የቴዲ አፍሮ ‹‹የሙዚቃ ዝግጅቱን ሁሉም የሚፈልገው ስለሆነ የፀጥታ ችግር አይኖርም ›› አማራ ክልል

ለሕዝብ ድምጽ እጅግ ቅርብ የሆነውና በሚያቀርባቸው የጥበብ ፈጠራዎች ብስለት ክብር የተጎናጸፈው ቴዎድሮስ ካሳሁን -ቴዲ አፍሮ የሚያቀርበው የሙዚቃ ድግስ ከጸጥታ ችግር ነጻ እንደሆነ ክልሉ አስታወቀ። ክልሉ እንዳለው ‹‹የሙዚቃ ዝግጅቱን ሁሉም የሚፈልገው ስለሆነ የፀጥታ ችግር አይኖርም፤››

Continue Reading

Advertisements

የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ተራዘመ ፤ ሕዝብ ሁሌም ይሰማል!!

“ዛሬ የምንቃወመውንም ሆነ የምንደግፈውን ጉዳይ መለየት ተስኖናል” ይላል። ይቀጥልና ቴዲ አፍሮ ባህር ዳር ኮንሰርቱን እንዲያቀርብ የተፈቀደው በህዝብ ትግል ግፊትና ጫና ነው። የቴዲ አፍሮን ዘፈኖች ግብር በሚከፍልበት ቴሌቪዥን እንዳይመለከት የተፈረደበት ህዝብ፣ ከቴዲ ጋር ማር እስከጧፍን በባህር ዳር እንዲያስነካው መፈቀዱ የህዝብ ትግል ውጤት ቢሆንም፣ ክልሉ ‘ በአክብሮት’ ፈቃድ መስጠቱ በበጎነት የሚታይ ነው። ኮንሰርቱ ከስያሜው ጀምሮ ታላቅ ዓላማ ያለው በመሆኑም የሚሰጡ አስተያየቶች በማስተዋል የተሞሉ መሆን ይገባቸዋል። አጉራ ዘለል አስተያየትና ዓላማው ግራ የሚያጋባ ተቃውሞ መሰራጨት ከአማራ ክልል ካድሬዎች ማነስ ነው። 

Continue Reading

የቴዲ ተስፋ! በተስፋ ቢሱ የፖለቲካ ጋንግሪን ውስጥ

ይህ ክስተት የሆነ የጥበብ ሰው ሁሌም ተሰፋኛ ነው። ተስፋ የሚያደርገው ደግም በተስፋ ቢሱ የአገራችን የፖለቲካ ጋንግሪን ውስጥ ሆኖ ነው። ቴዲ አፍሮ ስርዓት የበደለው፣ የረገጠው፣ የሚከታተለው፣ ጫና የሚያደርግበት፣ ሁሌም ምክንያት የሚፈልግለት፣ ከዚህም በላይ ቃታቸውን ደጋግመው ቢስቡበት ምኞታቸው የሆነ ምክንያት አልባ “ሰዎች” አጠገብ የሚኖር ቁጥር በማይሰፍራቸው የሚወደድ ሰው ነው።

Continue Reading

C’est la vie (Such is life)

 

“What is promise if not something that’s impossible to live up to? Promise is inchoate and promise is what binds us. Some of us died, some got sick, some got rich, some had bad luck, some of us were fortunate, more than others. But failed promise only truly fails when it leads to lowered expectation.” […]

via C’est la vie (Such is life). — THOUGHT AVENUE: Speak your mind

Continue Reading

“የጉለሌው ሰካራም” በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አጭር ልብ ወለድ ድርሰት

ብዙውን ጊዜ ኢትዮጵያውያን “የመጀመሪያው” ማለት ያበዛሉ በሚል እንታማለን፡፡ እኔ ግን ሃሜቱንም ሆነ ቀልዱን አልቀበለውም፡፡ የመጀመሪያው ማለት የምናበዛውም በምክንያት ነው ብዬ አስባለሁ፡፡ በብዙ ነገሮች ቀዳሚ የሆንን የመጀመሪያ ህዝቦች ነንና፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ እንዲያው በእኛ ላይ ተጋነነ እንጂ በሆነ ነገር ቀድሞ መገኘትና የመጀመሪያው ማለት የማይወድ አገርና ህዝብ ያለ አይመስለኝም፡፡
 የመጀመሪያው ከማለትም አልፈው በሁሉም ነገር “አባት” ነን ማለት የሚወዱት ምዕራባውያንስ ምን ይባሉ? የባዮሎጂ አባት፣ የፊዚክስ አባት፣ የጂኦግራፊ አባት …ኧረ ምን አባት ያልሆኑበት የትምህርት ዓይነት አለ፡፡

Continue Reading

“ዋሸሁ እንዴ?” – ነን ሶቤ – የጥበብ ቶርቸር

ሃጫሉ ትንታግ ሲያወርድ፣ በጥበብ ቶርቸር ሲገርፍ – አባ ዱላን፣ ለማ መገርሳን እና አብይን፣ ሞቱማን እንዲሁም እዛ የታደሙትን ባለስልጣኖች ፊት የቴሌቪዥን መስኮቱ በየተራ ያሳየቸው ነበር። ጌሬርሳውን እንደ መብረቅ ሲያዘንበውና ማጎሪያ ቤቶችን እየጠራ መድረኩ ላይ ሲቁነጠነጥ ሁሉም ባለስልጣኖች ዓይናቸው በአንድ ክፉኛ ስሜት ቀዞ ነበር። ስሜታቸው ስለመነካቱ በማያጠራጥር መልኩ አይናቸው ሲያሳብቅ የልብ ምታቸው ምን ያህል ይደልቅ እንደነበር አንድ ቀን ታሪክ ፊት እነሱው ይመሰከሩት ይሆነ? አቤት የኪነት ሃይል!! አቤት የጥበብ ሚስጢር!! ምናለ ሁሉም ጥበበኞች የህዝብ አፍ ቢሆኑ ? ምንኛ ባማረባቸው !!

