የቅዱስ ጳውሎስ የእግር ብረት! (ሊነበብ የሚገባው)

የእሥር ቤቱ ጠባቂ ከእንቅልፉ ሲነቃ በሮቹ ሁሉ ተከፍተው አየ፥እስረኞቹ ያመለጡ ስለመሰለውም ራሱን ለማጥፋት ሰይፉን መዘዘ።በዚህን ጊዜ ቅዱስ ጳው ሎስ ድምፁን ከፍ አድርጐ “በሰውነትህ ልዩ ክፉ አትሥራ፥በገዛ እጅህ ታርደህ አትሙት፥ማንም ያመለጠ እስረኛ የለም፥ሁላችንም ከዚህ ነን፤”አለው።የገረፈውን ያሰቃየውን እና ያሠረውን ወታደር ከሞት አዳነው።“ለማንም በክፉ ፈንታ ክፉ አትመልሱ፥በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ፤”ብሎ በቃል ያስተማ ረውን በተግባር አሳየ

Continue Reading

Advertisements

Photos: The architectural mastery of Ethiopia’s ancient churches

Ethiopia is legendary for its medieval, rock-hewn churches, the cruciform and colorful frescoes of which have attracted tourists from across the world. The ancient kingdom of Abyssinia, which we now know as modern-day Ethiopia and Eritrea, was probably the site of the first Christian nation, and the churches still serve as religious sanctuaries and draw pilgrims celebrating the Ethiopian Christian calendar.

Continue Reading

ወንጌላዊው ‘መምህር’ ግርማን “ይዋጣልን” ሲል ጋበዛ

“ሃዋሪያ” ሃብታሙ፣ ይዲዲያ “መምህር” ግርማ ወንድሙን በአካል ተገናኝተው እንዲጸልዩ፣ አስፈልጊም ከሆነ እሳቸውን መሰል በሙሉ ተሰባስበው እሱ ብቻውን መጥቶ ትክክለኛው መንፈስ እንዲገለጥና ትውልድ እንዲድን ጥያቄ አቀረበ። ብዙም ጭፈራና ዝላይ የማይወዱ አገልጋይ ከሆኑት መካከል አንዱ ” ጉዳዩ የመንፈስ ጉዳይ ነው፤ በጸሎት ማሸነፍ እንጂ የአደባባይ ፉከራ ዋጋ የለውም፤ መንፈስ የሚሸነፈው በመንፈሳዊ ጦርነት እኒ በአደባባይ ግብግብና በቲፎዞ ፊት በሚደረገ ግጥሚያ አይደልም” ብለዋል።

Continue Reading

የሮማው ጳጳስ፤ አባታችን ሆይ ፀሎት ማሻሻያ ያስፈልገዋል አሉ

ፓትርያርኩ አባ ፍራንሲስ፣ እነዚህ አባባሎች፣ በተሳሳተ አተረጓጎም ሳቢያ የተዛባ መልዕክት ያዘሉ ናቸው ብለዋል። ፈጣሪ ለፈተና ይዳርገናል የሚል የተዛባ መልዕክት የያዙ የተሳሳቱ አተረጓጎሞች እንዲስተካከሉ እፈልጋለሁ ሲሉም ተናግረዋል – ጳጳሱ። “…let us not into temptation” በሚል አባባል መስተካከል እንዳለባቸውም ጳጳሱ ገልፀዋል።

Continue Reading

በሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ መሠረት ሶስት ካህናት ላይ እገዳ ጣለባቸው

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያኑን ሕግና ቀኖና ለማሰከበር ባለበት ኃላፊነት በተለይም የምእመናን መለያየት ክፉኛ ስላሳስበው የወሰደው መንፈሳዊ እርምጃ መሆኑ ታውቆ አባ ኃ/ጊዮርጊስ ተሾመ፣ ቄስ አብርሃም ቦጋለ እና ቁስ አለምእሸት አብርሃ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ አገልግሎታቸው እውቅና የሌለው በመሆኑ ተቀባይነት ስለሌለው ምዕመናን ይህንኑ በመረዳት ማንኛውንም ክህነታዊ አገልግሎት ከነዚህ ግለሰቦች ባለመቀበል ለቀኖና ቤተክርስቲያን ዘብ እንዲቆም ቤተክርስቲያን ጥሪዋን እንደምታቀርብ ውሳኔው ዘግቧል።

Continue Reading

ቅ/ሲኖዶስ በአንድነት በመሥራት ለምእመናን አቤቱታ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ

“የተሐድሶ ኑፋቄ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ሊመክት ይገባል፤” ብፁዕ አቡነ እንጦንስ

 • የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ መክፈቻ ጸሎት ተካሔደ፤
 • የተሐድሶ ኑፋቄ፣ በጸሎትና በርቱዕ አስተምህሮ ካልተመከተ፤ ከዮዲት ጉዲት ጥፋትና ከግራኝ ወረራ ይልቅ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና እንደሚያናጋ ብፁዕነታቸው አሳሰቡ፤
 • የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከትን፣ በሃይማኖታዊና አስተዳደራዊ በደሎች ያስቸገሩት ብፁዕ አባ ማርቆስ እንዲነሡ፥ ግፉዓን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች ጠየቁ፤
 • ችግሮቹ መፍትሔ ሳይበጅላቸው ከቀጠሉ፣ ለሀገረ ስብከቱና ለመላዋ ቤተ ክርስቲያን ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች እንደሚያስከትሉ አሳስበዋል፤
 • “ምክር ዝክር የሌላቸው ግራ አጋቢ” ያሏቸውን ብፁዕ አባ ቶማስን አስጠነቀቁ፤ ብፁዕ አባ ማርቆስን እየደገፉ በሚከተሉት፣ ወጣቱን ትውልድ ከቤተ ክርስቲያን የሚያርቅ አካሔዳቸው ወቀሷቸው፤
 • ከደብረ ማርቆስ፣ ብቸና እና ደጀን የተውጣጡትና በ7 አውቶቡሶች ተጓጉዘው የደረሱት ከ500 በላይ ካህናትና ምእመናን፣ የአቤቱታ ድምፃቸውን ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰምተዋል፤
 • የምልአተ ጉባኤው መክፈቻ ጸሎት መርሐ ግብር በተደረገበት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ አቤቱታቸውን ያሰሙ በርካታ ምእመናን፤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እና ለሕገ ቤተ ክርስቲያን መከበር ጥብዓት ላሳዩት፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል፤

†††

 • በማዕከል የተቋቋመው፣ የፀረ ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ ጉባኤ፣ በአግባቡ ባለመሥራቱ ዳግም እንዲቋቋም፣ የአዲስ አበባ ወጣቶችና ጎልማሶች ማኅበራት ኅብረት ጠየቁ፤
 • የማኅበራት ኅብረቱ፣ ለምልአተ ጉባኤው ባቀረበው ባለ13 ነጥቦች አቤቱታ፤ በመዋቅር የተሰገሰጉ የኑፋቄው ቅጥረኞች ታግደው እንዲመረመሩ፤ ተወግዘው የተለዩት ለሕዝቡ በይፋ እንዲታወቁና ለኑፋቄያቸውም በሊቃውንት ጉባኤው ምላሽ እንዲሰጥ፤
 • ውጉዛኑ፥ በቤተ ክርስቲያን አስማተ ማዕርጋት፣ አልባሳት፣ ንዋያተ ቅድሳትና የትምህርት ማስረጃዎች እንዳይጠቀሙ በሕግ እንዲከለከሉ፤ ባለቤትነትና ባለመብትነት የሕግ ጥበቃ እንዲያገኝ፤
 • ታግደውና ተሰናብተው ጉዳያቸው በተያዘው ውሳኔ እንዲሰጥ፤ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ በመምህራን ላይ የተደረገው“ጅምላ እግድ”እንዲስተካከል፤
 • በኑፋቄ ለተደናገሩ ምእመናን፣ በቤተ ክርስቲያናችን የብዙኃን መገናኛዎች ምላሽ እንዲሰጥና የዐውደ ምሕረት ጉባኤያትም እንዲዘጋጁ፤
 • በተለያዩ ቦታዎች፥ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን በማፍረስ፣ ታቦታትንና ንዋያተ ቅድሳትን በየቦታው በመጣል የሚፈጸመው ድፍረት እንዲቆም፤
 • የቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና እንዲከበር፤ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚደረጉ ጫናዎች ተወግደው፣ በቤተ ክህነቱ የቴሌቭዥን ጣቢያ የአየር ሰዓት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፤

“ሕጋዊው” የኢት/ኦ/ቅ/ሲ/ – “ሕዝባችን አሁን ያለበት ሁኔታ በየትኛውም አቅጣጫ ተስፋ ያለው ሁኖ አይታይም”

ከሕጋዊው ኢት/ኦርቶዶስክስ ቅዱስ ሲኖዶስ  የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

«ለሀገርና ለከተማ ሰላምን ፈልጉ፥ ስለ እርስዋም ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።» ኤር 29፡7

ነቢዩ በስደት አገር ለሚኖሩት ስደተኞች እሥራኤላውያን ለሀገር ሰላም ፈልጉ የሀገር ሰላም የሕዝብ ሰላም ነውና ይላል ዛሬም ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ለሕዝባችን ለሀገር ሰላም ጸልዩ የሚል መልእክት ያስተላልፋል

የተከበራችሁ ኢትዮጵያውያን! በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ምን እየተከናወነ እንደሆነ የኢትዮጵያን ጉዳይ የሚከታተል ሁሉ ይረዳዋል ብለን እናምናለን  አሁን አገዛዙ አቅም አጥቶ ነግሮች ሁሉ እየተበላሹ ናቸው የዚህ ወጤት ደግሞ ህዝባችን ወዴት ሊወሰደው እንደሚችል ከወዲሁ እየታየ ነው   ባለፉት ሳምንታት «በተባብሩ ጉባኤ» ላይ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያቀረብው ሐሳብ የዚህን ስጋት ነበር

እንደ ወቅቱ ሁኔታ አገሪቷ ያልፈረሰቸው ሕዝባችን ፈረሃ እግዚአብሔር ያደረበትና  ጨዋ ሕዝብ ስለሆነ እንጅ መንግስት እንደ መንግሥት  ስለሚያሰተዳድር አይደለም ፤ እርሱ ከቀረ አመታት ተቆጥረዋል።  በዚህ አጋጣሚ ሕዝባቸን በማሳየት ላይ ያለው  ኢትዮጵያዊ  ጨዋነት በቤተ ክርስቲያንና በኢትዮጵያ ስም  ሳናመሰግን እናልፍም።  መንግሥት ተብየው  እንደሚሰራው ተንኮል ቤሆን ኑሮ  ኢትዮጵያ ሞቃድሾን በሆነች ነበር።  ከጥቂት የፖለቲከኞችን በተለይም የገዢውን ፓርቲ ተንኮል በሚያራምዱ ግለሰቦች አማካይነት  የሚያመጡት መፈናቀል ከልሆነ በቀር  በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች የሚኖሩ የተለየየ ቋንቋ  የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ፤ ሕዝብ እንደ ሕዝብ አንዱ በአንዱ ላይ ይህን አላደረግም እናም ሕዝባችን ምስጋና ይገባዋል። አንዱ በሌላው ላይ  ሳይነሳ እሰከ አሁን መንግሥት ያሰበው ሳይሳካ ሕዝብ  በሚያደርገው የአስተውሎት ሒደት  አገር እንደ አገር  አለች  ወደፊትም  በጣም አጭር አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች  አይኖሩም  አገርና ሕዝብ ግን ይኖራል።  ውድ ኢትዮጵያውያን! እስከ አሁን የተከተላችሁትን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ይዛችሁ በመቻቻል ይህን የመከራ ቀን  እንድታሳልፉት ከአክብሮት ጋር  ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያቀርባል።

የሚከተለው ጥሪ ለአማራጭ ኃይሎች ይሆናል፦ ውድ ወግኖቻችን! የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፖለቲካና የታሪክ ምሁራን አገራችን ኢትዮጵያ ከገባችበት አጣብቂኝና ሕዝባችን ላይ እያንዣባበ ያለውን አደጋ  ዛሬ አንድ ሆናችሁ  ለሕዝባችሁና ለአገራችሁ ካልሠራችሁ ነገ የዘገየ እርምጃ ነው ፤ ምን አልባትም እድልም ላይኖር ይችላል።  ዛሬ ግን  እግዚአብሔር እድልን ሰጥቷል  ስለሆነም ልዩነታችሁን ወደ ጎን ትታቸሁ አገር በማዳኑ  በወቅቱ ሁኔታ ላይ ትሰለፉ ዘንድ፤እየተራበ በሚገደለው፣ በታሠረው፣ በሚሰደደውና በሚሰቃየው ሕዝባችን ሰም  ጥሪ እንቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ Nov 1st ጀምሮ በኦሃዮ ኮሎምበስ በደብረ መድሐኒት መድኃኔ ዐለም ቤ/ክ በሚካሄደው  የሕጋዊ  ይቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ ላይ መንፈሳዊና አገራዊ አጀንዳዎች መካከል በዋነኛነት የሜቀርበው አጀንዳ የሀገራችን የእርቅና የሰላም ጉዳይ ነው።

እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ

የህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ሕዝብ ግንኙነት  መምሪያ

አባ ጴጥሮስ የአውስትራሊያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

የኢትዮጵያ ኦርቶ ዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን

ዛሬም እንደ ትናንትናው ታሪካዊ ድርሻዋን ለመወጣት ዝግጁ ናት !

ከሁሉ አስቀድመን ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ለመወያየት ይህንን ዝግጅት ያደራጁትንና ቤተ ክርስቲያንን በቅዱስ ሲኖዶስበኩል የጋበዙትን ሰዎች ልናመሰግን እንወድዳለን ። በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ወክለን ስንገኝ

አንደኛ ቤተ ክርስቲያናችን ከእግዚአብሔር የተሰጣትን ሰማያዊ አደራና ሐዋርያዊ ተልእኮ መሠረት በማድረግ ፣

ሁለተኛ ኢትዮጵያ ሀገራችንና በታሪኳ የገጠሟትን ተመሳሳይ ሀገራዊ ፈተናዎችን እንዴት እንዳለፈችና ፣ እንዴትስ እኛ ትውልድ ዘንድ በክብር እንደደረሰች የሚያሳየውን አኩሪና መሳጭ ታሪካዊ የተጋድሎ ጉዞ በመመርመርና በዚያም ውስጥ የነበረውን የቤተ ክርስቲያናችንን ታላቅ አስተዋጽኦ መነሻ በማድረግ ፣

ሦስተኛ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የሚገኙ ሀገሮችና ሕዝቦች ከገጠማቸው ተመሳሳይ ችግሮች እንዴት በድል አድራጊነት እንደ ወጡና ህልውናቸውን አስቀጥለው የተጓዙበትን ልምድ ግብዓት በማድረግ ሲሆን ፣ ዛሬ ሕዝባችን ከደረሰበት ታሪካዊ ውርደትና ፈተና ፣ ሀገራችንን ካንዣበበባት የመተራመስና  የመፍረስ አደጋ ለመታደግ ይረዳ ዘንድ ፥ ከእናንተ ከልጆቿና ከወዳጆቿ ጋር እጅና ጓንት በመሆን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ልታበረክት የምትችለውን አስተዋጽኦና የተጋድሎ ድርሻ በሚመለከት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያምንበትን የመፍትሔ ሐሳብ ለማቅረብ ነው ።

ክፍል አንድ

የት ነን ?

