Advertisements

German goalkeeper decides to join Arsenal

Bayer Leverkusen goalkeeper Bernd Leno has decided that he wants to join Arsenal. According to The Mirror, Leno has snubbed interest from Italian side Napoli to close in on a switch to the Premier League.

Continue Reading

Advertisements

የስፔን ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ከሃላፊነት ተነሱ

ስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጣኝ ዩለን ሎፔቴጉይን ከሃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ። የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ሉዊስ ሩቢያሌስ፥ አሰልጣኝ ሎፔቴጉይ ፌዴሬሽኑን ሳያማክሩ ሪያል ማድሪድን ለማሰልጠን በመስማማታቸው ምክንያትት ከሃላፊነት ለማንሳት መገደዳቸውን ተናግረዋል።

Continue Reading

ዛሬ የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ቡድንን እንዲህ ነው ዳኛ እያሳደዱ የደበደቡት፤ ክለቡ ” ከበባ ነው ይቅርታ” ይላል

በዛሬው እለት መከላከያና  የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ እግር ኳስ ቡድንን እየተጫወቱ ሳለ መከለከያ ወደ ግብ የላካት ኳስ መስመር አልፋለች በሚል ጎል አድርገው ያጸድቃሉ። ከዛ በሁዋላ ሁሉም ተጨዋቾች ዳኛውን ማባረር ይጀምራሉ። ዳኛው ነብሴን አውጪኝ ብለው ሜዳ ለሜዳ ይሮጣሉ።

Continue Reading

ዓለም ዋንጫ ድልድል

በሩሲያ የዓለም የ2018 የዓለም እግር ኳስ ዋንጫድልድል ታውቋል። ለ 28 ቀናት ማለትም ከሰኔ 5 – ሀምሌ 8 የሚካሄደው ፉክክር የምድብ ድልድል በዛሬው ዕለት ማምሻውን ሞስኮ ተከናውኗል። በድልድሉ መሰረት ሩሲያ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅ እና ኡራጉያ አንድነት ተደልደለዋል።  በሁለተኛው ምድብ ስፔን ፣ ፓርቹጋል ፣ሞሮኮና ኢራን ይገናኛሉ። ምድብ ሶስት ፈረንሳይ፣ አውስትራሊያ ፔሩና ዴንማርክ ሲደለደሉ፤ አርጀንቲና አይስላንድ፣ክሮሽያና ናይጀሪያ በመጨረሻው ምድብ ተደልድለዋል። ሙሉውን ከሰንጠርዡ ይመልከቱ

Beckham £1bn, Giggs £2bn – Keane on transfer fees

Roy-Keane-Manchester-United

MANCHESTER, ENGLAND – NOVEMBER 3: Roy Keane

Roy Keane jokes former Manchester United team-mate Ryan Giggs would be worth £2bn in the current transfer market.

The Republic of Ireland assistant manager says fellow ex-Red Devils players Ruud van Nistelrooy and David Beckham would be worth £1bn but adds he would go for a modest £3.75m, the fee United paid for him in 1993.

Earlier this summer, Neymar joined PSG from Barcelona for £200m, with Barca signing Ousmane Dembele from Borussia Dortmund in a deal that could be worth £135.5m.

 

አርሰናል – መጨረሻው የማይፈታ ቀውስ ሆነ – ባለቀ ሰዓት አብዮት? ሲቲ ስተርሊንን ማባበበያ አቀረበ፤

Football pundit Phil Neville“Now it seems like a crisis, a moment in the club’s history when you think something has to change, whether that’s the manager, the board, the players…There have to be big changes.”

” በክለቡ ታሪክ ያልታየ ቀውስ ነው አሁን እየታየ ያለው ። ዌንገር፣ ቦርዱ፣ ወይም ተጨዋቾች ሊቀየሩ ይገባል ፤ ለውጥ መኖር አለበ” ፒል ኔቭል

አርሰን ዌንገር አሁን የከፋ ችግር ውስጥ ናቸው። ነባር ተጫዋቾች ማጽናኛና ወቀሳ እየላኩ ነው። ለመድፈኞች ያበረከቱትን ታላቅ ታሪካና ሽግግር ገደል ሲገባ እያዩት ነው። ዋንጫ አንስቼ እሰናበታለሁ በሚል ከርሳቸው ጋር የገቡት እልህ የቀደመውን ስብዕናቸውን እየበላው ነው። ቀደም ሲል የገነቡትን መልካም ስም እያከሰሙት ነው። ዌንገር ትዳራቸውን ያፈረሰው ይኽው ” አይበቃኝም ” የሚለው እልሃቸው ነው። ” በአምላክ ላይ እምነትና ኳስ በህይወቴ ትልቅ ቦታ አላቸው” የሚሉት ዌንገር አሁን ይህንን ፈተና ማለፍ የሚችሉ አይመስልም። እናም ወደ አምልኳቸው ቢያተኩሩ የሚሻል ይመስላል

Image result for arsenal manager in anger

” ታሪክህ አጠፋኸው ፤ ለቀቅ” የሚሉ ጠንካራ አስተያየቶች በስፋት እየተስተጋቡ ነው። ” ለውጥ ፣ አንድ የሆነ ለውጥ” እንደሚያስፈልግ ተጨዋቾች ተናግረዋል። የቀድሞ ተጫዋቾችና ተንታኞች ዌንገርን ከአሰላለፍ ምርጫ ጅምሮ በከረረ የትችት ቢላዋ እየበለቱዋቸው ነው። የክለቡ ደጋፊዎች የቁጣ ድምጽ እየመረረ ነው። አሁን ያላው የአርሰናል ውጥንቅጡ የወጣና የተዘባተለ አቋም እንዴት እንደሚቀጥልም ሆነ እንዴት እንደሚቀረፍ የታወቀ ነገር የለም።

በኳስ ዓለም ” ውርጅብኝ” የሚባል እውነት አለ። ይህ የሚከሰተው በአንዳንድ አጋጣሚ ያልተጠበቁ ጎሎች ይቆጠራሉ። የተመቱ ኳሶች ምክንያት እየፈለጉ ጎል ይሆናሉ። እንዲህ ያለውን አጋጣሚ መቀበል ግድ ነው። የኳስም ተፈጥሮ ነው። የአሁኑን / የሊቨር ፑልን/ ሽንፈት መቀበል ግን በማንኛውም መስፈርት የሚቻል አይሆነም። በአርሰናል በኩል የመጫወት ፍላጎትና ተጋጣሚን የመፎካከር ስሜት የለም ነበር። በማለት ፒተር ቼክ ከጫወታው በሁዋላ ተናግሯል። በመልበሻ ክፍልም የከረረ እሰጥ አገባ ነበር።

የማንችስተሩ ጋሪ ኔቭል ” ክብረ ነክ” ሲል ነው የአርሰናል ተጫዋቾችን የዘለፈው። በተለይም ሳንዜዝ፣ ቼምበርሊን፣ ራምሴ፣ ቤረሊን፣ ኦዚልን ስም ጠቅሶ ለማሊያቸው የማይጫወቱ አሳፋሪዎች ብሏቸዋል። ለአስለጣኙ ሳይሆን ለራሳቸውና ለክለቡ ክብርና መለያ እንደሚጫወቱ ያልተረዱ መሆናቸው ከሽንፈቱ በላይ አሳዛኝ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ የሰላ ትችት አውርዶባቸዋል።