Continue Reading

“ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም።” (ቅዱስ ሲኖዶስ)

ከሕጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክስ ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ
አባ ጴጥሮስ፣ የአውስትራልያ ሀገረ ስብከት ጳጳስና፣ የሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ

“ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም ፥ ኃያልም በኃይሉ ብዛት አያመልጥም ።” መዝ 33 ፥ 16 ።

በዓለም ላይ ሰዎች የራሳቸውን ሥልጣን ለማስጠበቅና ዘላለማዊ ለማድረግ ብዙ እንደ ጣሩ ከታሪክ እንረዳለን ። እንደነዚህ ያሉ መሪዎች ሥልጣናቸውን ለማቆየት እጅግ የበዛ ግፍ በሕዝባቸው ላይ ይፈጽማሉ ። ይህን ግፋቸውን የሚፈጽምላቸው የታጠቀ ሠራዊት ያዘጋጃሉ ። ሠራዊቱም ተቀጣሪ ስለሚሆን ያገኘውን ይገድላል ፥ ያሰቃያል ፥ ያስራል ፥ ያሳድዳል ። ግፈኞች ይህን ድርጊታቸውን “ለሀገር አንድነትና ለሕዝብ ደኅንነት ነው” በማለት የመልካም መንግሥት ስም ይቀቡታል ።

ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም press releas

Continue Reading

የእምብርት ዘመን ሲሄድ የቂጥ ዘመን መጣ

‹‹ ምን ዓይነት ዘመን ነው  ዘመነ ዲሪቶ

አባቱን ያዘዋል ልጁ ተጎልቶ ››

እያለ አቀንቅኗል ድምጻዊ ተሾመ ደምሴ ፡፡ ተሾመ ልማዳዊው ህግ ወይም ስርዓት ተጣርሷል የሚል ጭብጥ ለማስተላለፍ የሞከረ ይመስላል ፡፡ ዜማውን በምሳሌያዊ አነጋገር ለውጡ ብንባል

‹‹ዘመነ ግልንቢጥ

ውሻ ወደ ሰርዶ

አህያ ወደ ሊጥ ›› የሚባለውን ብሂል መጥቀሳችን አይቀሬ ነው ፡፡

በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ምን ዓይነት ዘመን መጣ ያሰኘው የሴቶቻችን አፈንጋጭ አለባበስ ነበር ፡፡ ዘንድሮ ዘመነ ግልንቢጥ የተባለው ደግሞ በወንዶች ጉዳይ ሆኗል ፡፡ ለመሆኑ እንዴት ነው አህያ ወደ ሊጥ የሄደው ? የሚለውን ጥያቄ ከመፈተሻችን በፊት ትንሽ ስለቀደመው እናውራ ፡፡

ስለሴቶቹ …

መቼም ዘመኑን ሆን ብሎ የሚያጠና ሰው ቢኖር ስለ እያንዳንዱ ግዜና መጠሪያ ስለሚሆነው ጉዳይ ስያሜ አያጣለትም ፡፡ ለአብነት ያህል በ1997 አካባቢ ሴቶቻችን በታይት ተወረው ነበር ፡፡ ይህን ግዜ ‹‹ የታይት ዘመን ›› ብሎ መጥራት ይቻላል ፡፡ የዛኔ የዘፈን ውድድር አለመፈጠሩ እንጂ ለታይት ለባሾቻችን ‹‹ ቀይ ›› ፣ ‹‹ ቢጫ በቀይ ›› ‹‹ ሙሉ አረንጓዴ ›› እያልን ጥሩ ማነጻጸሪያ መስጠት በተቻለ ነበር ፡፡ ታይት የሰውነት ቅርጽንና ውበትን አጋልጦ የማሳየት ኃይሉ ከፍተኛ ስለነበር ራሳቸውን ‹‹ ለቁምነገር የሸጡ ›› ወጣቶችም ጥቂቶች አልነበሩም ፡፡

አንዳንድ ሴቶች ደግሞ ታይትን ያለ ግልገል ሱሪ በማጥለቅ በየጎዳናው የሚያለከልኩ ወንዶች እንዲበዙ አድርገዋል ፡፡ የነዚህኞቹ ግብ በወንዶች ላይ ‹ ሙድ › ይዞ መዝናናት ይሁን ወይም የግብዣ ማስታወቂያ መስራት በውል የሚታወቅ አልነበረም ፡፡ ለሚነሳባቸው የተጃመለ ትችትም ‹‹ መብታችን ነው ! ›› በማለት የተንዥረገገ ነገር ግን የማይበላ የወይን ፍሬ ነው የሚባልለትን ህገመንግስት ተደግፈው የሚያወሩ ሴቶች ጥቂቶች እንዳልነበሩ እናስታውሳለን ፡፡ ህገመንግስቱ እንኳን የማስልበስን ራሱ የመገንጠልን ካባ በመከናነቡ አያስገርመንም የሚሉ አሽሟጣጮች በበኩላቸው የትራክተር ጎማ የሚያህል መቀመጫ ያላት ሴት በታይት ተወጣጥራ ስትንከባለል እያየን ላለማሳፈር መጣር ከጨዋነት አያስቆጥርም ይሉ ነበር ፡፡ ድርጊቱ የሳቅ ቧንቧን ቷ ! አድርጎ በመክፈቱ በየቦታው አይንና አፍን በመሸፈን የሚንፈቀፈቁ ሰዎች እንዲበራከቱ መንገድ ከፍቷልና ፡፡

