አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም

አሁን ኢትዮጵያ ልትጓዝበት እየተጠረገ ያለው መንገድ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ይመስላል። አዲሱ መንገድ ጥላቻን በመስበር የኢትዮጵያን ህዝብ ያለ ልዩነት በፍቅር ተጋምዶ እንዲጓዝበት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው።

Continue Reading

Advertisements

መሬት ጠብ ያላለው ሃሳብ

                                                       ቀደምት አባቶቻችን አንድ ጉዳይ በተገቢው ወቅት፣ በትክከለኛ ሁኔታ ተነግሮ ሲያበቃና ማህበረሰቡም ወዲያውኑ ተቀብሎት በስራ ላይ ሊያውለው ሲንቀሳቀስ አሊያም ሲተገብረው ሃሳቡን “መሬት ጠብ ያላለ ነው” ይሉታል። ይህም ሃሳቡ በማህበረሰቡ ተቀባይነት ያለው ከመሆኑም በላይ፤ ለተግባራዊነቱም በነቂስ ድጋፍ የሚቸረው እንዲሁም መሬት ጠብ ሳይል በአየር ላይ እንደሚያዝ ኳስ ወደ ህብረተሰቡ አዕምሮ በቀጥታ ዘልቆ የሚገባ መሆኑን ያስረዳናል ብዬ አስባለሁ። ሃሳቡ ወደ ሰዎች አዕምሮ በፍጥነት ዘልቆ ከመግባት ባሻገር፤ ሳይውል ሳያድር ፈጣን ግብረ መልስም የሚሰጠው ነው።

Continue Reading

የማይገቡንና ማብራሪያ አልባ ጩኸቶች – ” እንበታተናለን”

“እንበታተናለን” የሚለው ማስፈራሪያ ሰልችቶናል። ” አገር አልባ ትሆናላችሁ” የሚለው ቀረርቶ አታካች ነው። ” እንደ አገር አንቀጥልም” የሚለው ማላዘንም አንገሽግሾናል። ከሁሉም በላይ እንዲህ ያሉት ጩኸቶች ማብራሪያ አልባ፣ መሰረት የሌላቸው ሲሆኑብን ያጥወለውለናል። ዛሬ ዛሬ ብታምኑም ባታምኑም እንዲህ ያለው ግልብ አስተሳሰብ የሚገለማ ሆኗል።

Continue Reading

ሳበር – የቀዝቃዛ ጦርነት ግንባር

ጀርመኖች የዌመር ሪፐብሊክ የውድቀት ታሪክ ምን እንደነበረ አሳምረው ያውቃሉ፡፡ ከዚያ ውድቀት ወዲህ፤ ‹‹ሰርድሪኽ›› የጎተተባቸውን መከራ ፍፁም አልዘነጉትም፡፡ ሐገራቸው ለሁለት መከፈሏ ቢቆጫቸውም ከዚያ መዐት ተርፈው፤ ምዕራብ ጀርመኖቹ ‹‹ዜሮ ሰዓት›› ብለው ከሚጠሩት ከ1945 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) ጀምሮ፤ ጉዟቸውን እንደ አዲስ ቀጠሉ፡፡ የዌመር ሪፐብሊክ የፈፀማቸውን ስህተቶች ላለመድገም በብርቱ እየተጠነቀቁ አዲስ ሐገር እና ህብረተሰብ ለመፍጠር ጉዞ ጀመሩ፡፡

Continue Reading

የኢትዮ – ሱዳን አዋሳኝ ድንበር ጉዳይ እና የህወሓት መጨረሻ

ለረዥም ዓመታት በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የዘለቀው ግንኙነት ወጥ የሆነ መልክ ያለው አልነበረም። የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን ከመጽናቱ ቀደም ብሎ በነበሩ ጊዜያት የኢትዮጵያ ነገሥታትና የጦር አበጋዞች በኢትዮ – ሱዳን ጠረፍ አካባቢ ከግብጽ ተስፋፊ ኃይልና ከሱዳን የንቅናቄ (መሃዲስት) ኃይል ጋር ተደጋጋሚ ጦርነት ተፈጥሮ ያውቃል።

Continue Reading

ኢህአዴግ ወዴት አለ?

ኢህአዴግ በ1983 ዓ/ም ሰኔ የተመሰረተውን የሽግግር መንግስት፤ በኋላም በኢፌዴሪ መንግስት በገዢ ፓርቲነት ሃገሪቱን ሲመራ መቆየቱ ይታወቃል። በድምሩ ከሃያ ሰባት ዓመታት በላይ ሃገሪቱን መርቷል። ኢህአዴግ እንደ ግንባር የፌደራል መንግስቱን ሲመራ ግንባሩን የመሰረቱት አራት እህትማማች ብሄራዊ ድርጅቶች – ህወሃት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድና ደኢህዴን ደግሞ የትግራይን፤ የአማራን፤ የኦሮሚያንና የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልላዊ መንግስታትን ሲመሩ ቆይተዋል። የተቀሩትን ክልሎች – አፋር፣ የኢትዮጵያ ሱማሌ፣ ሃራሪ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝና የጋምቤላ ህዝቦች ክልሎች ደግሞ የኢህአዴግ አባል ባልሆኑ ሆኖም ከኢህአዴግ ጋር የዓላማ አንድነት ባላቸውና በአጋርነት በተሰለፉ ብሄራዊ ድርጅቶች ሲመሩ ቆይተዋል።

