ደንቡ ምን ይላል? በጨረፍታ

በፓርቲው ሕገ ደንብ የትኛውም ቦታ ሊይ ከየትኛውም ብሔራዊ ፓርቲ እጩ ተወዲዲሪ በወረፋ መቅረብ አለበት የሚል ይዘት ያለው አንቀፅ የለም፣ ባለፈው ጊዜ የዚህኛው ፓርቲ የግንባሩ ሉቀመንበር ነበር፣ አሁን ደግሞ የዚያኛው ፓርቲ ተራ ነው የሚባል ነገር የለም፣

Continue Reading

Advertisements

በምዕራብ ኦሮሚያ ኦነግ ጥቃት ፈጸመ፤ ወታደራዊ ካሚዎንና ወታደሮች ላይ ጉዳት አድርሷል፤ የጸጥታ ሃላፊው አምነዋል

የኦነግ ተዋጊዎች በምዕራብ ኦሮሚያ ጥቃት ማካሄዳቸው ተሰማ። በጥቃቱም በመከላከያ ሰራዊት አባላትና በተሽካሪዎቻቸው ላይ ጉዳት መድረሱ ተመልክቷል። እንደመረጃዎቹ ከሆነ በዚሁ ማጥቃት በሁለት ኦራል የወታደራዊ ካሚዮን ተሳፍረው በነበሩ የሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል። አንድ ኦራል ማምለጥ ሲችል ሌላኛው ካሚዮን ከጫናቸው የመከላክያ ሠራዊት አባላት ጋር መወደሙ ተጠቁሟል። ጥቃቱን እንደተፈጸመ የአካባቢው አስተዳደር መዋቅር አረጋግጧል።

Continue Reading

« የስልጣን እይታ ብልሽትና የፓርቲ መበስበስም ስላጋጠመን ነው ወደ ችግር የገባነው» ሽፈራው ሽጉጤ

የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሽፈራው በሳምንት ጊዜ ውስጥ ፓርቲያቸው ለሚመራቸው ሚዲያዎች ሁለት የተለያዩ መረጃዎችን ሰጡ። ከአስራ አምስት ዓመት በሁዋላ በድጋሚ ፓርቲው መበስበሱን ተናገሩ። ኢህአዴግ አገራዊ ፓርቲ እንዲሆን ስምምነት መደረሱን፣ በስምመነቱ አጋር ፓርቲዎችም የሚካተቱበት ሁኔታ እንደሚታይ አመለክቱ። የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አመራር አሰያየምን አስመልክቶ ፓርላማ ከመቅረቡ በፊት የአራቱ ፓርቲዎች አመራሮች ተስማምተው ነበር አሉ። ቀደም ሲል  ” በተባበረ” ድምጽ እንደተወሰነ ይፋ አድርገው ነበር። 

Continue Reading

የአማራ ፖለቲካ ሃይሎችን ወደ አንድነት ለማምጣት የተደረገ ጥረት ፤ ሂደትና ፤ ውጤቱ!

ሻለቃ ዳዊት ወልደጎርጊስ፣ ፕሮፌሰር ጌታቸው በጋሻው እና ኃይለገብርኤል አያሌው

በትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ኢትዮጵያ ሃገራችን በታሪኳ አይታ ወደማታውቀው የትርምስና የጭለማ ዘመን የደረሰችበት ሁኔታ ላይ ከወደቀች ቆየች:: የአማራው ህዝብም በማንነቱ ምክንያት በተከፈተበት የጥላቻ ዘመቻ ለከፋ የህልውና አደጋ ተጋልጦ ሃገሩንና አብሮነቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል በታላቅ ትዕግስት መሪር መስዋዕትነትን እየከፈለ ቆይቷል::

Continue Reading

ፈተናው ቢከብድም ማለፍ ግን ይቻላል!

አገሪቱ ከሁለት ዓመታት በላይ የገባችበት የቀውስ አዙሪት፣ በተለያዩ ገጽታዎች የተለያዩ ክስተቶችን እያስተናገደ ነው፡፡ የወቅቱን ፈታኝነት በሥጋት የሚመለከቱ ያሉትን ያህል፣ ከሥጋት ባሻገር የተሻለ ጊዜ ይመጣል ብለው ተስፋ የሚያደርጉም አሉ፡፡ ወቅቱ ያረገዘው ሥጋት ፈተናውን እንዳከበደው እርግጥ ቢሆንም ተስፋ መቁረጥ ግን አይገባም፡፡ ኢትዮጵያ በታሪኳ ያላጋጠማት ፈተና፣ ያላየችው መከራና ሥቃይ የለም፡፡ አገርን ሊወሩ ከመጡ ወራሪዎችና ተስፋፊዎች፣ እስከ ውስጣዊ የሥልጣን ትግልና ትንቅንቅ በርካታ ጦርነቶችና ግጭቶች ተካሂደውባታል፡፡ ለማመን የሚከብዱ ፈተናዎችን በቆራጥና በአይበገሬ ልጆቿ አማካይነት መጋፈጥ የቻለችው ይህች ታሪካዊ አገር፣ በአሁኑ ትውልድም እውነተኛ የአገር ፍቅር ስሜት ከገባችበት ማጥ ውስጥ ለመውጣት አያቅታትም፡፡