ከዚህ ዘመን በኃላ ደግሞ አጭር ቀሚስ የፋሽን መገለጫ ሆኖ መጣ ፡፡ በርግጥ አጭር ቀሚስ ከማለት ይልቅ መሃሉ የተከፈተ ቁምጣ ማለት እውነቱን ቀረብ ያደርገዋል ፡፡ ሴቶቹ ቁጭ ሲሉ ገላቸውን ላለማሳየት ያቺን ምላስ የምታህል ጨርቅ በግድ ሊያረዝሟት ሲታገሉ ማየት ያስቃል ፡፡ ‹ ለምን ለበሱት – ለምን ይጨነቃሉ ? › የሚል ገረሜታ አእምሮን ይወራል ፡፡ የሴቶችን ፍላጎት ጠንቅቀን እናውቃለን የሚሉ ሴት አውሎች ግን በለበሱት ለመጨናነቅ ፣ ለማፈር ፣ የይቅርታ ፊት ለማሳየት መሞከር ሁሉ ድምር ውጤቱ ‹ ሆን ተብሎ የሚተወን የትኩረት መሳቢያ ድራማ  › ነው ባይ ናቸው ፡፡ በርግጥ አጭር ቀሚስ ወዲህ ወዲያ ሲሄዱበት የሚያምር ከሆነ በመቀመጥ ግዜ ገላን ላለማጋለጥ ነጠላ ወይም ሻርብ ነገር እግር ላይ ጣል ማድረግ በተቻለ ፡፡ ይህን የሚያደርጉት ግን ከስንት አንድ ናቸው ፡፡ ስለዚህ የአጭር ቀሚስ አላማ ከፋሽንነትም በላይ የሚሻገር ነው የሚሉ አስተያየት ሰጪዎችን ሀሳብ መናቅ የትም አያደርስም ፡፡  ዘንድሮ ይህ ድርጊት ተገልብጦ በመምጣቱ የጭን መጋለጥ ሴቶችን ‹ አያሰጋም › ፡፡ ሱሪያቸው ግን ከኃላ ሆን ተብሎ ያጠረ በመሆኑ ለምሳሌ ያህል ከታክሲ የሚወርዱ ሴቶች መቀመጫቸውን ላለማሳየት ከላይ የለበሱትን ልብስ እስኪቀደድ ድረስ ወደታች ይጎትቱታል ፡፡ እኛም ልብስ መቀየሪያ ክፍል የገባን ያህል ላለማሳፈር ይሁን ላለመሳቀቅ ፊታችንን እናዞራለን – በጨዋ ደንብ ፡፡ ከወረዱ በኃላ ደግሞ  ‹ ምን ያለበሰቸውን ሱሪ ለመልበስ ትታገላለች ! ›  በማለት እናብጠለጥላታለን – በሀሜት ደንብ ፡፡

ታይትንና አጭር ቀሚስን ተሻግሮ በአደባባይ ብቅ ያለው ሱሪም ቀሚስም አይደለም – እምብርት እንጂ ፡፡ እንኳን ከዘመነ ጭን ወደ ዘመነ እምብርት አሸጋገራችሁ – አልናቸው እህቶቻችንን ፡፡  እምብርትን አጋልጦ ለማሳየት መደበኛ ሱሪም ሆነ ታይት መጠቀም ይቻላል ፤ ከላይ ደግሞ አጭር አላባሽ ፡፡ እድሜያቸው 14 እና 15 ያልሞላቸው ህጻናት ፣ የደረሱ ወጣቶች ፣ ብዙ ልጆች ያፈሩ እናቶች ሳይቀሩ እምብርታቸውን በየአደባባዩ አሰጡት ፡፡ ለብዙ ወንዶች ትርጉሙ ግልጽ አልነበረም ፡፡

ሴቶቹ በደፈናው ‹‹ ፋራ አትሁኑ ! ፋሽን ነው ›› አሉ ፡፡ መነሻው ህንድ ይሁን ሱርማ ፤ ጥቅሙ ሀሴት ያምጣ ግርማ ልብ ያለ ግን አልነበረም ፡፡ ወንዶቹ ‹‹ ከፋሽኑ ጀርባ ምን አለ ? ›› በማለት ጠየቁ ፡፡ ይህ ጥያቄያቸው በተለይ ከውበት ጋ የተያያዘ ነበር ፡፡ ምክንያቱም ወንዶች ጸጉር ፣ አይን ፣ አንገት ፣ ጡት ፣ ዳሌ ፣ ሽንጥና ባት እያሉ ሊያዜሙ ፣ ሃሳባቸውን ሊገልጹ ወይም ሊጽፉ ይችላሉ ፡፡ እስካሁን ግን ‹‹ እምብርትሽ ›› ብሎ ያቀነቀነ ዘፋኝ ወይም የጻፈ ደራሲ ወይም ያደነቀ አፍቃሪ አልተሰማም ፡፡ ታዲያ የእምብርት ፋይዳ ምን ይሆን ? መባሉ ግድ ነው ፡፡ አንዳንድ ሴቶች እምብርታቸው ላይ ጉትቻ እስከማንጠልጠል በመድረሳቸው ወንዶቹ እንደሚከተለው አሾፉ ‹‹ እምብርት ምድር ቤት የሚገኝ ጆሮ ነው  እንዴ ? ›› ወይም ‹‹ ከላይኛው የጆሮ ገጽ የዞረ መሆኑ ነው ? ››