ኢያን ራይትስ በመልበሻ ቤት ያለው የተጨዋቾች ይሚታየው ሁኔታ፣ የክለቡ ታክቲክ፣ የተጨዋቾች ችሎታ፣ የአሰላለፍ ምርጫ … በጥቅሉ ከዌንገር ውጭ ሆኗል ወይም ተስኗቸዋል። ሶስት የክለቡ ወሳኝ የሚባሉ ተጫዋቾች የኮንትራት ሁኔታ በወጉና በጊዜው እልባት ሳይሰጠው እዚህ ደረጃ መድረሱ የአስተዳደር ችግር ነው። አሁን የተጨዋቾች ዝውውር ጊዜ ጫፍ በመሆኑ ለማስተካከልም ጊዜ አለመኖሩን ይናገራል። ሆኖም አሁን የሚፈለገው በማንኛውም መልኩ ተመልሶ ስለመጠናከር ሲሆን ይህም ከቦርዱ እንደሚጀመር ነው።

Sanchez exchanged a handshake with Arsene Wenger

አሁን እየተነሳ ያለው የአርሰናል ችግር ከዌንገር ክለቡ ውስጥ ረዥም ጊዜ መቆየት ጋር ተያየዞ የተደራረበ መሆኑ ነው። አርሰናል ካለው ስምና ዝና አንጻር የያዛቸው ተጫዋቾች መካከል ክለቡን የማይመጥኑ ይበዛሉ። አንዳንዶች በቲውተር ” ይህ ሽማግሌ ለቃሚ ሰብስቦ ከለቡን ገደለው” በማለት ሲዛለፉ፤ በተመሳሳይ ዌንገር አርሰናልን ትልቅ ክለብ ማድረጋቸው የማይካድ መህኖኑን ጠቁመው ነው እዲበቃቸው የሚጠይቁት።

የአሰላለፉን ስህተት ለማሳየት ምሳሌ ያሳየው ኮዌን እየሊቨርፑሉ ማኔን ፍጥነትና አስቸጋሪነት አርሰን ዌንገር ግንዛቤ ውስጥ እንደከተቱ ይጠራጠራል። ለዚህም ነው ” ልምድ የሌለውን ተከላካይ ሆልዲንግን ለተኩላዎች አሳልፈው ሰጡት” ያለው። እሱ ብቻ አይደለም። ቼምበርሊን በቀኝ መስመር ሲመላለስ ማኔን እየተመለሰ በማገድ፣ እንዲሁም ወደፊት ጫና በማብዛት ማኔን ወደሁዋላ የመመለስ ስራ መስራት ሲገባው ራሱንም ማሊያውንም ንቆ መታየቱንም ጸሃፊው ይተቸዋል። ከሁሉም በላይ መጫወት የማይፈልገውን ሳንቼዝን ማሰለፍና ፣ ቤላሪንን በግራ መስመር አድርጎ አዲሱን ኮላሲናክ ማሰቀመጥ ከላላካዜት አለምኖር ጋር ተዳምሮ የዌንገር አብይ ስህተት አድርጎ ይወሰደዋል።

አርሰናል የመሃል ሜዳ መሪ አልባ ቡድን ነው። አርሰናል በተሰበረ የመሃል ሜዳ ሲዳክር አስር ዓመት ሞልቶታል። ዌንገር እንደ አንድ ልምድ ያልው አሰልጣኝ ይህንን ክፍተት ሳይሞሉ ይህን ያህል ዓመታት የመቆየታቸው ሚስጢር ለማንም ግልጽ አይደለም። ታዳጊ ተጫዋች ማሳደገና ማዘጋጀት የሚቻልበትን የጊዜ ዘመን ከቪየራ በሁዋላ መችታ መርጠዋል። አርሰናል ጉድለት ያለብትን ቦታ ሳይደፍን ጊዜ እየተበላና በሽርፍራፊ ውጤት እየተድበሰበሰ ለዚህ ታሪካዊ ቀውስ መብቃቱ አስደንጋጭ ሆኗል።

ይህ በእንዲህ እያለ ማንችስተር ሲቲ ስተርሊንግን ማባበያ በማድረግ ሳንቼዝን የጋልቸው ለማድረግ ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ተሰምቷል። ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንደሚያሳዩት ሃሙስ ከሚዘጋው የዝውውር መስኮት ጋር የተያዘው ግብግብ በአረሰናል ቤት ውስጥ ምን እንደሚፈጥር አልታወቀም። ይሁን እንጂ የቼምበርሊን ወደ ቼልሲ መግባት ያለቀ መሆኑና ፤ አርሰናልም የኒሱን አማካይና ተከላካይ ሊያስፈርም እንደሚችል ወሬዎች አሉ።

የትንታኔ ጥንቅር የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ቅድመ ቅኝት

የ 2017 ተጠባቂው የባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ የ 32ቱ ቡድኖች ምድብ ድልድል ባሳለፍነው ሀሙስ ምሽት በሞናኮ ፈረንሳይ በተደረገ ልዩ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይፋ ሆኗል። እኛም በአርቡ የቅድመ ትንታኔም ክፍል አንድ ጥንቅራችን ከ 32 ቱ የአውሮፓ ሀያላን የ 16ቱን ቡድኖች ወይም የመጀመሪያ አራት ምድቦች ቅድመ ትንታኔ እንዳስመለከትናችሁ አይረሳም። ቀጣዩ የክፍል ሁለት ዝግጅት ደግሞ ቀሪዎቹን አራት ምድቦች […]

via የትንታኔ ጥንቅር (ክፍል ሁለት) / የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድል ቅድመ ቅኝት — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የ 2017 ተጠባቂው የባለትልቁ ጆሮ ዋንጫ የ 32ቱ ቡድኖች ምድብ ድልድል ባሳለፍነው ሀሙስ ምሽት በሞናኮ ፈረንሳይ በተደረገ ልዩ የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይፋ ሆኗል። እኛም በአርቡ የቅድመ ትንታኔም ክፍል አንድ ጥንቅራችን ከ 32 ቱ የአውሮፓ ሀያላን የ 16ቱን ቡድኖች ወይም የመጀመሪያ አራት ምድቦች ቅድመ ትንታኔ 


ምድብ ሀ

ቤኔፊካ፣ ባሴል፣ ማንችስተር ዩናይትድ እና ሲኤስኬ ሞስኮ

ጆሴ ሞውሪንሆ ያለምንም ጥርጥር የፈለጉትን አይነት የምድብ ድልድል አግኝተዋል። ዩናይትድ በዚህ ክረምት ሮሜሉ ሉካኩን በፊት መስመር ላይ ዳግም ካመጣው ዝላታን ጋር አጣምሮ ይዟል። የቡድኑን አማካኝ መስመር ለማጠንከርም ማቲች ኦልትራፎርድ ደርሷል።

በሌላ በኩል ኤደርሰን፣ ቪክተር ሊንድሎፍ እና ሌንሰን ሴሜዶን በዚህ ክረምት የሸጠው ቤኔፊካ የውድድሩ ምርጥ የፖርቹጋል ተወካይ ነው። በቤኔፊካ ቤት ብሩኖ ቫሬላ ለኤደርሰን በጣም ጥሩው ተተኪው ሲሆን ፒዚና አሌክስ ግሪማልዶን ማቆየታቸው ደግሞ ለቀጣይ ዋስትና ይሆናቸዋል።

ሲኤስኬ በበኩሉ ከሌሎቹ አንፃር ደካማ እንቅስቃሴ ቢያደርግም ባለፉት ሳምንታት ትልቅ ለውጥ አምጥቷል። የሩሲያው ተወካይ በአዲሱ አሰልጣኙ ኢጎር አክኒፌቭ ስር ለ 11 አመታት በቻምፒዮንስ ሊግ ሁሌም ጎል እየተቆጠረበት የሚወጣበትን ታሪክ ከሰሞኑ መቀየር ችሏል።

ሌላኛው የምድቡ አራተኛ ቡድን ባሴል በበኩሉ ዝነኛውን ተጫዋቹን ማቲያስ ዴልጋዶን ያሰናበተ ሲሆን የምድቡን ግርጌ ይዞ እንደሚያጠናቅቅም ተገምቷል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ማንችስተር ዩናይትድ 2 ቤኔፊካ 3 ሲኤስኬ ሞስኮ 4 ባሴል