«እግዚአብሔር እንዲህ ይላል  የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ  ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች  የሉምና ስለልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች» (ኤር 31 ፥ 15)

የማኅበረሰብ መሪዎች ራሳቸውን የክፉና የደግ መለኪያ ቱንቢ አድርገው “ስገዱልን!” ሲሉ ፣ ጎልማሶች ራስ ወዳድነትን ሙጥኝ ብለው የእርስ በርስ መበላላት መኖርና ሥቃይ አንድ ሲያደርጋቸው ፣ ወጣቶች በመንፈስ ልዕልና ከመኖር ይልቅ በድንገት የሚገነፍሉ  የንዴት ስሜቶቻቸውን እየተከተሉ መልሕቅ እንደሌለው መርከብ በትርጉም አልባነት ማዕበል ሲንገላቱ ፣ በእግዚአብሔር ሕይወት ለዘለዓለም እንዲያብቡ የተፈጠሩት የሰው ልጆች የተፈጠሩበትን ክብር ዘንግተው ለመሞት ተራ የሚጠብቁ እንስሳት ሁነው መመልከት ሕሊናን ያቆስላል ።

ማኅበረሰብ ሲፈርስ ፣ የሰው ልጅ ክብሩ ሲጣል ፣ እረኞች በጎቹን እየቀለጣጠሙ ያለርኅራኄ ሲበሏቸው ማየት ሕሊናን ይጠዘጥዛል ። አልቃሻው ነቢይ ኤርምያስ ቁስሉ ቢያመው ሞት ልጆቿን እንደ ነጠቃት ራሔል ጉንጮቹ የእንባ መፍሰሻ ቦዮች ሆኑ ። መዝሙሩ ልቅሶ ፣ ጸሎቱም እዬዬ ሆነ ። የእስራኤል ስደተኞችም በመዝሙር መጽሐፋቸው ይህንኑ የእንባ መዝሙር በመዘመር ከኤርምያስ ጋር ተባበሩ ፣ እንዲህ ሲሉ

«በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን  ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን  በአኻያ ዛፎቿ ላይ መሰንቆቻችንን ሰቀልን የማረኩን በዚያ የዝማሬን ቃል ፈለጉብን  የወሰዱንም ፦ የጽዮንን ዝማሬ ዘምሩልን አሉን  የእግዚአብሔርን ዝማሬ በባዕድ ምድርእንዴት እንዘምራለን ? ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ  ባላስብሽ  ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ  ከደስታዬ ሁሉ በላይኢየሩሳሌምን ባልወድድ» ። መዝ 136 ፥ 5 ።

እግዚአብሔር የሌለበት ዓለም ቢሆን ኑሮ የራሔል እንባ ፈስሶ በቀረ ፣ የመከረኞቹም ሥቃይ ትርጉም ባጣ ነበር ። ነገር ግን ፣ የድኻ አደግ አባት ፣ የተሰበሩት ምርኩዝ ፣ የተሰደዱት መጠለያ ወደብ ፣ የሕይወት ደራሲዋ የሆነው እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ አለ ። ስላለም የራሔል እንባ ፈስሶ አልቀረም ። የኤርምያስ ጉንጮች በሰቀቀን እንባ ተሸርሽረው አልቀሩም ። ምድር ላይ ጠብ ያለው የራሔል እንባ ምድሩን ብቻ አጨቅይቶ አልቀረም ፣ ሰማያትንም አረስርሷል ፤ ከዘለዓለም የታወጀው የእግዚአብሔር ምሕረት ደምቆ ታውጆበታል ።

ፖለቲካዊ ፈቃድ የተሰጣቸው ሌቦች ልብሰ ተክህኖ ለብሰው ሥርዓተ አምልኮውን ተውኔት ባደረጉበት ፤ የእምነቱን አቡጊዳ የማያውቁ ሥራ አጦች የመምህራንን ካባ አጥልቀው ፣ ሰውን ወደ እግዚአብሔር ቃል ከመምራት ይልቅ ፥ ኪሳቸውን ለመሙላት ሲሉ ከንቱነትን እየነገሩ ሰዉን የአእምሮ ድኻ በሚያደርጉበት ማኅበረሰብ ውስጥ ሥነ ምግባር ብርቅ ቢሆን ምን ይገርማል?

እነሆ ! ሁሉም በየፊናው የበላይ ለመሆን ይሮጣል ። በዙሪያው ያሉት ሁሉ በእርሱ ዙሪያ ተሰብስበው እስኪሰግዱለት ድረስ ይቸኩላል ። ራሱን የሁሉ ነገር ማዕከል (አምላክ) አድርጎ ለመገኘት የማይቧጥጠው ገደል ፣ የማይፈነቅለው ደንጊያ ፣ የማይቆርጠው ዛፍ የለም ። እየሆነ ያለው ይህ ነው ። እንደ ኤርምያስ ለሰው ልጆች ክብር ፣ ለወገኖቹ ርኅራኄ የተመላ ልብ ያለው ቅን ካለ ፣ ምንም እንኳ አስተሳሰቡ እንደ ዕብድ ቢያስቆጥረውም ያለቅሳል ። ስለ ወገኖቹ ስሕተትና ዕብደታቸው ስለ ወለደው ሥቃይ ያለቅሳል ። የሰው ልጅ ለእግዚአብሔር ፍቅር የልቡን በር ካልከፈተና ወንድሙን እንደ ራሱ ሊራራለት ካልቻለ ፣ የወንድሙን ሥቃይ የራሱ ሥቃይ አድርጎ ማሰብ ካልቻለ ፥ የትኛውም ፖለቲካዊ ዲስኩርና አደረጃጀት ከመበላላት አያድንም ።

አንድ የ20ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓዊ ፈላስፋ ማኅበረሰብንና የሥልጣን ጥምን በተነተነበት ድርሳኑ እንዲህ ይላል፡- “Every man would like to be God, if it were possible. Some few find it difficult to admit the impossibility. These are the men framed after Milton’s Satan, combining like him nobility with impiety.” [1]

ፈላስፋው እንዲህ ዓይነት ሰዎች ክቡርነትን ከክፉነት ጋር ቀላቅለዋልና ሰይጣንን ይመስላሉ ይላል ። ሰይጣንን በሚመስል ኑሮ እየኖርን የእግዚአብሔርን ዕረፍት ከወዴት ልናገኝ እንችላለን ?

ሕዝባችን አሁን ያለበት ሁኔታ በየትኛውም አቅጣጫ ተስፋ ያለው ሁኖ አይታይም ። በሀገሪቱ ያሉ ዐበይት ቤተ እምነቶች በየክፍላቸው አንዳቸውም የተስማሙ አይደሉም ። አንድ ቤተ እምነት ነው ተብሎ የሚጠራ ቡድን አምስት ስድስት ዓይነት ዶክትሪን ያስተምራል ። የእርሱን ዶክትሪናዊ ትንተና ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ እርሱን የማይቀበሉትን ለማስጠላት በፍቅር ፈንታ ጥላቻን ይሰብካል ። ይህ ደግሞ ተከታዮቹን በጥላቻ ይመርዛቸዋል ። ከጥላቻ የተረፉትንም ተስፋ መቁረጥ ይጫናቸዋል ። በሥልጣን ላይ ያለው ሴኪዩላሪስት ቡድን እንዲህ ባለው ሃይማኖታዊ ውዥንብር ተጠቃሚ ነው ። የሃይማኖት ተቋማት የተጠናከረ ተቋማዊ አደረጃጀት እንዳይኖራቸው አበክሮ ይሠራል ። መንግሥቱ የቆመው ማኅበረሰቡን ከፋፍሎ እርስ በርሱ እንዲፈራራ በማድረግ ስለ ሆነ ፣ በማኅበረሰቡ ውስጥ የአብሮነትና የደኅንነት ስሜት (sense of security) እንዲኖረው የሚያስችል ፣ እርሱ የማይቆጣጠረው ምንም ዓይነት ተቋም እንዲኖር አይፈቅድም ። ቡድኑ ወደ ሥልጣን ሲመጣ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ ነጻነት ማሳጣት የመጀመሪያ ሥራው ያደረገበት ምክንያትም ማኅበረሰቡን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ለማዋል ነበር ።

የሀገራችን ሕዝብ ንቅሐተ ሕሊና በተረዳው መጠን እግዚአብሔርን በመፍራት ላይ የተመሠረተ ስለ ነበር አኗኗሩ ሰብአዊ ርኅራኄ የተመላበት ነበር ። ማኅበረ ሰባዊ ልዩነቶች ተቻችለው የኖሩት ፣ ጎሣዎች ሲፋቀሩ ተጋርተው ፣ ሲጣሉ ዕርቅ አውርደው የኖሩበት ምክንያት ሕይወትን የሰው ልጆችን ሁሉ እኩል አድርጎ ከፈጠረው ከእግዚአብሔር አኳያ የመመልከቻ ነጥብ ስለ ነበራቸው ነው ። የሀገር ሽማግሌዎች በማኅበረሰቡ ውስጥ ታላቅ ስፍራ ይዘው የኖሩበት ምክንያት በሰከነ መንፈስ ያንን ነጥብ ጠብቀው ጊዜያዊ ስሜቶችንና ግጭቶችን ማርገብ ይችሉ ስለ ነበር ነው ። ዛሬ ያ ሁሉ አለ ለማለት ያስቸግራል ።

ማኅበረሰቡ አሉኝ የሚላቸውን ማኅበረሰባዊ ተቋማቱንና ተቋማቱ ተገንብተውባቸው የነበሩበትን ማኅበረሰባዊ ዕሤቶች (social values) ሙሉ በሙሉ ማለት እንኳ ባንችል በአብዛኛው በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ፈርሰዋል ። ዕድርና ዕቁብ ሳይቀሩ በካድሬዎች እይታ ሥር ናቸው ። “Big Brother is watching you!” እንዲሉ ። [2] የኢትዮጵያውያን መከራ ዛሬም አላቆመም ። የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብት ሙሉ በሙሉ የተቆጣጠረው ቡድን በሀገሪቱ ውስጥ ላለው ወጣት ትውልድ ሥራ መፍጠር አቅቶታል ። የወጣቶች ተስፋ ማጣት ኢትዮጵያ ውስጥ ከመኖር እንጀራ ፍለጋ በሊብያና በግብፅ በረሀዎች ሞትን እየተጋፈጠ ነው ። ጎሣዊ ቁርሾዎች የሚያስታግሣቸውና የሚያስታርቃቸው ማኅበረሰባዊ ሥርዓት አጥተዋል ። ትናንት በሀገር በቀል የዕርቅ ሥርዓቶች ይፈቱ የነበሩ ግጭቶች ዛሬ የአንድ አካባቢ ሕዝብ ከኖረበት ቀዬ እንዲፈናቀል እስከማድረግ እየደረሱ ነው ። የጎሣ ግጭቶች አሁን ፍጹም መንግሥታዊ መልክ ይዘዋል ። እንደ ድሮው በምሥራቃዊ የሀገሪቱ ክፍል ውስጥ ያሉ ሱማሌዎችና ኦሮሞዎች ሲጋጩ ግጭቱ በሽማግሌዎች የሚፈታ የጥቂት ወጣቶች ጠብ ሳይኾን የጎሣ ክልሎቹ መንግሥታት የድንበር ግጭት ይሆናል ። በቅርብ ጊዜ የተፈጠረው ከምሥራቅ ኢትዮጵያ የተሰማው ክፉ ዜና በዚህ ዓይነት ሀገሪቱ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር መቀጠሏን ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው ።

ፖለቲካዊ ሥርዓቱ ወደ ዘመነ መሳፍንት እየተመለሰ ይመስላል ። ልዩነቱ ምናልባት የአሁኑ ዘመን መሳፍንት የታጠቁት መሣሪያ የመግደል ፍጥነቱ በጣም የተሻሻለ በመሆኑ ብቻ ሳይሆን አይቀርም ። የምድሪቱ ድኾች አሁንም ይራባሉ ፣ አሁንም ይሰደዳሉ ፣ አሁንም በግፍ ይታሠራሉ ፣ አሁንም ይገደላሉ ። የተረፉትም በፍርሃትና በጭንቀት ተወጥረው ይኖራሉ ። ውኃ ፥ መብራት ፥ የመኖሪያ ቤት ፥ የተመጣጠነ ምግብ ለኢትዮጵያውያን ዛሬም ብርቅ ናቸው ። በዜና ማሠራጫዎች ዜና የሚሆነው ኢትዮጵያውያን ውኃ የማጣታቸው ሳይሆን የእንትን ቀበሌ ነዋሪዎች “ንጹሕ የመጠጥ ውኃ” ማግኘታቸው ነው ። ይዘረጋሉ የሚባሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎች ፥ ዐዋጅ ከተነገረላቸው ከዓመታት በኋላ እንኳ የት እንደደረሱ መጠየቅ አይቻልም ።

ቅዱስ ሲኖዶስ በሥልጣን ላይ ያለው ሴኪዩላሪስት ቡድን ላለፉት 26 ዓመታት በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ያደረሰውን መከራ እየተመለከት ሲያዝን ፣ ግፉ እንዲያቆምም ሲያሳስብ ቆይቷል ። እኛ በስደት የምንገኝ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በምንሰበሰብበት ጊዜ ሁሉ ስለ ወገናችን ያልጸለይንበት ጊዜ የለም ። የኤርምያስ እንባ ዛሬም ይፈስሳል ። ቅዱስነታቸው ከሰው መወያየቱን ትተው በዝምታና በእንባ ከእግዚአብሔር ጋር መወያየቱን መርጠዋል ።

ባለፉት ከሃያ በላይ ለሚቆጠሩ ዓመታት ቅዱስ ሲኖዶስ ከአርባ በላይ የሰላምና የአንድነት ጥሪዎችን አድርጓል ። ጥሪዎቹ በአብዛኛው በመንግሥት ስም ለተቀመጠው ቡድን ብቻ ሳይሆን ስለ ኢትዮጵያ እንቆረቆራለን ለሚሉ ፖለቲካዊ ቡድኖችም ነበር ። እንደ አለመታደል ሁኖ ለዚህ የቤተ ክርስቲያን ጥሪ በጎ አጸፋ የሰጠ ተቋምም ሆነ ግለ ሰብ ታይቶ አይታወቅም ። ይህ ከምን መጣ ? የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ ነጻነት ለሀገሪቱ ነጻነትና ማኅበረሰባዊ ዕድገት ያለውን ትእምርታዊና ተግባራዊ (symbolic and practical) አስፈላጊነት ካለመገንዘብ ? ወይስ የኢትዮጵያን ማኅበረሰብ ታሪክም ሆነ የአስተሳሰብ ሥሪት ለመረዳት የቤተ ክርስቲያን ሚና ምን ያህል ጕልሕ እንደ ሆነ ካለማስተዋል ? በስደት የሚገኘው ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ግን አሁንም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነት እስከሚረጋገጥ ድረስ ጥሪውን አያቆምም ።