ስለ ወንዶቹ …

እነሆ ዘመኑ ተገልብጦ ሴቶች በወንዶች ድርጊት እያዘኑ አልፎ አልፎም እያስካኩም ይመስላል ፡፡ የሴቶቹ እምብርት ተረት ሆኖ የወንዶቹ ቂጥ ወቅታዊ ማፍጠጫ ጉዳይ ስለሆነ ፡፡ ምናለፋችሁ በከተማችን ‹‹ የሚዝረከረኩ ወንዶች ›› ተበትነዋል ፡፡  ‹ እረ ወንድ ልጅ ሴታ ሴት ሲሆን ያስጠላል ! › የሚሉ ቆነጃጅትና እማወራዎች በዝተዋል ፡፡ ‹ ልጆቻችን ምን እስኪሆኑ ነው የምንጠብቀው ? › በማለት በሴት እድሮችና ማህበሮች ላይ ጉዳዩ የመወያያ አጀንዳ እንዲሆን የጣሩ ሴቶች ሞልተዋል ፡፡ ‹ ግብረ ሶዶማዊያን በዛ እያሉ እግዚኦ የሚሉ የሃይማኖት ተቋማትና ጋዜጠኞች የወንዶችን ልብስ መጣል እንዴት ዝም ብለው ያያሉ ? › የሚሉ ተቆርቋሪ እህቶች ሰሚ ያጡ ይመስላሉ ፡፡

የሀገራችን ሴቶች ወንዶች ቀበቷቸውን እንዲያላሉ በህጋዊ መንገድ የሚጠይቁት በአንድ መንገድ ብቻ ነው  ፤ በምጥ ወቅት ፡፡ በርግጥ  በፍቅር ጨዋታ ወቅት የሚኖረውን ውልቂያ የትኛው ክፍል እንደምንመድብ ሳያስቸግርን አይቀርም ፡፡ ታዲያ ዛሬ በህገወጥ መንገድ ቀበቶ አላልቶ ፤ ሱሪውን ከወገቡ ቁልቁል አርቆ ፤ የውስጥ ሱሪውንና የቂጡን ቀዳዳዎች እያስጎበኘ ላይ ታች በሀገራዊ ኩራት የሚጓዘው ‹ ትንሽ – ትልቅ › አበዛዙ ቀላል አልሆነም ፡፡

ወደው አይስቁ አሁን ይመጣል ፡፡ አንዳንድ የውስጥ ሱሪዎች የተቀደዱና ውሃ ካያቸው ዘመናት ያስቆጠሩ ሊሆኑ ይችላሉ  ፡፡ አንዳንድ የውስጥ ሱሪዎች ደግሞ ገመዳቸው ላልቶ ነው መሰለኝ ወደ ውስጥ የሰመጡ ናቸው ፡፡ በተለያየ ምክንያት የሚጎነበሱ ፋሽነኞች ታዲያ የሚያስጎበኙት የተራቆተ መቀመጫ በንጽህ ወንድ / አፍቃሪ ግብረሶዶም እና እንስት ባልሆነ / ከታየ ለአይን የሚቆረቁር ፣ የመንፈስ ልዕልናና ክብርን ዝቅ የሚያደርግ ነው ፡፡ ምክንያቱም  የአንዳንድ ሰው ቂጥ በጎርፍ የተቆረሰ ደለል ይመስላል … የአንዳንድ ሰው ቂጥ በላብና እድፍ ተቦክቶ ልስን የሚጠብቅ ግድግዳ ይመስላል … የአንዳንድ ሰው ቂጥ ወፍጮ ቤት ከዋለ ፊት ጋር  አንድ ነው ፡፡

አሁን ደግሞ የማይገባዎትን ጥያቄ ይወረውራሉ ፡፡ ፋሽኑ ሱሪው ነው ? የላላው ቀበቶ ነው ? ፓንቱ ነው ? የፓንቱና ሱሪው ደረጃ ሰርቶ መታየቱ ነው ? ወይስ የሰውየው ቂጥ ? ከግርምት ፣ ትዝብትና ሳቅ በኃላ ለመሆኑ ምንድነው ዓላማው ? ወይም ፋሽን ተከታዮቹን ምን ያህል ያስደስታል ? ለማለት ይገደዳሉ ፡፡ አብዛኛው ፋሽን ተከታይ በጆሮ ፣ ጸጉር ፣ ጃኬት ፣ ቲሸርት ፣ ጫማ ወዘተ ላይ ሲታይ እንደቆየው የዘመናዊነት መገለጫ ሳያካብዱ መመልከት እንደሚገባ የሚያስገነዝቡ ናቸው ፡፡ ፋሽን ይመጣል ፋሽን ይሄዳል እንዲሉ … ለምን ይቅርብኝ  ወይም ከማን አንሳለሁ በሚል ድሃ መነሻ የማያምርባቸውን ብቻ ሳይሆን የማያውቁትን ነገር የሚከውኑ ወንዶችም ሴቶችም የሚታዘንላቸው ናቸው ፡፡ እነዚህ ምስኪኖች ከሚሆኑትና ከሚለብሱት ዉጪ ስለ ጉዳዩ  አነሳስና ከጀርባው ስለሚጠረጠረው ጉዳይ ለማሰብ ግዜ የሚወስዱ አይደሉም ፡፡ 