ምድብ ለ

ባየር ሙኒክ፣ አንደርሌክት፣ ፒኤስጂ እና ሴልቲክ

በዚህ ምድብ ሁሉም አይኖች በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደረጃ የሚያስቀምጠኝን የኔይማርን ዝውውር ፈፅሜያለሁ ብሎ በተኩራራው ፒኤስጂ ላይ ማረፋቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ዣቪ አሎንሶንና ፊሊፕ ለሀምን የሸኘው ባየር ሙኒክ የአምና ጥንካሬው ላይ መገኘቱ የሚያጠራጥር ነው።

ሴልቲክ በበኩሉ ከአንደርሌክት ሶስተኛ ደረጃን እንደሚነጥቅና በሜዳው ባየርንና ፒኤስጂን ሊያስቸግር እንደሚችል የሚጠበቅ ነው። ነገርግን ምድብ ለ ትልቅ የአቅም አለመመጣጠን ችግር ያለው ምድብ መሆኑ የማያጠራጥር ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ባየር ሙኒክ 2 ፒኤስጂ 3 ሴልቲክ 4 አንደርሌክት

ምድብ ሐ

ቼልሲ፣ ሮማ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ እና ካራባጅ

አትሌቲኮ ባለፉት አራት አመታት በውድድሩ ላይ ለሁለት ጊዜያት ለፍፃሜ የመድረሱን ስኬት ከተመለከትን የስፔኑ ክለብ የምድቡ በላይ ሆኖ እንደሚጨርስ ይገመታል። አትሌቲኮዎች በተወሰነባቸው የዝውውር እገዳ ከሲቪያ የገዙትን ቪቲሎን ጭምር በውሰት ለመስጠት ቢገደዱም ግሪዝማን በክለቡ መቆየቱ አንድ ጥሩ ነገር ነው።

ቼልሲ በበኩሉ ከበርንሌይ ጋር በነበረው ጨዋታ ከቅርፅ ውጪ ሆኖ ቢታይም በጥብቅ መከላከል ቶትነሀምን 2-1 በመርታት ማንሰራራቱን ያሳየ ቢሆንም ኮንቴ ከዚህ ቀደም በጁቬንቱስ በ 2012/13 ቡድናቸው ከሩብ ፍፃሜው ማለፍ ሲሳነው በቀጣዩ አመት ምድቡን መሸጋገር በራሱ አቅቶት እንደነበር አይረሳም።

ሮማ በበኩሉ በአዲሱ የስፖርት ዳይሬክተሩ ሞኑቺ አማካኝነት መሀመድ ሳላ፣ አንቶኒ ሩዲገርን የመሰሉ ኮከቦችን ሲሸጥ መተኪያ የሌለውን ፍራንሲስኮ ቶቲን በጡረታ አጥቷል። ነገርግን በተቃራኒው 10 ተጫዋቾችን መቀላቀሉ ለሶስተኛነት እንኳን እንዲገመት ያደርገዋል።

ካራባጅ በበኩሉ አዘርባጃንን በምድቡ የወከለ የመጀመሪያው ቡድን ሲሆን አሰልጣኙ ጉርባን ጉርባኖቭ ከ 2008 አንስቶ በክለቡ አሰልጣኝነት የቆዩና የደቡብ አፍሪካውን ዲኖ ድሎቩን ቀዳሚ ማረፊያ በማድረግ በሶስት አጥቂ መጫወትን ይመርጣሉ።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት  :  1 አትሌቲኮ ማድሪድ፣ 2 ቼልሲ 3 ሮማ 4 ካራባጅ

ምድብ መ

ጁቬንቱስ፣ ኦሎምፒያኮስ፣ ባርሴሎና፣ ስፖርቲንግ ሊዝበን

ባሳለፍነው አመት በሩብ ፍፃሜው ባርሴሎናን ያሰናበተው ጁቬንቱስ ከስፔኑ ክለብ ዳግም የሚፋጠጥበት ከባድ ምድብ ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች በዚህ ክረምት ዋነኛ ተጫዋቾቻቸው የሆኑት ሊኦናርዶ ቦኑቺ ሳይጠበቅ ሚላንን ሲቀላቀል ኔይማር በበኩሉ ኒውካምፕን ለቆ ወደ ፓሪስ አምርቷል።

ጁቬ በጣሊያን የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ከላዚዮ ጋር በነበረው ትንቅንቅ በመከላከል ላይ ምን ያህል መድከሙ የታየ ቢሆንም የቱሪኑ ክለብ ምርጥ ስብስብ ያለውና ፌደሪኮ በርናንዲሽን በ 35.7  ሚሊዮን ፓውንድ ከፊዮረንቲና በማስፈረም ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በሌላ በኩል በባርሴሎና ቤት ማርኮ ቬራቲ አለመፈረሙና በምትኩ የቀድሞው የስፐርስ አማካኝ መምጣቱ በባርሴሎና ደጋፊዎች ዘንድ ሀዘን ቢፈጥርም የካታላኑ ክለብ ስብስቡን ለማጠናከር ፊሊፔ ኩቲንሆንና ኦስማን ዴምቤሌን ለማስፈረም እየተጋ ይገኛል።

በአዲሱ አሰልጣኙ ቤስኒክ ሀሲ ራሱን እያደሰ የሚገኘውና በዝውውር መስኮቱ 20 ሚሊዮን ፓውንድ ያወጣው ኦሎምፒያኮስ በበኩሉ ምድቡን በሶስተኛነት እንደሚያጠናቅቅ ግምት ያገኘ ሲሆን አማካኙን ዊሊያም ካርቫልሆን የሸጠው ስፖርቲንግ ደግሞ ከሁሉም ያነሰ ግምት ተሰጥቶታል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት  :  1 ጁቬንቱስ 2 ባርሴሎና 3 ኦሎምፒያኮስ 4 ስፖርቲንግ

ምድብ ሠ

ስፖርታክ ሞስኮ፣ ሊቨርፑል፣ ሲቪላ እና ማሪቦር

በዚህ ተመጣጣኝ ቡድኖችን በያዘው ምድብ ሊቨርፑል ባለፉት ሶስት አመታት ሶስት የተለያዩ አሰልጣኞች ከቀያየረው ሲቪላ ቀድሞ ምድቡን ከላይ ሆኖ እንደሚያጠናቅቅ ትልቅ ግምት አግኝቷል።

በሌላ በኩል ግን ኤድዋርዶ ቤሪዞ የሚመራው የስፔኑ ክለብ ቪቶሎን ለአትሌቲኮ ሸጦ በምትኩ ኤቨር ባኔጋ፣ ጂሰስ ናቫስ እና ኖሊቶን ማስፈረሙ ከፊት መስመር ላይ የሚያስፈራውን ነገርግን የኋላ መስመሩ የሳሳውን የየርገን ክሎፕ ስብስብ ለመፈተን መጠነኛ አቅም እንደሚፈጥርለት መጠርጠር ይገባል።

የሩሲያው ስፖርታክ በበኩሉ ባሳለፍነው አመት ከ 2001 በኋላ የመጀመሪያ የሊግ ድሉን ከአስደናቂ ብቃት ጋር ቢያሳይም ዘንድሮ 11ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ እና የአንቶኒዮ ኮንቴ ምክትል የነበሩት የክለቡ አለቃ ማሲሞ ካሬራ ቡድናቸው እያሳየ ባለው ደካማ አቋም የስንብት እጣ ሊደርሳቸው የሚችልበት እድል ሊኖር የሚችል ሲሆን የቡድኑ ሆላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ኪዊንስ ፕሮምስ ግን የቡድኑ ያልተነገረለት ከባድ የጥቃት ሀይል ነው።