ብዙ ሰዎች “ይህ ፖለቲካ ነው ። ቤተ ክርስቲያን እዚህ ውስጥ ምን አገባት?” ይላሉ ። እርግጥ ነው ቤተ ክርስቲያን የእኔ የምትለው የፖለቲካ ፓርቲም ሆነ ቡድን ሊኖራት አይችልም ። ነገር ግን የትኛውም የፖለቲካ ቡድን የሰው ልጆችን ክብር ሲደፈጥጥ ስታይ ፥ “ስለ ምን ታሳድደኛለህ!” የሚለውን የሰው ልጆችን ስቃይ የራሱ ያደረገውን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን የምታመልክ ቤተ ክርስቲያን ግፍና በደልን እያየች ዝም ልትል አትችልም ። ዝም ካለችማ የተጠራችበትን ለሚገፉት ጠበቃ የመሆን ዓላማዋን አሽቀንጥራ ጥላዋለች ማለት ነው ።

ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነቷን ከኢትዮጵያውያን ነጻነት ለይታ አታየውም ። የኢትዮጵያን ሕዝብ ነጻነት የማያከብር ማናቸውም ፖለቲካዊ ሥርዓት ፥ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ነጻነቷን ሊያከብርላት አይችልም ።

ክፍል ሁለት

የታሪክ ምስክርነት

የዚህ ጉባኤ አዘጋጆችና ታዳሚዎች ወገኖቻችን !! የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ሀገራዊ ታሪክ ውስጥ በመውደቁም በመነሣቱም ውስጥ ግንባር ቀደም ተዋናይ ነበረች ። እንዲሁ አሁንም ከፊት መሥመር ላይ ትገኛለች ።

ኢትዮጵያን በመገንባት ፣ በማሳደግ ፣ ድንበሯን በማስከበርና አንድነቷን በማጽናት ወዛቸውን ከደማቸው በመቀላቀል ደማቅ ታሪክ ፣ አኩሪ ሀገርና ፣ ኩሩ ሕዝብ ትተውልን ያለፉ ቀደምቶቻችን በጉዟቸው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን መሪዎችንና ታቦታቱን ከፊት በማስቀደም እንደ ነበር ታሪክ ያዘክረዋል ። የሀገራችን ታሪክ ሲጠና ከፊት ለፊት የሚታይ የሚጨበጥ የሚዳሰሰ ታሪክ ያለው ወይ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ፤ አልያም በቤተ ክርስቲያን የተሠራ ሁኖ ይገኛል ። ይህ ሊያስተባብሉት የሚችሉት ነገር አይደለም ። የኢትዮጵያን ማንነት ከኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለመለየት መሞከር የአውሮፓን ሥልጣኔ ከአውሮፓ ቤተ ክርስቲያን ወይም የመካከለኛው ምሥራቅን ባህል ከእስልምና ውጪ ለማቅረብ የመሞከር ዓይነት ከንቱ ልፋት ነው ። ቤተ ክርስቲያን የሀገሪቱ ሕዝብ ማንነት ከተሸመነባቸው ዋና ድሮችና ማጎች አንዷና ዋነኛዋ ናት ። ይህ በጎው ነው ።

በአንጻሩ ደግሞ ኢትዮጵያን ለማዳከምና ብሎም ለማፍረስ ፣ ሉዓላዊነቷን በመድፈር ፣ ሕዝቧን በማሰቃየትና በመግደል ፣ ታሪኳንና ባህሏን በማጥፋት ፣ በአጠቃላይ ሀገራዊ ህልውናዋንና የሕዝቧን አንድነት ፣ ሰላምና ነጻነት አደጋ ላይ የጣሉ ኃይሎች በሙሉ ማለት ይቻላል ተቀዳሚ የጥቃት ዒላማቸው የሚያደርጉት ይህቺኑ ቤተ ክርስቲያን ነው ።

ይህን ለመረዳት ብዙ የምርምር ሥራ መሥራት አስፈላጊያችን አይደለም ። ሌላው ቀርቶ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን ጥብቅ ውሕደት መቀበል የማይፈልጉ ወገኖች በምርምርና በእኵልነት ስም መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለውን ኢትዮጵያ የሚል ስም እንኳ ሳይቀር ለእነርሱ አጀንዳ እንዲመቻቸው ቀይረው አንዴ ሱዳን ሌላ ጊዜ ኩሽ ሲሉ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ታዝበናል ።

ይህ ሥራ ሲካሄድ በኢትዮጵያ ያለው በመንግሥት የተወከለው አካል አንድም ቃል ሲተነፍስ አልታየም ። በዚያ ፈንታ ሕጋዊውን ቅዱስ ሲኖዶስ ሲያጥላላ ፥ ስም ሲስጥ ፣ በስደት ያለውን ማኅበረ ሰብ እንኳ እንዳያገለግልና የእነርሱን ጥፋት እንዳያጋልጥ ዘመቻ ሲያቀናብር ሃያ አራት ሰዓት ዕረፍት የለውም ። ሕዝቡም ጠላት የሰጠውን ስድብና የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቀብሎ የገዛ ቤተ ክርስቲያኑን የሚያገለግሉትን አባቶቹን እየሰደበ ፣ ማኅበረሰባዊ ራስን የማጥፋት ትንቅንቅ ላይ ይገኛል ።

ቆም ብሎ ማስተዋል ይገባል ! ዐውደ ምሕረት ላይ ሰው በሽጉጥ የተገደለው በማን የፕትርክና ዘመን ነበር ? 1993 ለተቃውሞ ሰልፍ ወጥተው ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው የነበሩ ተማሪዎችን አሳልፎ እንደ እባብ ለቀጠቀጣቸው የመንግሥት ኃይል የሰጠው ማን ነበር ? 1997 ያ ሁሉ ደም ሲፈስስ ሕዝቡን ጥፋተኛ አድርጎ ወንጅሎ መግለጫ ያወጣው ማን ነበር ? ከዚያም በኋላ በተደጋጋሚ ሕዝብና መንግሥት ሲጋጩ በቤተ ክርስቲያን ስም ሕዝቡን ጥፋተኛ እያደረገ በአደባባይ የወነጀለ ማን ነበር ? እልፍ አእላፍ በግፍ ሲታሠሩና ሲገደሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ በቤተ ክርስቲያን ስም ስለ ልማትና ዕድገት የደሰኮረልን ማን ነበር ? ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ !

የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ! ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰዎችን ምንነት ስለ መለየት ባስተማረበት ክፍል “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” እንዳለው ሁሉ የማንኛውም ግለ ሰብ ሆነ ስብስብ መታወቂያው ዕለት በዕለት የሚሠራው ሥራ ነው ። የቋንቋ ልዩነትን መሠረት ያደረገው በአንድ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሰለጠነው መንግሥት እንደ ቀደሙት ፀረ-ኢትዮጵያውያን ሁሉ የሰሜኑን የሀገራችን ክፍለ ሀገር ኤርትራን አስገንጥዬ ፣ ትግራይን እገነጥላለሁ ብሎ ሲነሣ ቀጥተኛ ትርጉሙ ኢትዮጵያን አፈርሳለሁ ማለት ነው ።

አላማዬን ለማሳካት እንቅፋት ይሆናሉ በሚል በቅድሚያ እንዲጠፉ ከተፈረደባቸውና በግንባር ቀደምትነት የጥቃት ኢላማ ከተደረጉት ሁለት ዋነኛ አካላት መካከል ይህቺው ቤተ ክርስቲያናችን አንዷ ናት። የዚህ ማሳያ ሁኖ የሚቀርበው ለራሱ ሥራ አስፈጻሚ ይሆኑ ዘንድ የመደባቸው ሟቹ አባ ጳውሎስ የሥራ ቀናቸውን የጀመሩት የኢትዮጵያን መልክአ ምድር ቅርጽ ይዞ የነበረውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዓርማ በመቀየር ነው ።

ይሁን እንጂ ፣ ኢትዮጵያ በቀላሉ የምትፈራርስ ሁና አትታይም ! የሕዝቧን አንድነት ፣ ሰላምና ነጻነት እናስከብራለን ብላችሁ የምትደክሙ ወገኖቻችን ! እንደ ቀደሙት የሀገራችንና የሕዝባችን ባለውለታ አባቶቻችን በመንገዳችሁ ያስቀደማችሁት ፣ በጉባኤዎቻችሁ የምትጋብዙትና ፣ የትግላችሁ አጋር ያደረጋችሁት ይህቺኑ ቤተ ክርስቲያን ነው ። በዚህም ቅዱስ ሲኖዶሱ እጅግ በጣም ደስተኛ ነው ።

ውድ ወገኖቻችን !! ዛሬ በዚህ ቦታ ከእናንተ ጋር በዚህ ጉባኤ በመገኘት ስለምንወዳት ሀገራችንና ስለምንሳሳለት ሕዝባችን አንድነት ፣ ሰላምና ህልውና ስንመክር በቀደሙት ደጋግና እውነተኛ አባቶቻችን እግር ሥር ስለ መተካታችንና የነሱንም ፈለግ ተከትለን እየተጓዝን ስለ መሆናችን ማረጋገጫ ይሰጠናል ። በዚህም አባቶቻችን የሰጡንን የነጻነት ዓርማ ይዘን አሁን ያለብንን ብዙ ዓይነት ችግር በድል እንደምንወጣው ተስፋችን ብሩህ ፥ እምነታችንም ጽኑ ነው ። ይኽ ችግራችን እግዚአብሔር ለኢትዮጵያ ከአለው መለኮታዊ አላማና ከእኛ እነድነት በላይ አይደለም

በአንጻሩ ደግሞ ከእናንተ ጋር በመሆናችን የተደሰትነውን ያህል በዘር ላይ ብቻ ተመሥርቶ በመንግሥት ስም የተቀመጠው  በመንግሥት ስም በተቀመጠውና በግብረ አበሮቹ በመገፋታችንና በመሳደዳችን እንዲሁ እጅግ ደስተኞች ነን ። ምክንያቱም የእኛ ስደት የኢትዮጵያን አንድነትና ሉዓላዊነት ለማፍረስ አቅደውና አልመው በተነሡ ፣ የሕዝብን ሰላምና ነጻነት በጠመንጃ ኃይል በቀሙ ፀረ-ሰላም ኃይሎች አሳዳጅነት በመሆኑ ነው ። በዚህም የእውነተኞቹ አባቶቻችን የእነ አቡነ ጴጥሮስና የእነ አቡነ ሚካኤል ልጆች የመሆን ዕድልን አግኝተናል ። በአንጻሩም አሳዳጆቻችን በምግባራቸው የእነማን ልጆች ስለመሆናቸው ነጋሪ አያሻውም ። ለዚህም ታሪክ ሕያው ምስክር ነው ።

ክፍል 3

የቤተክርስቲያን የመፍትሔ ሐሳብ

ይቅርታና ዕርቅ

አማኙ ማኅበረሰብና ሌላውም ዜጋ በጠቅላላው ምን ቢያደርግ አሁን ካለንበት አጣብቂኝ ውስጥ መውጣት ይችላል ? ይህን ጥያቄ ለመመለስ የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስቀድሞ መጠየቅ ግድ ነው ።

ሀ/ እስካሁን ድረስ ኢትዮጵያ ዛሬ ከምትገኝበት ችግር ላይ እንዳትደርስ መደረግ የነበረበት ፣ ነገር ግን ሳይደረግ የቀረ ያልተሞከረ መፍትሔ ምንድን ነው ?

ለ/ የተሞከረውና ያልተሳካውስ ምንድን ነው ?

ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ከተቻለ ችግሩን ለመፍታት የምንሄድበትን አቅጣጫ በግልጽ እናየዋለን ። ከዚህ በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎችን በማቋቋምና ያሉትንም ለማስተባበር ተደጋጋሚ ጥረቶች ተደርገዋል ። በኢትዮጵያ ከመቶ በላይ ፓርቲዎች ተቋቁመው እንደ ነበር መረጃዎች ያሳያሉ ። አሁንም እንኳ የተለየያዩ በቋንቋና በዘር የተቋቋሙ ፓርቲዎች አንድ ልንሆን ነው እያሉ በየጊዜው መግለጫ ይሰጣሉ ። ለየብቻ ያሉትንና በውል የታወቁትን ከቆጠርን ከሃምሳ በላይ ፓርቲዎች አሉ ። ነገር ግን እነዚህ ፓርቲዎች በልዩ ልዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች የተነሣ ለሕዝቡ ማበርከት የሚገባቸውን አገልግሎት መስጠት ተስኗቸው እዚህ ደርሰናል ። ስለዚህ ዛሬ አዲስ ፓርቲ መመሥረት ለችግራችን መፍትሔ ሊሆን አይችልም ።

ፓርቲዎችን የሚያስተባብር ኮሚቴ ለማቋቋም መሞከርም ከዚህ ቀደም ከታየው ተሞክሮ በመነሣት ዛሬ ላለው ችግር መፍትሔ ሊያመጣ አይችልም ። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ ፓርቲዎችን ለማስተባበር ተሞክሯል ። ሙከራዎቹ ሁሉ ግን ከማስተባበር ይልቅ በማለያየት ፣ ከማቀራረብ ይልቅ በማራራቅ ሲጠናቀቁ ተመልክተናል ። አንዳንድ የአስተባባሪ ኮሚቴዎችም ፓርቲዎችን ይበልጥ ከማራራቅም አልፈው የራሳቸውን ፓርቲ ወደ ማቋቋም ደርሰዋል ።

የፓርቲዎች ውሕደትስ ? በዚህ ውጥረት በተሞላ ጊዜ ውስጥ ለማካኼድ መሞከር በራሱ ችግር ፈጣሪ ሊሆን ይችላል ። ከዚህ በፊት ፓርቲዎች ተባበሩ ተብሎ የተመሠረቱት እንደ ኢድሀቅ ቅንጅት ፥ ኅብረት ፥ መድረክ ፥ ኢሕአዴግ ፥ ወዘተ ችግር ፈቺ ከመሆን ይልቅ የሀገሪቱ ችግር አካል ሁነው ታይተዋል። በመሆኑም ፣ ዛሬ የፓርቲዎች ኅብረት ወይም ውሕደት ለመመሥረት መሞከሩ ለኢትዮጵያ ችግር አፋጣኝ መፍትሔ የማምጣት ዐቅሙ ሚዛን የሚደፋ አይደለም ።

*ፖለቲከኞችን አስተባብሮ አሁን ያለውን ሥርዓት ለውጦ የሽግግር መንግሥት ቢቋቋምስ ? ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪኳ ሦስት የሽግግር መንግሥታትን አይታለች-