 አነሳሱ  …

ሱሪን ከቂጥ በታች አውርዶ መልበስ የተጀመረው በአሜሪካ እስር ቤቶች ውስጥ ነው ፡፡ Sagging Pants ይሉታል ፡፡ እስረኞች ቀበቷቸውን ራሳቸውን ለመግደልና በሌሎች ላይ ወንጀል መስሪያ መሳሪያ ማድረጋቸው ስለተደረሰበት እንዳይጠቀሙ ታገደ ፡፡ በዚህም ምክንያት ሰፊ ቱታቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው ሱሪያቸው ታች መውረዱ ግድ ሆነ ፡፡

የጀርባው ንባብ  …

ይህ ‹‹ ፋሽን ›› በጥርጣሬ ጨጎጊቶች የተከበበ ነው ፡፡ አንዳንዶች በእስር ቤት ልብስን ዝቅ አድርጎ መልበስን የሚያገናኙት ከግብረ ሶዶማዊነት ተግባር ጋ ነው ፡፡ የወሲብ ግንኑነታቸው መጠቆሚያ ስልት ነው በማለት ፡፡ አንዳንዶች የእስር ቤት አስተሳሰብ መሆኑን በመግለጽ በተለይ ጥቁሮች ‹ አሁንም እስር ላይ ነን › የሚል መልዕክት ያስተላልፉበታል ይላሉ ፡፡ አንዳንድ ጉዳዩን ያጠኑ ምሁራን ደግሞ ‹‹ በአሜሪካ የባርነት ዘመን ነጭ አለቆች የአፍሪካን ጥቁር ወንዶች አስገድደው ይደፍሯቸዋል ፡፡ ተግባሩ ከተፈጸመ በኃላ ተጠቂው ሱሪውን ዝቅ አድርጎ እንዲለብስ ይደረጋል ፡፡ ምክንያቱ ደግሞ አለቃው በቀጣይነትም ግንኙነት መፈጸም ሲፈልግ በቀላሉ እንዲለየው ነው ›› በማለት ቃላችን ርግጠኛ ነው ሲሉ ይደመጣሉ ፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ በ 1990ዎቹ አካባቢ የሂፕ ሆፕ አርቲስቶች ሱሪን አውርዶ መልበስን በማስፋፋት ረገድ ትልቅ ሚና መጫወታቸው ብዙዎችን ያስማማል ፡፡ ምክንያታቸው ደግሞ ባህልና ፋሽንን ከመግለጽ በተጨማሪ የነጻነት ማሳያም እንደሆነ ይጠቆማል ፡፡

በዚህ እሳቤ የኛዎቹ ፋሽን ተከታዮች ምን መልዕክት እያስተላለፉ መሆኑ ግራ ያጋባል ፡፡ በርግጥ በሀገራችን ግብረሰዶማዊነት እየተስፋፋ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ የሱሪው መውረድ ሰምና ወርቅ ፋሽንና ያልተለመደ ወሲባዊ ግንኙነትን እያመላከተ ይሆን ?  ግብረ ሰዶማዊያን ለመግባቢያነት ይረዳቸው ዘንድ ጆሮአቸው ላይ ጌጥ ያደርጋሉ ፤ ሱሪ አውርደው ከሚፏልሉት ወገኖቻችን ገሚሶቹም ጆሮአቸውን ማስዋብ ይወዳሉ ፡፡ ግብረ ሰዶማዊያን  አንድ ጆሮ ላይ ጌጥ ካደረጉ ‹ አልተያዝኩም › ማለት ፈልገው ነው ፤ ሱሪ አውራጆቻችንስ ‹ አልተያዝኩም › ነው ወይስ  ‹ የማውቀው ነገር የለም ›  እያሉ  ነው የሚገኙት ፡፡ ሀገራችን እንደ ሌሎች አፍሪካዊያን ቅኝ ያልተገዛችና የባርነት ቀንበር ያልቀፈደዳት ቢሆንም ከሀገራዊ ባርነት መቼ ተላቀን እያሉበት ይሆን ? ነው አለማቀፉን ምልከታ ያልተረዳ ተራ የፋሽን ጉዳይ ?

ያን ግሩም ሙዚቀኛ ‹ ተቀበል ! › ማለት አሁን ነበር ፡፡

አቦ ተቀበል ! አፈሩ ይቅለልህና

‹ እሺ ልቀበል ! › …

‹‹ ምን ዓይነት ዘመን ነው በል ! ››

‹ ምን አይነት ዘመን ነው › …

‹‹ ምን አይነት ዘመን ነው – ዘመነ ዥንጉርጉር

 በምናገባኝ ቅኝት በኬሬዳሽ መዝሙር

 እንደሰጡት ሆኖ እንዳጣው የሚያድር

 አይገደውም ከቶ

 ‹ አይገደውም ከቶ › …

ለማያውቀው አንቀጽ ውል አጥብቆ ሲያስር

 በእውር ፈረስ ጀርባ ሽምጥ ሲኮረኩር ››

በልልኝ አቦ !!