በመጨረሻም የምድቡ አራተኛው ተፋላሚ ማሪቦር እስካሁን በታሪኩ ካደረገው 12 የቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ አንድ ብቻ ያሸነፈ ደካማ ስብስብ ሲሆን የአጥቂ አማካኙን ዴር ቭርስኪን ማጣቱ ሲታከልበት በምድቡ ከባድ ፈተና እንደሚጥቀው የሚታመን ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሊቨርፑል 2 ሲቪያ 3 ስፖርታክ ሞስኮ 4 ማሪቦር

ምድብ ረ

ሻክታር ዶኔስክ፣ ናፖሊ፣ ማንችስተር ሲቲ እና ፌይኖርድ

በክረምት የዝውውር መስኮት ከ 220 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ ዋጋ ላወጣው የፔፕ ጋርዲዮላ ስብስብ ምንም አይነት ምህረት አይኖርም። ከዚህ ጋር በተያያዘም የስፔናዊው አለቃ ስብስብ ምድቡን ዘና ብሎ ከላይ ሆኖ የመጨረስ ግዴታ ያለበት ሲሆን ምድቡ አስደናቂውን የማውሪዚዮ ሳሪን ስብስብ ናፖሊ መያዙ እና ሲቲ አሁንም ያለበት የኋላ መስመር መሳሳት በምድቡ የበላይ ሆኖ ለማጠናቀቅ ፈተና ሊጠብቀው እንደሚችል ይነግረናል።

ድሬስ ሜርትንስ፣ ጆሴ ካሌጆን፣ ሎሬንዞ ኢንሲግን፣ አርካዲሁዝ ሚሊክ እና ማርክ ሀምሲክን የያዘውና ከየትኛውም ቦታ ጎል ማስቆጠር የሚችለው ናፖሊ እውነትም አስፈሪ ነው። በሌላ በኩል አምና የዩክሬን ሊግን ክብር በሰፊ የነጥብ ብልጫ የወሰደውና በቅርብ ጊዜ አሌክስ ቴክሴራ እና ዱጋላስ ኮስታ አይነት ኮከቦቹን ያጣው ሻክታር ብዙም ተገማችነት አላገኘም።

በመጨረሻ ደግሞ ከ 18 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በቫን ብራንክሆረስት እየተመራ የሆላንድ ሊግን ያነሳው ፌይኖርድ ዲርክ ኳይትን በጡረታ፣ ትሬንስ ኮንጎሉን እና ሪክ ካርስዱርብ የተሰኙ ወሳኝ ተጫዋቾቹን ደግሞ በሽያጭ ማጣቱ የቡድኑን የምድብ ተፎካካሪነት ይበልጥ እንደሚያወርድበት ይጠበቃል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ማንችስተር ሲቲ 2 ናፖሊ 3 ሻክታር ዶኔስክ 4 ፌይኖርድ

ምድብ ሰ

ሞናኮ፣ ቤሽኪሽታሽ፣ ፖርቶ እና ሊፕዚግ

ከሁሉም ምድቦች በጣም ተቀራራቢ ቡድኖች የተሰባሰቡበት እና ሁሉም እኩል የማለፍ እድል ያለው ፍትሀዊ ምድብ የተባለለትን ምድብ ሞናኮ በርናንዶ ሲልቫ፣ ቤንጃሚን ሜንዲ እና ቲሞ ባካዮኮ የመሳሰሉ ኮከቦቹን ቢያጣም በቀዳሚነት እንደሚያጠናቅቀው ይገመታል።

የፖርቹጋሉ ተወካይ ፖርቶ በበኩሉ አንድሬ ሲልቫን ለሚላን አሳልፎ ቢሰጥም በቲኪኖ ሶአሬዝ ጠንክሮ እንደሚመለስና በአዲሱ አሰልጣኙ ሰርጂዮ ኮንሲካኦ እየተመራ ምድቡን በማለፍ በስኬት እንደሚያጠናቅቅ ሲጠበቅ የውድድሩ አዲስ ተካፋይ የጀርመኑ ሊፕዚግ በበኩሉ የውድድሩ ልምድ አልባነቱ ምድቡ እንዲከብደው ሊያደርግ እንደሚችል ይታሰባል።

በመጨረሻም የክረምት የዝውውር መስኮት ቀንደኛ ተሳታፊ የነበረው ቤሽኪሽታሽ በበኩሉ ፔፔ፣ ጀርሜን ሌንስ እና ጋሪ ሜድል የመሰሉ ተጫዋቾችን ማግኘቱ ተፎካካሪነቱን እንደሚጨምረው ቢጠበቅም የምድቡ ዝቅተኛ ተገማች ነው።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሞናኮ 2 ፖርቶ 3 አርቢ ሊፕዚግ 4 ቤሽኪስታሽ

ምድብ ሸ

ሪያል ማድሪድ፣ ቶትነሀም፣ ቦሩሲያ ዶርትሙንድ እና አፖል ኒኮሲያ

የአምናው ሻምፒዮና ማድሪድ ዘንድሮም ቀዳሚ ተገማች ሲሆን ከ 1974-76 የባየር ሙኒክ ገድል በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የበርናባው ስብስብ ሶስተኛ ተከታታይ የቻምፒዮንስ ሊግ ድሉን እንደሚያስመዘግብ ተጠብቋል።

የስፔኑ ክለብ ትልልቅ ኮከቦቹን በቡድኑ ማቆየት ችሎና ማቲኦ ኮቫቺች፣ ማርኮ አሳንሲዮስ እና ዳኒ ሴባሎስን በመሰሉ ወጣቶች ይበልጥ ገዝፎ የውድድሩን ምድብ ድልድል መጀመር ሲጠብቅ ኦስማን ዴምቤሌን ለባርሴሎና አሳልፎ የሰጠው ዶርትሙንድ በፒተር ቦዝ አሰልጣኝነት ስር ፒዬር ኤምሪክ ኦቦምያንግን በቡድኑ ማቆየት ችሎ እና ጁሊያን ዊግል የመሰለ ኮከቡ ዳግም ብቁ ሆኖለት ይህን የምድብ ድልድሉን ደረጃ ሁለት የሞት ምድብ ከማድሪድ በመቀጠል በሁለተኛነት ሾልኮ እንደሚያልፈው ተጠብቋል።

የምድቡ ሌላኛው ተወካይ ቶትነሀም በበኩሉ በምድቡ ያገኘው ግምት ከስፔንና ጀርመን አቻዎቹ ያነሰ ሲሆን የምድብ እንቅፋቱን በጣጥሶ ለማለፍም በቀጣይ አመት ወደ አዲሱ ስታዲየሙ እስኪዘዋወር ድረስ ዘንድሮ በጊዜያዊነት በሚጠቀምበት ዌብሌይ ያለበትን መጥፎ ገድ ማስወገድ እንዳለበት እየተነገረለት ይገኛል።

ባሳለፍነው የውድድር ዘመን ኮከብ ጎል አስቆጣሪውን ፒሮስ ሶትሪዩን ያጣው አፖል በበኩሉ የምድቡን ግርጌ ታኮ እንደሚቀመጥ ተገምቷል።

የምድቡ አጨራረስ ደረጃ ግምት : 1 ሪያል ማድሪድ 2 ቦሩሲያ ዶርትሙንድ 3 ቶትነሀም 4 አፖል

አርሰን ቬንገር / የፈረንሳዊው አለቃ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ቃል   

via አርሰን ቬንገር / የፈረንሳዊው አለቃ ሳምንታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሙሉ ቃል    — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የአርሰናሉ አለቃ አርሰን ዌንገር ቡድናቸው በፕሪሚየር ሊጉ መክፈቻ አርብ ምሽት ከሌስተር ሲቲ ጋር ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድመው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

☞ ስለ ቡድኑ የጉዳት ዜና 

” ብዙ እርግጠኛ ያልሆንባቸው ተጫዋቾች አሉ በተለይም ከቼልሲ ጋር ያልተጫወቱ ተጫዋቾች እንደ ኦዚል ፣ ሜርቲሳከር  ፣ ራምሴ የመሳሰሉ ተጫዋቾች ”