= የልዑል አልጋ ወራሽ የሽግግር መንግሥት ፣

= የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ መንግሥት ፣

= የኢሕአዴግ የሽግግር መንግሥት” ።

እነዚህ ሦስቱም የሽግግር መንግሥት እየተባሉ ቢቋቋሙም ሀገሪቱን ከጭንቅ ወደ እፎይታ ፣ ከጭቆና አገዛዝ ወደ ሕዝባዊ መንግሥት የወሰዱ አልነበሩም ። ይልቁንም ሁሉም የአገዛዝን ቀንበር በሕዝቡ ጫንቃ ላይ በመጫን ዛሬ ካለንበት የጥፋት አፋፍ አድርሰውናል ።

ታዲያ ምን ይሻላል ? ቤተ ክርስቲያን ምን ብታደርግ ከዚህ ሀገራዊ አጣብቂኝ መውጣት እንችላለን ? ላለፉት አንድ መቶ ዓመታት መንግሥት አፍርሶ መንግሥት በመተካት የመገዳደልና የበቀል መንፈስ ተጠምደን እዚህ ግባ የሚባል የሕዝቡን ሕይወት የሚለውጥ የልማት ሥራ ሳንሠራ ይኸውና አራት ትውልድ አለፈ ። እነሆ አሁን የህልውናችን ጉዳይም ጥያቄ ውስጥ ከገባበት ዘመን ላይ ደረስን ።

በግፍ የሚፈስ የንጹሐን ደም መዘዙ ብዙ እንደ ሆነ ከመጽሐፍ ቅዱስም ከታሪክም እንማራለን ። ትናንት በግፍ የፈሰሰ ደም ለዛሬ መከራ ከዳረገን ፣ ዛሬ የሚፈስሰው ደም ምን እንደሚያመጣ ለምን ማስተዋል ተሳነን ? የትናንት ፖለቲከኞች እርስ በርስ መበላላት ለዛሬው መከራ ዳርጎናል ። ዛሬ ካለፈው ተምረን እርስ በርሳቸው የማይበላሉ ፖለቲከኞች ማየት ያልቻልነው ለምንድነው ? አንድን ስሕተት ደግመን ደጋግመን እየሠራን ከቅድሙ መጥፎ ውጤት የተለየ ውጤት የምንጠብቀውስ ስለ ምን ይሆን? አልበርት አንስታይን“Insanity is doing something over and over again and expecting something different.” ይላል ።

ክፉውን ያርቅልንና ፣ አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ከፍተኛ የሕዝብ ዕልቂት በሦስት መንገዶች ሊፈጠር ይችላል ።

ሀ/ በገዢው አካል በሚቀነባበር ሤራ ምክንያት ።

ገዢው አካል አሁን ካለው ነባራዊ ሁኔታ እንደምናስተውለው ሁለት አማራጮች ብቻ ያሉት ይመስላል ።

አንደኛው ሀገር ማስተዳደር እንደ ተሳነው በማመን ለራሱ የመውጫ መንገድ አበጅቶ የአደራ መንግሥት በመመሥረት ገለል ማለት ነው ።

ሁለተኛው ደግሞ ፣ አሁን እየሆነ እንዳለው በአምባ ገነንነቱ ቀጥሎበት የቻለውን ያህል ሕዝቡን ፈጅቶና አፋጅቶ በመጨረሻ ራሱ መጥፋት ነው ። ዛሬ አገዛዙ የያዘው መንገድ በዚህኛው ትልም ላይ ያለ ስለ ሆነ ከዚህ የጥፋት መንገድ ለማምለጥ የሚደረገው ጥረት በይደር የሚተው አይደለም ።

ለ/ ልዩ ልዩ ፍላጎቶች ባሏቸው የፖለቲካ ቡድኖች ምክንያት ።

በሀገሪቱ ያለው ማዕከላዊ አስተዳደር መዳከም በልዩ ልዩ ቦታ የሚገኙ ቡድኖች ኃይል እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል ። የእነዚህ ቡድኖች መጎልበት በራሱ መጥፎ ባይሆንም ቡድኖቹ ከሀገራዊ ራእይ ይልቅ ጥቃቅን አካባቢያዊ ጥቅሞች ላይ ብቻ በማተኮር ጠላቶቻችን ያሏቸውን ወደ መፍጀት ሊያመሩ ይችላሉ ። ይህ አሁን በዓይናችን የምናየው የሶማሌና የኦሮሞ ግጭት ፣ አንዱን አማርኛ ተናጋሪ ሕዝብ “ሁለት ነህ ! የአንተ ስም ቅማንት ነው !” “የአንተ ደግሞ አማራ ነው !” “አንተ በእርሱ ስትጨቆን ኑረሃል ፤ ለዚህ ጭቆና እኔ መፍትሔ ይዣለሁ ። የያዝኩት መፍትሔ እርስ በርስህ ስትጋደል ብቻ ነው” በማለት መሣሪያ ወድሮ ሳንጃ መዞ ለማጋደል የተጠነሰሰው የጥፋት መጠጥ ውሱን ጥቅመኞች ለመጠጣት ተዘጋጅተዋል ። ይህ ለእነርሱ የሚጠቅም ይምሰላቸው እንጂ መጨረሻው መላው ምሥራቅ አፍሪካን ለውድመትና ለቀውስ ሊዳርግ የሚችል አደጋ ነው ። በሦስተኛው ዓለም ውስጥ ያለች የ100 ሚሊየን ሕዝብ ሀገር ስትፈራርስ የአካባቢው ፖለቲካዊና ምጣኔ ሀብታዊ ሕይወት በነበረበት ይቀጥላል ብሎ ማሰብ ትልቅ ጭፍንነት ነው ።

በመሆኑም የፖለቲካ ፓርቲዎችና የፖለቲካ አቀንቃኞች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ በጥበብና በሀገራዊ ተስፋ ላይ መመሥረት እንዳለበት አበክሮ ማሳሰብ ያስፈልጋል ። ሀገራዊ ተስፋን ችላ በማለት ጊዜያዊ ቀበሌያዊ ሥልጣንና የቢሆን ዓለም ምኞታቸውን (utopia) ብቻ እንከተላለን ቢሉ የሚሠሩት ስሕተት የኢትዮጵያን ሕዝብ እጅግ በጣም ከባድ የደም ዋጋ ሊያስከፍለው እንደሚችል መገንዘብ አለባቸው ። ሕዝቡ የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ሰለባ በመሆን በጎሪጥ እንዳይተያይ ሀገራዊ ተስፋ ላይ የተመሠረተ ከፍተኛ ሕዝብን የማንቃትና ተስፋን የማስጨበጥ ሥራ የመሥራት ኃላፊነት እንዳለባቸው ሊገነዘቡ ይገባል ። በዚህ ረገድ እነርሱ ላይ ከፍ ያለና የማያቋርጥ የውትውታና የማሳሰብ ሥራ መሠራት አለበት ።

ሐ/ የተበዳይነት ስሜት ባዘሉ ሰዎች ቂም ምክንያት ።

ሌላው አስፈሪውና የእልቂት ደመና ያንዣበበው በሀገሪቱ ውስጥ ላለፉት 26 ዓመታት በኢሕአዴግ ጎሠኛና ጨቋኝ አገዛዝ የተፈጸመው ተቆጥሮ የማያልቅ ግፍ በብዙ ሰዎች ላይ ያልሻረ ቁስልና የግንባር ጠባሳ ማሳረፉ ነው ። የአገዛዙ ዐቅም ማጣት እነዚህ ግለሰቦች አጠቁን በሚሏቸው ሰዎች ላይ ቂማቸውን የሚወጡበት አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላል ። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ ደግሰውልን የነበረውን የሩዋንዳ እልቂት በሰው አእምሮ አስቀምጠው አልፈዋል ። ዛሬም ቢሆን አሉ ከሚባሉ የመለስ ራእዮች አንዱ ይህ መሆኑን አሁን በዓየናችን እያየነው ነው ። ይህ ግን ማኅበረሰቡን ወደማያልቅ የመገዳደል አዙሪት ከመድፈቅ ውጪ የሚፈውሰው አንድም ማኅበረሰባዊም ሆነ ግለሰባዊ ነቀርሳ እንደሌለ የማሳመን ከፍተኛ ሥራ ይጠበቅብናል ። በተለይ የሃይማኖት ተቋማት በዚህ ረገድ ከፍተኛ ኃላፊነት እንዳለብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በጽኑዕ ታምናለች ።

ሕዝብን ከእልቂት ለማዳን የሚያስፈልጉ ሦስት ዋና ዋና ጉዳዮች

ለእንዲህ ያለ ድርጅት የሃይማኖት ተቋማት ትልቅ ተሳታፊ መሆን አለባቸው ። ከዚህም ጋር ፓርቲዎች ሕዝብን በሚያደራጁበት ወቅት ሀገራዊ ተስፋን እንጂ ማኅበረሰባዊ ቂምና ጠባሳ ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ የሚያቅብ የሥነ ምግባር ሕግ ማውጣት ፣ የምክርና የማስተባበር ሥራ መሥራት ሲሆን ከዚህ ጎን ለጎን የሚቀጥሉት ሥራዎች ደግሞ የሚከተሉት ሲሆኑ መተግበር ያለባቸውም በፖለቲከኞች ፥ በሀገር ሽማግሌዎችና በምሁራን ይሆናል ።

1/ ጊዜያዊ የአደራ መንግሥት ማቋቋም 

2/ ሕገ መንግሥት ማርቀቅ ።

3/ የይቅርታ የእርቅ  ኮሚሽን ማቋቋም

ቤተ ክርስቲያን እነዚህን  መፍትሔዎች መጠቆም እንጂ  እነዚህን ሁሉንም ራሷ   በኃላፊነት ተረክባ መሥራት አትችልም ። የይቅርታና የእርቁን ጉዳይ ግን ፥ ፈቃደኛ የሆኑ ኢትዮጵያውያንንና ሌሎችንም ሰላም ወዳድ ወገኖችን ይዛ መሥራት እንዳለባት ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል ።

የሚያፍለጉንና የምናደርጋቸው ጉዳዮ

1/ እውነተኝነትና ግልጽነት፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ «እውነትም አርነት ያወጣችኋል» ብሏል ። በኅብረተሰባችን ዘንድ አሁን የጠፋው መተማመን የሚለው ቃል ነው ። ቀድሞ ሲባል የምንሰማው “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” ነበር ። አሁን ግን የችግራችን ምንጭ የሆነው ድብቅ አጀንዳ የሚባለው ነገር ነው ። በአንድ ወቅት አንድ ስለ እውነት ፍልስፍና ያጠና ወንድም ስለ ኢትዮጵያውያን አብሮ የመሥራት ጅግር ሲናገር “ለእውነት ቦታ ያለ መስጠት ጅግር ነው” ይል ነበር ። የኢትዮጵያ ፖለቲካ በዚህ በእጅጉ ተጎድቷል ። አንዱ የፖለቲካ ድርጅት ሌላውን ማመን አይችልም ። በአንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ እንኳ ካለው አለመተማመን የተነሣ ብዙው ነገር ለገዛ አባላት ሳይቀር ምሥጢር ነው ።

አንድ ምሥጢር ያልሆነ ነገር አለ- እርሱም የኢትዮጵያውያን ተቆጥሮ የማያልቅ ችግር ነው ። ይህ ፈላስፋ ይህንኑ ጉዳይ ሲያብራራው ለእውነት ቦታ ስለማንሰጥ በቦታው እውነት ያልሆነ ነገር ይተካበታል ። ያ በእውነት ቦታ የተተካ እውነት ያልሆነ ነገር በግልጽ ሲቀመጥ ውሸት ይሆናል ። እያንዳንዱ ሰው ከዚህ እውነት ካልሆነ ነገር ላይ ልቡን ካሳረፈ በውሸት ላይ ቁሟል ማለት ነው ። ይህ ሰው ራሱ እውነት ስለሌለው ሌሎችን እያምንም ማለት ነው ። እርሱንም ሌሎች ሰዎች ባያምኑት አይደንቀውም ምክንያቱም እርሱም ያው ስለ ሆነ ።

ብዙዎች እንደሚያስቡት ሐሳብ የማመንጨትና መርሐ ግብር የመንደፍ ችግር የለም ። ችግሩ ያለው ሐሳብና ራእይን በአንድ ላይ አድርጎ መሄድ ላይ ነው ። ከዚህ የተሰበሰብን ሁላችን ለሕዝብ ዕድገት ለሀገር ብልጽግና እውነተኛ ግንዛቤ እንዲኖረን ያስፈልጋል ። መቼም ራስን ከማቃጠል የበለጠ ሌላ ሊታይ የሚችል የችግር መግለጫ ቋንቋ የለም ። ለሕዝብ ፍትሕ ቁሙ ። ደግሞም አጽናኑ ። እውነተኛ ሁኑ ። በአመክንዮ ላይ የተመሠረተ ውይይት ተወያዩ ። አንዱ ሲሠራ ሌላው አይቀልድ ። አንዱ ሲሞት ሌላው አይሳቅ ። ግትር አቋም በፖለቲካ የሚሠራ አይደለም ። ባለፉት አርባ ዓመታት ይደረግ የነበረ የሽኩቻና ያለመተማመን ፖለቲካ አካሄድ እስካሁን ድረስ ለፖለቲከኞቹ አልበጀም ። ለሕዝቡም መከራን እንጂ በረከትን አልሰፈረለትም ። ታዲያ ይህ ገና በውጥኑ የከሸፈ አካሄድ ስለ ምን በመተማመን ፣ በመደማመጥ መንገድ አይቀየርም ? የየትኛውም የሠለጠነ ሀገር ፖለቲካ በግትርነት ሲራመድ ታይቷልን ? መደማመጥን ፥ መቻቻልን ፥ በዚህ ጉዳይ ላይ ወንድሜ ከእኔ ይሻላል እርሱን ማድመጥ ይገባኛል ብሎ ማሰብን እንደ እሾህ የሚፈራ ትውልድ ቢሆንም መነገር ግን አለበት ። በአንድ ጉዳይ ላይ ልዩ ልዩ አመለካከት ያላቸው ሰዎች ሲነሡ አንጃ ተብለው ድምጥማጣቸው ይጠፋል ። ትግሉ  ሥልጣን መያዝን ሳይሆን ሀገራዊ ተስፋን ማዕከል ባደረገ መልኩ የጋራ ወደ ሆነ አስማሚ ነጥብ መጓዝ ግድ ይላል ። ለዚህ ደግሞ የሚጀመረው ከይቅርታና ከእርቅ ላይ ነው ።

2/ የይቅርታና የሰላም ሂደት ማካሄድ

የደቡብ አፍሪካው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞንድ ቱቱም የማኅበረሰባዊ ይቅርታን አስፈላጊነት ሲያሳስቡ “ያለ ይቅርታ የወደ ፊት መልካም ዕድል የሚባል ነገር የለም” ብለዋል ። “There is no future without forgiveness”