የአንድ ትውልድ እድሜ ያህል ማለትም ለሶስት አስርት ዓመታት ያህል ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ገዢ ፓርቲ ሆነው መቆየታቸው ያላስደሰታቸው ወገኖች አሉ። በመሰረቱ አንድ ፓርቲ ወደስልጣን የመጣበት መንገድ ዴሞክራሲ የህዝብ ውክልና የተረጋገጠበት ከሆነ ለሁለትና ለሶስት ትውልድም ገዢ ፓርቲ ሆኖ መቆየቱ በራሱ እንደችግር ሊነሳ አይችልም። በዴሞክራሲያዊ ስርአት የስልጣን ውክልና የሚገኝበት ብቸኛው መንገድ በምርጫ የሚገኝ የስልጣን ውክልና ብቻ በመሆኑ፣ በዚህ ሂደት ወደስልጣን የሚወጣ ፓርቲ ለበርካታ ዓመታት ገዢ መሆኑን መቀበል የግድ ነው። በዴሞክራሲያዊ ስርአት ስልጣን በምርጫ የሚገኝ እንጂ በተራ የሚዘዋወር ባለመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም። አንድ ፓርቲ ስልጣን ላይ የሚቆየው ዴሞክራሲን በሚያፋልስ መንገድ ከሆነ ግን ተቀባይነት አይኖረውም። እናም የኢህአዴግ ለአንድ ትውልድ ዘመን ያህል ስልጣን ላይ የመቆየት ጉዳይ ከላይ ከተገለጸው የዴሞክራሲ አካሄድ አኳያ ብቻ የሚታይ ነው የሚሆነው።

በተደጋጋሚ ሲነገር እንደቆየው የተቃውሞው ቀዳሚ መነሻ ምክንያቶች የተከማቹና ህዝብን ያንገሸገሹ የመልካም አስተዳደርና የፍትህ መጓደል፣ ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል መዛባትና ከተሞችን ያጥለቀለቀ የስራ አጥነት ችግሮች ናቸው። በቀላል አብላጫ የምርጫ ስርአት ኢህአዴግና አጋር ድርጅቶቹ ከጊዜ ወደጊዜ የፌደራልና የክልል መንግስታትን ስልጣን ሙሉ በሙሉ እየተቆጣጠሩ ሄደው፣ ሌሎች የተቃውሞ ድምጾች የሚሰሙበት እድል የተዘጋበት ደረጃ ላይ መድረሱም ተቃውሞውን ከዚያ ቀደም ከነበረው እንዲባባስ በማድረግ ረገድ ጉልህ ድርሻ እንዳላለው ይታመናል።ይሁን እንጂ ኢህአዴግ ስልጣን ላይ የቆየው በዴሞክራሲያዊ መንገድ (ፍጹም ጥሩ ፓርቲ ሆኖ ሳይሆን ከነችግሮቹ ከተፎካካሪዎቹ የተሻለ ሆኖ) የህዝብ ውክልና አግኝቶ ነው ብለን ብንወስድም ከተቃውሞ አለማምለጡ ግን ገሃድ እውነት ነው። በተለይ በአምስተኛው ዙር ምርጫ አሸንፎ ስልጣን በተረከበ በጥቂት ወራት ውስጥ ቀደም ሲል ከነበረው የመረረና የከረረ ህዝባዊ ተቃውሞ አስተናግዷል።

ይህን ሁኔታ አንዳንድ ወገኖች ኢህአዴግ ሃገር ማስተዳደር የሚያስችል መተማመኛ ድምጽ እንዳጣ አድርገው ወስደውታል። ይሁን እንጂ ሃይል የተቀላቀለባቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎችን ብቻ በመመልከት የመተማመኛ ድምጽ ማጣት አመላካች አድርጎ መወሰድ አይቻልም። የአደባባይ ተቃውሞዎች በተለይ ሃይል የተቀላቀለባቸው የአደባባይ ተቃውሞዎች ከዚህ ውጭ ከሆኑ ከፍተኛ ቁጥር ካላቸው ዝምተኛ ደጋፊዎች ድምጽ እጅግ በበለጠ ጎልቶ የመሰማት ጉልበት ስላለው የአደባባይ ተቃውሞን የመተማመኛ ድምጽ ማጣት አመላካች አድርጎ መወሰድ ትክክል አይመስለኝም።