” እንዲሁም የተመለሱ ተጫዋቾች አሉን ነገር ግን ሳንቼዝ በሆድ ቁርጠት ምክንያት ከቡድኑ ውጪ ነው ”

☞ በአዲሱ የውድድር ዓመት ምን እንጠብቅ 

” ዘንድሮ የተሻለ መስራት አለብን ፡፡ እቅድህን ማስቀመጥ ከባድ ነው ስድስት  ወይም ሰባት የሚሆኑ አሰልጣኞችን ኢንተርቪው ብታደርግ ሁሉም ዋንጫውን ማንሳት እንደሚፈልጉ ነው የሚነግሩህ :: ሌላው ቡድን ምን ያህል እንደጠነከሩ አላውቅም እኛ ስለ ራሳችን ነው ትኩረት ማድረግ ያለብን ”

☞ ፒኤስጂ አሁንም ሳንቼዝን ይፈልጋል

” በጣም ቆይቷል ከናስር ጋር አውርቼ አላውቅም ፡፡ ጋዜጦች ላይ እንዳነበብኩት አሁን ወደ ምባፔ ፊታቸውን አዙረዋል ”

☞ ስለ ኦክስሌድ ቻበርሊን 

” በጉዳት የታጀበ ጥሩም እንዲሁም መጥፎ የእግርኳስ ህይወት አሳልፏል ፡፡ ይመስለኛል ይሄ ነገር ብቃቱን እንዳያሳይ አድርጎታል ፡፡ ከባለፈው የውድድር ዓመት ጀምሮ ደግሞ ያለውን አቅም እያሳየ ይገኛል ለወደፊቱ ጥሩ ተጫዋች የመሆን አቅም አለው ”

☞ ስለ ኦስፒና

” እሱን እንዲቆይ ማሳመን ቀላል አልነበረም ፡፡ አሁንም በሩ ለፉክክር ( ከቼክ ጋር ) ክፍት ነው ”

☞ አሌክሲስን ሽጡልን የሚል ጥያቄ ቀረቦሎታል ? 

” ይሄንን መናገር አልችልም ለሁሉም ለምንም አይነት ጥያቄ በራችን ዝግ ነው ”

ኔይማር የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎናን ሊከስ ነው — ኢትዮአዲስ ስፖርት

​ የአለም ሪከርድ በሆነ ዋጋ ታላቁን ባርሴሎና ለቆ ወደፈረንሳዩ ክለብ ፔዤ የተዘዋወረው ነይማር ጁኒየር የቀድሞ ክለቡን በፊፋ ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተዘገበ፡፡

via ኔይማር የቀድሞ ክለቡ ባርሴሎናን ሊከስ ነው — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የአለም ሪከርድ በሆነ ዋጋ ታላቁን ባርሴሎና ለቆ ወደፈረንሳዩ ክለብ ፔዤ የተዘዋወረው ነይማር ጁኒየር የቀድሞ ክለቡን በፊፋ ለመክሰስ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተዘገበ፡፡

እንደግሎቦስፖርት ዘገባ ከሆነ ነይማር የካታላኑን ክለብ ለመክሰስ የወሰነው ባለፈው አመት ውሉን ባደሰበት ወቅት “ሊከፈለኝ የሚገባ የ 23 ሚልየን ፓውንድ የጉርሻ ክፍያ አልተከፈለኝም ” በሚል ነው፡፡

እጅግ ተወዳጅ ከነበረበት የኑካምፕ ቤት ወደፓሪስ ያቀናው ነይማር ወኪሉ ከሆኑት አባቱ ጋር በመሆን ለክስ እየተዘጋጁ መሆኑ መሰማቱ በክህደት እያብጠለጠሉት ለሚገኙት የብሉ ግራናዎቹ ደጋፊዎች ይበልጥ ጥላቻን የሚፈጥር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ባርሴሎና በበኩሉ በቃል አቀባዩ ጆሴፍ ቪቬስ አማካኝነት ገንዘቡን እንደማይከፍሉና ለዚህም በቂ ምክንያት እንዳላቸው አሳውቀዋል፡፡

እንደቃል አቀባዩ ገለፃ ” የጉርሻ ገንዘቡን የማንከፍልበት ሶስት በቂ ምክንያቶች አሉን፡፡ የመጀመሪያው ከ ጁላይ 31 በፊት ከየትኛውም ክለብ ጋር ድርድር እንዳያደርግ የተደረሰውን ስምምነት መጣሱ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በስምምነታችን መሰረት የኮንትራት ውሉን ለማጠናቀቅ መወሰኑን በይፋ ለህዝብ ማሳወቅ ነበረበት፡፡ የመጨረሻውና ሶስተኛው ደግሞ ክፍያውን ለመፈፀም የወሰነው ሴፕቴምበር 1 ላይ ነበር፡፡(ከአንድ ወር በኋላ) ይህም ተጫዋቹ ከኛ ጋር መቆየቱን እርግጠኛ ለመሆን ነው፡፡እነዚህ ሶስት ስምምነቶች በመጣሳቸው ለተጫዋቹ የምንከፍለው ምንም አይነት ገንዘብ አይኖርም” ብለዋል፡፡.

ከሳምንት በፊት በ198 ሚልዮን ፓውንድ የዝውውር ዋጋ ወደፈረንሳይ ያቀናው ኔይማር እሰካሁን ለአዲሱ ክለቡ እንዳልተጫወተ ይታወቃል፡፡

“ማንችስተር ዩናይትድ በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ አይደለም” ጆሴ ሞውሪንሆ

via “ማንችስተር ዩናይትድ በባርሴሎና እና ሪያል ማድሪድ ደረጃ ላይ የሚገኝ ክለብ አይደለም” – ጆሴ ሞውሪንሆ — ኢትዮአዲስ ስፖርት

Continue Reading

የቼልሲ ተጫዋቾች በኩንጉፉ የታገዘ አስቸጋሪ ልምምድ

via ዝግጅት/ የቼልሲ ተጫዋቾች በኩንጉፉ የታገዘ አስቸጋሪ ልምምድ ሰሩ — ኢትዮአዲስ ስፖርት

የቼልሲ ተጫዋቾች የቅድመ ውድድር ዘመን ዝግጅት ጉዟቸውን በዚህ ሳምንትም ቀጥለው በሻውሊን መነኩሴ እገዛ ከዚህ ቀደም በእግርኳስ ላይ ያልተለመደ የልምምድ ጊዜ አሳልፈዋል።ሰማያዊዎቹ በአሁኑ ጊዜ የእሲያ ጉዟቸው አንዱ አካል በሆነው እና ከአርሰናልና ባየር ሙኒክ ጋር በተጫወቱበት ሲንጋፖር ይገኛሉ። በእቅዳቸው መሰረት ከባየር ሙኒክ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ውጤት የተሸነፉት ቼልሲዎች በኩንጉፉ ማርሻልአርት ባለሙያው የቡድሃ መነኩሴ አለማማጅነት በተለይም ለተከላካዩ ጋሪ ካሂል ከባድ የሆነ ልምምድ ሰርተዋል።

Gary Cahill's face was a picture of concentration as he attempted a balancing exercise

ጋሪ ካሂል “የፈረስ አቋቋም” የሚባለው ልምምድ በእጅጉ ያስቸገረው ይመስላል

Centre back Cahill was watched over by goalkeeper Willy Caballero and a Shaolin monk