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዚህም ረገድ እንደሌላው ሁሉ እንዋሻለን ። እኔ ከማንም ጋር አልተጣላሁም እንላለን ። ግን ሁላችንም በበቀል መንፈስ የሰጠመ ልብ እንደያዝን አጋጣሚዎች ሁሉ ይመሰክሩብናል ። ለዚህም ዋነኛው ማሳያ ለበጎ ነገር አብረን መሥራት አለመቻላችን ነው ። ብዙዎቻችን ሳናውቀው በልባችን ያጠራቀምነው ቀን ጠብቆ የሚፈነዳ የቂም መግል በቀል አለብን ። ይህ መርዝ በይቅርታ ፈርጦ ካልተፈወሰ ቀን የሚጠብቅ ፈንጂ ነው ። ስለዚህም ይህን ማኅበራዊ ነቀርሳ መንግሎ ለማውጣት ቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰባዊ ይቅርታን በኃላፊነት መምራት ይገባታል ብሎ ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ያምናል ።

ፖለቲከኞች ኅብረት የሚሉት የፖለቲካ ስምምነት ብቻውን ፣ ለኢትዮጵያ ጥቅም አይሰጥም ። ይህ ዓይነት ስምምነት ፣ ከአሁን ቀደም ተሞክሮ ያልተሳካ ውጤት አምጥቶ ዛሬ ለሚዘንብብን የመከራ ዶፍ ዳርጎናል ።

የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ፣ ከስደት ተመልሶ ሕጋዊ መስተዳድር ሲያቋቁም ፣ ሦስቱን ቡድን አቀራርቦ በይቅርታና በዕርቅ ፣ ችግሩን በማቃለል ፈንታ በዐዋጅ አንድ ሁኑ በሚል ማስተዋል የጎደለው መንግሥታዊ ትእዛዝ ደም የተቃቡ ዐርበኛና ባንዳን ፣ በጎሪጥ የሚተያዩ ዐርበኛና ስደተኛን ፣ የሚጠላሉ ባንዳንና ስደተኛን በጉልበት አንድ ለማድረግ ተሞክሮ ነበር ።

ይህ ውሳኔ የንጉሡን ሥልጣን ለማቆየት ቢጠቅምም ማኅበረሰቡን ግን አንድ ከማድረግ ይልቅ በቂምና በጥላቻ ልቡ እየሻከረ እንዲሄድ አድርጎታል ። የደም አብዮት ወልዶ ፣ የደም ጦርነት አሳድጎ ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነት አናግቶ ፣ የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ንዶ ፣ እጅግ ክፉ የአገዛዝ ቀንበሮችን በሕዝቡ ጫንቃ ላይ ተክሎ ኼደ ። አሁንም መንፈሳዊ የይቅርታና የዕርቅ ሂደት ካልተከናወነና የማኅበረሰቡ መንፈስ በይቅርታ ካልታደሰ ፣ የፖለቲካ ሥርዓት ለውጥ ብቻውን ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሀገሪቱን ወደሚፈለገው የሰላምና የአንድነት ጉዞ ማድረስ አይችልም ።

በአሁኑ ጊዜ የሚጻፉ መጻሕፍት ፣ የሚያሳዩት ይህን ያለ ይቅርታና ዕርቅ የተደረገ በሰው ልጅነት መተዛዘንንና መደጋገፍን ሳይሆን እከክልኝ ልከክልህ የሚል ጊዜያዊ መጠቃቀምን ብቻ መሠረት ያደረጉ ስምምነቶችን ውጤቶች ነው ። ቀደም ሲል የተቋቋሙትን ኢድሀቅ ከተባለው የፖለቲካ አንድነት አንሥቶ አሁን አገራዊ ንቅናቄ እስከ ተባለው ድረስ ያሉትን ስምምነቶችና እነርሱንም ተንተረስው የሚጻፉትን ከ“ያ ትውልድ እስክ ባለቤት አልባ ከተማ” ድረስ ስንመለከት ፣ ውስጣዊ በቀልና ፉክክር የተሞሉ ናቸው ። በኅብረተ ሰባችን ያለውን የበቀል ጥርቅም በሚያሳዝን ሁኔታ ያስነብቡናል ። ለምሳሌ ያህል እነዚህን፣ ጥቂቶቹን ገለጽን እንጂ ፣ በየትኛውም በማኅበረ ሰባችን ውስጥ በየአቅጣጫው ያለው የበቀል ጥርቅም እንዲህ በቀላሉ ተገልጦ የሚያልቅ አይደለም ፤ ባጤኑት ቁጥር ልብ የሚያስበርግግ ይዘት አለው ።

በዚህ በቀል ውስጥ እንዳሉ ፣ አንድነት መመሥረት ማለት ፈንጅ በተጠመደበት ድልድይ ላይ እያወቀ መኪና እየነዳ በመሄድ ሞትን የመረጠ ሰው መሆን ነው ። ለዚህ መድኃኒቱ ዕርቅ ነው ። ቤተ ክርስቲያን ይህን ዕድል ተጠቅማ በአማራጭ ኃይሎች ወገን በኩል የሚከናወን የዕርቅና የሰላም ሂደት ማድረግ ያስፈልጋታል ብለን እናምናለን ። ምክንያቱም የቅዱስ ሲኖዶስ የስደቱ መነሻ በሀገሪቱ  የፖለቲካ ነጻነት አለመኖር  የሃይማኖት ነጻነትም እንዳይኖር ስለ አደረገው ነው ። በሌላ አባባል ቤተ ክርስቲያንም የዚሁ የመንግሥት ፖለቲካ ተጠቂ ስለ ሆነች ይመለከታታል ማለት ነው ።

በወያኔ ዘመነ መንግሥት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ይካሄድ የነበረውና አሁንም እየተካሄደ ያለውን የሃይማኖት ተጽዕኖ ስንመለከት ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ ግን ከዛሬ ሃያ አምስት ዓመት ጀምሮ የሃይማኖት ተጽዕኖ በመካሄድ ላይ ነው ። በዚያ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደት ፣ እንደ ግለሰቦች ጉዳይ ተደርጎ ነበር የተወሰደው ። ግን አሁንም የገዳማት መደፈር ፣ የአብያተ ክርስቲያናት መቃጠል ፣ እንደ ቀጠለ ነው ። አሁን እኛ ክዚህ እየተወያየን የኢየሩሳሌሙ ገዳማችን  በመፍረስ ላይ ነው አሁን በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንን የሚክል አካል ስለሌለ ምንም ነገ እንዳልተፈተረ ዝም ብለዋል ምንስ ሊሉ ይችላሉ የሚፈልጉት ከተሳካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን  መዳከም በዚህ ምክንያት ፣ በኢትዮጵያ የሕዝብንና የሃይማኖትን ነጻነት የሚያከብር መንግሥት እስኪቋቋም ድረስ ቤተ ክርስቲያን ጥረቷን ትቀጥላለች ። ከሥራዋም አንዱ ፣ ይህንን የሰላምና የዕርቅ ጉዞ በመሪነት ማከናወን ነው ።

ዛሬ በራሳችን ላይ ውሳኔ መወሰን ይኖርብናል ። አሁን ከስምምነት ያለፈ አንድነት ያስፈልጋል ። ከመቀናጀት ያለፈ አንድነት ያስፈልጋል ። አሁን ይቅርታን ለሀገራችንና ለሕዝባችን እንደ ሰጠነው ስጦታ አድርገን ልባችንን መክፈት ያስፈልጋል ። አሁን መጀመሪያ ራሳችን ከአምላካችን ይቅርታ መጠየቅና የተዘረጋችውን የይቅርታ እጁን በፍቅር መቀበል ያስፈልጋል ። ያን ባደረግን ጊዜ እኛ የይቅርታ ሰዎች እንሆናለን ። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ አንብቤ ሐሳቤን ልደምድም

«ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና  እርሱም  ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው  ነገር ግን እርስ በርሳችሁብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ» ። ገላ 5 ፥ 14-15 ።

እርስ በርስ ከመበላላት እርስ በራሳችን እንከባበር ፤ እንነጋገር ፥ ከሽፍታ ትክክለኛ ፍትሕ አንጠብቅም ። እኛ የፍትሕ ሰዎች ብንሆን ግን ፍትሕ ራሱ ከመካከላችን ይገኛል ። ከፍትሕም ሰላም ይመነጫል ። የሮም ሊቀ ጳጳሳት የነበሩት ዳግማዊ ዮሐንስ ጳውሎስ እንዳሉት “ያለ ፍትሕ ሰላም ፣ ያለ ይቅርታ ደግሞ ፍትሕ የለም (There is no peace without justice and there is no justice without forgiveness) 

[1] Russel, Bertrand. 1948. Power: A New Social Analysis.

[2] George Orwell. 1949. 1984.

ፓትርያርኩ የጠሩት የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ሳይካሔድ ቀረ

በቦታው የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ብቻ ናቸው ብዙዎቹ ዕለቱኑ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ እያሉም ያልተገኙ አሉ እንዳይገኙ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጥብቅ አዘዋል፤እስከ አየር ማረፊያ የሸኙም አሉ “ፓትርያርኩ ከቤተ ክህነቱ መዋቅር ላጡት ተቀባይነት ማሳያ ነው፤” ††† ትላንት በተጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ፍጻሜ ማግሥት፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው […]

via ፓትርያርኩ የጠሩት የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ሳይካሔድ ቀረ — ሐራ ዘተዋሕዶ

 • በቦታው የተገኙት የምሥራቅ ጎጃም ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ ብቻ ናቸው
 • ብዙዎቹ ዕለቱኑ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሲመለሱ እያሉም ያልተገኙ አሉ
 • እንዳይገኙ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጥብቅ አዘዋል፤እስከ አየር ማረፊያ የሸኙም አሉ
 • “ፓትርያርኩ ከቤተ ክህነቱ መዋቅር ላጡት ተቀባይነት ማሳያ ነው፤” 

ትላንት በተጠናቀቀው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ፍጻሜ ማግሥት፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል በድብቅ ጠርተውታል የተባለው የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ስብሰባ ሳይካሔድ መቅረቱ ተገለጸ፡፡

ስብሰባው፣ ለዛሬ፣ ጥቅምት 10 ቀን 2010 ዓ.ም.፣ ጠዋት 3፡00 ላይ በፓትርያርኩ ጽ/ቤት ተጠርቶ የነበረ ቢኾንም፣ ከአንድ ሀገረ ስብከት በቀር ብዙዎቹ ሥራ አስኪያጆች ወደ የአህጉረ ስብከታቸው በመመለሳቸው፣ አንዳንዶቹም በከተማው እያሉ ባለመገኘታቸው ሳይካሔድ እንቀደረ ተገልጿል፡፡

የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች በበኩላቸው፣ አጠቃላይ ጉባኤው የተጠናቀቀበትን መንፈስ ይዞ ስብሰባውን ማካሔዱ ፋይዳ እንደሌለው በመታመኑ፣ ትላንት ማምሻውን በተካሔደ ምክር እንዲሰረዝ መወሰኑን ነው የተናገሩት፡፡

በሥፍራው ተገኝተዋል የተባሉት፣ በብፁዕ አባ ማርቆስ የሚመራው የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ አባ ዕንባቆም ጫኔ ሲኾኑ፤ ስለሚናገሩበት ጉዳይ ከሊቀ ጳጳሱ ጋራ መክረው በስፋት ተዘጋጅተውበት እንደነበር ተነግሯል፡፡

ከእርሳቸው በቀር ሌሎች ተሰብሳቢዎች ባልተገኙበት ጧት፣ በመንበረ ፕትርክናው አካባቢ ለብቻቸው ሲዟዟሩ ታይተዋል፡፡ ምን እንደሚፈልጉና ምን ሊሠሩ እንደመጡ የፓትርያርኩ ረድእ መላልሰው ሲጠይቋቸውም ነበር፣ ተብሏል፡፡

የደብረ ማርቆሱ ሥራ አስኪያጅ ለአጠቃላይ ጉባኤው ባቀረቡት ሪፖርት፣ በሀገረ ስብከቱ የማኅበረ ቅዱሳንና የሰንበት ት/ቤቶች አባላት ላይ በርካታ ሐሰተኛ ውንጀላዎችን ያሰሙ በመኾኑ፤ ፓትርያርኩ ለዛሬ ጠርተውት የነበረው ስብሰባ ቢካሔድም ከዚሁ የተለየ እንደማያስረዱ ነው የተመለከተው፡፡

ፓትርያርኩ፣ “ጥብቅ መመሪያ” እያሉ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በጻፏቸው ደብዳቤዎች፣ ማኅበረ ቅዱሳን፣ “የሕግ አግባብነትና ድጋፍ እንደሌለውና ዛሬም ኾነ ለወደፊት በቤተ ክርስቲያን ስም እንዳይጠቀም የሚያስችል መመሪያ ተፋጥኖ ሥራ ላይ እንዲውል”አዝዘዋል፡፡

መመሪያው፣ የማኅበሩን አገልግሎት የሚያውቀውን የቅዱስ ሲኖዶስ(ቋሚ ሲኖዶስና ምልአተ ጉባኤ) ውሳኔ ያላገኘ ሕገ ወጥ በመኾኑ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ውድቅ ተደርጓል፤ ከአጠቃላይ ጉባኤው ሒደት ጋራ በተያያዘም የነበረው ተፈጻሚነት የተሸራረፈ ነበር፤ እንዲያውም፣ ጥቅሙ ለማኅበሩ አመዝኖ ፓትርያርኩ ማየትና መስማት የማይፈልጉትን ትርፍ ነው ያስገኘለት፡፡

ፓትርያርኩ፣ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችን ስብሰባ የጠሩት፣ ማኅበሩንና አባላቱን ከአህጉረ ስብከቱ ጋራ ተቀናጅተው እንዳይሠሩ በማራራቅ፣ ዳግመኛ እንዲህ ዓይነት ሪፖርት እንዳያቀርቡ መመሪያ ለመስጠት ነበር፡፡

36ኛው ዓመታዊ ስብሰባ ትላንት ቀትር ላይ ሲጠናቀቅ፣ ከዚህ በኋላ የሚኖረው ስብሰባ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ብቻ እንደኾነ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ በአጽንዖት ማሳወቃቸውና ጉባኤተኞችም ወደየሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ ማሳሰባቸው፣ ፓትርያርኩ ስለጠሩት ስብሰባ እንደሚያውቁና አግባብነት ስለሌለውም እንዳይሳተፉ ለማስጠንቀቅ እንደኾነ ታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት፣ ሰኞ ለሚመጀረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ዐዲስ አበባ የሚሰነብቱት ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ሥራ አስኪያጆቻቸው በስብሰባው እንዳይገኙና ወደ የሀገረ ስብከታቸው እንዲመለሱ በጥብቅ አሳስበዋል፡፡ በተለይም፣ ፓትርያርኩ፣ በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ላይ በሰነዘሩት ዘለፋ ከተቆጡ አባቶች፣ ሥራ አስኪያጆቻቸውን እስከ አየር ማረፊያ ድረስ ሔደው የሸኙ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡

“ሀገረ ስብከት” ማለት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተለይቶ የተከለለና በሊቀ ጳጳስ ወይም በኤጲስ ቆጶስ የሚመራ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ክልል ነው፡፡ በክፍሉ/በዞኑ/ ለሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት፣ አጠቃላይ አመራርና አስተዳደር የሚሰጥ የሥራ አስፈጻሚ አካል በመኾኑ፣ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ተጠሪነት ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት ነው፡፡ የሥራ አስኪያጁ ተጠሪነት ለሊቀ ጳጳሱ፣ የሊቀ ጳጳሱም ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ በመኾኑ፣ ፓትርያርኩ በራሳቸውና በቀጥታ ሥራ አስኪያጆችን ጠርተው መሰል ሕገ ወጥ መመሪያ ሊያስተላልፉ የሚችሉበት አግባብ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑም ይኹን በሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ደንቡ(ቃለ ዐዋዲው) የለም፡፡

ከሥራ አስፈጻሚው አካል በውል የተዘጋጀ የጥሪ ደብዳቤ ሳይኖር፣ ለሥራ አስኪያጆቹ በግል በመንገር ስብሰባውን የጠራው የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ ለፓትርያርኩ የአስተዳደር አገልግሎት ድጋፍና ለጽሕፈት ነክ ሥራዎች ብቻ የታሰበ ቢኾንም፣ ያለአግባብ ራሱን ከፍተኛ የመዋቅርና የሥልጣን አካል አድርጎ እየሠራ ይገኛል፡፡ ይህም፣ ለሕግና ሥርዓት መዛባት፣ ለመልካም አስተዳደር ዕጦትና ለመሳሰሉት ችግሮች ቀዳዳ የከፈተ አሠራር ኾኖ እንደሚታይ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡

ዛሬም፣ ካለአንዱ በቀር ከ48 ያላነሱ የአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ‘ቦይኮት’ የተደረገው ስብሰባው፣ ከአሠራር ብልሽቱ ጋራ ተያይዞ የፓትርያርኩ ተቀባይነትና ተደማጭነት ማጣት፣ በመካከለኛው የቤተ ክህነቱ መዋቅርም በግልጽ የታየበት ተደርጎ ተወስዷል፡፡

 

ፓትርያርኩ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ በቃል ጠየቁ፤ ጫና ለማሳደር የታሰበ ስልት መኾኑ ተጠቆመ

ከሥልጣን የመገለል ስጋት ባይኖራቸውም፣ተገቢነታቸው ብርቱ ጥያቄ እየተነሣበት ነው “በአቅም ማነስ ያጡትን ተቀባይነት ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ነው፤” ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ምክር የሰጡት ምላሽ፣ ብዙዎችን ቢያሳዝንም ሊያግዷቸውም ዛቱ የተወነጀሉት ብፁዕነታቸው፣ በምልአተ ጉባኤ እና በሕግም እንደሚጠይቋቸው ተጠቆመ በሀ/ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡት ብፁዕ አባ ማርቆስ፣በቦታቸው ለመተካት እየሠሩ ነው ††† ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው ተቀባይነት እያጣ መምጣቱ በብርቱ አሳስቧቸዋል የተባሉት፣ ፓትርያርክ […]

via ሰበር ዜና – ፓትርያርኩ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ በቃል ጠየቁ፤ ጫና ለማሳደር የታሰበ ስልት መኾኑ ተጠቆመ — ሐራ ዘተዋሕዶ

 • ከሥልጣን የመገለል ስጋት ባይኖራቸውም፣ተገቢነታቸው ብርቱ ጥያቄ እየተነሣበት ነው
 • “በአቅም ማነስ ያጡትን ተቀባይነት ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ነው፤”
 • ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ምክር የሰጡት ምላሽ፣ ብዙዎችን ቢያሳዝንም ሊያግዷቸውም ዛቱ
 • የተወነጀሉት ብፁዕነታቸው፣ በምልአተ ጉባኤ እና በሕግም እንደሚጠይቋቸው ተጠቆመ
 • በሀ/ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡት ብፁዕ አባ ማርቆስ፣በቦታቸው ለመተካት እየሠሩ ነው

ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው ተቀባይነት እያጣ መምጣቱ በብርቱ አሳስቧቸዋል የተባሉት፣ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ “መሥራት አልቻልኩም፤” ሲሉ ከሓላፊነታቸው ለመልቀቅ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በቃል ጥያቄ ማቅረባቸው ተሰማ፡፡

ፓትርያርኩ ጥያቄውን ያቀረቡት፣ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ አውጭና ወሳኝ አካል ከኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ እና ከሥራ አስፈጻሚው የጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደራዊ አካል ጋራ ያላቸው ግንኙነት ከፍተኛ ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየታየ ባለበት ወቅታዊ ኹኔታ ውስጥ ነው፡፡

“መፍትሔ ሊሰጠኝ ይገባል፤” በማለት በሓላፊነታቸው ለመቀጠል እንደተቸገሩ በቃል ለከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መናገራቸውንና በቅርቡም በጽሑፍ እንደሚያሳውቁ ነው፣ ምንጮች የጠቆሙት፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የፓትርያርኩ ሢመትና ርደት ጉዳይ የሚወስነው ቅዱስ ሲኖዶስ ኾኖ ሳለ፣ ጥያቄያቸውን ለባለሥልጣናት ማቅረባቸው፣ በቅዱስ ሲኖዶስና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዘንድ በአስከፊ ኹኔታ እያጡ የመጡትን ተደማጭነትና ተቀባይነት በተጽዕኖ ለመመለስ፣ ከአማካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት መኾኑን እንደሚያሳይ ተነግሯል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱ፣ የመጀመሪያ ዓመታዊ የምልአተ ጉባኤ ስብሰባ፣ ከነገ በስቲያ፣ ጥቅምት 12 ቀን እንደሚጀመር እያወቁ፣ ከሓላፊነት ለመልቀቅ ጠይቀዋል፤ መባሉ ይህንኑ ጫና የማሳደር ስልታዊነቱን እንደሚያረጋግጥ ነው የተገለጸው፡፡

ማኅበረ ቅዱሳን ጋራ በተያያዘ የሚያቀርቡት የእግድ አጀንዳ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ አካላት(ቋሚ ሲኖዶስ እና ምልአተ ጉባኤ) ውድቅ መደረጉ፤ ቡድን ፈጥረው እየመከሩ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሚያስተላልፉት መመሪያ መሸራረፉ ሕመም እንደኾነባቸው ነው የተስተዋለው፡፡

የማኅበሩ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሥርጭት፣ ከቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ውጭ እንዲታገድ ያስተላለፉት መመሪያ ተፈጻሚነት ሲያጣ፣ ከአጠቃላይ ጉባኤው 36ኛ ዓመታዊ ስብሰባ ተሳትፎ እንዲታገድ ወደ ማዘዝ ቢሸጋገሩም፣ እንዳሰቡት ሳይሳካላቸው ቀርቶ፣ በተፃራሪው፣ የማኅበሩ የማዕከልና የአህጉረ ስብከት ሥራዎች በጉልሕ እንዲስተጋቡ ምክንያት ኾኗል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤው መክፈቻ ምሽት፣ የማኅበሩ ተወካዮች እንዳይሳተፉ በማድረጋቸው፣ “የእኛን ሥልጣን ማወቅ አለባቸው፤ ሥልጣናችንን መረዳት አለባቸው፤” በማለት ከእነብፁዕ አባ ሩፋኤል፣ ብፁዕ አባ ማርቆስ እና ብፁዕ አባ ቶማስ ጋራ ውሎውን የገመገሙ ቢኾንም፤ በቀጣዩ ቀን፣ ማኅበሩ ከአህጉረ ስብከት ጋራ በመቀናጀት ያከናወናቸው ተግባራት በድምቀት እየተነገሩ በመዋላቸው፣ በጋራ መግለጫውና ቃለ ጉባኤው ላይ፣ የቴሌቭዥን ሥርጭቱ ሕገ ወጥ እንደኾነና እንዲዘጋ የሚጠይቅ አንቀጽ በጣልቃ እንዲገባ አርቃቂዎቹን አዝዘዋል፡፡ ሐሳቡን የተቃወሙ የአርቃቂ ኮሚቴው ሦስት አባላት፣ “የማኅበር ተላላኪዎች” ተብለው በሰብሳቢው የተዘለፉ ሲኾን፣ ሥርዋጹም በግድ እንዲገባና በድፍረት እንዲነበብ ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ ጉባኤው ያልተነሣ ጉዳይ በቃለ ጉባኤው የውሳኔ ሐሳብ ተብሎ መስፈሩ አግባብነት እንደሌለው ወዲያውኑ ከጉባኤተኛው ተቃውሞ የተሰማበትና በምክትል ሰብሳቢው ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁም ክፉኛ ቢተችም፣ ርእሰ መንበር የኾኑት ፓትርያርኩ ግን ሕገ ወጥነቱን ነው የተከላከሉት፡፡ ስሕተቶችን በፍጥነት እያረሙ፣ የአጠቃላይ ጉባኤውን ሒደት በጥብቅ እየተቆጣጠሩ፣ ማኅበሩን የማስወገዝና ሥልጣናቸውን የማግነን ምክራቸውን ያፈረሱባቸውን ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን፣ የመዝጊያ ንግግር እንዳደርግ ስለ ፈቀዱልኝ አመሰግናለሁ፤” በማለት በማጠቃለያ ቃለ ምዕዳናቸው በአሽሙር መናገራቸውም ተሰብሳቢዎችን ፈገግ አሰኝቷል፡፡

የቤቱን ፈገግታ ያከሰመው፣ የፓትርያርኩ ክብረ ነክ ንግግር ግን ወዲያው ነበር የተሰማው፡፡ “ተናግሮ አናጋሪ የትላንቱ ሰውዬ” ያሏቸውን ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን በመዝለፍ፣ ለአጠቃላይ ጉባኤውም ለመንበረ ፕትርክናውም ክብር በማይመጥን ንግግር፥ ደጋፊዎቻቸውን ሳይቀር አሳፍረዋል፡፡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በእጅጉ አዝነዋል፤ ቁጣቸውን በግልጽ ያሳዩም ነበሩ፡፡

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል፣ ፓትርያርኩ በሚሰጧቸው ሕገ ወጥና ረብሕ የለሽ መመሪያዎች እንዲጠነቀቁ፣ የቤተ ክርስቲያን ልጆችን አቅርበው ማነጋገርን እንዲያስቀድሙ ነበር ምሳሌያዊ ምክር የሰጡት፤ ቅዱስ ሲኖዶሱንም ያሳሰቡት፡፡ እንደተለመደው ግን፣ በዚያው ዕለት ማምሻውን፣ በተጠቀሱት ክፉ አማካሪዎች፣ ምሳሌያዊ ምክሩ በአሉታ እየተተነተነ የፓትርያርኩ ቁጣ እንዲጋጋም መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

“አቡነ ፋኑኤል፣ በፈንጅና ጭስ መስለው የተናገሩትን [አማካሪዎቻቸው]ይዘው፣ ቅዱስነትዎ የሚጽፉት ደብዳቤ ከዚህ ግቢ ውጭ የማይሠራና አቅም የሌለው እንደኾነ፤ ምንም ቢጽፉ የትኛውም አካል የማያስፈጽመው ነው፤ ነገር ግን መነጋገርያ እየኾነ ብዙ ሰው እያደናገረ ነው፤ ብለው ተርጉመውላቸዋል፤ ይህም ሕመም ፈጥሮባቸው አድሯል፤”


ነውረኛ ንግግራቸው፣ በአጠቃላይ ጉባኤው ተሳታፊዎች ላይ የፈጠረውን ስሜት ቢያዩም፣ ይብሱኑ፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን ከሀገረ ስብከታቸው እንደሚያግዱ ነው የዛቱት፡፡ በሀገረ ስብከታቸው ተቀባይነት ያጡትና የመባረር ዕጣ የሚጠብቃቸው ብፁዕ አባ ማርቆስ፣ “ሀገረ ስብከቱን ለማኅበረ ቅዱሳን አሳልፎ ሰጥቶታል፤” እያሉ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤልን በማሳጣት በቦታቸው ለመተካት የፓትርያርኩን እልክ እየገፋፉ እንደሚገኙ ተነግሯል፡፡ “ምን ሲኖዶስ አለ፤ ሲኖዶስ እኛው ነን፤” በማለት ፓትርያርኩ፣ ሌሎችንም አባቶች እንዲያስተባብሩም እየወተወቱ ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል በበኩላቸው፣ ለተሰነዘረባቸው ውንጀላ ፓትርያርኩን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ደረጃና በሕግም እንደሚጠይቁ ነው፣ የተጠቆመው፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ርእሰ አበው እንደመኾናቸው መጠን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ለቤተ ክርስቲያኒቱ አጠቃላይ አመራር የመስጠት ግዴታ አለባቸው፡፡ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ እንደተደነገገው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ እያስወሰኑና ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋራ እየተማከሩ መሥራት የሚጠበቅባቸው ቢኾንም፣ ከዚህ ውጭ እየመከሩ የሚከተሉት ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ አካሔድ፣ ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት እንዲያጣ፤ በባለሥልጣናትም ዘንድ አቅመ ቢስ ተደርገው እንዲናቁ አድርጓቸዋል፡፡ የመንግሥት ሹማምንትን ባገኙ ቁጥር፣ “ማኅበሩን ዝጉልኝ” የሚለው የዘወትር ውትወታቸው በእጅጉ እንዳስናቃቸውና ተደማጭነት እንዳሳጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

በቃል አሳውቀውታል፤ የተባለውና በቀጣይም በጽሑፍ እንደሚያቀርቡ የተጠቆመው ከሓላፊነት የመልቀቅ ጥያቄ መነሻዎች ባለሥልጣናቱን እያነጋገረ ነው፣ ተብሏል፡፡ ከሥልጣን ለመልቀቅ ፍላጎት እንዳላቸው ከማሳየት ይልቅ፣ ከመንግሥት ያጡትን ትኩረት ለመመለስ፤ በዚህም፣ በቀጣዩ ሰኞ በሚጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ጫና ፈጥረው ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም፣ ከእኩይ መካሪዎቻቸው ጋራ የወጠኑት ስልት ሊኾን እንደሚችል ተጠቁሟል፤ “ትቼላችሁ እሔዳለኹ፤” እያሉ ማንገራገራቸው ዐዲስ እንዳልኾነ በማስታወስ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኾኖ የተሾመ አባት ከመዓርጉ የሚወርደው፡- ሃይማኖትን የሚያፋልስ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ፤ በተሾመበት ቀን የፈጸመውን ቃለ መሐላ ካልጠበቀ፤ ታማኝነቱና መንፈሳዊ አባትነቱ ተቀባይነት ያጣ ከኾነና ይህም በተጨባጭ ተረጋግጦ በቅዱስ ሲኖዶስ ሲወሰን እንደኾነ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ 33/1(ሀ)፣ (ለ) እና (ሐ) ተደንግጓል፡፡

መርከቧ በባሕሩ ላይ፣ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ላይ?