ያም ሆነ ይህ፤ ኢህአዴግ በተለይ በኦሮሚያ በሰፊው፣ በአማራና በደቡብ አንዳንድ አካባቢዎች ያልተቋረጠ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል። ይህ ተቃውሞ ኢህአዴግ ውስጡን በጥልቀት ፈትሾ ዳግም የመፈጠር ያህል ራሱን እንዲያድስ አስገደዶታል። ይህን ያለማደረግ አማራጭ አልነበረውም። ይህ የመታደስ እንቅስቃሴ በመጀመሪያ በኦህዴድ ውስጥ፣ በመቀጠል በሌሎች አጋር ድርጅቶች ውስጥ የአመራር ለውጥ እንዲካሄድ አድርጓል። በመንግስት መዋቅርም ውስጥ ከፌደራልና ከክልል የካቢኔ አባላት ጀምሮ እስከ ወረዳና ቀበሌ መዋቅር የአመራር ለውጥና ተያያዥ እርምጃዎች እንዲወሰድ አድርጓል። የዚህ የአመራር ለውጥ ዓላማ ህዝቡን ያስቀየመውንና የስቆጣውን ችግር ማቃለል ያልቻሉ የድርጅቱንና የመንግስት አመራሮችን አንጓሎ በማስወገድ መፍትሄ አማጭ አመራር ማስቀመጥ ነበር። ይህ የአመራር ለውጥ በመጨረሻም የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የመፍትሄው አካል ለመሆን በሚል በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን እንዲለቁ እስከማድረግ ዘልቋል። ይህም አዲስ የተሃድሶው ውጤት የሆነ አመራር ወደኢህአዴግ ሊቀመነበርነትና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርነት ሃላፊነት እንዲመጣ አድርጓል። የአሁኑ የኢህአዴግ ሊቀመነበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ወደስልጣን የመጡት በዚህ ሂደት ነው።

ይህ በኢህአዴግ ውስጥ የታየው የአመራር ለውጥና የአቋም ማስተካከያ በድርጅቱ ውስጥ ባለ ተቃርኖ የመጣ ተፈጥሯዊ የእድገት ሂደት ውጤት ተደርጎም ሊወሰድ ይችላል። ኢህአዴግ እንደ ድርጅት በማንኛውም አካል (entity) ውስጥ የሚኖረው የነባርና አዲስ የሚወለድ አመለካካት ተቃርኖ (contradiction) ትግል ይካሄድበታል። ይህም ድርጅቱን በመሰረቱና እስካሁን በዘለቁና፣ አዲስ በተፈጠሩ ወጣት የድርጅቱ አባላትና አመራሮች መሃከል ባለ የአመለካከት ልዩነት ተቃርኖ የሚገለጽ ነው። ይህ ተቃርኖ እንደችግር የሚታይ አይደልም። በማንኛው አካል ውስጥ የማያቋርጥ እድገት እንዲኖር የሚያደርግ ነባራዊ ሁኔታ ነው። ጤናማም ነው። በውስጡ ተቃርኖ የሌለው አካል የለም። ካለም ሙት ነው፤ ከጊዜ ጋር ሳይለወጥ በተወዘተበት ቦታ የሚኖር ሙት። እናም ኢህአዴግ ሙት ስላልሆነ ይህ የተቃርኖዎች ፍትጊያ የለውጥ ሂደት ሲካሄድበት ቆይቷል።

በዚህ የተቃርኖዎች ፍትጊያ የለውጥ ሂደት ነባሩ በቀላሉ እጅ ይሰጣል ተብሎ አይጠበቅም፣ መጪውም የሚኖርበትን አካል ሳይለውጥ አንቀላፍቶ ለዘለቄታው መኖር አይችልም። ቅራኔዎች የሚስተናገዱበት ስርአት ባለበት አካልና ማህበረሰብ ውስጥ የለውጥ ሂደቱ ሳሰይስተዋል በአዝጋሚነት ይቀጥላል። ቅራኔዎች እነደተፈጥሯዊ ባህሪ በማይወሰዱበትና የሚስተናገዱበት ስርአት በሌለበት አካል/ማህበረሰብ ውስጥ ግን ይካረሩና ለውጡ የመፈንዳትና እመርታዊ የመሆን ባህሪ ያሳያል። አብዮት ታፍኖ የሚካረር ቅራኔዎች የለውጥ ደረጃ ነው።

አሁን ኢህአዴግ ውስጥ በመሪዎችና በድርጅታዊ አቋሞች ሽግግር የተገለጸው ለውጥ በግንባሩ ውስጥ የነበረ ተፈጥሯዊ የተቃርኖዎች ፍትጊያ የእድገት ሂደት ውጤት ነው። በተወሰነ ደረጃ ተቃርኖዎችን እንደተፈጥሮ ህግ የመስወድ ክፍተት ግን የነበረ ይመስለኛል። ለውጡ አዝጋሚ ከመሆን ይልቅ በተወሰነ ደረጃ እመርታዊ ባህሪ ማሳየቱ የዚህ አመላካች ነው። በለውጡ ዙሪያ ያሉ ያአሁንም ልሰከኑ ሁኔታዎችም ይህን ያመለክታሉ። ይህ በኢህአዴግ እመርታዊ ለውጥ ዙሪያ የሚታየውን ያልሰከነ አቧራ አንዳንድ ወገኖች እንደ ኢህአዴግ ፍጻሚ ማሳያ አድገው የወሰዱበት ሁኔታ ታይቷል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። ኢህአዴግ በውጫዊ ግፊትና በውስጣዊ ተቃርኖ ፍትጊያ ሂደት መሰረታዊ ባህሪውን ሳይቀይር አዲስ መልክ ይዞ ወጣ እንጂ አልከሰመም፤ እየከሰመም አይደለም።