‹  በእውር ፈረስ ጀርባ ሽምጥ ሲኮረኩር › …

ማስታወሻ፡- ይህ ፅሑፍ በቁም ነገር መፅሔት ቅፅ 12 ቁጥር 159 ላይ የወጣ ነው፡፡ ፅሑፉን በሌላ ሚዲያ ላይ የምትጠቀሙ ከሆነ ምንጩን እንድትጠቅሱ ትለመናላችሁ፡፡

Alemayehu Gebeyehu አሌክሶ ገጽContinue Reading

« አውሮራ » – የጦርነት አረር ፣ የፍቅር ቀለሃ

via-  አሌክሶ ገጽ – ታሪኩ የተገነባው ብዙዎቻችን በምናውቀው እውነት ላይ ነው ። ጠላትህ ጠላቴ ነው ተባብለው የተማማሉ ሁለት ብሄርተኛ ቡድኖች ለረጅም አመታት ታግለው እንደ ሀገር የሚያስበውን ቡድን አሸንፈው ስልጣን ያዙ ።

በስልጣን ማግስት ሀገር የፈለገውን ይበል ብለው መስመር ባለፈ ፍቅር ከነፉ ። እንደ ደራሲ ከበደ ሚካኤል ግጥም ‹ ሁለት አፍ ያለው ወፍ › ሆኑ ። በፍቅር ተጎራረሱ ። ተቃቅፈው በረሩ ፣ አለም ጠበባቸው … ተጣብቀው ዘመሩ ‹ አይበላንዶ  …  › እያሉ ።ተያይዘው ፈከሩ ! ‹ ነፍጠኛ ሰመጠ ፣ ተራራ ተንቀጠቀጠ › በማለት … አብረው ተዛበቱ ‹ ትግል ያጣመረውን ህዝብ አይለየውም › በሚል ስልቂያ … ኪስህ ኪሴ ነው ፤ ሚስትህ ሚስቴ ናት ፤ ግዛትህ ግዛቴ … ምን ያልተባባሉት አለ ?

 ከአይን ያውጣችሁ ያላቸው ግን አልነበረም ።

እየቆየ አይንና ናጫ ሆኑ … በአጎራረስህ እየተጎዳው ነው በሚል አንደኛው አፍ የጫካ ውንድሙን ካደ ። የእህል ምርቱንም ሆነ የሚያጌጥበትን ማእድን ደበቀ ። የብር ኖቶችን ቀየረ ፣ የድንበር ንግድ ግብይት በዶላር እንዲሆን ድንገተኛ ህግ አረቀቀ ። ይህ ተግባር ለሁለተኛው አፍ የማይታመን ክህደት ነበር ። ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ አለ ። ጠፍጥፎ በሰራው ልጅ ተናቀ … ሹካ አያያዝ አስተምሬው ? በኔ ደም ለወንበር በቅቶ እንዴት ክብሬን ያራክሳል በማለት ለጦርነት ተዘጋጀ ።

‹ አውሮራ › ይህን የምናውቀውን ታሪክ ይዞ ነው መዋቅሩን የገነባው ። የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት እንዴት ተጀምሮ እንደምን እንዳለቀ እናውቃለን ፣ ምን እንዳስከተለም የብዙ ወገኖች መረጃ አለን ። የመንግስት ሚዲያዎችን ጨምሮ የድርጅቶቹ ልሳኖች የአውደ ውጊያውን ታሪክና የታሪክ ሰሪ ሰዎችን ህይወት በመዳሰስ አታካች በሆነ መልኩ በተከታታይ አቅርበውልናል ። ታዲያ አውሮራ ምን የተለየ ነገር ሊነግረን ታሪክ ቀመስ ልቦለድ ሆነ ? ቢባል ትክክል ነው ።

ደራሲው ሀብታሙ አለባቸው ግን ብልህ ነው ፣ ገና በጠዋቱ ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ያስተዋወቀንን የታሪክ በከራ እንዴት ሳይሰለች እያጠነጠነ እስከ ምዕራፍ 43 መዝለቅ እንዳለበት በሚገባ ተረድቷል ። ስለተረዳም ሳቢና ተነባቢ አደረገው ።

ይህን ለማከናወን ከረዳው ስልት አንደኛው የትረካውን ኳስ ለመለጋት በመረጠው የመቼት አንግል የተወሰነ ይመስለኛል ። ደራሲው 80 ከመቶ የሚሆነውን ታሪክ የሚያቀብለን ከኤርትራ አንጻር ሆኖ ነው ። በትረካው የአስመራን ውበት ፣ የወታደራዊ ካምፖችን ሚስጢር ፣ የደህንነት ተቋማት ፕሮፓጋንዳ ፣ ሳዋ ስለተባለው የሰው ቄራ ፣ የፕሬዝዳንቱን ጽ/ቤት ከነተግባርና ግዴታቸው እንመለከታለን ። የህዝቡን አበሻዊ ጥላቻ ፣ ፖለቲካዊ ሹክሹክታ እና ስነልቦና እንመረምራለን ። የባለስልጣናቱን በተለይም የፕሬዝዳንቱን እምነት ፣ አስተሳሰብ እና ፍላጎት እንታዘባለን ። በአጠቃላይ ከአስመራ የምናገኘው አዲስ መረጃ ታሪኩ ሰቃይና አጓጊ እንዲሆን ትልቅ ሚና ተጫውቷል ። የታሪኩ ልጊያ ከአስመራ እየተነሳ ወደ ኢትዮጽያ ፣ ጅቡቲና ሌሎች አካባቢዎች ሲያመራ ደግሞ ተዝናኖት ብቻ ሳይሆን አማራጭ እሳቤ ይፈጥርልናል ። በመሆኑም የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት አዲስ ሆኖ እንዲሰማን አድርጓል ።

