Category: Video and Audio

በኦሮሚያ በርካቶች እየታሰሩ ነው

ኢትዮጵያ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የአይን ምስክሮች አስታወቁ። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት እና የኃይማኖት መሪዎች ጭምር መታሰራቸዉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተቃዋሚ የፓለቲካ ፓርቲው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላቱን ጨምሮ በርካቶች በተለያዩ ቦታዎች መታሰራቸውን መረጃ እንደደረሰው ገልጿል፡፡ Advertisements

የወልቂጤ ህዝብ ድምጹን አሰማ – ስሜቱ የኖረ ችግር ክምር የፈጠረው ነው

 በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡት ነዋሪዎች እንደገለጹልን፤ ለዛሬው ሰልፍ ዋና ምክኒያት በከተዋ ይሰራል ተብሎ የመሰረት ድንጋይ የተጣለለት ሆስፒታል ገንዘብ ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሯል የሚል መረጃ ስለደረሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ኢሳያስ ምን እያሉ ነው?

የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፉወርቂ የግብጽና የአረብ ኢሚሬትስ የጦር ሃይሎች ሳዋ ሰፍረዋል መባሉን ያጣጥላሉ። ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ ያደረገው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ዘጋቢ ያሰራጨው ዜና የፈጠራ መሆኑንን ይናገራሉ። አልጀዚራ ሆን ብሎ ከሀወሃት ጋር በመሞዳሞድ ዜናውን አየር ላይ እንዳዋለው ደጋገመው አንስተዋል። የአልጃዚራ አዘጋጅ አዲስ አበባ ሲገባ የተደረገለትን አቀባበልም እንደ አንድ ማሳያ ያሳያሉ፤

የማይቋጨው የአባይ ጣጣ

የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከመጭዉ ረቡዕ ጥር 9/2010 ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት  በግብፅ ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያደርጉ እየተገለፀ ነዉ። በዚህ የጠቅላይ ሚንስትሩ ጉብኝት ኢትዮጵያ እየገነባችዉ ያለዉ ታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋነኛ አጀንዳ ሆኖ እንደሚቀርብ የሚጠበቅ ሲሆን፤ በተለይም  ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ዉድቅ የተደረገዉ። 

ኸርማን ኮሆን – ዛሬ ላይ ሆነው ሲያስቡት እንደሚጸጸቱ ተናገሩ፤ እርቅ ግድ ነው

ኸርማን ኮሆን ተጸጽቻለሁ ይላሉ። ኢህአዴግን ገዢ እንዲሆን ስልጣን ሲያከናንቡት በዚህ ደረጃ አምባ ገነን ይሆናል የሚል ግምት እንዳልነበራቸው በመግለጽ ነው መጸጸታቸውን ዛሬ ላይ ሆነው ከ26 ዓመት በሁዋላ የተናገሩት። ስልታኑንን፣ ፖለቲካውን፣ ኢኮኖሚውን በሙሉ መቆጣጠራቸው ይፋ የተናገሩት ኮሆን አሜሪካ የበኩሏን ልትወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የኢየሩሳሌም ዋና ከተማነት እና የቁጣ ቀን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌምን በእስራኤል ዋና ከተማነት እዉቅና መስጠታቸዉን በማውገዝ በአብዛኛው የዓለም ክፍል ዛሬ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ። ከፍልስጤም አንስቶ ሙስሊሞች በሚያመዝኑባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ አገራት፤ በእስያ እና በአፍሪቃ አደባባይ የወጡ ሰልፈኞች እስራኤልን እና አሜሪካንን ኮንነዋል። ፍልስጤማዉያን ብቻ ሳይሆኑ የአረቡን ዓለም አስቆጥቷል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ከዛሬው የሙስሊሞች የጁማ […]

ሕወሐት ዘመኑ የሚጠይቀዉን አመራር መስጠትና መፍጠር አልቻለም

“…የቻለ ይሩጥ፣ ያልቻለ ያዝግም ፣ የተቸከለ ይነቀል…” የህወሃት የቀድሞ የትግርኛ አባባል “ሕወሀት ዘመኑ የሚጠይቀዉን አመራር መስጠትና መፍጠር አልቻለም” ሲሉ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አቶ የማነ ዘርዓይ ተናገሩ። አቶ የማነ እንደሚሉት ቆራጥነት ካለ መንግስትና ፓርቲ እንዲለያዩ ከምግባባት ላይ መደረስ አለበት። ከዚህም በላይ በምርጫ ለመውደቅና ለመነሳት መስማማት […]

ከኦሮሚያና ከሶማሌ ክልሎች ቃል አቀባዮች ጋር የተደረጉ ቃለ ምልልሶች

ከመስከረም 2/2010 ዓ.ም አንስቶ በተፈጠሩ ግጭቶች በአወዳይ በጅጅጋና እና በጭናቅሰን ከተሞች እና አካባቢዎቻቸው የሁከት የጅምላ ግድያ አና የጅምላ መፈናቀል ሁኔታዎች ታይተዋል፡፡ ይህንን አስመልክቶ ከኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አዲሱ አረጋና ከሶማሌ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እድሪስ እስማኤል ቃለ ምልልሶችን አድርገናል፡፡

ያልታደለ ሕዝብ በግልጽም ይሁን በድብቅ ለሚደገስለት እብደታዊ ተውኔት – “ይቅርታ?” አማራና ኦሮሞ ተናከስ !!

የትግራይን የመሬት መልሶ ማልማት ዓለም አቀፋዊ ሽልማት ተከትሎ ኢቢሲ ያሰራጨው የዜና ማስደገፊያ ካርታ ” ምን እየተደገሰ ነው?” የሚለውን የኖረ ጥያቄ ወለል አድርጎ አሳይቶታል። ተቃውሞውን ተንተርሶ ኢቢሲ ከኢንተርኔት የተወሰደ ካርታ መሆኑንን ጠቁሞ ይቅርታ ቢጠይቅም፣ ይቅርታው ሰሚ ያገኘ አይመስልም። ዓለምነህ ሚዛን የሚደፋ ዘገባ አቅርቧል። ከላይ በምስሉ የሚታየው ከእድሜ ጠገብ ደኖች […]

አሜሪካ ለድርቅ የ137 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ዕርዳታ ይፋ አደረገች

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ምላሽ የሚሆን የ137 ሚሊዮን ዶላር ሰብዓዊ ዕርዳታ ዛሬ ይፋ አደረገች። ይህ አዲስ ድጋፍ አሜሪካ በዘንድሮው 2017 ዓ.ም ብቻ ለኢትዮጵያ የሰጠችውን ዕርዳታ 363 ሚሊየን ዶላር እንደሚያደርሰው፣ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምቀፍ ልማት ኤጀንሲ የምግብ ለሠላም መርኃግብር ተጠባባቂ ዳይሬክተር ለቪኦኤ በተለይ በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል። አሜሪካ ይፋ […]