ቼልሲዎች አብዛኛውን የክረምቱን ልምምዳቸውን የሚያሳልፉበት ሲንጋፖር ቡድሂዝም በሰፊው ተከታይ ያለው እምነት ነው።

የመኃል ተከላካዩ እንግሊዛዊው ጋሪ ካሂል የማርሻል አርቱ እንቅስቃሴ በሆነው እና ሁለት ጡቦችን በሁለት እጆች እንዲሁም በራስ ቅል ላይ ደግሞ በውሃ የተሞላ ክፍት ሳህን አድርጎ “ሆርስ ስታንድ” የተሰኘውን አቋቋም ለመስራት ሲቸገር ታይቷል።

ካሂል እንቅስቃሴው ፈተና ሆኖበታል

ይህ ብቻም ሳይሆን ተከላካዩ በጨርቅ የታሰሩ ጡቦችን በእንጨት ላይ በመጠምጠም የእጅ ጥንካሬን ለመስራት የሚደረገውን ልምምድ ለማከናወን በእጅጉ የተቸገረ ተጫዋች ሆኗል።

ጋሪ ካሂል የእጅ ጥንካሬ ስራው በእጅጉ አቸግሮታል

ይህን ልምምድ ቲቧ ኮርትዋ፣ ዊሊ ካባሌሮና ማርኮስ አሎንሶም ሰርተውታል።

የሰማያዊዎቹ ቁጥር 1 ግብ ጠባቂ የሆነው ኮርትዋ በኩንጉፉ እንቅስቃሴ መሰረታዊ የሆነውን በጣት የመቆም አቋቋምን ለመስራት ያደረገው ሙከራም በቡድን አጋሮቹ ዘንድ ፈገግተን ጭሯል። በአንፃራዊነት የተሰጡትን የኩንጉፉ ልምምዶች በተገቢው በመስራት ተወዳዳሪ ያልነበረው ስፔናዊው ተከላካይ አሎንሶ ነበር።

የቼልሲ ተጭዋቾች “የፈረስ አቋቋምን” እንዲህ ሰርተዋል

 

ህመም/ አሌክሲ ሳንቼዝ “ህመም” ላይ ነው

 

via ህመም/ አሌክሲ ሳንቼዝ “ህመም” ላይ ነው — ኢትዮአዲስ ስፖርት

በአርሰናል ያለው ቆይታ እርግጥ ያልሆነው አሌክሲ ሳንቼዝ “ህመም” የሚል መግለጫ ያለው ፎቶግራፉን በግል ኢንስታግራም ገፁ ላይ ለጥፏል።

ይህ የማህበራዊ ሚዲያው አዲስ መረጃ የወጣው ደግሞ አርሰን ቬንገር ተጫዋቹ በመጪው እሁድ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደሚመመስ በገለፁ የ24 ስዓታት ጊዜ በኋላ መሆኑ ነው።

አርሰናል በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ የሳምንቱ መጨረሻ ቀናት የኤመራትስ ዋንጫ ጨዋታዎችን ያደረጋል። ነገር ግን ከኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር በኋላ የተራዘመ የክረምት የእረፍት ጊዜ የተሰጠው ቺሊያዊው ተጫዋች በዚህ ውድድር ላይ ይሰለፋል ተብሎ አይጠበቅም።

ምንም እንኳ ሳንቼዝ ኤመራትስን ለቆ እንደሚሄድ ዘገባዎች እያማለከቱ ቢገኙም፣ ቬንገር ግን ሐሙስ ዕለት የ28 ዓመቱ አጥቂ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ወደልምምድ እንደሚመለስ ገልፀዋል።

“አሌክሲስ እና ሙስታፊ የመጀመሪያውን የልምምድ ጊዜያቸውን ከሲቪያ ጋር ጨዋታችንን [በኤመራትስ ዋንጫ] በምናደርግበት ቀን፣ እሁድ ይጀምራሉ።” ሲሉ ቬንገር ስለአርሰናል ተጫዋቾች በተናገሩበት መግለጫ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ የአሌክሲ ሳንቼዝ ወቅታዊ የኢንስታጋርም መልዕክት እንደሚያመለክተው ከሆነ ግን የቀድሞው የባርሴሎና አጥቂ የአርሰናል የተጫዋቾች ስብስብን በተባለው ቀን መቀላቀል መቻሉ አጠራጣሪ ነው።

በማህበራዊ ሚዲያው ላይ በለጠፈው ምስል ከውሻው ጋር በመሆን እና አንገቱ ላይ ጥቁር ስካርፍ በማስር ድብት ያለው የሚመስለው ሳንቼዝ “ህመም” ከሚል ገለፃ ጋር የመድሃኒት ገለፃ ያለው ኢሞጂም አብሮ ከፅሁፉ ጋር አስፍሯል።
ሳንቼዝ በዚህ ክረምት ስሙ ከማንችስተር ሲቲ እና ፒኤስጂ ዝውውር ጋር በሰፊው የተቆራኘ ቢሆንም ቬንገር ግን ክለቡ የፊት ተጫዋቹን የመሸጥ አቋም እንደሌለው ገልፀዋል።

በለንደኑ የ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ አትሌቶች ታወቁ፣ ቀነኒሳ ” ብቁ አይደለሁም”

 

TIRUNESH-DIBABA-interview-header.jpg

በሎንደን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ኢትዮጵያን የሚወከሉ አትሌቶችን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ይፋ አደረገ። ተምዘገዛጊዋ አልማዝ አያና በአስርና አምስት ሺህ ርቀት ትወዳደራለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሻለቃ ሃይሌ ገብረስላሴን መሪ ካደረገ በሁዋላ በወጣቶች እያሳየ ያለው ውጤት፣ የአጨራረስ ብቃትና ብልጠት የቀድሞውን ጊዜ አትሌቶች ያስታወሰ እየሆነ ነው። ተፎካካሪያቸው  የኬንያ አትሌቶች ላይ የያዙት ብልጫ በሎንዶን የሚደረገውን ውድድር ከወዲሁ እልህ የተሞላው እንደሚያደርግ ይገመታል። መልካም እድል !!

በ800 ሜትር ወንዶች

1 መሃመድ አማን
2 ማሙሽ ሌንጮ

በ800 ሜትር ሴቶች

1 ሀብታም አለሙ
2 ኮሬ ቶላ
3 ማህሌት ሙሉጌታ

በ1500 ሜትር ሴቶች

1 ገንዘቤ ዲባባ
2 ጉዳፋይ ጸጋዬ
3 በሱ ሳዶ

በ1500 ሜትር ወንዶች

1 አማን ወጤ
2 ሳሙኤል ብርሃኑ
3 ተሬሳ ቶሎሳ

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ሴቶች

1 ሶፊያ አሰፋ
2 እቴነሽ ዲሮ
3 ብርቱካን ፈንቴ

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ወንዶች

1 ጌትነት ዋሴ
2 ተስፋዬ ሰቦቃ
3 ተስፋዬ ዲባባ

በ5 ሺህ ሜትር ሴቶች

1 አልማዝ አያና
2 ገንዘቤ ዲባባ
3 ሰንበሬ ተፈሪ
4 ለተሰንበት ግደይ

በ5 ሺህ ሜትር ወንዶች

1 ሙክታር እድሪስ
2 ሰለሞን ባረጋ
3 ዮሚፍ ቀጀልቻ
4 ሀጎስ ገብረህይወት

በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች

1 ጥሩነሽ ዲባባ
2 አልማዝ አያና
3 ዲራ ዳዲ

በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች

1 አባዲ ሀዲስ
2 ጀማል ይመር
3 አንዱአምላክ በልሁ

በወንዶች ማራቶን

1 ታምራተ ሞላ
2 ጸጋዬ መኮንን
3 የማነ ጸጋዬ

በማራቶን ሴቶች

ብርሃኔ ዲባባ
ሹሬ ደምሴ
አሰለፈች መርጊያ
ማሬ ዲባባ

በእርምጃ ሴቶች

የኋላሸት በለጠ
አያልነሽ ደጀኔ

በዚህ ቡድን ውስጥ ጥሩነሽ ዲባባ፣ አልማዝ አያናና ገንዘቤ ዲባባ ተካተዋል።  አትሌት ቀነኒሳ አሁን ያለኝ ብቃት በለንደን ማሸነፍ የሚያስችለኝ አይደለም በማለቱና ከፌዴሬሽኑ ጋረ በመስማማቱ ከቡድኑ ውጭ ሆኗል።