ሌላም አለ ። ታሪኩን የሚደግፉት የሴራ ቅንብሮች ባለሁለት አፍ ወፎቹ ይፋ በሆነ መልኩ በመድፍ እንዲቆራቆሱ ብቻ አይደለም የሚያደርገው – ወፎቹ በየሰፈራቸው በተዳፈነው ረመጥ እንዲለበለቡም ጭምር እንጂ ።

የአስመራው ወፍ / ኢሳያስ / ክብሩንና ጥቅሙን ለማስጠበቅ መጠነ ሰፊ ፣ የተደራጀና ህቡዕ ተኮር እንቅስቃሴ ያደርጋል ። ኢትዮጽያዊው ወፍ / መለስ / አንድም አናት አናቱን ከሚጠቀጥቁት ወንድም ግንደ ቆርቁሮች በሌላ በኩል ከሩቅ አጎቱ የሚወረወርበትን ሞርታር ለመከላከል መከራውን ሲበላ እንመለከታለን ።

በነገራችን ላይ ከአስመራ ወደ ኢትዮጽያ የሚጋልበው የታሪክ ጅረት ሁለት መቆጣጠሪያ ቤተመንግስቶች አሉት ። የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና የአቶ ሃይላይ ሃለፎም ። በፍትህ ሚ/ሩ አቶ ሃይላይ ቤት አራት የታሪኩ ቁልፍ ሰዎች ይገኛሉ ። ቤተሰቦች ናቸው ። ሳህል በረሃ የተወለደችው ፍልይቲ ፣ ወንድሟ ሰለሞን እና ባለስልጣን እናታቸው አኅበረት ። ሃይላይ በርግጥም ለሰላምና ፍትህ የቆመ ብቸኛ ሚኒስትር ነው ። ከኢትዮጽያ ጋር የሚደረገው ጦርነት መሰረት የሌለው የዜሮ ድምር ፖለቲካ በመሆኑ መቆም አለበት በሚለው አቋሙ ከዋናው ቤተመንግስት ሰውዪ ጋር ይጋጫል ።

በሌላ በኩል ኢሳያስ የሃይላን ልጅ ፍልይቲን እንደ ጆከር ሲጠቀምባት እናያለን ። ኢ/ያ ውስጥ የሚከናወነውን የዶላር ዘረፋ ፣ የስለላ ስራና ህቡዕ ግድያ ትመራለች ። በጅቡቲ ወደብ ወደ ኢ/ያ የሚገባውን ስትራቴጂካዊ ንብረት ለማውደም ተመራጭዋ ሰው እሷ ናት ። ባድመ በመዝመት ለሌሎች ያስቸገሩ የመረጃና የተመሰጠሩ መልእክቶችን የመፍታት ስራ ትሰራለች ። ፍልይቲ የፕሬዝዳንቱ ቀኝ እጅ ፣ ብሩህ አእምሮ ያላት ፣ ደፋር ፣ አፍቃሪ እና ጨካኝ ገጸባህሪ ናት ።

ከኤርትራ ህዝብ አንጻር / አማራ ጠላት ነው የሚል ቆሻሻ ሀሳብ / ግን አንድ ይቅር የማይባል ክህደት ትፈጽማለች ። ክህደቱ ለኤርትራ የቴሌ እና ኤሌክትሮኒክስ ግንባታ ትልቅ ድርሻ ያከናወነውን ኢትዮጽያዊ ሰው በማፍቀሯ ነው ። አስራደ ሙሉጌታ ይባላል ። ሻእቢያ ጉልበቱንና እውቀቱን እንደ ሽንኮራ ከመጠጠው በኋላ ሊያስወግደው ቀነ ቀጠሮ ይዞለታል ። ለአስመራ ፖለቲካ ትልቅ አይን የሆነችው ፍልይቲ ከመንግስታዊው ተልዕኮ ጎን ለጎን ፍቅረኛዋን ለማዳን ህቡዕ ትግል ስታከናውን እንመለከታለን ። የሃይላይ ወንድ ልጅ ሰለሞን ‹ ናጽነት › በሚለው ነጠላ ዜማው በከተማው የታወቀ ዘፋኝ ሆኗል ። ሙዚቃው ማዝናኛ ብቻ ሳይሆን የዘመቻ መቀስቀሻም ነው ። ናጽነት ብሎ የዘፈነው ግን በኢሳያስና በአባቱ ለተመራው ትግል ማስታወሻ ለመስራት ብቻ አይደለም ። እንደውም በዋናነት የዘፈነው ነጻነት የተባለች ቆንጆ ወጣት በማፍቀሩ ነው ። ነጻነት ለኤርትራ ወጣት የእግር እሳት ወደሆነበት ሳዋ ስትገባ እሱም እንዳላጣት ብሎ ፈለግዋን ይከተላል ። እሷን ፍለጋ ላይ ታች ሲል ነጻነት በሁለት የባደመ ጦር ጄነራሎች አይን ውስጥ ትወድቃለች ። ልክ እንደ ባድመ መሬት ሊቆጣጠሯት ሌት ተቀን ስትራቴጂክ ይነድፋሉ ።

እናም የአንደኛው ቤተመንግስት ሰውዪ ከኢ/ያ ድል ለማግኘት ሲራራጥ ፣ የሁለተኛው ቤተመንግስት አባላት ደግሞ ከራሱ ከኢሳያስ ጭቆና ለመላቀቅ እንዲሁም ፍቅረኛዎቻቸውን ለመታደግ ላይ ታች ሲሉ በታሪኩ ተወጥረን እንያዛለን ።