የኢህአዴግ ሊቀመንበርና የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና ከእርሳቸው ጋር ያለው የአመራር ቡድን የዚህ የኢህአዴግ ለውጥ ውጤቶች ናቸው። የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የተወሰዱ የታራሚዎችና የተጠርጣሪዎች ይቅርታ፣ በሃገር ውስጥ ህጋዊ ሆነው ከሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ድርድር ለማድረግ የተላለፈው ጥሪ፣ ከመንግስትና ከኢህአዴግ በተቃራኒ ጽንፍ ቆመው ሲታገሉ ለነበሩ ድርጅቶችና ሚዲያዎች የተላለፈው የሰላም ጥሪ፣ ለሁለት አስርት ዓመታት ያህል የዘለቀውን የኢትዮጵያና የኤርትራ የሰላም ችግር ለመፍታት የተወሰደው እርምጃ አዲስ ሆኖ የወጣው ኢህአዴግ ውሳኔ ውጤት ነው።

በመሆኑም፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድንና የአመራር ቡድናቸውን፣ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እየተወሰዱ ያሉ እርምጃዎችና እያስገኙት ያለው ከአመታት በፊት ይሆናል ተብሎ ያልተገመቱ ውጤቶች ከኢህአዴግ ተነጥለው የሚታዩ አይደሉም። የእመርታዊነት ባህሪ ባለው ለውጥ አዲስ መልክ ይዞ የወጣው ኢህአዴግ ውጤቶች ናቸው።

በተለይ ከ2008 ዓ/ም መግቢያ ጀምሮ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ውስጥ የነበረውና ተቃውሞው ሊያመጣ የሚችለውን አሉታዊ ውጤት ይናፍቅ የነበረው ህዝብ ለኢህአዴግ ሊቀመነበርና ለኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ፣ እንዲሁም ኢህአዴግ ላሳለፋቸውና በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተግባራዊ ተደርገው ወጤት ላሰገኙ እርምጃዎች ይሁንታውን ሰጥቷል። ሰሞኑን በአዲስ አበባና በተለያዩ የክልል ከተሞች የተካሄዱ የእውቅናና የምስጋና ህዝባዊ ትዕይንቶች የዚህ ይሁንታ መገለጫዎች ናቸው።

ይህን በኢህአዴግ ውስጥ የተካሄደ ለውጥና ለውጡ ያስከተላቸውን እርምጃዎችና የተገኙ ውጤቶች አለመቀበል፣ አይቀሬ የሆነውን የለውጥና እድገት ሂደት ያለመቀበል ግትርነት ነው። ይህ ግትርነት አይቀሬና ተፈጥሯዊ የሆነውን፤ የህዝብ ይሁንታ ያገኘውን የለውጥ ሂደት የመቀልበስ አቅም የለውም። እናም የኢህአዴግን ተፈጥሯዊ የለውጥ ሂደት ያመጣውን እመርታዊ እድገትና ወጤቶቹን መቀበል አስተዋይነት ብቻ ሳይሆን አማራጭ የሌለው ነው።

ኢብሳ ነመራ 06-29-18

AIGA

“ያልተሰማው ነብይ – ያሬድ ጥበቡ!” በተመስገን ደሳለኝ

በ1960ዎቹ አጋማሽ በ“ጥናት ክበብ” ስም በየመንደሩ ለውይይት መሰባሰብ ፋሽን በነበረበት በዚያን ዘመን፣ ታላላቅ አገራዊና ወቅታዊ አጀንዳዎችን በግራ-ዘመም አስተምህሮ በማጥናት የፖለቲካ “ፊደላትን” ሀሁ… ብሎ መቁጠር የጀመረው ያሬድ ጥበቡ፣ ከአቻዎቹ ጋር “አብዮት” የተሰኘ ፀረ ዘውድ ምስጢራዊ ቡድን ከመመሥረት ያገደው አልነበረም፡፡

Continue Reading

ምኞታችን እንዲሳካ ከቸልተኝነት የፀዳ ጥንቃቄ ያስፈልገናል!

‹ሌብነትን እምቢኝ አሻፈረኝ ያላችሁ ዕለት እኔን እንዳመሠገናችሁ ይቆጠራል፡፡ ይኼ ክልል የእኔ፣ ይኼ ወሰን የእኔ ነው ውጡልኝ መባባልን አቁመን፣ በፍቅር ተግተን ለአገራችን መሥራት የጀመርን ዕለት ያኔ ምሥጋናችሁ በሌላችሁበት እንደደረሰን ቁጠሩት፡፡

Continue Reading

ይድረስ ለሕወሓቶችና ለነገ ሠልፈኞች! ይነጋል በላቸው

የተከበራችሁ የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የጥቅም ተጋሪዎች!

በተራ እውነት እንነሳ፡፡ ጦርነት ሁሉ በግድ በጠበንጃ አይካሄድም፡፡ የጦርነት ዓይነቱ ብዙ ነው፡፡ ይህንንም በሀገራችን ሰሞነኛ ክስተቶች እየተገነዘብን እንገኛለን፡፡ በጥይት አረር የሚካሄድ ጦርነት ጊዜያዊ አሸናፊዎችን ይለያል፤ ተዘውትሮ እንደሚጠቀሰው በኃይል ሚዛን በልጦ በመገኘት በጥይት እሩምታ የሚካሄድን አንድ ጦርነት ማሸነፍ ብቻውን ጦርነቱን በአሸናፊነት መውጣትን አያመለክትም – ቀን ጠብቆና ኃይልን አደራጅቶ ጦርነቱ ማገርሸቱ አይቀርምና፡፡ በፍቅር ጦርነት ግን ዘላቂው አሸናፊ ይታወቃል፡፡