ዜናው የፋና ብሮድካስቲንግ ነው ፎቶ ሪፖርተር

“ከአለማችን ግዙፍ ክለብ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ የማይቀበለው ማን ነው?” ሉካኩ 

via “ከአለማችን ግዙፍ ክለብ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ የማይቀበለው ማን ነው?” – ሮሜሉ ሉካኩ  — ኢትዮአዲስ ስፖርት

 

ሮሜሉ ሉካኩ ማንችስተር ዩናይትድን ‘የአለም ግዙፉ ክለብ’ ብሎ በመጥቀስ ከኦልትራፎርዱ ክለብ የቀረበለትን የዝውውር ጥያቄ ወዲያው መቀበሉንና ጥያቄውን በድጋሚ ለማጤን አለመፈለጉን የሚገልፅ አስተያየት ሰጥቷል።

ዩናይትድ ከቀናት በፊት ከኤቨርተን ጋር በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ከስምምነት ላይ መድረሱን መናገሩ የሚታወስ ሲሆን የስምምነቱ አንድ አካል የሆነው ዋይኒ ሩኒም ከሰአታት በፊት የጉዲሰን ፖርኩ ክለብ ተጫዋች መሆኑ በይፋ ተረጋግጧል።

በሎሳንጀለስ በእረፍት ላይ የሚገኘው ሉካኩ ቢበዛ እስከ ነገ ባሉት ቀጣይ ሰአታት ውስጥ ወደ ኦልትራፎርዱ ክለብ የሚያደርገውን ዝውውር በማጠናቀቅ ለቅድመ ውድድር ዝግጅት አሜሪካ የከተመውን የሞውሪንሆ ስብስብ እንደሚቀላቀል ይጠበቃል።

ቤልጄማዊው ኮከብ ዝውውሩን አስመልክቶ ከኢኤስፒኤን ጋር በነበረው ቆይታ “ዩናይትድ የአለማችን ግዙፍ ክለብ ነው። በድጋሚ የፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ለማንሳትና በድጋሚ የአለም የበላይነት ለመቆጣጠር የሚፈልግ ክለብ ነው።

“ይህ እድል ከልጅነቴ ጀምሮ ሳልመው የነበረው ነው። እነሱ እንደፈለጉኝ ሳውቅም ሁለት ጊዜ ማሰብ አላስፈለገኝም ነበር። የዚህ ታሪክ አንድ አካል በመሆኔ በጣሙን ተደስቻለሁ።

“ከአለማችንን ግዙፍ ክለብ የቀረበለትን ጥያቄ የማይቀበለው ማን ነው? በእንግሊዝ ምርጥ ስታዲየም፣ ምርጥ ደጋፊና ምርጥ እድሎች ያሉት ክለብ ነው።” በማለት ዩናይትድን በመቀላቀሉ የተሰማው ደስታ ልዩ መሆኑን ተናግሯል።

ሉካኩ በ 28 ሚሊዮን ፓውንድ ሪከርድ ዋጋ በ 2014 ከቼልሲ ወደ ኤቨርተን ከመጣ ጊዜ ጀምሮ 87 ግቦችን ማስቆጠር የቻለ ሲሆን ለሀገሩ ቤልጄም ደግሞ በ 2010 በ 16 አመቱ መሰለፍ ከጀመረ አንስቶ ለሀገሩ 23 ጎሎችን ከመረብ ላይ አሳርፏል።

የቀድሞው የአንደርሌክት ተጫዋች “አሁን ጊዜው ከዚህ በፊት ከነበረው በተሻለ ጠንክሮ የመስራት ነው። ይህን እንደማሳካና ነገሮች በጥሩ መንገድ እንደሚጓዙ አስባለሁ።” በማለት በዩናይትድ ቤት ለሚጠብቀው ፈተና ጠንክሮ መስራትን እንደ መፍትሔ አስቀምጧል።

ዩናይትድ 18 ቀናት የሚፈጀውን የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን ለማድረግ ወደ አሜሪካ ያቀና ሲሆን በቀጣይም ከሜጀር ሊግ ሶከር ክለቦች ሎስ አንጀለስ ጋላክሲና ሪል ሳልት ሌክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎችን ያደርጋል።

ከዚህ በተጨማሪም በቀጣይነት ከጎረቤቱ ማንችስተር ሲቲ፣ ከስፔኖቹ ሀያላን ክለቦች ባርሴሎናና ሪያል ማድሪድ ጋር የአቋም መፈተሻ ጨዋታዎች እንዲያደርግ ቀጠሮ ተይዞለታል።

MONACO QUOTE ARSENAL HUGE PRICE FOR LEMAR, 80 ሚሊዮን ፓውንድ!!

Villarreal v Monaco: UEFA Champions League

VILLARREAL, SPAIN – AUGUST 17: Thomas Lemar of Monaco looks on during the UEFA Champions League play-off first leg match between Villarreal CF and AS Monaco at El Madrigal on August 17, 2016 in Villarreal, Spain. (Photo by Manuel Queimadelos Alonso/Getty Images)

ቶማስ ለማርን የሚፈልጉት ክለቦች በርካታ ናቸው። በርካታ ብቻ ሳይሆኑ አሉ የሚባሉት ክለቦች ናቸው። አስገራሚው የተጨዋቹ መፈለግ ብቻ ሳይሆን በተቃራኒው ሞናኮ በዝውውር መናጡ ነው። አምስት ሚሊዮን ባልሞላ ግዢ ያገኙት ለማርን ከሚፈልጉት ከለቦች መካከል አርሰናል አንዱ ነው። አርሰናል 32 ሚሊዮን ቢያቀርብም አልሆነም። ተጨዋቹን የትም አትሄድም ሲለው የነበረው ሞናኮ በስተመጨረሻ 80 ሚሊዮን ፓውንድ የግዢ ዋጋ ማሰቀመጡን ከፈረንሳይ የሚወጡ ዜናዎች አብስረዋል።

በሳንቼዝ ጉዳይ ቁርጥ አቋም ላይ ያልደረሱት ዌንገር፣ ቀጣይ ውሳኔያቸው ምን እንደሚሆን ግልጽ አይደለም። ይሁን እንጂ የቺሊው ጋዜጠኛ መልካም ወሬ ይዞ ብቅ ማለቱ ምን አለባትም ለማርን እንደ ላካንቴ ውሎ አደሮ፣ ወይም ዓመት ቆጥሮ ለማስፈረም እቅድ ይያዝ ይሆናል። የቺሊውን ጋዜጠኛ መነሻ በማድርግ በርካታ ሚዲያዎች ሳንቼዝ አርሰናል እንደሚቀጥልና በሚቀጥለው ዓመት በነጻ ዝውውር ወደ አሻው ክለብ የመሄድ እቅድ እንዳለው ጠቁመዋል።

ይህ በንዲህ እንዳለ አሌክሳንደር ላካዜት በክለቡ ሪኮርድ አርሰናልን መቀላቀሉ ታውቋል። በሌላ በኩል ጅሩ ኤቨርተን ወይም ማርሴል የገባል ተብሎ በስፋት ሲወራ አርሰናል ለመቆየት ማሰቡን ማምሻውን የወጡ ዜናዎች ያመለክታሉ። ዘንደሮ እልህ የተጋቡ የሚመስሉት ዊንገር አማካይ ካልቫሮንና የክንፍ ተጨዋቹን ከፖርቶ ለመግዛት ያቀረቡት ገንዝበ ላይ ጨምሩ መባላቸው ተደምጧል። እንደ ወሪዎች ከሆነ ለሁለቱ ተጫዋቾች  ፖርቶ 80 ሚሊዮን ጠይቋል። ለማንኛውም ለማርን አስመልክቶ ይህ ነው የተዘገበው

Arsenal’s pursuit of AS Monaco midfielder Thomas Lemar has been well documented over the course of the last month.