ዳንኤል ክብረት

‹‹በዚህ ሃይማኖቴ መናፍቃን እያወገዙኝ እኔም እያወገዝኳቸው ዕድሜ ልኬን በዚህ ዓለም ኖርኩ፤
              የእግዚአብሔር ልጆች ከጋኔን ልጆች ጋር አንድነት ስምምነት የላቸውምና ››

Ark of Noah

ታዋቂው ሩሲያዊ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ባለሞያ ዶክተር ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹Reformation in the Orthodox Perspective> በተሰኘውና እኤአ በ1998 ባወጣው መጽሐፉ ላይ በሕንድ፣ በጆርጅያና በዩክሬይን የተደረገውን የተሐድሶ እንቅስቃሴ ባጠናበት መጽሐፉ ላይ ‹በቤተ ክርስቲያን ጉዞ ውስጥ ዋናው ጥያቄ – መርከቧ በባሕሩ ላይ ትሂድ ወይስ ባሕሩ በመርከቧ ውስጥ ይሂድ የሚለው ነው› ይላል፡፡ ለዚህ ሐሳብ መነሻ ያደረገው በሦስቱ ሲኖፕቲክ ወንጌሎች ላይ በማቴ.8፥23፤ሉቃ. 8፥22 እና በማር. 4፥35 የተጻፈውን ታሪክ ነው፡፡

በእነዚህ የወንጌል ክፍሎች ላይ ጌታችንና ሐዋርያት በመርከብ ወደ ገሊላ ማዶ ሲሻገሩ ጌታችን ተኝቶ ነበረ፡፡ በመንገዱ መካከል መጀመሪያ ነፋስ፣ በኋላም ማዕበል ተነሣ፤ በመጨረሻም ማዕበሉ የባሕሩን ውኃ ወደ መርከቧ ውስጥ መጨመር ጀመረ፡፡ ማቴዎስ ‹ማዕበሉ ታንኳይቱን እስኪደፍናት ድረስ›፣ ማርቆስ ‹ውኃ በታንኳዪቱ እስኪሞላ ድረስ› ሉቃስ ‹ውኃም ታንኳዪቱን ይሞላ ነበር› በማለት የገለጡት አደጋ ተከሠተ፡፡ መርከቧ በውኃው ላይ መሄዷ ቀርቶ ውኃው በመርከቧ ላይ መሄድ ጀመረ፡፡ ያን ጊዜ ሐዋርያቱ ተጨነቁ፡፡ ጌታችንንም ቀሰቀሱት፡፡ እርሱም ‹እናንተ እምነት የጎደላችሁ‹ በማለት መጀመሪያ ሐዋርያትን ቀጥሎም ማዕበሉን ገሠጸው፡፡
መርከቧ ቤተ ክርስቲያን በውኃ ላይ እየተንሳፈፈች፣ እየተላጋችና ከፍ ዝቅ እያለች መሄዷ የተለመደ ነው፡፡ ይህም ምንም ፈታኝ ቢሆን ጤናማ ጉዞ ነው፡፡ ‹በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›(ዮሐ.16፥33) የተባለው ይፈጸማልና፡፡ ውኃው ወደ መርከቡ ከገባ ግን አደጋ ይከሰታል፡፤ ወይ መርከቧ ትሰምጣለች ወይም መርከቧ ትሰበራለች፡፡ ቤተ ክርስቲያን እየተፈተነች በዓለም ላይ መጓዟ ችግር የለውም፡፡ ፈተናውም ቤተ ክርስቲያንን ያጠነክራታል፣ አያሌ ቅዱሳንንም ያስገኝላታል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ‹ወደ አግዚአብሔር መንግሥት በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናል› (የሐዋ.14፥23) ያለው ይሄንን ነው፡፡ የዓለም አስተሳሰብ ወደ መርከቧ ቤተ ክርስቲያን መግባት ከጀመረ ግን በመጨረሻ ውኃ በታንኳዪቱ ይሞላል፤ ቅዱስ ማርቆስ እንደገለጠውም ‹እስኪደፍናት ድረስ› ይደርሳል፡፡ በዚህ ውኃ ተደፍነው የቀሩ መርከቦችም አሉ፡፡ እናም የቤተ ክርስቲያን ዋናው የህልውና ጥያቄ – መርከቧ በውኃው ላይ ትሂድ ወይስ ውኃው በመርከቧ ላይ? የሚለው ነው፡፡

የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ቅድስና የሚወሰነው ውኃው ወደ መርከቧ እንዳይገባ በምታደርገው ተጋድሎ ነው፡፡ ውኃው ወደ መርከቧ ውስጥ የሚገባው ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በሚያጋጥማቸው የእምነት ጉድለት ነው፡፡ ለዚህ ነው ክርስቶስ ማዕበሉን ከመገሠጹ በፊት ሐዋርያትን የገሠጻቸው፡፡ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና መምህራን የእምነታቸው ጥንካሬ ሲላላ፣ ማዕበሉ መጀመሪያ እነርሱን ይመታቸዋል፡፡ ቀጥሎም ቤተ ክርስቲያንን ይመታታል፡፡ ምንጊዜም በታሪክ ውስጥ ከውጭ ያሉ ኃይሎች ያለ ውስጥ ኃይሎች ርዳታ ውኃውን ወደ መርከቧ ለማስገባት ችለው አያውቁም፡፡ ሰይጣን ወደ ሔዋን የሄደው ገነት ለመግባት በምትችለው በዕባብ አድሮ ነው፤ ሰይጣን ክርስቶስን ለአይሁድ አሳልፎ የሰጠው በጉባኤ ሐዋርያት ውስጥ በነበረው በይሁዳ በኩል ነው፤ ግኖስቲኮች የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከፍልስፍና ጋር ሊቀላቅሉ የሞከሩት ወደ ክርስትና ገብተው መምህራን በሆኑ ሰዎች በኩል ነበር፡፡ እነ አርዮስ፣ ንስጥሮስና ሰባልዮስ የማዕበሉ የውስጥ ወኪሎች ሆነው ነው ቤተ ክርስቲያንን ሊደፍኗት ደርሰው የነበሩት፡፡ መስፍኑ ሶምሶን ‹በጥጃዬ ባላረሳችሁ፣ የዕንቆቅልሼን ትርጓሜ ባላወቃችሁ› ያለው ለዚህ ነበር(መሳ. 14፥18)፡፡
‹ተሐድሶ (Reformation) ሌላ ትርጉም የለውም› ይላል ሰርጌይ ላቭሮች ‹ተሐድሶ ማለት ውኃውን ወደ መርከቧ ማስገባት ማለት ነው፡፡ በምዕራቡ ዓለም ያደረገውም ይሄንኑ ነው፡፡ ቀደምት ክርስቲያኖች በየጉባኤያቱ እየወሰኑ የተከላከሉትን፣ ቀኖና ሠርተው ያገዱትን፣ መጻሕፍትን ወስነው የገደቡትን፣ ትውፊታቸውን አጽተው አናስገባም ያሉትን ማዕበል ወደ መርከቧ ውስጥ ማስገባት፡፡ የስሕተት መምህራን በቅዱሳት መጻሕፍት ስም ስሕተትን ማስተማር ሲጀምሩ ነው አበው የቅዱሳት መጻሕፍትን ቁጥር የወሰኑት፡፡ ከዚያም አልፈው በምዕራፍና በቁጥሮች ለክተው ያስቀመጡት፡፡ ዓላማው ማዕበሉን ማገድ ነው፡፡

‹ክርስቲያኖች በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ አራት ማዕበሎችን ሲከላከሉ ኖረዋል› ይላል ሰርጌይ ላቭሮቭ፡፡ የተሳሳተ ትምህርትን፣ ፍልስፍናን፣ ወገንተኝነትንና ፖለቲካን፡፡ እነዚህ አራቱ ማዕበሎች ለመግባት በቻሉ ጊዜ እንኳን ቶሎ ጠልቀው ያወጧቸው ነበር፡፡
ጌታችን እንዳስተማረን የተሳሳተ ትምህርት ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት የሞከረው ከመጀመሪያው ነው፡፡ የስንዴውና የእንክርዳዱ ምሳሌ ይህንን ነው የሚያሳየን(ማቴ. 13፥24-30)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ገና በሕይወት እያለ ሄሜኔዎስና ፊሊጦስ የተባሉ መናፍቃን እርሱ ስለ ትንሣኤ ሙታን ያስተማረውን ትምህርት ማጣመም ጀምረው ነበር(2ኛጢሞ. 2፥17)፡፡ ለዚህ ነበር የኤፌሶንን ቀሳውስት ‹እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፤ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ ዐውቃለሁ› በማለት ያስጠነቀቃቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በራእዩ የገለጠውን ‹ሺ ዓመትን› በተመለከተ የተሳሳተውን ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ ማስተማር የጀመረው ቀሪንጠስ የተባለ መናፍቅ ነው፡፡ ቀሪንጠስ ይህን ትምህርት ማስተማር ሲጀምር ቅዱስ ዮሐንስ በምድር ላይ ነበር፡፡ የቀሪንጠስ የተሳሳተ ትምህርት ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰጠውም ቅዱስ ዮሐንስ በነበረበት በኤፌሶን ከተማ ነው፡፡(1) ቀሪንጠስ ክርስቲያን አልነበረም፤ የግኖስቲኮች ትምህርት አቀንቃኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ፍልስፍናንና ክርስትናን ቀላቅሎ ያስተምር ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ 1ኛና 2ኛ መልእክቱን የጻፈው ልጆቹ ከዚህ ሰው ትምህርት እንዲቆጠቡ መሆኑን ሊቃውንት ይናገራሉ፡፡ በአንድ ወቅት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ በኤፌሶን የሚገኝ የሕዝብ መታጠቢያ ገንዳን ሲጎበኝ አንድ ሰው መጣና በዚያ ቀሪንጠስ እንደሚገኝ ነገረው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም ደቀ መዛሙርቱን ‹ጣሪያው ተንዶ ሁላችንንም ሳይገድለን በፊት ፈጥነን ከዚህ ለቅቀን እንሂድ› አላቸው› ይባላል፡፡
ጌታ ጸራዊ(ጠላት)፣ ሐዋርያት ቢጽ ሐሳውያን፣ ሊቃውንትም መናፍቃን ያሏቸው የስሕተት መምህራን ማዕበሉን ወደ መርከቧ እንዳያስገቡ በትምህርት፣ በመጽሐፍና በዓለም አቀፍ ጉባኤያት አበው ታግለዋቸዋል፡፡ የኒቂያ፣ የቁስጥንጥንያና የኤፌሶን ጉባኤያት ዓላማ ውኃው ወደ መርከቧ እንዳይገባ፣ ገብቶም እንዳይደፍናት ለመከላከል ነበር፡፡ የውግዘታቸውም ምክንያት ወደ መርከቧ የገባው ውኃ ጥፋት ከማድረሱ በፊት ወደ ባሕሩ ለመመለስ ነው፡፡

መርከቧ በውኃ እንድትሞላ የሚያደርጋት ዋናው ምክንያት የማዕበሉ ብርታት ሳይሆን የአገልጋዮቹ የእምነት ጉድለት ነው፡፡ የቀደሙት አበው የስሕተት ትምህርቶችን ነቅተው በመጠበቅ ‹የማይተኙ እረኞች› ነበሩ፡፡ ቅዱስ ሄሬኔዎስ ‹በእንተ ኑፋቄ› አቡሊዲስ ዘሮም ‹መድፍነ ኑፋቄ›፣ የተሰኙ መጻሕፍትን የዛሬ 1700 አካባቢ የጻፉት ማዕበሉን ለመከላከል ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረው የሰርምኔሱ ፖሊካርፐስ መርቅያን የተባለውን መናፍቅ ‹የሰይጣን የበኩር ልጅ› ይለው ነበር፡፡ እነ አባ ጊዮርጊስ ‹መጽሐፈ ምሥጢርን›ና ‹ፍካሬ ሃይማኖት›ን፣ በ17ኛው መክዘ የነበሩ አበው ‹መዝገበ ሃይማኖት›ንና ‹ከአፍርንጅ የምንለይበት›ን፣ እነ መልአከ ብርሃናተ አድማሱ ጀንበሬ ‹ኮኩሐ ሃይማኖት›ን፣ እነ አለቃ አያሌው ታምሩ ‹መች ተለመደና ከተኩላ ዝምድና›ን የጻፉት ማዕበሉን ለማቆም ነው፡፡ አባ ጊዮርጊስም ይህንን ተጋድሎ ሲገልጠው በፍካሬ ሃይማኖት መጽሐፉ ማጠቃለያ ላይ እንዲህ ብሏል፡-
‹‹በዚህ ሃይማኖቴ መናፍቃን እያወገዙኝ እኔም እያወገዝኳቸው ዕድሜ ልኬን በዚህ ዓለም ኖርኩ፡፡
              የእግዚአብሔር ልጆች ከጋኔን ልጆች ጋር አንድነት ስምምነት የላቸውምና፡፡››

ሌላው ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት ሲሞክር የሚኖረው ማዕበል ፍልስፍና ነው፡፡ ፍልስፍና ሃማኖትን እንደ አንድ ፍልስፍና ስለሚቆጥረው ከእርሱ ጋር መሳ ለመሳ መጓዝን ይፈልጋል፡፡ በዚህም የተነሣ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከፍልስፍና ጋር መቀላቀል የሚፈልጉ ሰዎች ቤተ ክርስቲያንን ሲፈትኗት ኖረዋል፡፡ ለቤተ ክርስቲያን ሺ ጥያቄዎችን በማቅረብና የክርስትናን ትምህርት በፍልስፍና መርሖዎች በመተንተን ለማሳፈር ጥረዋል፡፡ የመጀመሪያዎቹ ግኖስቲኮች ዋና ዓለማ የነበረው የአፍላጦናውያንንና(Platonisem) የሐዲሳን አፍላጦናውያንን (Neo Platonism) አስተምህሮ ከቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ጋር ለመቀላቀል ያደረጉት ጥረት ነው፡፡ እንደ ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያና እንደ አርጌንስ ያሉት የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትም ፍልስፍናውን ከክርስትና ጋር ለማስማማት በሄዱት ርቀት ውድቀት ገጥሟቸዋል፡፡ ፍልስፍናናን ከቤተ ክርስቲያን የድኅነት ትምህርት ውስጥ ነቅሎ ያወጣው ሐዋርያዊው አትናቴዎስ ነው፡፡