Continue Reading

የሃገርኛ ጀርመንኛ – እውን ኢህአዴግ አለወይ? ትርጉም ወደ አማርኛ – መላኩ ከአትላንታ

አሉላ ዮሃንስ የተባለ ሰው በትግራይ ኦንላይን ላይ እውን ኢህአዴግ አለወይ በሚል አርዕስት የከተባት ነገር ሳበችኝና ተመለከትኳት።ፅሁፏ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ ከሆነች ፀሃፊውን ከአንገቴ ዝቅ ብዬ አድናቆቴን እገልፃለሁ።ከተሳካ ግሩም ሙከራ ነው።ነገር ግን አቶ አሉላ በእውን ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ነበረ አሁን ግን የት ገባ ብሎ የፃፈውን የሚያምን ከሆነ ግን ትልቅ ችግር አለ። አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል ያለው አይነት መሆኑ ነው። ፅሁፉ የሚጀምረው በሚከተለው  ነው።

Continue Reading

በባድመ ጉዳይ ማነው ተጠያቂው? አቻምየለህ ታምሩ

የትግራይ ብሔርተኞች ዳግማዊ ምኒልክን ባልዋሉበት እያነሱ ካላብጠለጠሉ ፖለቲካ የሰሩ ስለማይመስላቸው በነጋ በመሸ ክብራቸው የሚነካ ነገር ያገኙ በመሰላቸው ቁጥር አጀንዳ ያደርጓቸዋል። ከሰሞኑ ባድመ የምትባል አጀንዳ አግኝተው በሊቀመንበራቸው በመለስ ዜናዊ ፊርማ ለሻዕብያ በተሰጠችው ባድመ አመካኝተው ዳግማዊ ምኒልክን እያወገዙ ናቸው። «ምኒልክ የሸጣት ባድመ ትመለስልን» በማለት እያላዘኑ ይገኛሉ።

Continue Reading

የሽግግር መንግስት አስፈላጊነት – ሰማሃኝ ጋሹ

አሁን በኢትዮጵያ እየተካሄደ በሚገኘዉ የለዉጥ ሂደት በተቃዋሚዉ ሃይል በኩል ሊወሰዱ ስለሚገባቸዉ እርምጃዎች የተለያዩ ሃሳቦች እየተሰነዘሩ ይገኛሉ። በአንድ በኩል ዶ/ር አብይ እየወሰዳቸዉ የሚገኙት እርምጃዎች አበረታች በመሆናቸዉ እሱን እየደገፍን የተሻለ ለዉጦች እንዲደረጉ ግፊት እናድርግ የሚል ነዉ።

Continue Reading

ዶ/ር ዐቢይና ሥር ነቀል ለውጥ በኢትዮጵያ – በዶ/ር ተክሉ አባተ

ዶ/ር ዐቢይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ ጀምሮ ኢትዮጵያውያን ልዩ ልዩ አመለካከቶችን በማንጸባረቅ ላይ ይገኛሉ። ጠቅለል ባለ ዳሩ ግን ጥናታዊ ባልሆነ መልኩ ሲታይ ዶ/ሩ ከሚናገሯቸውና ከሚያከናውኗቸው ሥራዎች አንጻር ኢትዮጵያውያንን በአመለካከታቸው በአራት ምድብ ማስቀመጥ ይቻላል። የመጀመሪያዎቹ ለውጡን በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው የሚወዱ ዶ/ሩንም እንደ መሲህ የሚመለከቱ ናቸው።Continue Reading

“ፍቅር እና እዉነት ያሸንፋል! የክፉዎች ሴራ ይከሽፋል!” አቶ ታዬ ደንደኣ

ባለፈዉ ዓመት ኢሉ አባቦር ላይ በኦሮሞ እና በአማራ መሀከል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። ያ ግጭት ግብ ነበረዉ። ግቡ በሁለቱ ታላላቅ የኢትዮጵያ ብሔሮች መሀከል የነበረዉን ምናባዊ መጠራጠር ይበልጥ በማጠናከር በኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ እና ባርነት መበልፀግ ነዉ። ግን ህልም ሆኖ ቀርቷል። ግጭቱ ኦሮማራን ወልዶ የሴራኞችን ጉልበት እንዳልነበረ አድርጓል። ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ጥሩ ተስፋ ማየት እንደ ጀመረ ለማሳየት ምስክር መጥራት አያስፈልግም።

Continue Reading

የአማራን ‘የሲቪክ ብሔረተኛ’ አደረጃጀት ለምን ይደገፋል?

1. አማራ መደራጀት ለምን አስፈለገው? ምክንያቱስ?

