ላይ የቀሩ ናቸው። ይሄ ሁሉ ድብደባ ደርሶብኝ ሰውነቴም መግሎብኝ ህክምና እንኮን አለገኘሁም ነበር።

Continue Reading

“… አስቀድሜ ከአንድ ወር በፊት እንደምታሰር አውቅ ነበር “

          • ህዝቡ ራሱ በመረጣቸው መሪዎች መተዳደር ይፈልጋል  • ኦህዴድንና ግለሰብ አመራሮችን ለይቶ ማየት ያስፈልጋል

የኦፌኮ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርና በቅርቡ ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ከተለቀቁ ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት አቶ በቀለ ገርባ ስለ እስራቸው ጉዳይ፣ ስለ ሀገሪቱ ወቅታዊ ፖለቲካና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ እንደሚከተለው አነጋግሯቸዋል፡፡

Continue Reading

ዶ/ር አቢይ አህመድ የተቃዋሚዎችና የህወሃት-ወያኔ የጋራ ዕጩ ጠቅላይ ሚኒስትር!

ሐይሉ አባይ ተገኝ – 

ሀ) ህወሃት-ወያኔ በመንግስት ውስጥ ያለ ሌላ መንግስት ነው!

ህወሃት-ወያኔ በመንግስት ውስጥ ያለ ሌላ መንግስት ነው (State within a State/”Deep State” or Imperium Imperio)። ‘በመንግስት ውስጥ ያለ ሌላ መንግስት’ ስንል በመንግስት መዋቅር ውስጥ በሚስጥር የተደራጀና ጭንብል ያጠለቀ መንግስታዊ የውስጥ አካልና ዋና አንቀሳቃሽ (Internal Organ) ሃይል ሲሆን፤

Continue Reading

“በለው እያሉ ሲገድሉ ነበር፤ አስር አስከሬን አይቻለሁ፤ ይህ በስህተት ነው? “

ስሜቷን መቆጣጠር ያቃታት ሴት ትናገራለች። ” በለው” እያሉ ሲገሉ እንደነበር ምስክርነቷን ተሰጣለች። እሷ ባለችው መልኩ አስር ሰዎች ተገለው አይታለች። ” በስህተት” ግድያው መፈጸሙ አስመልክታ ስትናገር እየተጣሩ መግደላቸውን፣ ያልሞተውን ወድቆም እያለ በጥይት በተደጋጋሚ መምታታቸውን በመግለጽ የማይሆን ምክንያት መሆኑንን ተናገራለች። ይህች ሴት ከሞያሌ ተሰዳ የወጣች ናት። ድምጿን ከተያያዘው ፍያል ያድምጡ። ሙሉውን የቢቢሲ ዘገባ የሚከተከው ነው።

Continue Reading

ሃፍረታችን – እኔ ካልመራሁ ኢትዮጵያ ትደፋ!!

” ዋጋ ተከፍሎበታል” የሚል ግራ የሚያጋባ ጉዳይ በተደጋጋሚ ይሰማል። ሕዝብ በቃ ሲል፣ ሕዝብ ሲያምጽ፣ ሕዝብ ሲነሳ ” ዋጋ ተከፍሎበታል” የሚል ተረት ከህወሃት ደጋፊዎችና አፍቃሪዎች ይሰማል? የምን ዋጋ? ሌላው ጥይት ተኩሶ እንደማያውቅ፣ ሌላው ጨካኝ መሆን እንደማይችል፣ ሌላው አልሞ መምታት እንደማይችል፣ ሁሉም ጋር ብሶት ጀግኖችን እንደምይፈጥር፣ ብሶት ትግራይ ብቻ ተወልዶ በሌሎች አካባቢዎች የመከነ እስኪመስል መመጻደቅ… 

Continue Reading

በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ጥቃት ፈጸመ፤ ወታደራዊ ካሚዎንና ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ የጸጥታ ሃላፊው አምነዋል

የኦነግ ተዋጊዎች በምዕራብ ኦሮሚያ ጥቃት ማካሄዳቸው ተሰማ። በጥቃቱም በመከላከያ ሰራዊት አባላትና በተሽካሪዎቻቸው ላይ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል። እንደመረጃዎቹ ከሆነ በዚሁ ማጥቃት በሁለት ኦራል የወታደራዊ ካሚዮን ተሳፍረው በነበሩ የሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል። አንድ ኦራል ማምለጥ ሲችል ሌላኛው ካሚዮን ከጫናቸው የመከላክያ ሠራዊት አባላት ጋር መወደሙ ተጠቁሟል። ጥቃቱን እንደተፈጸመ የአካባቢው አስተዳደር መዋቅር አረጋግጧል።

Continue Reading