Category: Socity / ማህበራዊ

ደረጃ ባይኖረኝም … በግብር ከፋይነቴ እኮራለሁ፤ እኮራና ደግሞ አፍራለሁ …

እኮራና ደግሞ አፍራለሁ፡፡ ኮርቼ ሳላበቃ እንደገና አንገቴን እደፋለሁ፡፡ግብር መክፈል ክብር ከመክፈል አቻ ሆኖብኝ ተቸግሬአለሁ፡፡ክብሬን ከግብሬ ጋር ስለምከፍል አፍራለሁ፡፡ በስታዲየም በኩል አድርጌ ቀና ብዬ የባቡሩን መንገድ ሳይ እኮራለሁ… ጎንበስ ብዬ ደግሞ መንገድ ላይ እንደ ተረፈ ምርት፡ ውሃው እንደተጠጣ የፕላስቲክ ኮዳ ወገኔ ወድቆ ሳይ አፍራለሁ፡፡ያ ኮርቼበት ያላበቃሁት ባቡር በመብራት እጦት […]

የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል: ዐፅም እና የቀብር ሐውልት ስለ ማንሣቱ ማብራሪያ ሰጠ

ዐፅሞች እንዲፈልሱ፣ ሐውልቶች እንዲነሡ መደረጉ መካነ መቃብሩ ሞልቶ በመጨናነቁ ነው መካነ መቃብሩን ከማልማት እና ከመንከባከብ በቀር፣ ሕንፃ የመገንባት ዕቅድ ፈጽሞ የለንም ሐውልቶችን ብቻ በማንሣትና ሙሉ በሙሉ ዐዕፅምቱን በማፍለስ – በሁለት መልኩ ተፈጽሟል በበዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን ቅጽረ ግቢ 60፣ በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ 230 ዐፅሞች ተነሥተዋል የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ዐፅም፣ ከ8 ዓመት በፊት በክብር ፈልሶ በጋራ […]

እንጦጦን የቱሪስት መስህብ የማድረግ ውጥን

ባቡር መንገድ (የመኪና መንገድ) አዲስ አበባ ላይ የተጀመረው በ1894 ዓ.ም. ቢሆንም፣ በእንጦጦ ዳገት ላይ ባቡር መንገድ የተሠራው በ1897 ዓ.ም. ነው፡፡ መንገዱ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በእንጦጦ ዳገት ላይ እየተጥመዘመዘ እስከ ማርያም ቤተክርስቲያን ድረስ በመሐንዲሱ በሙሴ ካስተኛ ተቀይሶ ዳገቱ እየተቆፈረ መደልደሉን ብላታ መርስኤ ሐዘን ወልደቂርቆስ ‹‹የዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ አፄ […]

“የጣና ወዳጆችና ተቆርቋሪዎች ማህበር” ለማቋቋም እና ለአባላት ምዝገባ የቀረበ ጥሪ

  እምቦጭ አረም በቪክቶሪያ ሐይቅ፤ – ሙሉቀን ተስፋውእምቦጭ አረም በቪክቶሪያ ሐይቅ – ሙሉቀን ተስፋው የእምቦጭ አረም በአፍሪካ ትልቁ የሆነውን የቪክቶሪያ ሐይቅ መውረር የጀመረው በ1980ዎቹ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡ የእምቦጭ አረም (Water hyacinth) ከ1992 እስከ 1998 ባለው ጊዜ የቪክቶሪያ ሐይቅን ቀላል የማይባል ክፍል መሸፈን ችሎ ነበር፡፡ በ1998 እ.ኤ.አ ከ20 ሺህ […]

ሳዑዲ አዋጇን በሰላሳ ቀን አራዘመች

የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት ኢትዮጵያ የምህረት አዋጁ እንዲራዘም ያቀረበችውን ጥያቄ ተከትሎ አዋጁን ማራዘሙ ተነግሯል። የሳዑዲ ዓረቢያ መንግስት የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው የሌሎች ሀገራት ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የምህረት አዋጅ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም መጠናቀቁ ይታወሳል። የኢትዮጵያ መንግስትም የተጠናቀቀው የእፎይታ ጊዜ ይራዘም ዘንድ ከሳዑዲ […]

ቅድመ ዝግጅት በትግራይ

በትግራይ በክረምት ወቅት የሚተከለው የዛፍ ችግኝ ኩታገጠምን መሰረት በማድረግ ይከናወናል በትግራይ ክልል በተየዘው የክረምት ወቅት ለመትከል የተዘጋጀ ከ71 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ኩታገጠምን መሰረት በማድረግ እንደሚከናወን የክልሉ ግብርናና ገጠር ልማት ቢሮ ገለጸ። በቢሮው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ልማት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለኢዜአ እንዳሉት በክረምቱ  የሚተከለው ችግኝ […]

ይድረስ ለሚመለከታችሁ ባለስልጣናት

ነቢዩ ሲራክ –  ለአንባሳደር አሚንና ለአምባሳደር ውብሸት ባላችሁበት –  ቅጅ – ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ወርቅነህ ገበየሁ መረጃን ማቀበሌ ወንጀል ሆኖ “የነቢዩ ሲራክ ልጆች ከሚማሩበት የጅዳ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት እንዲታገዱ” የሚለው የካድሬዎች ሀሳብ ያን ሰሞን ቀርቦ እንደነበር በድጋሜ በማረጋገጤ አዝኘ ነበር ያደርኩት ። … ስለ እውነት ለመናገር ፣ ስለ […]

በኦሮሚያ ክልል ትናንት በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች የሞቱ ሰዎች ቁጥር 35 ደርሷል

በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ፣ ምእራብ ሀረርጌ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች በደረሱ ሶስት የትራፊክ አደጋዎች በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል። ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ላይ በምእራብ አርሲ ዞን ከሻሸመኔ ወደ አርሲ ነገሌ 15 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ ዶልፊን ተሽከርካሪ ቀርሳ አድቬንትቲስት ኮሌጅ አካባቢ ሲድርስ ድልድይ ውስጥ ገብቶ […]

ጥበበኛው ግንበኛ

click here for pdf ግንበኛው ድንጋዩን ይጠርብና በድርድሩ ላይ ሰክቶ አንዴ ፈገግ፣ አንዴ ተከዝ፣ አንዴ ቆም አንዴም ጎንበስ ይላል፡፡ ላት አይቶ በግ እንደሚገዛ ሰው በግራ በቀኝ ያገላብጠዋል፡፡ እንደ ገዳም ጸሎት ሲመሰጥ፣ እንደ ጉብታ ዛፍ ሲናወጥ ይታያል፡፡ እንደ ኮከብ ቆጣሪ ሲያፈጥ፣ እንደ ጥሩ ወጥ ቀማሽ ምራቁን ሲወጥ ይታያል፡፡ ድንጋዩን […]

ያልከፈለ ስደት

  የጠዋቷ ፀሐይ ፈንጥቃ ሙቀቷን ካጋራችው የሕንፃው በረንዳ አንዲት የተከናነበች ሴት ቡና ትቆላለች፡፡ ከፊት ለፊቷ የተወሰኑ መቀመጫዎች በክብ ተደርድረዋል፡፡ ዓረብ አገር ለሥራ ሄደው ገንዘብ ሳይሆን የአዕምሮ ሕመም ይዘው የተመለሱ ኢትዮጵያውያት የሚጠለሉበትን ሕንፃ ቃኝተን ወደበረንዳው ስንመለስ፣ የተወሰኑ ሴቶች ቡናውን ከበው ተቀምጠው ነበር፡፡ አንዷ ደግሞ የምትፈልገው ያለ ይመስል አንዴ ቤት […]