ላለፉት 27 ዓመታት የህወሃት “የጎሣ ፌደራሊዝም” ንድፍና ስርዐትና “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ” ርዕዮት አማራውን እንደ ህዝብ “ጨቋኝና በዳይ” በማድረግ ስሎና በራሱና ከሌሎች ጎሣ አባላት በቀጠራቸውና ባሰማራቸው ምንደኞች አማካይነት አሃዙን በቁጥር ማስቀመጥ የማይቻል ዕልቂት ፈፅሟል። ለምሣሌ ህወሃት ከኦነግና ሌሎች ጋር የፀረ-አማራ ግንባር ፈጥሮ በአርባጉጉ፣ በበደኖ፣ በጉራ ፈርዳ፣ በቤኒሻንገል፣ ኤሊባቡር ወ.ዘ.ተ. አማሮች ገደል እየተጨመሩ እንዲሞቱና እንዲገደሉ ተደርጓል። በኢሊባቡር፣ በጉራፈርዳና ቤኒሻንጉል ይህን የዘር ማፅዳትና ጭፍጨፋ (Ethnic Cleansing & Genocide) በአማራው ላይ ፈፅሟል። አማራውን ከኢትዮጵያዊ ጥቅሙ በመነጠል ተበድሏል። አማራው የመቋቋም እርምጃ ተደራጅቶ እንዳይወስድ ትግሬዎች በሚመሩት “ብአዴን” ጫናና እቀባ እየተደረገበት ቆይቷል።

አማራ ኢትዮጵያዊነቱን ጥሎ፤ ወይ በዘሩ አሊያም በኢትዮጵያዊነት እንዳይደራጅና መብቱን እንዳያስከብር ተገዶ በወያኔና ወያኔን ብቻ እንዲያገለግል ታስቦ በደደቢት በረሃ በተነደፈውና በጠላትነት በፈረጀው “የጎሣ ፌደራሊዝም” ስርዐት ስር በባርነት እንዲኖር ተፈርዶበትና “በእብዮታዊ ዴሞክራሲ” መፅሃፈ-ዲያቢሎስ ርዕዮት ማለትም “በዴሞክራሲያዊ ብሄረተኝነት” እንዲደራጅ ለዚህም የህወሃት ኮንዶም “ከኢህዲን” ወደ “ብአዴን” ስሙ የተቀየረው ድርጅት አማራውን በምስለኔነት እንዲያደራጅ ተወጥኖ የቆየ መሆኑን ለሁሉም ግልፅ ጉዳይ ነው። የዚህም ህወሃታዊ ሴራ ግብ ኢትዮጵያዊነትን ከአማራው ውስጥ በማውጣት የቀስ በቀስ ኢትዮጵያን የማዳከምና የማጥፋት ውጥን የያዘም ነው። አማራንና ኢትዮጵያዊነትን ማጥፋት ነው። ልክ ቱርኮች የአርሜንያን ዘር ለማጥፋት የወጠኑት እቅድና ቀጥለውም የተገበሩት የእልቂት ንድፍ አካል ነው። ይህ ወያኔያዊው ፅንፈኛ ዕይታ ነው።

የአማራ ትግል ከማንነት ጋር የተያያዘ በመጥፋትና ባለመጥፋት ወይም በማንነቱ ላይ የተቃጣና በመቃጣት ላይ ያለን የህልውና ጥቃት (existential threat) ለመከላከልና ለመመከት የሚደረግ የህልውና ትግል ነው። አማራነትና አማራዊ አደረጃጀት ግብ እራስን መከላከል (self-defence) እንጂ በህወሃትና ኦነግ የፈጠራ ትርክት “የበላይነቱን” ዳግም ለመጫን የታለመ አይደለም። የበላይም የበታችም አልነበረም። ጣሊያን ልክ እንደ ህወሃት “አማራንና ሃይማኖቱን ማጥፋት” ተብሎም እየተዘመተበት ነው። ልብ ማለት ያለብንም ይህን የጣሊያን “አማራነትን የማጥፋት” ዕቅድ አፄ ሚኒሊክ ያመከኑት ኢትዮጵያዊነታቸውን ኮንነውና አማራነትን ብቻ ይዘውም አልነበረም። አማራነታቸውን ከኢትዮጵያዊነት ጋር አጋብተው የድላቸውም ሚስጥር በአማራነትና በኢትዮጵያዊነት መሃል ያለውን መስተጋብር ያጠነከሩበት ኬሚስትሪ ነው። አማራነትን ከኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነትን ከአማራ ውስጥ በቀዶ ጥገና ጥበብ ማውጣት አይቻልም። የአማራ ትግል እራስን የመከላከል ፍትሃዊና ህልውናን የማቆየት ተጋድሎ ነው። ኢትዮጵያን ለማኖር አማራ እራሱን ማትረፍ አለበት። እራሱንም ባተረፈ ቁጥር ኢትዮጵያም ትታደጋለች።

2. ምን አይነት አደረጃጀት ለአማራ?

የአማራ አደረጃጀት የሲቪክ ብሔረተኝነት የሚከተል መሆን አለበት። ከጎሣ ብሄረተኝነት የራቀ አደረጃጀት መሆኑንና ለዚህም የጠራና ግልፅ መስመር ማስመሩ እጅጉን ይበጃል። ይህ ‘የሲቪክ ብሔረተኝነት’ አደረጃጀት ልዩ ጥቅምን የምናስተውለው የሚከተለውን የካናዳዊው ፀሃፊና ፖለቲከኛ ሚካኤል ግራንት ኢግናቲፍ በሲቪክ ብሔረተኝነት (Civic Nationalism) እና በጎሣ ብሔረተኝነት የሣለውን ንፅፅር ስንቃኝም ነው።