እንዲያውም ምዕራባውያን ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ የሚመጡትን ጥያቄዎች በሃይማኖታዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ክርስትናውን ከሳይንስና ከቴክኖሎጂ ጋር ማስማማትን መርጠዋል፡፡ እንደ ክርስቲያን ሳይንስ፣ የብልጽግና ወንጌል ያሉ አስተምህሮዎች የመጡትም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ ዓለምን ለቤተ ክርስቲያን ከማስገዛት ይልቅ ቤተ ክርስቲያን ለዓለም እንድትገዛ አደረጓት፡፡ ወይም በሰርጌይ ላቭሮቭ አገላለጥ ‹ወንዙ በረሃውን ሊያጠጣ ሲገባው፣ በረሃው ወደ ወንዙ እንዲመጣ፣ በረሃማነትም እንዲስፋፋ ተደረገ፡፡ በረሃማነቱ ሲስፋፋም ወንዙን አደረቀው› ይላል፡፡ እንደ ግብረ ሰዶም ያሉትን ቤተ ክርስቲያን ወደ ውስጧ እንዳይገቡ ለዘመናት ስትከላከላቸው የኖረችውን ማዕበሎች ለማስገባት የተቻለው በዓለምና በቤተ ክርስቲያን መካከል ሊፈጠር የሚገባው አጥር ወደ ድልድይነት በመለወጡ ነው፡፡ ዛሬም ቤተ ክርስቲያን በእኩልነትና በመብት ስም ‹ውርጃን፣ የሴቶች ክህነትን፣ በፈቃድ መሞትን(Euthanasia)የሰው ዘርን ማዳቀልን(cloning)፣ እንድትቀበል እየተሞገተች ነው፡፡

‹አብዝኆ ፍኖት› (all roads) የተሰኘው ንቅናቄ ሃይማኖታዊ ሳይሆን ፍልስፍናዊ ነው፡፡ ይህ ‹በጠባቧ በር ግቡ› የተሰኘውን የወንጌል ትምህርት ንዶ ‹መንገዶች ሁሉ ወደ መንግሥተ ሰማያት ያደርሳሉ – all roads lead to heaven› ወደሚል የመጣው አስተምህሮ የስሕተት ትምህርቶችን ሁሉ ‹የአንድ ግብ ልዩ ልዩ መዳረሻዎች› አድርጎ የመመልከት አባዜ አለው፡፡ ይህ ግን ፍልስፍናዊ ወይም ሳይንሳዊ አስተሳሰብ እንጂ ሃይማኖታዊ አይደለም፡፡ ጌታችን በእርሱ በቀር ሌላ መንገድ መኖሩን አልነገረንም፤ በክርስቶስ አምኖና በእርሱ ሞትና ትንሣኤ በተገኘው ጸጋ ካልሆነ በቀር ሌላ መንገድ የለም፡፡ ክርስትና እምነቱ ይሄ ነው፡፡ በምሥጢረ ሥጋዌ በኩል ከተዘጋጀው መንገድ ውጭ ሌላ መንገድ የለውም፡፡ በክርስትና ውስጥ ያሉ ነገሮች ሁሉ በዚያ መንገድ ውስጥ የምናገኛቸው በረከቶች ናቸው፡፡

መለካዊነት ከቀደምቶቹ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎች ወገን ነው፡፡ መለካዊነት የንጉሥ ፈቃድ ፈጻሚነት ነው፡፡ ወይም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርትና ሕይወት ለዘመኑ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ ማስገዛት ማለት ነው፡፡ የሮም ነገሥታት ቤተ ክርስቲያንን ከውጭ ሆነው መርታት ሲያቅታቸው በክርስትና ስም ወደ ውስጥ ገቡ፡፡ ሐሳባቸውንና ርእዮታቸውንም የቤተ ክርስቲያን ለማድረግ ሞከሩ፡፡ አባቶች ግን አልተቀበሏቸውም፡፡ ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት አብረው በሠሩባቸው ዘመናት ሁሉ ‹ኅብረት በተዐቅቦ› በተሰኘው መርሕ ነው አበው የተጓዙት፡፡ ተዐቅቦው የመንግሥታቱ አስተሳሰብ ወደ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ጸሎት፣ ሕይወትና ሥርዓት ውስጥ እንዳይገባ ነው፡፡ እነ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ እነ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፣ እነ ቅዱስ አትናቴዎስ፣ እነ ቅዱስ እጨጌ ፊልጶስ፣ እነ አቡነ አሮን፣ እነ አቡነ አኖሬዎስ፣ እነ አቡነ በጸሎተ ሚካኤልና እነ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ፣ እነ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ፣ እነ አቡነ ተክለ ሐዋርያት፣ እነ አቡነ እንድርያስ ዘደብረ ሊባኖስ፣ እነ እጨጌ ዕንባቆም የመናዊ  መከራ የተቀበሉት ለዚህ ነበር፡፡ ‹ወንጌል ወደ ቤተ መንግሥት እንጂ፣ ቤተ መንግሥት ወደ ወንጌል አይግባ› ብለው፡፡

በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከ13ኛው መክዘ ጀምሮ አገልጋዮቿን ለሁለት የከፈለው ለመለካዊነት የከፈሉት ዋጋ ነው፡፡ በአንድ በኩል ‹ኅብረት በተዐቅቦ› የተሰኘውን የቤተ ክርስቲያን መርሕ የተከተሉ ገዳማውያን አባቶች ሲፈጠሩ በሌላ በኩል ደግሞ ‹እንደ ንጉሡ አጎንብሱ› የሚሉ ካህናተ ደብተራ ተፈጠሩ፡፡ ገዳማውያን አበው የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት፣ ሥርዓት፣ ጸሎት፣ አገልግሎትና ቅዱሳት መጻሕፍት ሲጠብቁ፤ ካህናተ ደብተራ ደግሞ የንጉሡን ክብር፣ ሥልጣንና አስተሳሰብ ይጠብቁ ነበር፡፡
የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍት የተጻፉትና የተተረጎሙት፣ የጸሎት መጻሕፍት የተዘጋጁትና የተጠበቁት፣ ሥርዓታት የተዘጋጁትና የጸኑት፣ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ሲሰጥ የኖረውና ወንጌል የተሰበከው፣ የቅዱሳን ሕይወትና ዜና ሲዘጋጅ የኖረው፣ የዝማሬና የቅዳሴ አገልግሎት የጸናውና የተጠበቀው በገዳማውያን አባቶች ነው፡፡ ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ታሪክ ታላላቅ ቦታ ያላቸው እንደነ ዐፄ ይኩኖ አምላክ፣ ዐፄ ዳዊት፣ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ፣ ዐፄ በዕደ ማርያምና ዐፄ ናዖድን የመሳሰሉ ነገሥታት ከዕለት ማስተዋሻ ያላለፈ የቅድስና ማዕረግ ያላገኙት፡፡ በዛግዌ ነገሥታትና ‹ሰሎሞናውያን› በተሰኙት ነገሥታት መካከል የሥልጣን ሽኩቻው እያለ ቤተ ክርስቲያን ግን ከ‹ሰሎሞናውያኑ› ይልቅ ለዛግዌ ነገሥታት የቅድስና ማዕረግ የሰጠችው በእነዚህ ገዳማውያን አበው ምክንያት ነው፡፡

ካህናተ ደብተራ ሥርዓት በመሥራት፣ ገድልና ድርሳን በመጻፍ፣ የጸሎትና የቅዳሴ መጻሕፍት በማዘጋጀት፣ ገዳማዊ ሕይወትን በማጽናትና የቤተ ክርስቲያንን የትምህርት መንገድ በመቅረጽ ቦታ አልነበራቸውም፡፡ እነርሱ ታሪከ ነገሥትና ዜና መዋዕል ሲጽፉ ነው የኖሩት፡፡ ዓላማቸውም ‹ርስት ሽልማት› ማግኘት ነው፡፡ አባ በጸሎተ ሚካኤል እንዲህ ብሎ የገሠጻቸው ለዚህ ነው ‹እናንተ ደብተራ ከምትባሉ በቀር ይህንን ሁሉ ያደረገ ማነው? ታመሰግኑታላችሁ፤ ታወድሱታላችሁ፤ እንዳንተ ያለ ኀያል ማነው ትሉታላችሁ፡፡ እንዳንተ ያለ ድል አድራጊ ማነው፣ እንዳንተስ ያለ ለጋሥ በሁሉ ዘንድ ወዴት አለ፣ እንዳንተ ያለ ምጽዋት ሰጭ የት አለ ትሉታላችሁ፡፡ እንዲህ ስታመሰግኑትም በኃጢአት ላይ ኃጢአት ይጨምራል፡፡›[2] ዛሬም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለው ተጋድሎ በሁለቱ መካከል የሚደረግ ነው፡፡

ሰርጌይ ላቭሮቭ ‹ሁሉም ርእዮተ ዓለማቸው ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሮጣሉ፤ መድረኳን መዋቅሯንና ሥርዓቷን መጠቀም ይፈልጋሉ፡፡ እነርሱን ደግፋ ሌላውን እንድትቃወም ይሻሉ፤ ዐውደ ምሕረቱን ዐውደ ፖለቲካ ያደርጉታል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሰው ልጆች ጉዳይ እንጂ የርዕዮተ ዓለም ጉዳይ አይመለከታትም፡፡ ጸሎቷና አገልግሎቷም ለሰው ልጆች ሁሉ እንጂ ለአንድ ርእዮተ ዓለም ተከታዮች አይደለም፡፡ ይህን በማይረዱ ፖለቲከኞችና ይህን በማይረዱ የራስዋም ልጆች ግን ትፈተናለች፡፡ አንዳንድ ጊዜም ማዕበሉ ወደ መርከቧ ገብቶ እስኪደፍናት ድረስ ታላቅ መናወጥ ያመጣባታል› ይላል፡፡

አራተኛው ማዕበል ዘረኝነት ነው፡፡ ዘረኝነት ማለት ቤተ ክርስቲያንን ማጥበብ ነው፡፡ ‹ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም ዓይነት የሰበሰበች መረብን ትመስላለች›(ማቴ.13፥47) የተባለውን ትቶ አንድ ዓይነት ዓሣ ብቻ እንድትሰበስብ ማስገደድ ነው፡፡ ከአራቱ የቤተ ክርስቲያን መገለጫዎች አንዱ ኩላዊነት(Catholicity)ነው፡፡ ይህም ክርስቲያኖች የክርስቶስ አካላት በመሆናቸው በክርስቶስ አንድ ናቸው ብሎ ማመን ነው፡፡ አንድ ሰው ክርስቲያን ሲሆን የዚህ አንድነት ሱታፌ ይኖረዋል፡፡ ትውልዱ፣ ሀገሩ፣ ዘሩ፣ ቋንቋውና ቀለሙ ዋጋ አይኖራቸውም፡፡ ኩላዊነት ሁለት መልክ አለው አፍአዊና ውሳጣዊ፡፡ አፍአዊ መልኩ የቤተ ክርስቲያን መልክዐ ምድራዊ መስፋፋት ነው፡፡ እርሱ ግን ሁል ጊዜ አይገኝም፡፡ ለምሳሌ በመጀመሪያዎቹ የክርስትና ዘመናት ቤተ ክርስቲያን ያልደረሰችባቸው ቦታዎች ነበሩ፡፡ ያ ግን ኩላዊነቷን አይቀንሰውም፡፡ በመጨረሻው ዘመንም ‹እምነት ያለው ሰው ያንሳል›(ሉቃ. 18፥8)፡፡ ኩላዊነቷ ሁሉም ቦታ ላይ ከመድረስ አንጻር ሳይሆን ለሁሉም ቦታዎች ክፍት ከመሆን አንጻር የሚመጣ ነውና፡፡ ለሐዋርያትም የተሰጠው ትእዛዝ ‹አሕዛብን ሁሉ›(ማቴ. 28፥20) ተብሎ የተሰጣቸው ትእዛዝ በአንድ ጊዜ አልተፈጸመም፤ እስካሁንም ተሟልቶ አልተደረሰም፤ ምንጊዜም ግን ቤተ ክርስቲያን መንገድ ላይ ናት፡፡

ሁለተኛው መልክ ደግሞ ውሳጣዊ ነው፡፡ እምነቷ፣ ሥርዓቷ፣ ሐዋርያዊ ትውፊቷና ትምህርቷ የሰውን ዘር ሁሉ ለማዳን የሚሠራ ማለት ነው፡፡ ለምታውቃቸው ብቻ ሳይሆን ለማታውቃቸውም ትጸልያለች፡፡ ወደ እርሷ ያልተጨመሩ፣ ከእርሷም የተነጠሉ ቢኖሩም እንኳን ኩላዊነቷን አያስቀሩትም፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ‹ኤቅሌሲያ ካቶሊኬ – Ekklêsia Katholikê – የሚለውን ቃል ሲጠቀሙ ‹በዓለም የተዳረሰች› ማለታቸው አይደለም፡፡ ከዓለም ሁሉ የላቀች ወይም ‹እንተ ላዕለ ኩሉ› ማለታቸው እንጂ፡፡ ከቡድኖችም፣ ከነጠላዎችም፣ ከስብስቦችም ሁሉ የላቀች፣ ከድምራቸውም በላይ የሆነች ማለት ነው፡፡ ሁሉን ለማካተት የምትችል – ቡድናዊነት፣ ንጣሌያዊነትና ግላዊነት (sectarian separatism and particularism) የሌለባት ማለት ነው፡፡ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም ኩላዊነት ማለት ‹የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ምንም ሳይሸራርፉ ለሁሉም ፍጹም በሆነ መንገድ ማስተማር (katholikôs kai anelleipôs)ማለት ነው› ይላል[3]፡፡ ኩላዊነትን ለመልክዐ ምድራዊ ስፋት በመስጠት ካቶሊክ የሚለውን ‹ዓለም ዐቀፍ› ብለው የተረጎሙት የምዕራብ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት ናቸው፡፡ ምክንያታቸውም አካባቢያዊ የሆነውን የዶናታውያንን[4] ትምህርት ለመቃወም ሲሉ ነበር፡፡

እነዚህ አራቱ ማዕበሎች ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመግባት ሲጥሩ ኖረዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜም ተሳክቶላቸው ለመግባት ሞክረዋል፡፡ ነገር ግን ‹እያንዳንዱ በሽታ የራሱን ሐኪም ያስነሣል› እንደሚለው የቻይኖች አባባል በየዘመናቱ ዐቃብያነ እምነት እየተነሡ ውኃው መርከቧን ከመድፈኑ በፊት ጌታቸውን ይቀሰቅሱታል፡፡ በተለይ ደግሞ ይህ ዘመን ዩኒቨርሳሊዝም(ሁሉም ትክክል ነው)፣ ሊብራሊዝም(እምነትን፣ ትውፊትንና ባሕልን ሁሉ ለሉላዊነት ሲሉ ማመቻመች)፣ እና ሴኩላሪዝም(ዓለማዊነት) የሠለጠነበት በመሆኑ የመርከቧን ከለላ ሰብሮ ውኃውን ለማስገባት የሚደረገው ዘመቻ ብዙም ከባድም ነው፡፡ ቅዱስ ሉቃስ ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር ወደ ሮም ሲሄዱበት የነበረው መርከብ በማልታ ደሴት አጠገብ ያጋጠመውን ፈተና ሲነግረን ‹ከማዕበሉ ግፊያ የተነሣ መርከቡ ይሰበር ነበር› እንዳለው (የሐዋ. 27፥41) ማዕበሉ በዝቶና ጠንክሮ ቤተ ክርስቲያንን ሰብሮ እንዳይገባ ነቅቶ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ እነሆ ጥያቄው አንድ ነው – መርከቧ በውኃው ላይ ትሂድ ወይስ ውኃው በመርከቧ ላይ?