መጽሐፉ ጥቃቅን ቴክኒካል ችግሮች የሉበትም ማለት አይቻልም ፣ ለአቅመ ግነት የሚበቁ ስላልመሰለኝ ዘልያቸዋለሁ ። ይልቁንስ ደራሲው የራሱ እምነት የሚመስል ጉዳይ መጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ቆስቁሶ እንዲረሳ ወይም እንዲጨነግፍ ማድረጉ የሚቆጭ ይመስለኛል ። ያነሳቸው ጥያቄዎች የአንባቢም መሰረታዊ ጥያቄዎች ሊሆኑ የሚችሉ ናቸው ። የባርካ ማተሚያ ቤት ባለቤት የሆኑ ግለሰብ አቶ ሃይላይ ሊጽፉ ባሰቡት መጽሐፍ ውስጥ አራት መሰረታዊ ጥያቄዎችን አዳብረው አንዲሰሩ ሀሳብ ያቀርባሉ ። ከቀረቡት ሃሳብ ውስጥ ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው ፣

1 . የኤርትራ ነጻነት ትግል ለምን በ 1885 ምጽዋ በኢጣሊያ መያዝን በመቃወም አልተጀመረም ?

2 . ከኤርትራ ልዩ ማንነት የተፀነሰ ትግል ከሆነ ለምን 30 አመታት ፈጀ ?

ደራሲው ስራውን ከሰሩት 285 ሺህ ናቅፋ እንደሚያገኙም ውል ታስሮ ነበር ። ሆኖም የማተሚያ ቤቱ ባለቤት ሲያዙ ፣ አቶ ሃይላይም ሲገደሉ ሃሳቡ ይመክናል ። እንደ ስነጽሁፍ ሃያሲ የሁለቱ ሰዋች መጥፋትን በአስመራ ወስጥ የመጻፍ ፣ የመናገር ፣ የማሰብ እና የዴሞክራሲ መሞትን ለመተርጎም ያስረዳን ይሆናል ። ከዚህ በላይ ግን ታሪኩ ባይጨነግፍ የበለጠ ጠቃሚ ያደርገን ነበር ብሎ መከራከር ያስኬዳል ። አቶ ሃይላይ ለእውነት የቆሙ ገጸባህሪ በመሆናቸው እየመረራቸውም ቢሆን ከኤርትራ ጀርባ የተደበቁ ጉዳዮችን ያነሱ ነበር ። ይሄን አንስተው ቢሞቱ ደግሞ ሞታቸውንም ይመጥን ነበር ። የበለጠ ጀግና መስዎዕት እናደርጋቸው ነበር ።

‹ አውሮራ › ጦርነት ላይ መሰረት አድርገው እንደተሰሩት ልቦለዶቻችን ማለትም ኦሮማይ እና ጣምራጦር የተሳካ ስራ ነው ። ድንበር ያቆራርጣል ፤ እዚህና አዚያ እንደ ቴኒስ ኳስ ሲያንቀረቅበን ጨዋታው ሰለቸኝ ብለን ከሜዳው ዞር ማለት አንችልም ። ፈጣን ነው ፤ በድርጊት የተሞላና በመረጃ የደነደነ ። መንቶ ነው ፤ ፍቅርና ጦርነትን በእኩል ጥፍጥና ከሽኖ ማቅረብ የቻለ ። ሰባኪ ነው – ፍቅር ያሸንፋል የሚል አይነት ፤ ተዛምዶ ተጋብቶ ተዋልዶ የተካደ ትውልደን የሚያባብል ። የሆነውን ብቻ ሳይሆን  የሚሆነውን ቁልጭ አድርጎ የሚናገር ። በተለይም የአንድነት አሳቢዎችን ገድለን ቀብረናል ብለው ለሚመጻደቁ ጠባቦች « ውሸት ነው ! » ብሎ ጥበባዊ ምስክርነት የሚሰጥ ።

በታሪኩ ውስጥ ማንነቱን ደብቆ ስሙን አቦይ ግርማ አስብሎ ቀን ከለሊት በባድመ የልመና ተግባር የሚያከናውነው እንኮዶ /የደርግ ኮማንዶ የነበረ / አንድ እጁ ስለተቆረጠና አይኑ ስለተጎዳ ማንም ግምት ውስጥ ያሰገባው አልነበረም ። ሆኖም መጀመሪያ የባድመን መሬት ፈልፍለው የገቡ የሻእቢያ ወታደሮችን ፣ በመጨረሻም እጁን በመጋዝ ቆርጦ የጣለውን ጄኔራል ግዜ እየጠበቀ መበቀል ችሏል « ለገንጣይና ጡት ነካሽ ዋጋው ይሄ ነው » እያለ ። ይህ ትርክት በስነጽሁፍ ቋንቋ ፎርሻዶው ወይም ንግር የሚባለው ቴክኒክ ነው – ነገ እንዲህ መሆኑ አይቀርም ለማለት ።

by 

የትውልዳችን ድምጽ፤ ድምጻዊት ሀኒሻ ሰለሞን!

ጥሎብኝ ለሚወዷት አገራቸው የወደቁና የደከሙ የኢትዮጵያ ጀግኖችን የሚያስታውሱ ቁም ነገረኛ ልጆችን ስራ ከልቤ እወዳለሁ። አርብ እለት በኢንተርኔት አማካኝነት የተለቀቀ የሀኒሻ ሰሌሞን «ከፍ በይ ሃገሬ» የሚለው ዜማ ነፍስ ያለውና ከቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ በኋላ ታላቁን የኢትዮጵያ ጀግና የራስ ጎበና ዳጨን ውለታ ያወሳ ነበር።

Continue Reading