ይህንን ሚካኤል ግራንት ኢግናቲፍ በዚህ መልኩ ያቀርበዋል “የሲቪክ ብሔረተኝነት (Civic Nationalism) ሐገርን በጋራ ዜግነት (common citizenship) ይገልፀዋል:: የሲቪክ ሐገር (Civic Nation) ማንኛውንም ጎሣ፣ ዘር፣ ሃይማኖት፣ ፆታና ቀለም ያላቸውን ሁሉ የሚጠቀልልና በመርሆ ደረጃም እኩል የሆኑ፣ መብታቸውን ያወቁና በአርበኝነት ስሜት ፖለቲካዊ ልማድና እሴትን የሚጋራ ማህበረሰብ ነው:: የሲቪክ ሐገር ነፃነትንና የራስ አስተዳደርን ለዜጎች ስለሚያረጋግጥ ዴሞክራሲያዊ ነው:: የአሜሪካንና የፈረንሣይን ሪፑብሊኮች የፈጠረውም ይኸው የሲቪክ (civic) ብሔረተኝነት ነው::
የጎሣ ብሄረተኝነት (Ethnic Nationalism) ሐገርን በጥቅሉ በጎሣ ወይም በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በልማድና ወግ ይገልፀዋል:: በጎሣ ብሔረተኞች እምነት ሐገርን የፈጠረው መንግስት ሣይሆን መንግስትን የፈጠረው ሐገር ነው (It is not the state that creates the nation but the nation that creates the state):: በተጨማሪም የጎሣ ብሄረተኞቹ “ህዝብን በአንድ ላይ አሰባስቦ የሚይዘው ህዝብ በጋራ የሚቋደሰው የፓለቲካ መብት ሳይሆን የጎሣ ባህሪያት ናቸው (The glue that holds people together is not shared political rights but pre-existing ethnic characteristics)” ይላሉ::

ሚካኤል ግራንት ኢግናቲፍ በመቀጠልም “የሲቪክ ብሔረተኝነት (Civic Nationalism)’ እንደ ‘ጎሣ ብሔረተኝነት (Ethnic Nationalism)’ ከእውነት ያልራቀና የሐገራዊ ማንነትና ምንነት መገለጫ ነው:: የጎሣ ብሄረተኝነት ወይም ማንነት በሌሎች ጎሣዎች ላይ ለመነሳት ይጥቀም እንደሁ እንጂ በራሱ በጎሣው ውስጥ ለሚነሱ ወይም ላሉ የመደብ፣ የፃታና የመዋዕለ ንዋይ ክፍፍል ችግርን ለመፍታት አይችልም:: በአንፃሩ የሲቪክ ብሄረተኝነት (Civic Nationalism) ልዩነቶችን ለመዳኘት የሚያስችል የህግ መዋቅር፣ የፖለቲካ ተሳትፎና የህግ አመንጭነት ዕድልን ያጎናፅፋል” ይለናል::

3. የአማራ አደረጃጀትና ኢትዮጵያዊነት

አማራ ያለው ብቸኛ ምርጫና መፍትሄው መጀመሪያ ጥቃትን ለመመከት በአማራነት ተደራጅቶ እራስን በማስከበር በመቀጠልም የኢትዮጵያን ትንሣኤ መታደግ ነው። አማራ የጠላቶቹን ጥቃት ከመከተ፤ ምከታው በራሱ ኢትዮጵያን ይታደጋል። አማራና ኢትዮጵያዊነት ይመጋገባሉ እንጂ አይጣረሱም። የአማራ ሲቪክ ብሔረተኝነት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቹ ተበታትነው የሚኖሩባትን ‘ኢትዮጵያን አላውቅም’፤ ‘ጉዳይሽ ጉዳዬ አይደለም’ ካለ የሚክደው ኢትዮጵያን ብቻ ሣይሆን እራሱንና እነዚህን ወገኖቹንም ነው። ኢትዮጵያን የመካድ አባዜም ህወሃታዊ ነው። ከዚህ የጥፋት መንገደኛም ጋር የአላማ አንድነት መፍጠር ነው።

እደግመዋለሁ። አማራነት ኢትዮጵያዊነት፤ ኢትዮጵያዊነትም አማራነት ነው። ኢትዮጵያዊነትን መካድ አማራን መካድ ነው። ለኢትዮጵያዊነት ደማቸውን ያፈሰሱትን አጥንታቸውን የከሠከሱትንና ህይወታቸውን ገብረው በነፃነት ያኖሩንን ጀግና አብቶቻችንንና አያቶቻችንን መካድ ነው። በኢትዮጵያዊነት ተሰልፈው ነፃ ሃገር ያቆዩንን አርበኞች እጀ ሠባራ ማድረግ ነው።

የአማራ እራስን የመከላከል ጉዞ ግቡ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሆነ አማራ እራሱን ያፈርሳል (self-distructive move or suicidal)። በኢትዮጵያዊ ማንነትና በአማራ ምንነት መካከል ሚዛን (delicate balance) የመጠበቅ ግዴታም የአማራው ነው። አማራው ይህንን ያውቃል። የአማራ እራስን የመከላከል አደረጃጀት አማራዊ የፓለቲካ ትርፍ እንጂ አማራዊ ፓለቲካዊ የስልጣን ግብ ሊኖረው አይገባም። የአማራ አደረጃጀት መመሥረት ያለበት በፓለቲካ ወጥነት (political uniformity) ላይ ሣይሆን በአማራዊ አንድነት (unity) ነው።