Continue Reading

በአሜሪካ የትግራይ ኮምዩኒቲዎች ፎረም በአገራችን ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ የተሰጠ የአቋም መግለጫ

  • ዜጎች የማንም ፖለቲካና ፓርቲ ደጋፊ በመሆናቸው ይሁን በብሄር ማንነታቸው እንደጠላት የሚፈርጁ፣ አደጋ የሚያደርሱና ለማድረስ የሚሞክሩ ሰዎች የሚቀጡበት “የጥላቻ ወንጀል መቅጫ ህግ” ካለ ተግባራዊ እንዲሆን ከሌለ ደግሞ እዲደነገግ ኣጥብቀን እናሳስባለን።
  • ኢትዮጵያ ውስጥ እየተፈፀመ ያለው መጠነ ሰፊና በትግራይ ህዝብ ላይ ያነጣጠረ የስም ማጥፋትና የጥላቻ ዘመቻ መሰረተ ቢስ ከመሆኑም በላይ በሃገራችን ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተፅእኖ ቀላል ስለማይሆን ይህ ዘመቻ በመንግስት፣ በሃይማኖት አባቶች፣ በታዋቂ ግለስቦችና ተቃዋሚ ሃይሎች በጥብቅ ተወግዞ ተከታታይ ትምህርትና እርምት እንዲሰጠው አበክረን እንጠይቃለን።         ሙሉወን አስፈንጣሪውን በመጫን ያንብቡ

tigrai-community-forum-north-america-resoultion-030618

ሩሲያ ለኢትዮጵያ የኑክሌር ማዕከል የመገንባት ዕቅድ እንዳላት አስታወቀች

Continue Reading

ለውጥ እና ሞት ለህወሓት አንድ ናቸው! ቀድሞ መጥፋት ወይስ ማጥፋት…?

ስዩም ተሾመ – በኦህዴድ እና ብአዴን የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በህወሓት ላይ ቀጥተኛ የሕልውና አደጋ ጋርጧል። የኦሮሞና አማራ ሕዝቦች እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ ተጎጂ የሚሆኑት የህወሓት አባላት እና ደጋፊ ልሂቃኖች ናቸው። ምክንያቱም የህወሓት አባላትና ደጋፊ ልሂቃን ከድርጅቱ ጋር ባላቸው አድሏዊ ግንኙነት የማይገባቸውን የመወሰን ስልጣን እና የኢኮኖሚ ሃብት አካብተዋል። በመሆኑም የኦሮሞ እና አማራ ሕዝብ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ተረጋገጠ ማለት እነዚህ ልሂቃን፤ አንደኛ፡- እስካሁን የያዙትን ያልተገባ ስልጣን ያጣሉ፣ ሁለተኛ፡- በኢኮኖሚው ውስጥ የነበራቸው ኪራይ ሰብሳቢነት እና የሚያገኙት ያልተገባ ጥቅም ይቋረጣል። ህወሓት በመንግስታዊ ስርዓቱ ውስጥ ያለው የስልጣን የበላይነት እና ኢ-ፍትሃዊ የጥቅም ግንኙነት ከተቋረጠ እንኳን ሀገርና ሕዝብን ራሱን ማስተዳደር ይሳነዋል። ስለዚህ  የኦሮሞና አማራ ሕዝብ እኩልነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ሲረጋገጥ የህወሓት ሕልውና ያከትማል።

Continue Reading

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ የአቋም መግለጫ

የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ላለፉት 24 ቀናቶች ስብሰባ ኣካሄዷል። የማዕከላዊ ኮሚቴው ስብሰባ የተካሄደው በአብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ስርዓታችን እና አጠቃላይ ሃገራዊ ህልውናችን ከፍተኛ አደጋ ላይ በወደቀበትና ይህንኑ መሰረት ያደረገው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው እያጋጠሙን ባሉ ፖለቲካዊና ሃገራዊ ችግሮች ዙሪያ ባደረገው ግምገማ አጠቃላይ መስማማት በመፍጠር ቀጣይ አቅጣጫዎችን ባስቀመጠ ማግስት ነው።

Continue Reading