Although no negotiations appear to be ongoing, it’s looking as though the move is set to be ruled out before it even got going. According to a report from the Mirrorthis evening, the Ligue 1 champions are ready to demand a huge fee of £80m.

The Gunners are poised to confirm the signing of Alexandre Lacazette for a fee of around £52m from Lyon in the coming days – a record transfer for the club.

However, this isn’t set to stop them spending in the window and Lemar is certainly appearing to be a target.

While a move looks unlikely if Monaco are to stand firm on their valuation, the Gunners will no doubt be keen to try Leonardo Jardim’s hand and attempt to lure Lemar away from the club.

ዝውውር፡ የዕለተ እሁድ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች — ኢትዮአዲስ ስፖርት

via ዝውውር፡ የዕለተ እሁድ አጫጭር የዝውውር ወሬዎች — ኢትዮአዲስ ስፖርት

 • • አርሰናል ለኪሊያን ምባፔ 125 ሚ.ፓ. በማቅረብ ሪያል ማድሪድ በሞናኮው ወጣት አጥቂ ላይ ያለውን ፍላጎት ለማስተጓጎል ተዘጋጅቷል።
 • • ምባፔ ከግል የትዊተር ገፁ ላይ ሞናኮን ማስወገዱን ተከትሎ በዝውውር ወሬው ላይ ቤንዚን አርከፍክፏል።
 • • አርሰናል በተከላካዩ ኪራን ጊብስ ላይ የ8 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለጠፈ።
 • • የርገን ክሎፕ ዳንኤል ስተሪጅ ሊቨርፑልን እንዳይለቅ ያግዳሉ። ምክኒያቱም እሱን ለመተካት ብዙ ገንዘብ ያስወጣቸዋል።
 • • የርገን ክሎፕ ተከላካዩን በቅድመውድድር ዘመን ለመጠቀም ማሰባቸውን ተከትሎ ሊቨርፑሎች ለጆ ጎሜዝ የሚቀርብላቸውን የዝውውር ጥያቄ ውድቅ የሚያደርጉ ይሆናል።
 • • ዌስት ሃሞች የቀድሞውን የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ የኻቪየር ኸርናንዴዝ የውል ማፍረሻ የሆነውን 13 ሚ.ፓ በመክፈል ተጫዋቹን ለማስፈረም ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ።
 • • ዌስት ሃሞች መረጋጋት ላይ የማይገኘውን የበርንሌይ አጥቂ አንድሬ ግሬይን በ15 ሚ.ፓ ለማዛወር እንቅስቃሴ ለማድረግ ተዘጋጅተዋል።
 • • ኒውካሰሎች የቪላሪያሉን አጥቂ ሰድሪች ባካምቡን ለማስፈርም ቢፈልጉም ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ግን የዝውውር ክብረወሰናቸውን መስበር ይጠበቅባቸዋል።
 • • ሞናኮዎች የማንችስተር ዩናይትድ ዒላማ ለሆነው ፋቢንሆ ከፒኤስጂ የቀረበላቸውን የ40 ሚ.ፓ የዝውውር ጥያቄ ውድቅ አደረጉ።

sunday telegraph

 • • ዲያጎ ኮስታ ቼልሲ ከክለቡ ሊቀንሰው መዘጋጀቱን ተከትሎ በከፍተኛ የክብር ስሜት ወደአትሌቲኮ ማድሪድ ለመመለስ ራሱን አዘጋጅቷል።
 • • የስዊንሲ ዒላማ የሆነው ሮኩ ሜሳ በ11 ሚ.ፓ ከላስ ፓልማስ የሚያደርገውን ዝውውር ለማጠናቀቅ ወደእንግሊዝ ይበራል።
 • • ኸደርስፊልዶች የቼልሲውን አማካኝ ካሲይ ፓልመርን ዳግም በውሰት ሊያስፈርሙ ሲሆን የኢዚ ብራውንንም ዝውውር እያጤኑበት ይገኛሉ።

sunday times

 • •  የአርሰናሉ አማካኝ አሌክስ ኦክስሌድ-ቻምበርሌይን አዲስ የቀረበለትን ኮንትራት ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ባልፈው አመት የፈረመውንና አሁን ከክለቡ ጋር ያለውን ኮንትራት ጠብቆ በሚቀጥለው ክረምት ኤመራትን ለመልቀቅ ፈልጓል።

mail on sunday

 • • አርሰን ቬንገር አሌክሲ ሳንቼዝ በዚህ ክረምት ማንችስተር ሲቲን እንደማይቀላቀል ነገረውታል።
 • • ቼልሲ በሶስት ዓመት ጊዜያት ውስጥ ከ10 ጨዋታ በታች ከተስለፉ ተጫዋቾች ሽያጭ 100 ሚ.ፓ ማግኘት ችሏል።
 • • አትሌቲኮ ማድሪዶች ዲያጎ ኮስታን ከቼልሲ ለማስፈረም የተዘጋጁ ቢሆንም በውሰት አሳልፈው ግን አይሰጡትም። ይህ ማለት ደግሞ የስፔኑ ክለብ ባለበት ተጫዋች የማስፈረም እገዳ ምክኒያት እስከጥር ወር ድረስ እግርኳስ የማይጫወት ይሆናል።
 • • ዎልቭሶች በሊቨርፑልና ቼልሲ የሚፈለገውን የፖርቶውን ኮከብ ሩበን ነቨስን ለማስፈረም እንቅስቃሴ ጀመሩ።
 • • ጆን ቴሪ ለአስቶን ቪላ ለመፈረም ይፋዊ የሆነ ንግግር ጀመረ።
 • • ኒውካሰል የማንችስተር ሲቲ እና እንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ የሆነው ጆ ሃርት ፈላጊ ሆኗል።
 • • በርንሌዮች በኤቨርተን የተፈለገውን ማይክል ኪን ምትክ ይሆናቸው ዘንድ የሼፍልዱን ቶም ሊን እየማተሩ ነው።

the sun on sunday

 • • ሆዜ ሞሪንሆ አልቫሮ ሞራታን ከሪያል ማድሪድ ቢያዛውሩም ባኤቨርተኑን አጥቂ ሮሜሉ ሉካኩ ላይ አሁንም ድረስ ፍላጎት አላቸው።
 • • ዋይኒ ሩኒ የኮንትራት አማራጩን ከፍ በማድረግ በማንችስተር ዩናይትድ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሊቆይ ይችላል።
 • • ኤቨርተን በአስገራሚ ሁኔታ ለአርሰናሉ አጥቂ ኦሊቪየ ዥሩ 20 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ለማቅረብ ተዘጋጅቷል።
 • • አርሰናል ለናፖሊው ኮከብ ጆርጊንሆ ያቀረቡት 15 ሚ.ፓ የዝውውር ዋጋ ውድቅ ተደረገበት።

sunday express

 • • የማንችስተር ሲቲው አለቃ ፔፕ ጋርዲዮላ እንግሊዛዊውን ግብ ጠባቂ፣ ጆ ሃርትን ወደተቀናቃኙ ዩናይትድ እንዲዛወር ፈቃደኛ ሆነ።
 • • የአርሰናሉ ተከላካይ ሄክቶረ ቤለሪን በአውሮፓ ከ21 ዓመት በታች ፍፃሜ ላይ ሁለተኛ በመውጣታቸው ሜዳዩን ያደረገ ብቸኛ ተጫዋች በመሆኑ የማህበራዊ ሚዲያው መሳለቂያ ሆኗል።