አማራን ማንነቱን ለመታደግና ጥቃቱን ለመከላከልየሚያደርገውን ፍልሚያ ወይም ወደ ፍልሚያው ያስገቡትና የመሩት “የጎሣ ብሔረተኞች” አይደሉም። በአማራ ላይ የተነጣጠረ የሚደርስበትና እየደረሰበት ያለው ግፍና በደል ነው። እስከሚገባኝ ድረስ አማራ በአማራነት ከነባሩ ሕብረ-ብሄራዊ ቀዘፋው ወርዶ እንዲደራጅ ያስገደደው ፀረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሆነው “የጎሣ ፌደራሊዝም” እና የደቀ መዝሙሮቹ ገደብ አልባ ጥቃት እንጂ “የጠባብ ብሔረተኞች” የገደል-መንገድ አለመሆኑን ማስመር ይገባል። የአማራ የመመከት ገድል ልክ አይሁዶች በነርሱ ላይ የተነጣጠረን የዘር ማፅዳትና ጭፍጨፋ ለመታደግ እንደተደራጁት ነው።

ከሁሉም በላይ አማራ ክልል ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ ያላነሰ በተለያዩ ክልሎች በመኖሩ ኢትዮጵያዊነቱን ያጎላል። አማራ ከተለያዩ ነገዶችና ጎሣ አባላትና ማህበረሰብ ጋር በፍቅር፣ በሠላምና በበጎ መስተጋብር ያለ ምንም የተለየ ዘር ተኮር የመንግስት ወይም የጎሣ ጥቃት ጠባቂ ሳያስፈልገው ለዘመናት መኖር የቻለው በኢትዮጵያዊ ማንነቱ ብቻ ነው። አማራ የሌለበት የኢትዮጵያ ግዛት የለም። አማራ ከተለያዩ የጎሣ አባላት ጋርም በከፍተኛ ቁጥር በጋብቻ የተጠላለፈ ህዝብ ነው። ሊፈጠር የሚችለውን ህዝባዊና ማህበራዊ ቀውስ ከስሜት በፀዳ መልኩ መቃኘት አለበት።

የአማራ ብሔረተኝነት ኢትዮጵያዊነትን የሚክድ ከሆነ ያነገበው ህወሃታዊ “ዴሞክራሲያዊ ብሔረተኝነት” ይሆንና የእራሱን ቤት በእራሱ ክብሪት ሊያቃጥል ነው። “ኢትዮጵያን የሚያብጠለጥልና የሚኮንን፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባኝም” የሚል “ብሔረተኝነት” አማራዊ የሲቪክ ብሄረተኝነት ሣይሆን የጠባቦች የጎሣ ብሔረተኝነት ይሆንና ውሉን ስቶ ወያኔያዊና ኦነጋዊ ይሆናል። በመላ ሃገሪቱ ተሰራጭተው ከቁጥር በላይ የሚኖሩት አማሮች ላይ እሣት መለኮስ ነው።

የአማራ ብሔረተኛነት ‘የሲቪል ብሄረተኝነት ነው። አላማውና ግቡ የአማራን መብት ማስጠበቅ፣ ጥቃትን መመከትና ለማንነቱ መቆም ነው።

ኢትዮጵያዊነትን የሚክድና የሚያስክድ በአማራ ስም የሚሣለቅ አደረጃጀት ህወሃታዊና ነው!

የአማራ ‘የሲቪክ ብሔረተኝነት’ ጊዜያዊ ግቡ አማራን አደራጅቶና የአማራን ጥቃት ታድጎ በዘለቄታው የኢትዮጵያን ትንሣኤ እንደ አባቶቹ ማብሠር ነው!!!

ሐይሉ አባይ ተገኝ

አዲሱን የአማራው ፓርቲ ማን ወለደው?

ጌታቸው ሺፈራው -ዛሬ ሰኔ 2/2010 ዓም በባህርዳር አዲስ የአማራ ፓርቲ ምስረታ ጉባኤ ተጀምሯል። በምስረታው ላይ ሁለት አይነት “የሕዝብ” ስሜት ይብፀባረቃል። አንደኛው ደስታ ነው። ሁለተኛው በጥቅሉ ትችት ይመስላል። በዘር ተደራጁ የሚል። ደስታው ሕዝብ ወኪል ከማጣቱ የመጣ ነው። የሕዝብን ብሶት የሚያሰማ አካል በመጥፋቱ አማራጭ ተገኘ ከሚል ነው።

Continue Reading

የአንዳርጋቸው ጽጌ አፈታት ለዶ/ር አብይ አስተዳደር ያለኝን እይታ ቀይሮታል – መሳይ መኮንን

የአንዳርጋቸው ጽጌ አፈታት ለዶ/ር አብይ አስተዳደር ያለኝን እይታ ቀይሮታል። በፊትም የለውጥ ሃይል ቤተመንግስት እንደገባ የሚሰማኝ ስሜት ላይ ተጨማሪ እምነት እንዳሳድር አድርጎኛል። ዶ/ር አብይ በየዕለቱ የሚወስዷቸው እርምጃዎች የራሳቸው ጥቅምና ጉዳት ቢኖራቸውም በጥቅል ስንመዝናቸው ሰውዬው አንዳች ታሪክ ለመስራት ከልብ ቆርጠው መነሳታቸውን መመስከር ግድ ይላል።

Continue Reading

ጉደኛው መሪያችን – ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

Continue Reading